TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ 2 ሺህ ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በመስጠት የተጠረጠረው ግለሰብ ተያዘ።

እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ በነበረው የዘር ማጥፋት እልቂት፣ ከጥቃት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ ሁለት ሺሕ #ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፏል በሚል የተጠረጠረው ግለሰብ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መያዙን የሩዋንዳውን የዘር ማጥፋት የሚከታተለው፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጦር ወንጀል ችሎት አስታውቋል።

የቀድሞው የፖሊስ አባል፣ ፉልጌንሴ ካይሼማ፣ ፍ/ቤቱ በይፋ ክሥ ከመሠረተበት ካለፉት 22 ዓመታት ጀምሮ በሽሽት ላይ ነበር።

በተመድ የተቋቋመው ችሎት፣ ሥራውን ለሩዋንዳ በማስረከቡ፣ ካይሼማ፥ ለሩዋንዳ ተላልፎ እንደሚሰጥ የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ካይሼማ ያለበትን ለሚጠቁም፣ የአምስት ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥ አስታውቆ ነበር።

ሌላው የዘር ማጥፋቱ ጠንሳሽ የተባለው ፌሊሲን ካቡጋ፣ ከ26 ዓመታት ሽሽት በኋላ ከሦስት ዓመት በፊት በፈረንሳይ ውስጥ መያዙ ይታወቃል።

እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ፣ በአክራሪ ሁቱዎች በተፈጸመ የዘር ማጥፋት፣ 800ሺሕ የሚሆኑ ቱትሲዎች መገደላቸው ይታወሳል።

#ቪኦኤ #ሩዋንዳ #Genocide

@tikvahethiopia
#ethio_telecom

የኢትዮ ቴሌኮምን አዲስ ሲም ካርድ ይበልጥ ተሻሽለው  ከቀረቡት የሲም ካርድ ማስጀመሪያ ጥቅሎች ጋር ሲገዙ ከ15 ብር የአየር ሰዓት በተጨማሪ እስከ 3 ጊ.ባ የሚደርስ የዳታ ስጦታ እንዲሁም ለአንድ ወር የሚያገለግል የጥሪ ማሳመሪያ አገልገሎት በነፃ ያገኛሉ

ሁሌም የተሻለውን፤ ምርጥ ምርጡን ለናንተ!
#SPECIALOFFER!!!  #buyandgetbonus
#Update

በ " ሸገር ከተማ " እየተካሔደ ያለውን የመስጅድ ማፍረስ ተግባር በመቃወም በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተለያዩ መስጂዶች የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።

እንደ ሀሩን ሚዲያ ዘገባ ፤ በተቃውሞው ሰልፎቹ የከተማ አስተዳደሩ እየሄደበት ያለው አካሔድ #ትክልል_አለመሆኑን እና #በአስቸኳይ እንዲያቆም የተጠየቀ ሲሆን ያፈረሳቸውንም መስጂዶች ይቅርታ ጠይቆ መልሶ እንዲገነባ ተጠይቋል።

በአንዋር መስጂድ በነበረው ተቃውሞ የፀጥታ ኃይሎች ተቃውሞውን ለመበተን ኃይል ስለመጠቀማቸው የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ በደረሰው መልዕክት የተጎዱ ሰዎች ስለመኖራቸው ለማወቅ ችሏል።

እስካሁን በከተማ አሰተዳደሩ በኩል የተሰጠ ማብራሪያ የለም።

በአዲሱ የሸገር ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ካለው የመስጂድ ፈረሳ ጋር በተያያዘ የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ከቀናት በፊት በሰጠው መግለጫ ድርጊቱን እንደሚያወግዝ ገልጾ የጁመዐ ኹጥባ በሸገር ከተማ የተደረገውን መስጂዶችን የማፍረስ ዘመቻን በማውገዝ እንዲሆን ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

እንደ የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት መረጀ ፤ በአስተዳደሩ እስካሁን ከ19 በላይ መስጂዶች ፈርሰዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትም ፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ መፃፉና በደብዳቤው በሸገር ከተማ እያፈረሱ ስላሉ መስጂዶች አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ መጠየቁ የሚዘነጋ አይደለም።

ማስታወሻ 1.  https://t.iss.one/tikvahethiopia/78657?single

ማስታወሻ 2. https://t.iss.one/tikvahethiopia/78541?single

ፎቶ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
#ሸገር

" እየፈረሱ ያሉት ቤቶች #አሁንም በመንግስት መዋቅር ዉስጥ ባሉ ሃላፊዎች ይሁንታ የተሰሩ ስህተቶች መሆናቸዉን እናምናለን " ሲሉ የሸገር ከተማ ከንቲባ አስታወቁ፡፡

በቅርቡ የተቋቋመውን የሸገር ከተማ ተከትሎ በተለይ ከቤት ፈረሳ ጋር ተያይዞ በርካታ ቅሬታዎች ከመነሳታቸው ባሻገር ዜጎች በመንግስት አካላት ፍቃድ ቤቱን እንደገነቡ ቢገልጹም መፍትሄ ማግኘት እንዳልቻሉ ይገለጻል፡፡

ፍቃዱን የሰጡ የመንግስት አካላት አሁንም በሃላፊነት ቦታ ላይ ሆነው የዜጎች ቤት እንዲፈርስ እያደረጉ ነው የሚለው ቅሬታም በተደጋጋሚ ጊዜ ይነሳል፡፡

ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ከአሃዱ መድረክ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሸገር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ተሸመ አዱኛ  ፤ ባለፈው የመንግስት መዋቅር ውስጥ በነበሩ የስራ ሃላፊዎች ስህተት ቤቶቹ እንደተሰሩ እንደሚያምኑ አስታዉቀዋል፡፡

#አሁንም እነዛ ሃላፊዎች በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን በመግለጽ ሆኖም ግን ለሰሩት ስህተት እርምጃ አለመወሰዱ ጥያቄ እያሥነሳ ቢሆንም ካለፈው ይልቅ ስለ ወደ ፊቱ በማሰብ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ያለዉ መሰል ስህተቶች እንዳይደገሙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቤት እየፈረሰባቸው ያሉ ዜጎች ለሚያነሱት ጥያቄ ምንም እንኳን በከተማዋ አስተዳደር ህገ ወጥ ስለሆናችሁ ነው የሚል ምላሽ ቢሰጣቸውም #ከመንግስት_አካላት ፍቃድ አግኝተው እንደሰሩ እየገለጹ ያሉ ግን በርካቶች ናቸው፡፡

Credit : Ahadu Mederk

@tikvahethiopia
" የአሁኑ ጥቃት ከከዚህ ቀደሙ ከበድ ያለ ነበር "

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ፤ በፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 14 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " በሰጠው ቃል ፤ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በሚገኘው ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 11 የፋብሪካው ሰራተኞች እና 3 የአካባቢው ነዋሪዎች መገደላቸውን አረጋግጧል።

ፋብሪካው በተፈጸመበት በዚሁ ጥቃት እና ዘረፋ ምክንያት ስራ ማቋሙም ገልጿል።

ጥቃቱ የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ግንቦት 12 ቀን 2015 መሆኑን የገለፀው የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ፤ ፋብሪካው ባለፈው 2014 ዓ.ም እና በዚህ ዓመት ተመሳሳይ ጥቃቶችን ቢያስተናግድም፤ የአሁኑ ከዚህ ቀደም ከነበሩት " ከበድ ያለ " እንደሆነ አመልክቷል።

የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ እና በስሩ ያለው የሸንኮራ አገዳ እርሻ፤ በአጠቃላይ በ67 ሺህ ሄክታር ይዞታ ላይ ያረፈ ነው።

የቀደሙት ጥቃቶች ይበልጥኑ ኢላማ የሚያደርጉት የፋብሪካው እርሻ ላይ እንደነበር የገለፀው ግሩፑ ታጣቂዎቹ የአገዳ እና የእርሻ ማሽነሪዎችን የማቃጠል ድርጊት ይፈጽሙ እንደነበር አስታውሷል።

የአሁኑ ከዚህ ቀደም ከነበሩት የሚለየው ታጣቂዎቹ ወደ ፋብሪካ ጭምር በመግባት ጥቃቶቹን በመፈጸማቸው እንደሆነ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ጥቃቱን እንዲመረምር ያቋቋመው ግብረ ኃይል ፤ በጥቃቱ 11 የፋብሪካው ሰራተኞች እና ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደተገደሉ ማረጋገጡን ኃላፊው አስታውቀዋል።

ሰኞ ዕለት ወደ አካባቢው የተሰማራው ይኸው ግብረ ኃይል፤ እንደ ልብ ተዘዋውሮ ለመስራት የሚያስችል ሁኔታ ባለመኖሩ የደረሱ ሌሎች ጉዳቶችን እስካሁን ሙሉ ለሙሉ ለማረጋገጥ እንዳልቻለ ተነግሯል።

ሆኖም ግብረ ኃይሉ እስካሁን ባሰባሰበው መረጃ ፦

- በታጣቂዎች ከተገደሉት ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች በተጨማሪ ጉዳት የደረሰባቸው ሌሎች አሉ።

- ውድመት እና ዘረፋ መፈፀሙ ተረጋግጧል።

- ቢሮዎች ወድመዋል። ፋብሪካው ውስጥ ያለ መቆጣጠሪያ ኮምፒውተር ተሰብሯል።

- የእርሻ ማሽነሪዎች፣ ትራክተሮች፣ አገዳ ወደ ፋብሪካው የሚያመላልሱ የተለያዩ [ተሽከርካሪዎች] ሙሉ ወድመዋል፤ የተጎዱም አሉ።

-  የፋይናንስ ሰነዶች ወድመዋል።

- ከተዘረፉት ንብረቶች ውስጥ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ ኮምፒውተሮች እና ፕሪንተሮች ይገኙበታል።

- ታጣቂዎቹ በፋብሪካው መጋዘን ውስጥ የተከማቹ ስኳር እና የአፈር ማዳበሪያ ዘርፈው ወስደዋል።

አጠቃላይ ጉዳቱን በዝርዝር ለማወቅ የሚያስችለው ምርመራ ገና አለመጠናቀቁ ተገልጿል።

ጥቃቱን ማነው የፈፀመው ?

ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች ማንነት በተመለከተ የተጠየቁት የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የህዝብ ግንኙነት እና ተሳትፎ ክፍል ኃላፊ አቶ ረታ ደመቀ ፤ በእርሳቸውን የስራ ኃላፊነት የታጣቂዎችን ማንነት ለይተው መናገር እንደማይችሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ከቅዳሜው ጥቃት በኋላ ፋብሪካው ወደሚገኝበት አካባቢ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲገቡ በመደረጋቸው በአሁኑ ወቅት በስፍራው " የተሻለ ሁኔታ "መኖሩን ኃላፊው አስረድተዋል።

ሆኖም አሁንም ቢሆን " በእርሻ መንደሮች አካባቢ ታጣቂዎች አሉ " የሚል ስጋት በሰራተኞች ዘንድ እንዳለ አመልክተዋል።

Credit : Ethiopian Insider

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ በፕሪቶሪያው የ #ሰላም_ስምምነት መሰረት የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች #የመጀመሪያው_ዙር የተሀድሶና መልሶ የማቋቋም መርሀ ግብር ዛሬ ከመቐለ ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ኩሓ በይፋ መጀመሩን ኢፕድ ዘግቧል።

በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ወቅት ላይ መንግስት በትግራይ ያሉ ታጣቂዎችን ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ወደመደበኛ ህይወታቸው እስኪመለሱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

Photo Credit : EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ዕግዱ ተነሳ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በማህበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ጥሎት የነበረውን #ጊዜያዊ ዕግድ ዛሬ አርብ ማንሳቱን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በ " ሸገር ከተማ " እየተካሔደ ያለውን የመስጅድ ማፍረስ ተግባር በመቃወም በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተለያዩ መስጂዶች የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። እንደ ሀሩን ሚዲያ ዘገባ ፤ በተቃውሞው ሰልፎቹ የከተማ አስተዳደሩ እየሄደበት ያለው አካሔድ #ትክልል_አለመሆኑን እና #በአስቸኳይ እንዲያቆም የተጠየቀ ሲሆን ያፈረሳቸውንም መስጂዶች ይቅርታ ጠይቆ መልሶ እንዲገነባ ተጠይቋል። በአንዋር መስጂድ…
#Update

ዛሬ በአዲስ አበባ የተለያዩ መስጂዶች ፤ በ " ሸገር ከተማ " እየተካሄደ ያለውን የመስጂድ ማፍረስ ተግባር የሚቃወሙ / የሚያወግዙ ሰልፎች መደረጋቸው ይታወቃል።

በተለይም በ " አንዋር መስጂድ " በነበረው ተቃውሞ ወቅት የፀጥታ ኃይሎች የኃይል እርምጃ መውሰዳቸውን የአይን እማኞች ገልፀው ነበር።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም በነበረው ሁኔታ በሰዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ማመልከታቸው ይታወቃል።

ማምሻውን በተገኘ መረጃ 2 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ስለ ጉዳዩ ምን አለ ?

ዛሬ አርብ (የጁምዓ) ሶላት ከተጠናቀቀ በኋላ በመርካቶ አካባቢ " ረብሻና ግርግር " ተፈጥሮ የሰው ሕይወት አልፏል፤ ህግ በማስከበር ስራ ላይ በተሰማሩ የፖሊስ አባላት ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል ሲል ገልጿል።

በአንዋር መስጂድ የጁምዓ ሶላት ከተጠናቀቀ በኋላ በሌሎች አካባቢዎች " መስጂዶች ፈርሰዋል " በሚል ምክንያት በመርካቶ ዙሪያ በተፈጠረ " ረብሻና ግርግር " የሁለት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ህግ በማስከበር መደበኛ ሥራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል ብሏል።

በተለይ በተለምዶ " ጋዝ ተራ " እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተፈጥሮ በነበረ " ግርግር " ሁለት ግለሰቦች ጉዳት ደርሶባቸው ለህክምና ሆስፒታል ከተላኩ በኋላ ሕይወታቸው አልፏል ሲል ገልጿል።

እንዲሁም አራት ግለሰቦች ጉዳት ደርሶባቸዋል ያለው ፖሊስ ህግን ለማስከበር በተሰማሩ 37 የፖሊስ አመራርና አባላት እንዲሁም 15 የሚሆኑ የተለያዩ የፖሊስ አጋዥ ሀይሎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ለህክምና ተልከዋል ብሏል።

" ረብሻውን ባስነሱት አካላት " ንብረትነታቸው የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሆኑ ሁለት አውቶቡሶች ላይ ጉዳት ደርሷል ያለው ፖሊስ ፤ " መነሻውን አንዋር መስጂድ ያደረገው ረብሻ በጋዝ ተራ ፣ ቆርቆሮ ተራ ፣ ሰባተኛ አካባቢ ፣ አመዴ እና በተለያዩ አካባቢ ለማዛመት የተሞከረ ቢሆንም በፀጥታ አካሉ ጥረት ረብሻው ሳይስፋፋ መቆጣጠር ተችሏል " ብሏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ " በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ ረብሻ እንደተነሳ ተደርጎ እየተናፈሰ ያለው መረጃ የተጋነነ ነው " ያለ ሲሆን " አጋጥሞ የነበረው ብጥብጥ በቁጥጥር ስር ውሎ አካባቢው ወደ መደበኛው እንቅስቃሴ ገብቷል ፤ ብጥብጡን በመምራትና በማስተባበር እንዲሁም ዋነኛ ተሳትፎ የነበራቸው 114 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር በማዋል በህግ አግባብ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው " ሲል ገልጿል።

ፖሊስ " በአዲስ አበባ በህዝበ ሙስሊሙም ሆነ በዕምነት ተቋሙ ላይ የተፈጠረ ችግር ሳይኖር በሌሎች ቦታዎች ላይ መስጂድ ፈርሷል በሚል ምክንያት ህገ-ወጥ ሰልፍ በማድረግ ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል " ያለ ሲሆን " በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አቅደው በተንቀሳቀሱ ግለሰቦች ላይ የፀጥታ አካላት እየወሰዱት ያለውን እርምጃ አጠናክረው ይቀጥላሉ ፤ የከተማችንን ሠላምና ፀጥታ ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ከህገ-ወጥ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ " ሲል አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia