TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዘሪሁን_ወዳጆ

አንጋፋው አርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ በህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

በሙዚቃ ስራዎቹ ለኦሮሞ ህዝብ ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከተ የሚነገርለት አርቲስት ዘሪሁን በህንድ አገር በሕክምና ላይ እያለ ህይወቱ እንዳለፈ ታውቋል።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ፤ አርቲስት ዘሪሁን ወዳጆች በህይወት በነበረበት ወቅት ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገሩ ስራዎችን መስራቱንና ለበርካታ አርቲስቶችም ምሳሌ መሆን የቻለ ከህዝብ አእምሮ የማይጠፋ አርቲስት እንደበር ገልጿል።

@tikvahethiopia
#MekelleUniversity

ትግራይ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ቀደመው የመማር ማስተማር ስራቸው ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።

ከነዚህም ውስጥ የኣክሱምና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው መማር ያልቻሉ ተማሪዎች በአጭር ቀናት ውስጥ በስልክ እየደወሉ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ለማስታወሻ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/77964

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ለሁሉም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ላልተመደቡ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።

ዩኒቨርስቲው በጦርነቱ ምክንያት ትምህርት ያቋረጡ የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች ቀጥሎ የተቀመጡትን መረጃዎች ከሚያዝያ 16-20/2015 ዓ.ም. ባሉት የስራ ሰዓታት ብቻ ከታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመጠቀም መረጃዎች እንዲያቀብሉ ጠይቋል።

ተፈላጊ መረጃዎቹ ምንድናቸው ?

👉 ሙሉ ስም
👉 የመታወቅያ ቁጥር
👉 ትምህርት ክፍል
👉 የስንተኛ ኣመት ተማሪ መሆንዎ

እነዚህን መረጃዎች የመላኪያ ስልክ ቁጥሮች ፦

1. EiTM - 0984026089 / 0984026059
2. MIT - 0984026727
3. CHS - 0984023986
4. CVS - 0984024072
5. CLG - 0984023987
6. CSSL - 0984023985
7. CBE - 0984024069
8. IPHC - 0984025512
9. CDAaNR - 0984025593
10. CNCS - 0984025582
11. Other Universities - 0984025589

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፅሁፍ መልእክቱን ሲልኩ #በእንግሊዘኛ እንዲልኩ አሳስቧል።

ዩኒቨርሲቲው በሌሎች የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩና በጦርነቱ ምክንያት ያቋረጡ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ከላት የተጠየቁትን መረጃዎች ፤ከዛ በተጨማሪ ሲማሩበት የነበረውን የዩኒቨርሲቲ ስም በማከል መረጃ እንዲያሳውቁ ጥሪውን አቅርቧል።

በሌላ በኩል ፥ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎቹን በቅርብ ጊዜ እንደሚጠራ ገልጿል።

@tikvahethiopia
የመምህራኑ ጥያቄ ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመምህራን ማኅበር በሥሩ ከሚገኙት አባላት መካከል የ29,500 አባላቱ የመኖሪያ ቤት ችግር እንዲፈታለት ከንቲባ አዳነች አቤቤን በደብዳቤ ጠይቋል።

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ለሪፖርተር ቃለ ምልልስ ሰጥተው ነበር። በዚህ ቃለምልልስ ምን አሉ ?

- ማህበሩ ከሁለት ሳምንት በፊት ለከንቲባዋ በጻፈው ደብዳቤ፣ በአስተዳደሩ ሥር የሚገኙ መምህራን የቤት ጥያቄ እንዲፈታ ጠይቋል፡፡

- የመምህራን ጥያቄ እየበረታ በመምጣቱ ከንቲባዋ ከመምህራን ጋር በ2013 ዓ.ም. በነበራቸው ስብሳሰባ፣ መምህራን በማኅበር ተደራጅተው ቤት እንዲገነቡ እንደሚደረግ ቢገለጽም፣ እስካሁን ምንም ዓይነት ተስፋ ሰጪ ነገር እየታየ አይደለም።

- ለከንቲባዋ በተፃፈው ደብዳቤ ለመምህራን የኑሮ ውድነትን የሚያረግቡ ድጎማዎች እንዲደረጉ፣ ከንቲባዋ በመድረክ ላይ የገቡት ቃል ወደ ታች ወርዶ እንዲፈጸምና በከተማ አስተዳደሩ በተጀመሩ ልማቶች የመምህራን ጥያቄዎች እልባት እንዲያገኙ ተጠይቋል።

- የመምህራን የደመወዝ ጥያቄ የከተማ አስተዳደሩ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ከተቻለ በልዩ ትኩረት በከተማው ደረጃ ውሳኔ ሰጥቶበት እንዲፈታ፣ ካልሆነም ደግሞ የሚመለከተው የፌዴራል ተቋም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት እልባት መስጠት እንዲቻል እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።

- የኑሮ ውድነት ማረጋጊያ ድጎማ 3,000 ብር የሚሰጥ ቢሆንም፣ ገንዘቡ ከችግሩ ጋር አብሮ የማይሄድ በመሆኑ ቢያንስ በእጥፍ እንዲያድግ መምህራኑ ይፈልጋሉ።

በተጨማሪ ለከንቲባዋ በተፃፈው ደብዳቤ ....

ለመምህራን ሁለተኛ መ/ ቤታቸው የሆነው የመኖሪያ ቤት ጥያቄ፣ ግንቦት 2013 ዓ.ም. መምህራንን ባወያዩበት ወቅት መምህራን በማኅበር ተደራጅተው ቤት እንዲገነቡ እንደሚደረግ የተገለጸ ቢሆንም፣ ነገር ግን እስካሁን በተፈለገው ርቀት ወደ ሥራ አለመገባቱን ያትታል፡፡

በዚህ የተነሳ ባለፉት ወራት ምንም ዓይነት ለውጥ አለመኖሩ መምህራንን ተጠቃሚ ከማድረግ ይልቅ፣ ጉዳዩን በተቃራኒ በጥርጣሬ እንዲያዩት አነሳሽ ምክንያት ከመሆኑም በላይ ተስፋ አስቆራጭነቱ እየሰፋ የመጣ ስለመሆኑ ይገልጻል።

ይህ ጉዳይ መምህራን ቃል የገቡልንን አልተገበሩልንም (አላስተገበሩልንም) የሚል ስሜት ፈጥሮ የመምህራንን ሞራል ያላሸቀ ፣ ቤት ባላቸውና በሌላቸው መምህራን መካከል የፍትሐዊነት ጥያቄ ያስነሳ መሆኑም በደብዳቤው ተመላክቷል፡፡

መምህራን የሚያገኙት የደመወዝ መጠንና በአሁኑ ወቅት ያለው ፦ የቤት ኪራይ ዋጋ፣ በተጨማሪም የኑሮ ውድነት መምህራንን ተረጋግተው እንዳያስተምሩ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ ከንቲባዋ ለመምህራኑ በገቡት ቃል መሠረት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ የመምህራን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ " አጥብቀን እንጠይቃለን " ብሏል።

በአሁኑ ወቅት ያለውን የኑሮ ውድነት መምህራኑ ከሚያገኙት ደመወዝና የኑሮ መደጎሚያ ጋር ተቋቁሞ መኖር ከባድ መሆኑን የሚያስረዳው ደብዳቤው፣ የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም ባደረገው የኑሮ መደጎሚያ ላይ ወቅቱን የሚመጥን ማሻሻያ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

ተጨማሪ ፦ https://telegra.ph/Reporter-04-23

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
#ነዳጅ #አዲስአበባ

በአዲስ አበባ ከነገ ሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል የክፍያ አማራጮች ብቻ ይደረጋል።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ያቀረበውን #ነዳጅ የተባለ መተግበርያ በመጠቀም ከ900 በላይ የሚሆኑ ማደያዎች ላይ የነዳጅ ግብይት መፈፀም የሚያስችል አሰራራር አስተዋውቋል።

የነዳጅ መተግበሪያን በመጠቀም እንዴት መገበያየት ይቻላል ?

- በመጀመሪያ የነዳጅ መተግበሪያን ከፕሌይ ስቶር ወይም አፕ ስቶር ያውርዱ፤

- ሙሉ መረጃዎን በማስገባት መተግበሪያው ላይ ይመዝገቡ ወዲያውኑ የነዳጅ መለያ ቁጥር በ አጭር የጽሁፍ   መልዕክት ይደርስዎታል።

- በመቀጠል መተግበርያው ላይ የተሽከርካሪዎን የሰሌዳ ቁጥር በማስገባት ተሽከርካሪዎን ይመዝግቡ።

- የነዳጅ መለያ ቁጥርዎን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ Utility ውስጥ በመግባት Utility payment በመምረጥ በመልእክት የደረሰንን የነዳጅ ID አስገብተን Link ማድረግ ወይንም በአቅራቢያዎት ወደሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ከሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ።

ከዚህ በኋላ ቀጥታ ከሂሳብ አካውንትዎ ግብይት መፈጸም ብቻ !

- ነዳጅ ለመቅዳት ማደያ በሚሄዱበት ወቅት የነዳጅ ቀጂ ባለሙያው የሰሌዳ ቁጥርዎን ፣  የሚቀዱትን የነዳጅ መጠን እና የገንዘብ መጠን በ(ነዳጅ ቀጂው) መተግበሪያ ላይ በማስገባት ግብይቱን ያስጀምራል።

- ወዲያውኑ በሚደርስዎት የአጭር የፅሁፍ መልዕክት የሚቀዱትን የነዳጅ መጠን እና የገንዘብ መጠን ትክክል መሆኑን በማረጋገጥ የሚስጥር ቁጥሩን(OTP) ለነዳጅ ቀጂ ባለሙያው በመንገር ግብይቱን ያጠናቅቁ።

ነዳጅን ለየት የሚያደርገው ፦

አንድ ጊዜ ብቻ ከሂሳብ አካውንትዎ ጋር በማስተሳሰር ቀጥታ ከአካውንትዎ የነዳጅ ግብይት የሚፈጽሙበት መሆኑ!

በአቅራቢያዎ ያሉ ነዳጅ ማደያዎችን እንዲሁም ነዳጅ መኖሩን እና አለመኖሩን አረጋግጠው መሄድ የሚያስችሎትን አማራጭ ይዞ መምጣቱ!

አንዴ በመተግበሪያው ላይ ከተመዘገቡ በኋላ የስማርት ስልክ አለማስፈለጉ!

መተግበሪያውን ለማውረድ ?

ፕላይ ስቶር:https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj

አፕስቶር : https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

አሰራሩ በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ማደያዎች ማከናወን ይቻላል።

#ነዳጅ #CBE #ኤግልላየን
#ድርድር

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሸኔ ወይም እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጋር የሚደረገው ድርድር ከነገ ወዲያ በታንዛኒያ እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ገልጸዋል።

ይህንን ያሳወቁት ፥ በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ግጭት በሰላም ስምምት እንዲቋጭ ቁልፍ ሚና ለነበራቸው አካላት የምስጋና እና የዕውቅና ሥነ ስርዓት በተካሄደበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ የወለጋ ሕዝብ እፎይ እንዲል ሁሉም ወገን የበኩሉን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል በቀጣዩ ሣምንት በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት የተመራ ልዑክ ወደ መቐለ እንደሚያቀና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሳውቀዋል።

ልዑኩ የሁሉንም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ያካተተ እንደሚሆን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

ፎቶ፦ ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ድርድር የኢትዮጵያ መንግሥት ከሸኔ ወይም እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጋር የሚደረገው ድርድር ከነገ ወዲያ በታንዛኒያ እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ገልጸዋል። ይህንን ያሳወቁት ፥ በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ግጭት በሰላም ስምምት እንዲቋጭ ቁልፍ ሚና ለነበራቸው አካላት የምስጋና እና የዕውቅና ሥነ ስርዓት በተካሄደበት ወቅት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ…
#ድርድር

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ስለ #ድርድር ምንድነው ያሉት ?

" ከኦነግ ሸኔ ጋር የሚደረገው ድርድር ከነገ ወዲያ በታንዛኒያ ይጀመራል።

ይህንን ድርድር የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህዝብ አብዝቶ ይፈልገዋል።

በዚህ ድርድር የሚሳተፉ ወገኖች ሁሉ የዛሬዋን ቀን እያሰቡ ፣ ከግጭት፣  ከጦርነት እንደማናተርፍ አውቀው ህግ እና ስርዓት ተከትለን ይቅር ተባብለን ሀገራችንን በጋራ ማነፅ እና መገንባት እንድንችል ፤ የወለጋ ህዝብ አሁን ካለበት ስቃይ እፎይ ማለት እንዲችል ሁሉም ወገን የበኩላቸውን እንዲያደርጉ ከወዲሁ ጥሪዬን አቀርባለሁ። "

ይህንን ድርድር በተመለከተ ከታጠቀው ቡድን (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት/ መንግሥት ኦነግ ሸኔ ከሚለው ቡድን) በኩል የሚሰጥ መግለጫ ሆነ መረጃ ካለ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
" የእኔን ወላጆች ጨምሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች አሉን መመለስ መቻል አለባቸው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ዛሬ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ " ጦርነት ይብቃ፣ ሰላምን እናፅና " በሚል መሪ ቃል የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት በሰላም እና በንግግር እንዲቋጭ ላደረጉ አካላት የምስጋና መርሀ ግብር ተካሂዶ ነበር።

በዚህ ስነስርት ላይ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት፣ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ፣ የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ አምባሳደር ማይክ ሀመር እና ሌሎችም በርካታ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተው ነበር።

በዚሁ መድረክ ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ንግግር አድርገው ነበር።

በንግግራቸው ምን አሉ ?

አቶ ጌታቸው ረዳ ፦

" የትግራይ ህዝብ ጦርነት ሰልችቶታል። ጠብመንጃ የመነቅነቅ አባዜ በፍፁም አይኖረም በዚህ አጋጣሚ ከትግራይ ይዤ የመጣሁት መልዕክት የሰላም እና የፍቅር መልዕክት ብቻ ነው።

አሁንም አራት ዓመት በላይ ትምህርት የሚባል ያላየሁ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ልጆች አሉን ትምህርት ቤት መግባት መቻል አለባቸው።

አሁንም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች አሉን የኔን ወላጆች ጨምሮ መመለስ መቻል አለባቸው ፣ ስራቸውን መስራት መቻል አለባቸው።

ሁሉንም ነገር ለሰላም በሚሆን መልኩ እናድርገው ፣ ከጎረቤት ወንድም ህዝቦች በተለይም ከአማራ እና ከአፋር ጋር ሊያጋጨን የሚገባ ነገር ሳይኖር ፣ ግጭት ተፈጥሮ በሁላችንም ዘንድ ታሪክ ይቅል ሊለው የማይገባ ብዙ ጥፋት ተፈፅሟል።

ይሄንን ነገር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ዘግተን ቋንቋችንን የሰላም እና የመከባበር፣ ልዩነቶቻችንን በመከባበር ፣ በመቻቻል እና በህግ ብቻ ለመፍታት እስከሰራን ድረስ በጋራ ሀገራችንን ከመገንባት አልፈን ፣ በሁለቱም በሶስቱም ጎረቤት እህትማማች፣ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ተጥሮ ያለውን መቃቃይ የሚመስል ስሜት አስወግደን ወደ ተሻለ ደረጃ የማናሳድግበት ምክንያት የለም።

... አሁንም ደግሜ ደጋግሜ የምለው የትግራይ ህዝብ ጦርነት ሰልችቶታል ፤ አንገሽግሾታል ይህ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አካባቢዎች እንደ ኖርማል የሚወሰዱ ህፃናትን ትምህርት ቤት በሰዓቱ መላክ መመለስ የሚመስሉ ጉዳዮች፣ ማረስ፣ ማለስለስ፣ ማጨድ መዝራት የሚባሉ ነገሮች ይናፍቁታል ፈጥነን ወደዚህ መመለስ መቻል አለብን።

ሁሉንም ለማድረግ የሁሉንም አቅም መጠቀም ያስፈልገናል። ከምንም ነገር በላይ ጠንካራ ሰራተኛ የሆነው የትግራይ ህዝብ ተመልሶ ወደ ስራው ተሰማርቶ የሰላም ችግር ሳይሆን ምን ያክል አተረፍኩ ምን ያክል አመረትኩ በሚል ፉክክር ውስጥ እንዲገባ ለማስቻል የጀመርነውን ጥረት አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል፤ ሁሉም ክልሎች የዚህ እንቅስቃሴ አካል እንደሚሆኑ እምነቴ የፀና ነው ፤ ከፌዴራል መንግሥት ጋር የጀመርናቸው መልካም ግንኙነቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ አውንታዊ በሆነ መልኩ ትልቅ ደረጃ ላይ እንደሚደርሱ እምነታችን የፀና ነው። "

@tikvahethiopia
#ExodusPhysiotherapy

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦
- ለአንገት፣ለትክሻ፣ለወገብ ህመም;ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ችግር፣ ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል፣ ለስፖርታዊ ጉዳቶች ፣ ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች ፣ በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ !

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ     #ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት
አድራሻችን ፦ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን።

ስልክ ፦ 0979099909/ 0911039377
በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic
#AmazonFashion

አማዞን ፋሽን ጥራት ያላቸው ዘመናዊ የቱርክ ሱፎችን በተለያየ አማራጭ ይዞላቹ ቀርቧል። በቡድን ለሚመጡ ተማሪዎች እና ሚዜዎች ጥሩ ቅናሽና ፓኬጅ አዘጋጅተናል።

አድራሻ: ፒያሳ ዶውንታውን ህንፃ ምድር ላይና 2ኛ ፎቅ   

ስልክ ፦ 0919339250 / 0911072936 

https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w
የኢትዮ ቴሌኮም መልዕክት!

ከዛሬ ሚያዝያ 16 ቀን ጀምሮ በአዲስ አበባ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ብቻ የሚፈጸም በመሆኑ ለተግባራዊነቱ በአዲስ አበባ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎች በቂ ዝግጅት ማድረጋችንን እንገልጻለን።

⛽️ ውድ ደንበኞቻችን ነዳጅ ለመቅዳት ወደ ነዳጅ ማደያ ስትሄዱ በቅድሚያ፡ የቴሌብር ሱፐርአፕን ከ onelink.to/75zfa5 በማውረድ ወይም *127# በመደወል የቴሌብር አካውንት በቀላሉ ክፈቱ፤

⛽️ ከቴሌብር ጋር በተሳሰሩ 20 ባንኮች ከሚገኝ የባንክ አካውንታችሁ፤ በየነዳጅ ማደያዎቹ በተመደቡ የቴሌብር ወኪሎች ወይም የአገልግሎት ማዕከሎቻችን እማካኝነት ገንዘብ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ማስተላለፍ ይችላሉ፤

⛽️ የነዳጅ ማደያ ሠራተኞች ስልክ ቁጥርና የሚከፍሉትን የገንዘብ መጠን ሞልተው ሲጨርሱ በስልክዎ በሚደርስዎ የማረጋገጫ መልዕክት ላይ የገንዘብ መጠኑ ትክክል መሆኑን በማየት የሚስጥር ቁጥር ማስገቢያ ሳጥኑ ውስጥ የሚስጥር ቁጥር (ፒን) በማስገባት ያረጋግጡ፡፡

በመጨረሻም ክፍያው መፈጸሙን የሚያረጋግጥ አጭር መልዕክት የሚደርስዎ ሲሆን ከቴሌብር ሱፐርአፕም ደረሰኝ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ bit.ly/3V3wjPF

(ኢትዮ ቴሌኮም)