TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ድርድር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ስለ #ድርድር ምንድነው ያሉት ? " ከኦነግ ሸኔ ጋር የሚደረገው ድርድር ከነገ ወዲያ በታንዛኒያ ይጀመራል። ይህንን ድርድር የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህዝብ አብዝቶ ይፈልገዋል። በዚህ ድርድር የሚሳተፉ ወገኖች ሁሉ የዛሬዋን ቀን እያሰቡ ፣ ከግጭት፣  ከጦርነት እንደማናተርፍ አውቀው ህግ እና ስርዓት ተከትለን ይቅር ተባብለን ሀገራችንን በጋራ ማነፅ እና መገንባት…
#Update

የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ትላንት " ኦነግ ሸኔ " እያሉ ከጠሩት የታጠቀ ቡድን ጋር ነገ ማክሰኞ በታንዛንያ ድርድር እንደሚጀመር ማሳወቃቸው ይታወሳል።

ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር የታጣቂው ቡድን /የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት / ማረጋገጫ ሰጥቶ ድርድር እንደሚጀመር አሳውቋል።

ታጣቂ ቡድኑ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ልዩነቶችን በንግግር ለመፍታት ከስምምነቱ መደረሱን ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል።

" የኢትዮጵያ መንግሥት ለድርድር ያስቀመጥነውን ቅድመ ሁኔታ ተቀብሏል " ያለው ታጣቂው ቡድን " ገለልተኛ ሦስተኛ ወገን ባለበት በድርድሩ ወቅት በዘላቂነት ግልጸኝነት እንዲኖር ተስማምተናል " ብሏል።

በሌላ በኩል የታጣቂ ቡድኑ መንግሥት ድርጅቱን  " ሸኔ " ብሎ ከመጥራት እንዲቆጠብ አሳስቧል።

" የድርጅታችን መጠሪያ፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ነው ፡ ሌላ ስያሜ ስህተት ከመሆኑም በላይ ማንነታችንን እና ዓላማችንን የሚወክል አይሆንም " ሲል ገልጿል።

ካመንግሥት ይህን አይነት የተሳሳተ መረጃ ከማሰራጨት ሊቆጠብ ይገባልም ብሏል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከመንግስት ጋር ያለውም ልዩነቶች በንግግር ለመፍታት ቀጠሮ መያዙ " ለፍትሕ፣ እኩልነት እና የራስን እድል በራስ ለመወሰን የለውጥ ምዕራፍ ጅማሮ ነው " ብሏል።

ከዚሁ ከድርድር ጋር በተያያዘ መረጃ ፤ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከፍተኛ አዛዥ አማካሪ ነኝ ያሉት አቶ ጅሬኛ ጉዳታ ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ በሰጡት ቃለ ምልልስ በታንዛኒያ የሚደረገው ድርድር ረቡዕ እንደሚጀምር አረጋግጣለሁኝ ብለዋል።

በታንዛኒያ የሚደረገው መድረክ የሂደት ማበጀት መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ መድረክ ማነው ሶስተኛው ወገን፣ በምን መልኩ ነው ሂደቱ የሚካሄደው ፣ የደህንነት ማረጋገጫ የሚያደርገው ማነው ? የሚሉና መሰል ጉዳዮች የሚወሰንበት ነው ብለዋል።

አቶ ጅሬኛ ድርድሩን እያማቻቹ ያሉ አካላት የኖርዌይ እና ኬንያ መንግሥታት መሆናቸውን ገልጸው ከአውሮፓም በሂደቱ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ዲፕሎማቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል። አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረትም በሂደቱ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው እኙሁ የሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዥ አማካሪ እንደሆኑ የገለፁት አቶ ጅሬኛ አሳውቀዋል።

" ድርድር መደረጉ እና ሰላም እንዲሰፍን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከፍተኛ ፍላጎት አለው " ያሉት አቶ ጅሬኛ ፤ " ሂደቱ ተስፋ ሰጪ ነው " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#Gondar

ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ አዲስ ከንቲባ ተሾመላት።

አቶ ባዩህ አቡሃይ በዛሬው ዕለት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል።

የጎንደር ከተማ ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ በሚገኘው 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ነው አቶ ባዩህ አቡሃይ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ የሾመው።

ምንጭ፦ የጎንደር ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#ብሔራዊ_ፈተና

" እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2015 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች የፈተና ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ/ም ድረስ ብቻ እንደሚካሄድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎቱ ፥ ማንኛውም የስም፣ የፆታ፣ የተፈጥሮ/የማህበራዊ ዘርፍ እና የፎቶ ማስተካከያ ከፈተና በፊት ስለማይደረግ እያንዳንዱ ተፈታኝና እና መዝጋቢ ትክክለኛነቱን የማጣራትና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት ብሏል።

ይህ መሆን ያለበትም ምዝገባው በበየነ መረብ በመሆኑ በትምህርት ቤት ደረጃ የተካሄደው የምዝገባ መረጃ በቀጥታ በማንም ሳይነካ ወደ ተቋሙ የመረጃ ቋት የሚገባ በመሆኑ ነው ሲል አስረድቷል።

ከሚያዚያ 20/2015 ዓ/ም በኋላ በግለሰብ ወይም በተቋም በኩል የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን #አላስተናግድም ሲል በጥብቅ ያሳሰበው አገልግሎቱ ፥ ፈተናው የሚሰጠው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥና የመፈተኛ ጊዜን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚገለፅ አሳውቋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፥ እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም ያለ ሲሆን ተፈታኞች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ #ዛይራይድ

ዛይራይድ በጋራ ሠርተን በጋራ እንደግ እያለ ባለቤትነቱን የሕዝብ ለማድረግ ለአሽከርካሪዎች እና ለማኅበረሰቡ የጀመረዉን የእክሲዮን ሽያጭ ቀጥሏል!
በዚህም መሰረት የአንድ አክሲዮን ዋጋ 1,000 (አንድ ሺህ) ብር፣ የትንሹ አክሲዮን ግዢ ብዛት ለአሽከርካሪዎች 25 (ሃያ አምስት) አክስዮን ወይም ሃያ አምስት ሺህ (25,000) ብር ሲሆን ከአሽከርካሪዎች ውጪ ላሉት የማህበረሰባችን ክፍል ደግሞ 75 (ሰባ አምስት) አክስዮን ወይም ሰባ አምስት ሺህ (75,000) ብር ነው፡፡

የትልቁ አክስዮን ግዢ መጠን ደግሞ ለሁሉም አክስዮን ገዢዎች 5,000 (አምስት ሺህ) አክስዮን ወይም 5 ሚሊዮን ብር መሆኑን በታላቅ ደስታ እንገልጻለን፡፡

የክፍያ አፈጻጸምን በተመለከተ ደግሞ ለማንኛውም የአክስዮን መጠን ግዢ ክፍያ በቅድሚያ (በአክስዮን ግዢ ወቅት) በአንድ ጊዜ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን እያሳወቅን አክስዮኑን Visa እና Mastercard ተጠቅመው መግዛት እንደሚችሉ ስንገልፅ በደስታ ነው።

የአክስዮን ግዢውን በኦንላይን ለመፈፀም ከታች የሚገኘውን የዛይራይድ መስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡፡ www.zayride.com
ሆሴዕ ሪልስቴት ለመቄዶንያ አረጋውያን ማዕከል ድጋፍ አደረገ።

ሆሴዕ ሪልስቴት የካፒታል ሆቴል እና ሰፖ እህት ኩባንያ ግምታዊ ወጪያቸው ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የሌሊት ልብሶችና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ሆሴዕ ሪልስቴት ፥ " በአጭር ጊዜ ውስጥ በሪልስቴት ዘርፍ በመንቀሳቀስ በቅርቡ በአያት 49 አካባቢ በ23 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ለ300 አባወራዎች በ2 ዓመት ከስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የሪል እስቴት ቤቶችን ገንብቶ በማስረከብ በርካታ ቤቶችን በአጭር ጊዜ በጥራትና በብቃት ገንብቼ ታሪክ ሰርቻለሁ " ብሏል።

የሆሴዕ ትሬዲንግ ሀውስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የማነ ገብረሥላሴ ለመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር የአንድ ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ የጽዳት መገልገያ ቁሳቁሶችን በእርዳታ ለግሰዋል።

ሆሴዕ ሪልስቴት ከሚያከናውኗቸው ስኬታማ ሥራዎች ባሻገር በመቄዶንያ አረጋውያንና ህሙማን ማዕከል በመገኘት ትናንት በሙያና በጉልበታቸው ሀገር ላቆሙ አረጋውያንና ልዩ ልዩ ወገኖቻችን ድጋፍ የሚሆን ፦
- አንሶላ፣
-ፎጣ፣
- ብርድልብስ፣
- ፍራሾችን  እና የተለያዩ የጽዳት መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በብር 1 ማሊዮን በመግዛት ለመቄዶንያ አረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን ማዕከል መሥራች ለዶ/ር ቢኒያም በለጠ በሆሴዕ ሪልስቴት ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ምትኩ ልዑል አማካኝነት ተበርክቷል፡፡

የሆሴዕ ትሬዲንግ ሀውስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ኩባንያው እስከዛሬ የተለያዩ ሀገራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ መቆየቱን የገለፀ ሲሆን በቀጣይም እንደ መቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር ላሉ በጎ ተግባር ላይ ለሚሳተፉ ተቋማት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥለል ብሏል።

ስልክ ፦ 6966 or 0902222225 

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ድርድር

መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አዛዥ መሮ ዲሪባ ፥ የታጠቂ ቡድኑን ከፌደራል መንግሥቱ ጋር የሚያደራድር ሦስተኛ አካል መኖሩን ለቢቢሲ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።

ጃል መሮ አደራዳሪዎቹ እነማን እንደሆኑ በስም ከጥቀስ ተቆጥበዋል።

መሮ ዲሪባ ታጣቂ ቡድኑን ወክለው ከመንግሥት ጋር የሚደራደሩ የልዑክ ቡድን አባላት ወደ #ታንዛኒያ ጉዞ እያደረጉ ስለመሆኑ አሳውቀዋል።

መሮ ዲሪባ ይህ ንግግር በታንዛኒያዋ ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው #ዛንዚባር ደሴት ላይ እንደሚከናወን ገልጸው፤ " የጥይት ድምጽ ሳይሰማ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ መልስ የሚያገኝ ከሆነ በራችን ሁሌም ክፍት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

መሮ ፥ በቅርቡ ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና መንግሥት ሦስተኛ ወገን ባለበት በኬንያ ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘው የታጣቂ ቡድኑ ተወካዮች በቦታው ቢገኙም የመንግሥት ተወካዮች ግን ሳይገኙ ቀርተዋል ብለዋል።

" በሌሎች አገራት ግብዣ በኬንያ ለመገናኘት ቀጠሮ ነበር። ነገር ግን መንግሥት ሳይገኝ ቀረ "  ያሉት መሮ " በአሁኑ ድርድር ስኬት ላይ ጥርጣሬዎች ቢኖረንም የንግግር ሂደቱ ሰላም ሊያመጣ ይችላል የሚል ተስፋ አለኝ " ሲሉ ተናግረዋል።

" ንግግር መጀመሩ ጥሩ ነው። መነጋገር እና መፍታት ያለብን ብዙ ነገሮች ስላሉ ጉዳዩ በአንድ ጊዜ የሚጠናቀቅ አይሆንም " ሲሉ አክለዋል።

ከዚሁ ድርድር ጋር በተያያዘ ቢቢሲ የኢትዮጵያ መንግሥት ከታጣቂ ቡድኑ ጋር በሚደረገው ንግግር ፦
- የስዊድን፣
- የኖርዌይ፣
- የኬንያ፣
- የአውሮፓ ኅብረት እና የአሜሪካ ዲፕሎማቶች እንደሚገኙ ሁለት ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ምንጮች እንደገለፁለት ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ድርድር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ስለ #ድርድር ምንድነው ያሉት ? " ከኦነግ ሸኔ ጋር የሚደረገው ድርድር ከነገ ወዲያ በታንዛኒያ ይጀመራል። ይህንን ድርድር የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህዝብ አብዝቶ ይፈልገዋል። በዚህ ድርድር የሚሳተፉ ወገኖች ሁሉ የዛሬዋን ቀን እያሰቡ ፣ ከግጭት፣  ከጦርነት እንደማናተርፍ አውቀው ህግ እና ስርዓት ተከትለን ይቅር ተባብለን ሀገራችንን በጋራ ማነፅ እና መገንባት…
#ታንዛኒያ

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ #ታንዛኒያ ገብተዋል።

አቶ ደመቀ በ4 የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት ያደርጋሉ የተባለ ሲሆን የመጀመሪያውን ጉብኝታቸውን በታንዛኒያ ጀምረዋል።

ከታንዛኒያ በመቀጠል በኮሞሮስ ፣ ቡሩንዲ እና ዩጋንዳ ጉብምት ያደርጋሉ ተብሏል።

አቶ ደመቀ ዛሬ ታንዛኒያ ከገቡ በኃላ #በዛንዚባር የሚገኘውን የአፄ ኃይለሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ታንዛኒያ ለጉብኝት ያመሩት ትላንት የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ " ኦነግ ሸኔ " ሲሉ ከተጠሩት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር መንግሥት ነገ በታንዛኒያ ድርድር እንደሚጀምር ካሳወቁ በኃላ ነው።

አቶ ደመቀ የታንዛኒያ ጉዟቸው በ4 የአፍሪካ ሀገራት ለሚያደርጉት ጉብኝት የመጀመሪያ ሀገር ከመሆኑ በዘለለ ይደረጋል ከተባለው ድርድር ጋር ይገናኝ እንደሆነ ወይም በዚህ ድርድር ላይ ይገኙ/አይገኙ የታወቀም ሆነ ይፋ የተደረገ መረጃ #የለም

@tikvahethiopia
#Tigray

" በሳምንት 3 የትምህርት ፕሮግራሞች የነበሩትን ወደ 5 እና 6 በመቀየር አንድ ሴሚስተር የሚጨርሰውን ጊዜ እናሳጥራለን " - ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ

ትግራይ ውስጥ ትምህርት የሚጀምርበት ቀን ይፋ ተደርጓል።

የትግራይ ትምህርት ቢሮ ለ4 ዓመታት በኮቪድ-19 እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር ቀን ቆርጧል።

የመንግሥትም ይሁን የግል ተቋማት ከሚያዚያ 18 /2015 ዓ/ም ጀምሮ ምዝገባ የሚያከናውኑ ሲሆን ሚያዝያ 23 /2015 ዓ/ም መደበኛ የትምህርት ሂደት ይጀምራል ብሏል።

የትግራይ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ ለትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፤ የትምህርት ሂደቱ የሚጀምረው የተሟላ አቅርቦት እና ምቹ ሁኔታ ላይ ተኩኖ ሳይሆን ትውልድ ለማዳን የሚደረገው ርብርብ አንዱ አካል በመሆኑ ነው ብለዋል።

ተማሪዎች ያለፋቸውን ትምህርት ለማካካስ ምን ይደረጋል ?

የትግራይ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ የትምህርት አሰጣጡን እና የማካካስ ሂደቱን በተመለከተ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

" የተለመደው ሁለት ሴሚስተሮች ናቸው ፤ ይህ ማለት 10 ወራት ናቸው ፤ እኛ በዛ ላይ ማሻሻሎችን አድርገናል። አንዳንዱ በሳምንት 3 የትምህርት ፕሮግራሞች የነበሩትን ወደ 5 እና 6 በመቀየር አንድ ሴሚስተር የሚጨርሰውን ደግሞ በማሳጠር ከሌሎች የዓለም ሀገራት ተሞክሮ በመነሳት የትግራይ ምሁራን በተረባረቡበት ስኬጁል (የትምህርት መርሃግብር) እንዲሰጥ ታስቧል። "

ከቀናት በፊት የህፃናት አድን ድርጅት (Save the Children) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ፤ የሰላም ስምምነት ቢፈረምም በትግራይ 2.3 ሚሊዮን ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ አሳውቆ ነበር።

በክልሉ 85 በመቶ ትምሀርት ቤቶች ከባድ ወይም ከፊል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ሁሉም የህዝብ ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ መሆናቸውን ፤ 22,500 መምህራንም ያለ ደሞዝ ከሁለት አመት በላይ መቆየታቸውን ገልጾ ነበር።

@tikvahethiopia
#AmazonFashion

አማዞን ፋሽን ጥራት ያላቸው ዘመናዊ የቱርክ ሱፎችን በተለያየ አማራጭ ይዞላቹ ቀርቧል። በቡድን ለሚመጡ ተማሪዎች እና ሚዜዎች ጥሩ ቅናሽና ፓኬጅ አዘጋጅተናል።

አድራሻ: ፒያሳ ዶውንታውን ህንፃ ምድር ላይና 2ኛ ፎቅ   

ስልክ ፦ 0919339250 / 0911072936 

https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEc8iQJX1Zjgepjq1w
#ቴክኖ

በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ቴክኖ ሞባይል አዲሱን ስፓርክ 10 ሲሪየስ ስልክ በገበያ ላይ አዋለ!

በተጠቃሚዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያፈራው ቴክኖ ስፓርክ ስልክ አሁን ደግሞ ይበልጥ የዘመኑ መገልገያዎችን በመያዝ አንዲሁም የተጠቃሚዎችን ፍላጎት ከግምት በማስገባት የተመረተውን አዲሱ የስፓርክ 10 ሞዴል ለኢትዮጲያ ገበያ አቀረበ።

ለአያያዝ እና አጠቃቀም ምቹ ሆኖ የተሰራው የስፓርክ 10 ሲሪየስ የተሰኘዉ ሞዴል በተለይ በባለ 32 ሜጋ ፒክስል የፊትለፊት ካሜራ ፣ ዘመኑ ያፈራው ሚዲያቴክ G88 ጌም ፕሮሰሰር ፣ ብሎም ረጅም የአገልግሎት ጊዜ እንዲኖረው ታስቦ የተገጠመለት በባለ 5000 ሚሊ አምፒር ባትሪ በሁሉም ረገድ ከፍተኛ አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተመረተ ስልክ አድርጎታል።

በየትኛውም የስልክ መሸጫ መደብሮቻችን ያገኙታል። ለበለጠ መረጃ: Facebook, Instagram, Tiktok

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Spark10Series #TecnoMobile #Ethiopia #Spark10pro