#ጫሞ
በደቡብ ክልል ጫሞ ሐይቅ ላይ በጀልባ ሲጓዙ የነበሩ 8 ሰዎች፤ ባጋጠማቸው የማዕበል አደጋ ምክንያት ሰጥመው ህይወታቸው አለፈ።
" ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " የአማሮ ልዩ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አደጋው የደረሰው ትላንት ቅዳሜ ከሰዓት ለኃላ ነው።
ባለሞተር ጀልባው የአማሮ ልዩ ወረዳ አልፋጮ ቀበሌ ነዋሪዎችን አሳፍሮ ወደ አርባ ምንጭ በመጓዝ ላይ ሳለ ነው በጫሞ ሐይቅ ላይ በነበረው ማዕበል የመስጠም አደጋው ያጋጠመው።
በአደጋው የጀልባውን ሹፌር ጨምሮ ስምንት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
አደጋው መከሰቱ እንደታወቀ የተጎጂዎችን ህይወት ለማትረፍ ጥረት ቢደረግም በጫሞ ሐይቅ ላይ በነበረው ከፍተኛ ማዕበል ምክንያት አልተሳካም።
ከአደጋው መድረስ በኋላ ከአርባ ምንጭ ከተማ በመጡ ዋናተኞች ጭምር ሕይወት ለማዳን ቢሞከርም በሰዓቱ የነበረው ማዕበል አላስቻለም ተብሏል።
በጫሞ ሐይቅ ላይ የነበረው ማዕበል ዛሬ ጠዋት ጋብ ማለቱን ተከትሎም ፤ የሟቾችን አስክሬን ለማግኘት ፍለጋው መቀጠሉን የወረዳው ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።
(እስካሁን የተገኘ አስክሬን የለም)
Credit : Ethiopia Insider
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#ጫሞ በደቡብ ክልል ጫሞ ሐይቅ ላይ በጀልባ ሲጓዙ የነበሩ 8 ሰዎች፤ ባጋጠማቸው የማዕበል አደጋ ምክንያት ሰጥመው ህይወታቸው አለፈ። " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " የአማሮ ልዩ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አደጋው የደረሰው ትላንት ቅዳሜ ከሰዓት ለኃላ ነው። ባለሞተር ጀልባው የአማሮ ልዩ ወረዳ አልፋጮ ቀበሌ ነዋሪዎችን አሳፍሮ ወደ አርባ ምንጭ በመጓዝ ላይ ሳለ ነው በጫሞ ሐይቅ ላይ በነበረው…
" ተሳፋሪዎችን ከዚህ በኋላ በሕይወት የማግኘት ተስፋው ተሟጧል " - የአማሮ ልዩ ወረዳ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ
የደቡብ ፖሊስ ትላንትና በ #ጫሞ_ሐይቅ ላይ ለሰመጠችው ጀልባ መንስኤው ከመጠን በላይ መጫን እና ባልተለመደ ሁኔታ የተከሰተ ማዕበል ነው ብሏል።
የዞን ፖሊስ በበኩሉ ጀልባዋ ከሥምንቱ ሰዎች በተጨማሪ #ሙዝ እና #ዕቃ መጫኗን አሳውቋል።
የሕይወት አድን ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ያለው ፖሊስ ለዚህም የተለያዩ ጀልባዎችና ዋናተኞች ፍለጋ ላይ መሆናቸውን ገልጿል።
በተከናወነው የፍለጋ ሥራ ከጫማዎች እና የተለያዩ አልባሳት ባለፈ የተገኘ ነገር እንደሌለ ተገልጿል።
የአማሮ ልዩ ወረዳ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጠው ቃል እስካሁን ድረስ በሕይወት የተገኘ አለመኖሩን ጠቁመዋል።
ተሳፋሪዎችን ከዚህ በኋላ በሕይወት የማግኘት ተስፋው መሟጠጡንም ቢሮው ገልጿል።
(ኤፍቢሲ)

ካህኑን ማን ገደላቸው ? " ኃይሌ ጋርመንት " የሁርሲሳ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ቀዳሽ ካህን ቀሲስ ዐባይ መለስ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ አካላት በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። ካህኑን የሚያውቋቸው አገልጋዮች /ምዕመናን ስለነበረው ሁኔታ / ስለጥቃቱ ምን አሉ ? (ለማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ከተናገሩት የተወሰደ) ቃላቸውን የሰጡ ምዕመን አንድ ፦ " ትላንት/መጋቢት…
#መግለጫ
በኢትዮጵያ ኦርቶኮስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ፤ መንግስት የቄስ ዓባይ መለሰን ገዳዮች ተከታትሎ ለፍርድ ያቅርብ አለ።
ሀገረ ስብከቱ በሰጠው መግለጫ ፤ " መንግሥት የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ በመሆናቸው ምክንያት በአሰቃቂ ሁኔታ በመንገድ ላይ ተደብድበው ሕይወታቸው እንዲያልፍ የተደረጉት የቄስ ዐባይ መለሰ ገዳዮችን ተከታትሎ ለፍርድ ያቅርብ " ብሏል።
አክሎም ፤ " ችግሩን ከሥር ከመሠረቱ በመፍታት የአገልጋዮችንና የምእመናን መብት እንዲያስከብር " ሲል ጠይቋል።
ከዚህ ባለፈ በሸገር ከተማ አስተዳደር አብያተ ክርስቲያናትን የማፍረስ ድርጊት እየተፈፀመ መሆኑን በመግለፅ ይህ ድርጊት በአስቸኴይ እንዲቆም እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።
እስካሁን የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያናት ቦታ ተመላሽ እንዲያደርግ እና የፈረሰውን ቤተ ክርስቲያንም በራሱ ወጪ እንዲያሠራ እንዲደረግ ሀገረ ስብከቱ ጠይቋል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

ፎቶ / ቪድዮ ፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ የሆነው ቼልሲ ትላንት እሁድ እለት በክለቡ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ክፍት የሆነ የ " ኢፍጣር " ስነሥርዓት በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም አስተናግዷል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን በምዕራብ ለንደኑ ግፉዝ ስታዲየም ተሰብስበው የኢፍጣር ስነስርዓቱን ያከናወኑ ሲሆን ስነስርዓቱ የተዘጋጀው በቼልሲ ፋውንዴሽን እና በ " ረመዷን ቴንት ፕሮጀክት " ነው።
Video Credit : Bein Sport
@tikvahethiopia
በመቶዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን በምዕራብ ለንደኑ ግፉዝ ስታዲየም ተሰብስበው የኢፍጣር ስነስርዓቱን ያከናወኑ ሲሆን ስነስርዓቱ የተዘጋጀው በቼልሲ ፋውንዴሽን እና በ " ረመዷን ቴንት ፕሮጀክት " ነው።
Video Credit : Bein Sport
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ብ/ጄነራል ተፈራ ማሞ ምን አሉ ?
የቀድሞ የአማራ ልዩ ኃይል አዛዥ ብ/ጄነራል ተፈራ ማሞ ፤ ከሀገር ውጭ ህክምናዬን እንዳልከታተል ያገዱ አካላት ለምን እንዳገዱ ምክንያት የላቸውም ፤ ህክምናዬን በአፋጣኝ ካላደረኩ ቀኝ እግሬን እስከማጣት ሊያደርሰኝ ይችላል ብለዋል።
ቀደም ሲል በእርስ በእርስ ጦርነት የጥይት ምት እንዳለባቸው የገለፁት ጄነራሉ በተለያዩ ምክንያቶች በአግባቡ ህክምና እንዳልተከታተሉ ገልጸዋል።
እግራቸው ውስጥ ወደ 8 የሚደርሱ ፍንጣሪዎች መሰግሰጋቸውን የገለፁት ጄነራል ተፈራ ፤ እየቆየ ሲሄድ ነርቫቸውን በተደጋጋሚ እየነኩ መሆናቸውን እና የህክምና ባለሞያዎች የተሻለ ህክምና ካላገኙ እየከፋ እንደማሄድ እንደገለፁላቸው አስታውሰዋል።
ለዚሁ ህክምና ወደ እስራኤል ሀገር ለመሄድ ስርዓቱን ጠብቀው ያለውን ነገር ጨርሰው ሊወጡ ሲሉ መከልከላቸውን አስረድተዋል።
ብ/ጄነራል ተፈራ ፥ " ዓላማዬ ህክምና ነበር ምንድነው ምክንያቱ ብዬ ስጠይቅ ' እንድትወጣ አልተፈለገም ' የሚል መልስ ሰጡኝ በዛ ምክንያት ጉዞው ተደናቀፈ ፤ አሁን ህመሙ እየጨመረ መጥቶ አላንቀሳቅሰኝ አለ ፤ የነርቭ ስርዓቴም እየተናካ በመሆኑ ለመርገጥም ተቸግሬያለሁ ፤ አንዳንዴ እስከ ጉልበቴ ድረስ ይሰማኛል " ብለዋል።
አክለው ፤ " ገንዘብ ስጡን አላልነም ፣ እኔ ሄጄ መታከም አለብኝ ነው። ለምን እንደሚያግዱ እንኳን ምክንያት የላቸውም ፤ ምንድነው ምክንያቱ ለማገድ ? ህክምና ማግኘት ያለብኝን ማግኘት አለብኝ ምንድነው ምክንያታቸው ፤ ሰው ቢሰቃይ ይደሰታሉ እነዚህ ሰዎች ፤ አሁን መሄድ የለበትም ብለው ነው ከፃፉት አለ ማስረጃው ምንድነው ምክንያታቸው ወደዚህ አይነት ነገር ለምንድነው የሚገቡት ፤ መታከም አለብኝ ጤንነት የመብት ጉዳይ ነው ጤንነቴ አደጋ ላይ ነው ። እነዚህ ሰዎች በሌላ ሰው ቁስል ይደሰታሉ እንዴ ? ምንድነው የሚያስደስታቸው ? እነዚህ ናቸው ሀገር እየመሩ ያሉት ሀገር ሲመራ ሰፋ ብሎ በእኩልነት አይቶ እንጂ ካገኘው ከግለሰብም ከዚያም ጋር እየተናከሰ ነው እንዴ የሚሄደው ? " ሲሉ ተናግረዋል።
ብ/ጄነራል ተፈራ ፥ አትሄዱም ብሎ የከለከላቸውን ኃላፊ " ለምንድነው የማልሄደው ? " ብለው እንደጠየቋቸውና ኃላፈው ሄደው እንዲታከሙ እንደሚፈልጉ ነገር ግን ከላይ ያሉት አካላት እግዱን እንደጣሉ እንደነገሯቸው አስረድተዋል።
ብ/ጄነራል ተፈራ ማሞ ዶክተሮች ያዘዙት የህክምና ማስረጃ እንዳላቸው ገልጸው አግባብ ያለሆነው እግድ ተነስቶ ህክምናቸውን እንዲከታተሉ እንዲደረግ ብለዋል።
" መንግስት ሆደ ሰፊ መሆን አለበት ምክንያቱም ሀገር ነው እየመራ ያለው " ያሉት ብ/ጄነራሉ " ከግለሰቦች ጋር በሚደረግ ንትርክ ብዙ ርቀት መሄድ አይቻልም ፤ የምለው ነገር ቀና ቢሆኑና ህክምናውን በወቅቱ ብወስድ ምክንያቱም ህግ እና ስርዓት አለ በዚህ መሰረት ሄጄ ታክሜ ምመጣበት እድል ቢፈጠር ይሄን ያለምንም ነገር እንደ በቀል ባይወስዱት " ብለዋል።
ብ/ጄነራል ተፈራ ማሞ ከባለሃብቶች ለህክምና ወጪያቸው እገዛ ይፈልጉ እንደሆነ ተጠይቀው " ባላሃብቶች ለኔ ከሚያደርጉ ስራ ላጣው ወጣት የስራ ዕድል ይፍጠሩ እኔ በራሴ እታከማለሁ የውጭ ጥያቄ አይደለም እኔ የምፈልገው እንድታከም እድሉን ላግኝ ነው " ብለዋል።
NB. ይህ የብ/ጄነራል ተፈራ ማሞ ቃል የተወሰደው " መድሎት " ለተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ ከሰጡት ቃለምልልስ ነው።

#ExitExam
ምን ያህል ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ?
የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ አመለወቅር ህዝቅኤል በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በተመለከተ (ምን ያህል ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ፣ ዝግጅት እና ፈተናውን ማለፍ የማይችሉ ተማሪዎችን በተመለከተ) ከሰሞኑን ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።
ምን አሉ ?
ወ/ሮ አመለወርቅ እዝቅኤል ፦
" አሁን የለየናቸው አሉ ፤ የደረሰን መረጃ አለ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎች ናቸው እጃችን ላይ ያሉት።
ነገር ግን ጥር ላይ በተለያየ ምክንያት ያላጠናቀቁ ልጆች በአንደኛ ሴሚስተር የሚያጠናቅቁና ወደ ምዘናው ሊመጡ የሚችሉ ልጆች ሊኖሩ ይችላሉ።
ከዛ ባሻገር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዚህ System ውስጥ የሚያልፉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የደረሱን መረጃዎች አሉ።
አሁን በቁጥር ነው የተቀበልነው ልክ እንደ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በስም እያንዳንዱ ስም በሚመጣ ሰዓት የተወሰነ የቁጥር ለውጥ ሊኖረው ይችላል አሁን ባለንበት ሁኔታ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎችን እንፈትናለን ብለን እናስባለን።
ከመጀመሪያው ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች በኩል ተማሪዎች መረጃው እንዲደርሳቸው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው የሚገኘው። ከዛ ባሻገር አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ሞዴል ፈተናዎች እንዲፈተኑ በማድረግ፣ psychologically እንዲዘጋጁ እንዲያጠኑ እየተሰራ ነው ተማሪዎችን በዛ ልክ አውቀው እየሰሩ ነው።
ፈተናው እንዴት manage ይደረጋል በሚለው ላይ የተለያዩ ማስፈፀሚያዎች ወደ ታች ወርደዋል በዚያ መሰረት ቅድመ ዝግጅቶች እየተደርጉ ነው የሚገኙት። "
የመጀመሪያውን ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ?
" ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች መልሰው መላልሰው የሚወስዱበት ዕድል አለ።
ይሄ የሚሆነው እንዴት ነው የመጀመሪያው ዙር መንግሥት በራሱ መንገድ የሚያስኬደው ነው ከዛ በኃላ ልክ 12ኛ ክፍል Private እንደሚፈተነው ሁሉ መውጫ ፈተና ላይም ዝግጁ ነን በሚሉ ሰዓት በተዘጋጁ እና ይሄን ፈተና አልፋለሁ ብለው እራሳቸውን አብቅተው በሚመጡበት ሰዓት መፈተን ይችላሉ። ተፈትነው ሲያልፉ ዲግሪያቸውን የሚወስዱበት አሰራር አለ።
እስከዛ ድረስ ደግሞ ለምሳሌ የመውጫ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ የሚያስገኘውን ፈተና ማለፍ ባይችሉ እንኳን ዝቅ ባሉ ደረጃዎች በLevel ደረጃ ባሉት (ከዲግሪ በታች ባሉ መመዘኛዎች) ተፈትነው ልክ COC እንደሚፈተነቱ ተፈትነው ማለፍ የቻሉበት ደረጃ ላይ Certify ይደረጋሉ በዛ ስራ ማግኘት የሚችሉበት አማራጭ ይኖራቸዋል። "

#AwashBank
ታታሪዎቹ !
የስራ ፈጠራ ውድድር በቅርብ ቀን በOBN እና ፋና ቴሌቪዥን ይጠብቁን !!
#Tatariwoch #EmpoweringTheVisionaries
(አዋሽ ባንክ)
ታታሪዎቹ !
የስራ ፈጠራ ውድድር በቅርብ ቀን በOBN እና ፋና ቴሌቪዥን ይጠብቁን !!
#Tatariwoch #EmpoweringTheVisionaries
(አዋሽ ባንክ)
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተሳፋሪዎችን ከዚህ በኋላ በሕይወት የማግኘት ተስፋው ተሟጧል " - የአማሮ ልዩ ወረዳ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ የደቡብ ፖሊስ ትላንትና በ #ጫሞ_ሐይቅ ላይ ለሰመጠችው ጀልባ መንስኤው ከመጠን በላይ መጫን እና ባልተለመደ ሁኔታ የተከሰተ ማዕበል ነው ብሏል። የዞን ፖሊስ በበኩሉ ጀልባዋ ከሥምንቱ ሰዎች በተጨማሪ #ሙዝ እና #ዕቃ መጫኗን አሳውቋል። የሕይወት አድን ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ያለው ፖሊስ ለዚህም…
" የአራት ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል " - የጋሞ ዞን ፖሊስ
በጫሞ ሐይቅ ላይ በደረሰው የሞተር ጀልባ መገልበጥ አደጋ ከሰጠሙ ሰዎች መካከል የአራቱ አስከሬን መገኘቱን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።
የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ም/ኮማንደር ደገፌ ደበላ እንደገለጹት በጫሞ ሐይቅ ላይ በደረሰ የጀልባ መስጠም አደጋ ከሞቱ ስምንት ሰዎች መካከል የአራት ሰዎች አስክሬን መገኘቱን ገልጸዋል።
እስከ አሁን የሶስት ወንዶች እና የአንዲት ሴት አስክሬን መገኘቱን የተናገሩት ምክትል ኮማንደሩ የሟቾችን አስክሬን የማፈላለግ ሥራው በጸጥታ ኃይሉና በጀልባ ኦፕሬተሮች በመታገዝ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።