TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ ፦ በፕሪቶሪያው የ #ሰላም_ስምምነት መሰረት የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች #የመጀመሪያው_ዙር የተሀድሶና መልሶ የማቋቋም መርሀ ግብር ዛሬ ከመቐለ ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ኩሓ በይፋ መጀመሩን ኢፕድ ዘግቧል።

በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ወቅት ላይ መንግስት በትግራይ ያሉ ታጣቂዎችን ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ወደመደበኛ ህይወታቸው እስኪመለሱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

Photo Credit : EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ዕግዱ ተነሳ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በማህበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ጥሎት የነበረውን #ጊዜያዊ ዕግድ ዛሬ አርብ ማንሳቱን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በ " ሸገር ከተማ " እየተካሔደ ያለውን የመስጅድ ማፍረስ ተግባር በመቃወም በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተለያዩ መስጂዶች የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። እንደ ሀሩን ሚዲያ ዘገባ ፤ በተቃውሞው ሰልፎቹ የከተማ አስተዳደሩ እየሄደበት ያለው አካሔድ #ትክልል_አለመሆኑን እና #በአስቸኳይ እንዲያቆም የተጠየቀ ሲሆን ያፈረሳቸውንም መስጂዶች ይቅርታ ጠይቆ መልሶ እንዲገነባ ተጠይቋል። በአንዋር መስጂድ…
#Update

ዛሬ በአዲስ አበባ የተለያዩ መስጂዶች ፤ በ " ሸገር ከተማ " እየተካሄደ ያለውን የመስጂድ ማፍረስ ተግባር የሚቃወሙ / የሚያወግዙ ሰልፎች መደረጋቸው ይታወቃል።

በተለይም በ " አንዋር መስጂድ " በነበረው ተቃውሞ ወቅት የፀጥታ ኃይሎች የኃይል እርምጃ መውሰዳቸውን የአይን እማኞች ገልፀው ነበር።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም በነበረው ሁኔታ በሰዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ማመልከታቸው ይታወቃል።

ማምሻውን በተገኘ መረጃ 2 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ስለ ጉዳዩ ምን አለ ?

ዛሬ አርብ (የጁምዓ) ሶላት ከተጠናቀቀ በኋላ በመርካቶ አካባቢ " ረብሻና ግርግር " ተፈጥሮ የሰው ሕይወት አልፏል፤ ህግ በማስከበር ስራ ላይ በተሰማሩ የፖሊስ አባላት ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል ሲል ገልጿል።

በአንዋር መስጂድ የጁምዓ ሶላት ከተጠናቀቀ በኋላ በሌሎች አካባቢዎች " መስጂዶች ፈርሰዋል " በሚል ምክንያት በመርካቶ ዙሪያ በተፈጠረ " ረብሻና ግርግር " የሁለት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ህግ በማስከበር መደበኛ ሥራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል ብሏል።

በተለይ በተለምዶ " ጋዝ ተራ " እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተፈጥሮ በነበረ " ግርግር " ሁለት ግለሰቦች ጉዳት ደርሶባቸው ለህክምና ሆስፒታል ከተላኩ በኋላ ሕይወታቸው አልፏል ሲል ገልጿል።

እንዲሁም አራት ግለሰቦች ጉዳት ደርሶባቸዋል ያለው ፖሊስ ህግን ለማስከበር በተሰማሩ 37 የፖሊስ አመራርና አባላት እንዲሁም 15 የሚሆኑ የተለያዩ የፖሊስ አጋዥ ሀይሎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ለህክምና ተልከዋል ብሏል።

" ረብሻውን ባስነሱት አካላት " ንብረትነታቸው የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሆኑ ሁለት አውቶቡሶች ላይ ጉዳት ደርሷል ያለው ፖሊስ ፤ " መነሻውን አንዋር መስጂድ ያደረገው ረብሻ በጋዝ ተራ ፣ ቆርቆሮ ተራ ፣ ሰባተኛ አካባቢ ፣ አመዴ እና በተለያዩ አካባቢ ለማዛመት የተሞከረ ቢሆንም በፀጥታ አካሉ ጥረት ረብሻው ሳይስፋፋ መቆጣጠር ተችሏል " ብሏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ " በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ ረብሻ እንደተነሳ ተደርጎ እየተናፈሰ ያለው መረጃ የተጋነነ ነው " ያለ ሲሆን " አጋጥሞ የነበረው ብጥብጥ በቁጥጥር ስር ውሎ አካባቢው ወደ መደበኛው እንቅስቃሴ ገብቷል ፤ ብጥብጡን በመምራትና በማስተባበር እንዲሁም ዋነኛ ተሳትፎ የነበራቸው 114 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር በማዋል በህግ አግባብ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው " ሲል ገልጿል።

ፖሊስ " በአዲስ አበባ በህዝበ ሙስሊሙም ሆነ በዕምነት ተቋሙ ላይ የተፈጠረ ችግር ሳይኖር በሌሎች ቦታዎች ላይ መስጂድ ፈርሷል በሚል ምክንያት ህገ-ወጥ ሰልፍ በማድረግ ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል " ያለ ሲሆን " በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አቅደው በተንቀሳቀሱ ግለሰቦች ላይ የፀጥታ አካላት እየወሰዱት ያለውን እርምጃ አጠናክረው ይቀጥላሉ ፤ የከተማችንን ሠላምና ፀጥታ ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ከህገ-ወጥ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ " ሲል አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በአዲስ አበባ የተለያዩ መስጂዶች ፤ በ " ሸገር ከተማ " እየተካሄደ ያለውን የመስጂድ ማፍረስ ተግባር የሚቃወሙ / የሚያወግዙ ሰልፎች መደረጋቸው ይታወቃል። በተለይም በ " አንዋር መስጂድ " በነበረው ተቃውሞ ወቅት የፀጥታ ኃይሎች የኃይል እርምጃ መውሰዳቸውን የአይን እማኞች ገልፀው ነበር። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም በነበረው ሁኔታ በሰዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ማመልከታቸው ይታወቃል።…
#Update

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው ፤ " መብቱን በሰላማዊ መንገድ ለመጠየቅ በወጣ ህዝበ ሙስሊም ላይ የተወሰደው እርምጃ ፍፅም ተቀባይነት የሌለው ፣ ኢ-ፍትሃዊና ኢ-ዲሞክራሲያዊ በመሆኑ እናወግዛለን " ብሏል።

ምክር ቤቱ ፤ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ሲቲ የመስጅድ ፈረሳ እንዲቆምና የፈረሱትም በአስቸኳይ መተኪያ እንዲሰጣቸው እንዲሁም በጉዳዩ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ለሚመለከተው አካል ለማሳወቅ የተሞከረ ሲሆን የመስጅድ ፈረሳው ባለመቆሙ ህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞውን በዛሬው እለት በአደባባይ ድምፁን በሰላማዊ መንገድ አሰምቷል ብሏል።

" ይህንንም ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ተከትሎ በታላቁ አንዋር መስጅድ የፀጥታ አካል በወሰዱት ኢ-ህገ መንግስታዊ እና ኢ ሰብአዊ እርምጃ የሰው ሂይወት አልፋል፣ ብዙሃን ቆስለዋል። " ሲል ገልጿል።

" ይህንን አስከፊ ጥቃት የፈፀሙ እና ያስፈፀሙ የፅጥታ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ አጥብቀን እንጠይቃለን " ያለው ምክር ቤቱ " በቀጣይም የሚመለከተው አካል በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ እየተከናወነ ያለውን ድርጊት እንዲያስቆምነና ወደ ውይይት በመምጣት ስር ነቀል የእርምትና እርምጃ ተጠናክሮ እንዲተገበር አጥብቀን እንጠይቃለን " ብሏል።

ምክር ቤቱ ፤ " የሀይማኖት ጉዳይ እና የእምነት ተቋማት ጉዳይ ሁሌም ቢሆን በስክነት መታየት ሲገባው ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በእምነት በተቋማቱ ጉዳይ ሲከተሉት የነበረውን አካያሄድ እንደ ተሞክሮ ከመውሰድ ይልቅ በዚህ አከያሄድ የተሰራው አስነዋሪ ተግባር የሀገራችንን ብሎም የከተማችንን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ እየጣለ ይገኛል። " ሲል አሳውቋል።

በሸገር ከተማ መስጅድን በተመለከተ እየተከናወነ ያለው ድርጊት፣ሀላፊነት የጎደለው፣ የህዝበ ሙስሊሙን ክብር ያዋረደ፣ ሀገራችን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ፣ የመንግስት የለውጥ ሪፎርምን ወደ ሀላ የሚመልስ በመሆኑ ጉዳዩ እንደ ሀገር ሊታሰብበት ይገባል ሲልም አስገንዝቧል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፤ በዛሬው እለት በመስጅድ ፈረሳ ሳቢያ በሰላማዊ መንገድ መብቱን ለመጠየቅ በወጣው ህዝበ ሙስሊም ላይ በተወሰደው ኢ-ህገ መንግስታዊ እርምጃ ሒይወታቸው ላለፉ አላህ (ሱ.ወ) ጀነትን እንዲወፍቃቸው፣ ለመላው ህዝበ ሙስሊምም መፅናናትን ተመኝቷል።

የከተማችንም ህዝበ ሙስሊሙ በቀጣይ ጉዳዩን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል አደራ ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዕግዱ ተነሳ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በማህበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ጥሎት የነበረውን #ጊዜያዊ ዕግድ ዛሬ አርብ ማንሳቱን አሳውቋል። @tikvahethiopia
#ምስጋና

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለባለሥልጣን መ/ቤቱ ፈጣን ምላሽ ምስጋና አቅርባለች።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በማኅበረ
ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ፣ ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ያስተላለፈውን ጊዜያዊ እገዳ እንዲያነሳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣  ለባለሥልጣን መ/ቤቱ ያቀረበችውን ጥያቄ በመቀበል፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የተጻፈለት ደብዳቤ እንደደረሰው ሳይውል ሳያድር ጊዜያዊ እገዳውን አንስቷል።

በዚህም ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያቀረበችውን ጥያቄ በአዎንታ ተመልክቶ አፋጣኝ ተግባራዊ ምላሽ በመስጠቱ፣ ከፍ ያለ ምስጋናን ማቅረቧን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አሳውቋል።

ፅ/ቤቱ ፤ " ለወደፊቱም ተቋማዊ ግንኙነታችንን የበለጠ በማጠናከር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መኾናችንን እንገልጻለን " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫው ፤ " መብቱን በሰላማዊ መንገድ ለመጠየቅ በወጣ ህዝበ ሙስሊም ላይ የተወሰደው እርምጃ ፍፅም ተቀባይነት የሌለው ፣ ኢ-ፍትሃዊና ኢ-ዲሞክራሲያዊ በመሆኑ እናወግዛለን " ብሏል። ምክር ቤቱ ፤ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ሲቲ የመስጅድ ፈረሳ እንዲቆምና የፈረሱትም በአስቸኳይ መተኪያ እንዲሰጣቸው እንዲሁም…
#Update

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሒምን ጨምሮ የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝዳንት ሀጅ ሱልጣን አማን እንዲሁም ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በትላንትናው እለት በጸጥታ አካላት ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል እያገኙ ያሉ ሙስሊሞችን ሆስፒታል በመገኘት መጠየቃቸውን ሀሩን ሚዲያ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፥ በትላንትናው ዕለት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራ ልዑክ በታላቁ አንዋር እና ኑር ( ሰፈር በኒ) መስጂዶች ከጁምዓ ሰላት በኃላ  በሸገር ከተማ አስተዳደር  "በሕገ ወጥ" ስም የፈረሱ መስጂዶች  ተቃውሞ ለማሰማት በወጡ ምዕመናንና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል የተፈጠረውን ችግር  በተመለከተ ወደ ፌደራል  ፖሊስ ኮሚሽን ዋናው መስሪያ  ቤት በማቅናት ከኮሚሽኑ የስራ ኃላፊዎች ጋር  ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በዉይይቱ መሰረትም በጊዜያዊነት በፖሊስ ተዘግቶ የነበረው ኑር (ሰፈር በኒ) መስጂድን ለሰላት ክፍት ማድረግ ተችሏል።

በቀጣይ የተፈጠሩ ችግሮችን የሚያጠናና የመፍትሔ አማራጮችን ለሚመለከተው የመንግስት አካል የሚያቀርብ ከሁለቱም ተቋማት የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሟል።

ኮሚቴው ፤ ከጠቅላይ  ምክር ቤቱ ፣ከአዲስ አበባ  እና ከኦሮሚያ  እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች ከእያንዳዳቸው ሶስት አባላት ያሉት ሲሆን ስራም እንደጀመረ ተነግሯል።

ሰላም ወዳዱ ሙስሊሙ ማህበረሰብ  በሁለቱ ተቋማት የተቋቋመው  መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ የደረሰበትን ውጤት እስኪያሳውቅ ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቅ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#Update

ጠቅላይ ምክር ቤቱ #በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አስቸኳይ ጉባዔ ተቀምጧል። 

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ እየተካሄደ ነው።

አስቸኳይ ጉባዔው በዑማ ሆቴል እየተካሄደ  ሲሆን መርሀ ግብሩን በቁርዓን የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማምና ኻጢብ በሆኑት በሼይኽ  ጧሐ ሙሀመድ ሐሩን መከፈቱ ተገልጿል።

የጠቅላላ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ይህንን ጉባዔ ስናካሂድ በሸገር ከተማ በርካታ መስጂዶች  የፈረሱበት የመስጂዶችን ፈረሳ ለመቃወም ከወጡ ሰዎች ዉስጥ መስዋት የሆነበት ጊዜ ነው ብለዋል።

" መስጂዶች የአሏህ ቤቶች ናቸው። ይህ ክስተንን ከሚመለከተው  አካል ጋር ለመመካከር የተደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል " ብለዋል።

" ሙስሊሞች  የሀገር የሰላም ዘብ ናቸው " ያሉት ፕሬዝዳንቱ " በሸገር ከተማ እየፈረሱ ያሉትን መስጂዶች ጉዳይ በሚመለከት  ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄ መቅረቡን አስታውሰዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ ነገሮችን ወዳልተፈለገ መልኩ በሚወስዱ ማህበራዊ ድረ ገፅ ላይ የሚፅፉ  አንዳንድ  አካላትን ከተግባራቸው  እንዲቆጠቡ  አሳስበዋል።

" በመንግስት ዉስጥ ሆነዉ መንግስትና ሕዝብን የሚያጋጩ አካላት በሕገ ተጠያቂ መሆንን ይኖርባቸዋል "ም ብለዋል።

በትላንትናው  ዕለት  በሸገር ከተማ በ " ሕገ ወጥ " ስም የፈረሱ መስጂዶችን  ለመቃወም ወጥተው መስዋዕት የሆኑ  ወንድሞች አሏህ ጀነተል ፍርዶስ እንዲወፍቃቸው ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መፅናናት እንዲሰጣቸው ጉዳት የደረሰባው ወገኖቻችን ከደረሰባቸው ጉዳት አፊያቸውን እንዲመልስላቸው ፕሬዜዳንቱ ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በጉባዔው የኦሮሚያና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች ሪፖርታቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#MyWishEnterprise

DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/MYWISHENT 
+251-913-356384  +251-912-710661  +251-910-626917  +251-928-414395
+251-911-606068  +251-922-475851  +251-935-409319  +251-911-602664
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ባለ አስራ አንድ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ጉባዔዉን አጠናቋል።

ከአቋም መግለጫዎቹ መካከል ፦

- በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ በአንዋር እና በኑር መስጂዶች የተፈጠረው ክስተት #እንዴት_እንደተፈጠረና የደረሰውን ሞትና ጉዳት መንስኤዎች የሚያጣራ ከመንግስትና የእስልምና ጉዳይ ም/ቤት በጋራ ያሉበት ገለልተኛ አጣሪ ቡድን #በአስቸኳይ እንዲቋቋም ተጠይቋል።

- በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በ " ሸገር ከተማ " ኢስላምንና ሙስሊሞችን በናቀ መልኩ በመስጂዶች ላይ እየተደረገ ያለው የጅምላ ፈረሳ ሂደት በአስቸኳይ እንዲቆም፥ እንዲሁም ለፈረሱት መስጊዶች የክልሉ መንግስት #ምትክ_ቦታ በመስጠት በአስቸኳይ ተመልሰው እንዲገነቡ በማድረግ ሕዝበ ሙስሊሙን በይፋ ይቅርታ በመጠየቅ እንዲክስ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

- በኦሮሚያ ክልልም ሆነ በሌሎች የሀገራችን ክልሎች ለእምነት ቦታዎች ተገቢውን ክብርና ጥበቃ እንዲደረግ፥ እንዲሁም ለመስጂዶች ካርታ በመከልከልና ሆነ ብሎ ቢሮክራሲውን በማንዛዛት ሕዝቡን ላማረሩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች መንግስት ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በአፋጣኝ እንዲፈታቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

- ሕዝበ ሙስሊሙ ከመሪ ተቋሙ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ጎን በመቆም ሃይማኖታዊ መብቶችን ለማስከበር የሚደረገውን ጥረት በሕጋዊ እና ሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

- መንግስት ኢስላም ጠል የሆኑ እና በመንግስት መዋቅር ዉስጥ በተለያዩ እርከኖች ያሉትን አካላት በመገምገም እና በማጥራት ሕዝብንና መንግስትን ሆነ ብለው ለማጋጨትና ሀገሪቷን ወደ ለየለት ቀውስ ለመውሰድ እየሰሩ ያሉ አካላትን ፈትሾ ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ መዋቅሩን እንዲያጠራ ጥሪ ቀርቧል።

(ዝርዝር የአቋም መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia