TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዘማሪት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

ዘማሪት ሂሩት ዘማሪ ከመሆኗ በፊት በህዝብ ዘንድ ዛሬም ድረስ የሚደመጡና የሚወደዱ እጅግ በርካታ የዘፈን ስራዎች ነበሯት።

ከዘፈን ዓለም ወጥታ ወደ መንፈሳዊ ዓለም ከገባች በኃላ የተለያዩ የመዝሙር አልበሞችን ሰርታ ለአድማጭ አቅርባለች።

ዘማሪ ሂሩት ዛሬ በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየች ሲሆን ፤ የ7 ልጆች እናት ፣ የ10 ልጆች አያት እና የ7 ልጆች ቅድመ አያት ነበረች።

@tikvahethiopia
#SUDAN

" ወደ ተኩስ አቁም ለማምራት መደላደል ነው " የተባለ ስምምነት በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) መካከል ተፈረም።

በሱዳን ወጊያ ላይ የሚገኙት ሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች ሳዑዲ አረቢያ ፣ ጅዳ ሄደው ባካሄዱት ድርድር የመጀመሪያ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነግሯል።

" የቅድሚያ ስምምነት መርሆች " መፈራረማቸውን የዘገበው አል አረቢያ  ሁለቱም ወገኖች ለሱዳን ሉዓላዊነትና አንድነት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል ብሏል።

ሁለቱ ኃይሎች የሱዳን ወዳጆች የሚያደርጉትን ጥረት በደስታ እንቀበላለን ማለታቸውንም ተነግሯል።

በመጀመሪያው ስምምነት መሰረት ፤ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ከሚያደርሱ ጥቃቶች እንደሚታቀቡ ፤ በሱዳን ያሉ ሲቪሎች ያሉባቸውን አካባቢዎች ለቀው እንዲወጡ ያስገድዳል።

ተፋላሚ ኃይሎቹ በሱዳን የመንግስትና የግል ተቋማትን ለቆ ለመውጣት፣ የህክምና ባለሙያዎችን እና የህዝብ ተቋማትን መጠበቅ፣ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት መፍቀድ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ስምምነቱን በደስታ መቀበሉን ገልጾ፤ የጅዳ ድርድር በሁለቱ ወገኖች መካከል እስከ 10 ቀናት የሚቆይና የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ እንደሚያተኩር አስታውቋል። 

" የደህንነት እርምጃዎቹ በአሜሪካ፣ በሳዑዲ አረቢያ እና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚደገፍ የተኩስ አቁም ቁጥጥር ዘዴን ያካትታል " ብሏል።

የአሜሪካ መንግስት በሰጠው መግለጫ ስምምነቱ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዳልሆነ ተናግሯል። የጂዳ ስምምነት ወደ ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያመራ መደላደል እንደሆነም ተነግሯል።

መረጃው የአል አረቢያ ቴሌቪዥን እና አል አይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከተማ 6ኛ ዙር የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ስራ ትላንት ተጀምሯል።

በ6ኛ ዙር በተመረጡ በሰባት ክፍለ ከተሞች ከግንቦት 03/09/2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ ተከታታይ አምስት ወራት 50 ሺህ የመሬት ይዞታዎችን የማረጋገጥ ስራ ይካሄዳል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታውቋል።

ኤጀንሲው ምዝገባው ፦

👉 በኮልፌ ቀራኒዮ፣
👉 በቂርቆስ፣
👉 በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣
👉 በቦሌ፣
👉 በአዲስ ከተማ፣
👉 በልደታና በአራዳ ክፍለ ከተሞች ባሉ 50 ቀጠናዎችና 211 ሰፈሮች እንደሚከናወን ገልጿል።

ይህ የይዞታ ማረጋገጥ እወጃ ከተላለፈ ከ15 ቀናት በኃላ የይዞታ ይረጋገጥልኝ ጥያቄዎች በክፍለ ከተማ ቅ/ጽ/ቤቶች ቀርበው ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይቻላል ተብሏል።

ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ በተመረጡ ቀጠናዎችና ሰፈሮች ስራው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ባለቱ አምስት ወራት ውስጥ የመረጃ ልዩነት እንዳይፈጠር ሲባል ምንም ዓይነት የስመ- ንብረት ዝውውር አገልግሎት እንደማይሰጥ ኤጀንሲው አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ በአዋጅ ከተቋቋመ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በ5 ዙር 147 ሺህ ይዞታዎችን በካዳስተር ሲስተም መመዝገቡ አስታውሷል።

መረጃው የአ/አ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethiopia
የወረዳ አመራሩ ተገደሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለባቸው አሞኜ በዛሬው ዕለት በቢሮአቸው ውስጥ ተገደሉ።

የክፍለ ከተማው ኮሚኒኬሽን ባሰራጨው መረጃ ፤ " አቶ አለባቸው አሞኜ ቢሯቸው ውስጥ ቁጭ ብለው የህዝብ አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ከአንድ #ተገልጋይ በደረሰባቸው #ጥቃት ህይወታቸው አልፏል " ብሏል።

ክ/ከተማው ምንም እንኳን ግድያውን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይፋ ባያደርግም ጥቃት ያደረሰው ተጠርጣሪ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን አመልክቷል።

ተገቢው የምርመራ ሂደት ተከትሎ ተጠያቂነት የማስፈን ስራ ይሰራልም ብላል።

" አቶ አለባቸው በስራ ቁርጠኝነት የሚታወቁ " ናቸው ያለው የቂርቆስ ክ/ከተማ " በበርካታ መንግስታዊና ህዝባዊ ተግባራት አርዓያነት ያለው ስራ የሰሩና ያስተባበሩ አመራራችን ነበሩ " ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ቴሌብር

በጉዞ ላይ ሆነው ነዳጅ ቢያልቅብዎ፤ በቴሌብር አካውንትዎ በቂ ገንዘብ ባይኖር ምን ማድረግ ይችላሉ?
አይጨነቁ… #ቴሌብር_እንደኪሴ እያለ የነዳጅ ታንከርዎ ባዶ አይሆንም!

የጎደሎትን በቴሌብር አሟልተው፤ ነዳጅዎን ሞልተው ጉዞዎን ይቀጥሉ፤ ታዲያ ለነዳጅ ክፍያዎ ቴሌብርን የሁልጊዜ ምርጫዎ ያድርጉ።

ቴሌብርን ይዞ .. የተሳካ ጉዞ!
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ግድያውን የፈፀመው የፖሊስ አባል ነው " - የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

በአዲስ አበባ ከተማ ፤ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አባቸው አሞኜ የእለት ከእለት ተግባራቸውን በማከናወን ላይ እንዳሉ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ/ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ #በፖሊስ አባል መገደላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳወቀ።

ግድያውን የፈፀመው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የካሳንቺስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የቀጠና ኦፊሰር የሆነ አባል መሆኑን ፓሊስ ገልጿል።

እንደ ፖሊስ መረጃ ግድያውን የፈፀመው ግለሰብ ፤ የግል ጉዳዩ እንዲፈፀምለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ  ለወረዳ 8 አስተዳደር ጽ/ቤት ያመለክታል፡፡

ወረዳው ጉዳዩን ተመልክቶ ምላሽ እንደሚሰጠው የተገለፀለት ቢሆንም " ጥያቄዬ እንዳይፈፀም የከለከልከው አንተነህ " በሚል ምክንያት የወረዳውን ዋና ስራ አስፈፃሚ ቢሯቸው ውስጥ በስራ ላይ እንዳሉ በታጠቀው ሽጉጥ ገድሏቸዋል።

ወንጀሉን የፈፀመው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

@tikvahethiopia
በትግራይ #ኔትዎርክ ተቋርጧል።

በትግራይ ክልል ከምሽት 12 ሰዓት አንስቶ የኔትዎርክ አገልግሎት መቋረጡን በዚህም ምክንያት " ምን ተፈጥሮ ነው ? " በሚል ጭንቀት እንደገባቸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰቡን አባላት መልዕክት ይዞ ኢትዮ ቴሌኮምን አነጋግሯል።

ኢትዮ ቴሌኮም ፤ እውነት ነው ኔትዎርክ ተቋርጧል ሲል አረጋግጦልናል።

" ኔትዎርክ የተቋረጠው ፋይበር ተቆርጦ " ነው ያለው ኢትዮ ቴሌኮም " ሰራተኞቻችን በጥገና ላይ ናቸው " ብሏል።

" ከማዕከል የሚያገናኘው ፋይበር ሁለት ቦታ ተቆርጧል፤ ዋናው እና የመጠባበቂያውን ጨምሮ " ያለው ኢትዮ ቴሌኮም ፤ ከመቐለ ፣ ከደሴ እና ከሰመራ ሰራተኞች ተሰማርተው በርብርብ እየሰሩ ይገኛሉ ሲል አሳውቋል።

የጉዳቱን መጠን በተመለከተ ላቀረብነው ጥያቄ " ምሽት በመሆኑ የጉዳቱን መጠን ማረጋግጥ አልተቻለም " ተብለናል።

@tikvahethiopia
#MyWishEnterprise

DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/MYWISHENT 
0913356384 / 0912710661  0910626917 / 0928414395
0911606068 / 0922475851  0935409319 /0911602664