TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የኤርትራ ጦር ከትግራይ የመውጣት ሂደት በጣም አዝጋሚ እና ገና ያላለቀ ነው " - ተመድ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ፤ የኤርትራ ሠራዊት ከትግራይ የመውጣቱ ሂደት " በጣም አዝጋሚ " ነው ብሏል።

በፕሪቶሪያ ግጭትን በዘላቂነት የማቆም ስምምነት እና በናይሮቢ የትግበራ ሰነድ መሰረት ኤርትራ ጦሯን ከትግራይ ማስወጣት እንዳለባት ቢያትትም ጦሯ ጠቅልሎ አለመውጣቱን የምክር ቤቱ ምክትል ኮሚሽነር ናዳ አል ናሺፍ ገልፀዋል።

ጄኔቫ ውስጥ እየተካሄደ ባለ 52ኛው ዓመታዊው የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ላይም ኮሚሽነሯ የኤርትራ ጦር ከትግራይ የመውጣት ሂደት " በጣም አዝጋሚ እና ገና ያላለቀ " ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ቀጣይነት ያለው ክትትል እንዲደረግ አሳስበዋል።

በተመሳሳይ በዚሁ ጉባኤ ላይ ፤  ኤርትራ ወታደሮቿን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከትግራይ እንድታስወጣ የአውሮፓ ኅብረት ጥሪ አቅርቧል። በኤርትራ ጦር የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲመረምርም ጠይቋል።

በዚሁ ጉባኤ ፤ የኤርትራ ሰብዓዊ መብት አያያዝ አሳሳቢ እና በአሁንም ወቅት መሻሻል አለማሳየቱን በተመለከተበት በዚህ ጉባኤ ላይ ተገልጿል፤ ጦሯ በትግራይ ውስጥ በፈጸመው መጠነ ሰፊ ጥሰትም ተጠያቂነት ለማስፈን ምንም አይነት እርምጃ አለመውሰዷ ተነስቷል።

ተመድ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጋራ ባደረጉት ምርመራ እነዚህ መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ይፋ ቢሆኑም፣ በኤርትራ በኩል ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ምንም አይነት ሥርዓት አለመዘርጋቱንዳ ተገልጿል።

የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ ከወራት በኋላ የኤርትራ ወታደሮች ግድያዎችን መፈጸማቸውን እንዲሁም የመድፈር ወንጀል ክሶች እየቀረበባቸው ይገኛል።

More : https://telegra.ph/BBC-03-07-2

#BBC

@tikvahethiopia
#EOTC

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አባቶች ጋር በወቅታዊ የቤተክርስትያን ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተገልጿል።

በዚህም ውይይት ወቅት ችግሮችን ለመፍታት ቃል የገቡ ቢሆንም አሁንም ችግሮች አልተፈቱም ተብሏል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ያቋቋመችው የሕግ ኮሚቴ አባል የሆኑት የሕግ ባለሙያና ጠበቃ አያሌው ቢታኔ ለአዲስ ማለዳ የሰጡት ቃል ፦

" ፕሬዝዳንቱ በቤተክርስያን ጉዳይ የታሰሩ ሰዎች እስከ ዛሬ ማክሰኞ ድረስ ይፈታሉ ብለው ቃል የገቡ ቢሆንም፣ ሽንገላ የሚመስል ነገር እየተከናወነ ነው።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥትና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ሕግን የማስፈጸም ግዴታ እያለባቸው ያለባቸውን ኃላፊነት ባለመወጣታቸው ምክንያት አሁንም በርካታ የሕግ ጥሰቶችና የንብረት ውድመቶች እየደረሱ ነው።

ትናንት ሰኞ በፍርድ ቤት እግድ የተጣለባቸውና ከቤተክርስትያኗ ቀኖና ውጭ የተሾሙ ግለሰቦች በአሰላ የአቡነ ያሬድ መንበረ ጵጵስናን ሰብረው የገቡ ሲሆን፣ ይህም በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ድጋፍ የሚደረግ ሕገ-ወጥ ድርጊት ነው።

ሻሸመኔና አርሲ ነገሌን ጨምሮ በበርካታ የኦሮሚያ አካባቢዎች አሁንም በርካታ ካህናትና ምዕመናን ያለምንም ጥፋት ታስረው ይገኛሉ።

ከዚህ በፊትም በመንግሥት በሁለት ቀን ውስጥ ይፈታሉ ተብለው የነበሩ ታሳሪዎች ሳይፈቱ በርካታ ቀናት ተቆጥረዋል።

ይህንንም ተከትሎ መንግሥት ራሱ ለገባው ቃል ተገዢ እየሆነ አይደለም። በዚህም ምክንያት ካህናትና ምዕመናን ለበርካታ ችግሮች ተጋልጠዋል ቤተክርስትያኗም ጉዳት እየደረሰባት ይገኛል።

ቤተክርሰትያኗ ከመንግስት ጋር የደረሰችው ስምምነት በመንግሥት በኩል  ሊደረግ ታስቦ የነበረውን ሰልፍ የማስቀረት ጉዳይ ብቻ ተደርጎ መታየት የለበትም።

አሁን ባለው ሁኔታ ችግሩ እየከፋ ነው እየሄደ ያለው።

ምዕመናኑ ምንም እንኳን በሚፈጸሙ ድርጊቶች ያዘኑ ቢሆንም የቤተክርስትያን አባቶችን ትዕዛዝ እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

መንግስት የገባውን ቃል አልመፈጸሙ፣ በሕግ እንዲያስፈጽም የተሰጠውን ኃላፊነት አለመወጣቱና የያዘው አካሄድ ሕዝብና አገርን ዋጋ የሚያስከፍል ነው።

ለዚህም እስከ ዛሬ ማክሰኞ ድረስ ሁሉንም ጉዳዮችና የሕግ ጥሰቶች ለማስተካከል በኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት ሽመልስ አብዲሳ የተገባው ቃል እንዲፈጸም እንጠይቃለን።

የቤተክርስትያን ጉዳይ ወደ ከፋ ነገር ሳያመራ መንግስት ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል። "

በሌላ በኩል ፤ በአዋሽ ሰባት ከታሰሩ ወጣቶች መካከል ከ300 በላይ የሚሆኑት መለቀቃቸው የተሰማ ሲሆን ወጣቶቹ ብጹአን አባቶች በቦታው ሊያደርጉት የታሰበው ጉብኝት መሰማቱን ተከትሎ መፈታታቸው ተነግሯል፡፡

ይሁንና አሁንም ድረስ በቦታው ታስረው የሚገኙ ወጣቶች እንዳሉ የታወቀ ሲሆን፣ ከሰላሳ የማይበልጡት ታሳሪዎች እንዲፈቱ ጊዜያዊ የሕግ ኮሚቴው እየሰራ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

(አዲስ ማለዳ ጋዜጣ)

@tikvahethiopia
The Jasiri Talent Investor Program is here to embark on the entrepreneurship journey with you! Jasiri is here to create a launchpad for you to become a change-maker in your community. Aspiring women entrepreneurs are highly encouraged to apply.

Visit jasiri.org/application to apply.
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙት ሃላፊ ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ትላንት ለአሀዱ በሰጡት ቃለ ምልልስ ወቅት የአቅም ማሻሻያ ትምህርት " ለአንድ ዓመት " በሚል የተገለፀው ስህተት እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀው እንዲታረም ብለዋል።

የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) የሚሰጠው ከዚህ በፊት እንደተገለፀው ለአራት ወራት እንደሆነ አመልክተዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከግማሽ በታች የሆኑትን በቅድመ መደበኛ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ጉድለታቸውን እንዲሞሉ ኮርስ እንደሚወስዱ ከዚህ ቀደም መግለፁ ይታወሳል።

እነኚህ ተማሪዎች ያለባቸውን ጉድለት የሚሞላው የሬሜዲያል ፕሮግራም ይከታተላሉ፤  ዋና ዋና ይዘቶች እና መታወቅ ያለባቸውን እስከ #አራት_ወር ተወስዶ ተማሪዎቹ አቅማቸውን የሚሞላ ትምህርቶችን እንዲማሩና እንዲከልሱ ይደረጋል።

የሬሚዲያል ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ተማሪዎች ተከታታይ ምዘና እንዲኖራቸው ተደርጎ በየተቋማት የሚሰጠው ምዘና 30 % እና በማዕከል የሚዘጋጀው ፈተና 70% ተመዝነድ በድምሩ አማካይና ከዚያ በላይ (50 ከመቶና በላይ) የሚያመጡት በመንግስት ተቋማት ሲከታተሉ የቆዩት በዚያው ተቋም መቀጠል የሚችሉ ሲሆን በራሳቸው ወጪ ሸፍነው ወደ ግል ተቋማት ሄደው መማር ቢፈልጉ መብታቸው የተጠበቀ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#AxumUniversity

አክሱም ዩኒቨርስቲ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሳቢያ የደረሰበት ጉዳት 15 ቢሊዮን ብር እንደሚገመት ማስታወቁን " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።

ላለፉት 19 ወራት ትምህርት መስጠት አቁሞ የቆየው ዩኒቨርስቲው፤  ሊያከናውነው ላቀደው ዳግም ግንባታ የድጋፍ ጥሪ አቅርቧል።

የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ገብረእየሱስ ብርሃነ የሰጡት ቃል ፦

- ዩኒቨርስቲው በጦርነቱ ሳቢያ በደረሰበት #ውድመት እና #ዘረፋ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የሚያስችሉት ቁሳቁሶች እና መሳሪያዎች አጥቷል።

- ሙሉ ለሙሉ የተዘረፉ እና ከወደሙ የዩኒቨርስቲው ንብረቶች ውስጥ ኮምፒውተሮች፣ የላብራቶሪ መሳሪያዎች፣ ሰርቨሮች እና የቢሮ በሮች ይገኙበታል።

- ዩኒቨርስቲው ከጦርነቱ በፊት የነበሩት 60 ገደማ ተሽከርካሪዎች ተዘርፈው እና ተቃጥለው አሁን በስራ ላይ የሚገኘው #አንድ_መኪና ብቻ ነው።

- በጥር ወር ላይ በተደረገ ዳሰሳ የደረሰው ውድመት 15 ቢሊዮን ብር ይደርሳል።

- ጉዳት የደረሰባቸውን ንብረቶች በተወሰነ መልኩ በመተካት ወደ ስራ ለመግባት ታቅዷል።

- ለሚያከናውነው ዳግም ግንባታ እና ጥገና ስራ የገንዘብ እና የማቴሪያል ድጋፍ እንዲደረግልን  ጠይቀናል። የድጋፍ ጥሪው ለዓለም አቀፍ እና ለሀገር በቀል አጋር ድርጅቶች፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ነው።

- ዩኒቨርስቲው የሚያገኘውን ድጋፍ በፌደራል መንግስት ከሚመደበለት በጀት ጋር በማጣመር በአጭር ጊዜ ውስጥ የመማር ማስተማር አገልግሎቱን ለመስጠት ታቅዷል። 

- ቁሳቁሶችን በተወሰነ መልክ ቅድሚያ እየሰጠን ካስገባን፤ የግዢ ሂደቱ ፈጣን ከሆነ፤ ተማሪዎችን #በሶስት_ወር ውስጥ ማስገባት እንችላለን። በትግራይ ክልል የሚኖሩ እና ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት ያቋረጡ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን ትምህርት ማስጨረስ ላይ ትኩረት ይደረጋል።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ከፌደራል መንግስት በጀት ባይለቀቅለትም፤ በስሩ ለሚገኘው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 43 መምህራንን ለመቅጠር ከ2 ሳምንት በፊት ማስታወቂያ አውጥቷል።

የቅጥር ሂደቱ የሚፈጸመው በትምህርት ሚኒስቴር ተፈቅዶ፣ በጀት ሲለቀቅ መሆኑ ተገልጿል።

ከፌደራል መንግስት የሚለቀቀው በጀት፤ ለዩኒቨርስቲው ሰራተኞች ደመወዝ ለመክፈል እና ትምህርት ለማስጀመር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

#አራት_ሺህ ገደማ የሚሆኑት የዩኒቨርስቲው መምህራን እና ሰራተኞች ከሐምሌ 2013  ዓ.ም. ወር ጀምሮ #ደመወዝ_አለማግኘታቸውን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።

Credit : www.ethiopianInsider.com

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል " - የንግድ እና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር

ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ የሌሎች ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህም ከየካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት እስከ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ፦

- የቤንዚን፣
- የኬሮሲን፣
- የነጭ ናፍጣ፣
- የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና ከባድ ጥቁር ናፍጣ የመሸጫ ዋጋ በየካቲት ወር #በነበረው_ዋጋ እንዲቀጥሉ መወሰኑ ተገልጿል።

የአውሮፕላን ነዳጅ ግን የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያ እንደተደረገበት እና በዚሁ መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ የአውሮፕላን ነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሊትር 70.60 (ሰባ በር ከስድሳ ሣንቲም) መሆኑን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ማስታወቁን ኢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ነፃ_የትምህርት_ዕድል

LG-KOICA Hope የቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግል ከፍለው መማር ለሚቸገሩ የመግቢያ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን #በነጻ ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

ኮሌጁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በላከው መልዕክት በዚህ ዙር እስከ 150 ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር መዘጋጀቱን ገልጾ የሀገር ዉስጥና የዉጭ ሀገር የሥራ ዕድል አማራጮችም እንዳሉት ጠቅሷል።

ከዚህ በተጨማሪ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸውና መስፈርቱን አሟልተው ለሚመረጡ የተመረጡ ተማሪዎች የምግብ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎችን እንደሚሸፍን ገልጿል።

ተጨማሪ ይመልከቱ : https://t.iss.one/tikvahethmagazine/18949

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" መንግስት በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ የጣለውን ገደብ ያንሳ " - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ም/ቤት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት መንግሥት በኢንተርኔት ግንኙት ላይ የጣለው ገደብ ሚዲያዎች ስራቸውን በአግባቡ ለህዝቡ ተደራሽ  እንዳያደርጉ እንቅፋት እየፈጠረ በመሆኑ ገደቡ እንዲነሳ መጠየቁን ለቲክቫህ በላከው መግለጫ አሳውቋል፡፡ ከሰሞኑን መንግስት በአንዳንድ የኢንተርኔት የግንኙነት መተግበሪያዎች…
#ETHIOPIA

ኢትዮጵያ ውስጥ የቴሌግራም፣ ፌስቡክ ፣ ዩትዩብ መሰል የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እስካሁን ምክንያቱ ግልፅ ባልተደረገበት ሁኔታ #ገደብ ከተደረገባቸው አንድ ወር ሊደፍን ነው።

የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ " ለምን ገደብ እንደተጣለ " እንዲሁም " ገደቡ መቼ እንደሚነሳ " በየትኛውም አካል በኩል #ለህዝቡ ማብራሪያም ሆነ ገለፃ ያደረገ የለም።

ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ እና ሌሎችም የማህበራዊ መገናኛዎች የተጣለባቸውን ገደብ በVPN በማለፍ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በላከው መግለጫ መንግሥት በኢንተርኔት ግንኙት ላይ የጣለው ገደብ ሚዲያዎች ስራቸውን በአግባቡ ለህዝቡ ተደራሽ እንዳያደርጉ እንቅፋት እየፈጠረ በመሆኑ ገደቡ እንዲነሳ መጠየቁ አይዘነጋም።

ምክር ቤቱ በሀገሪቱ ከተፈጠረው ኃይማኖታዊ አለመግባባቶች ጋር በተያያዘ የችግሩን ስፋትና ክብደት ከግምት በማስገባት ሊቀለበስ የማይችል አደጋን ምክንያት በማድረግ ካልሆነ በስተቀር ሕግን መሰረት በማድረግ #ሀሳብን_በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ መንግስት ገደብ ሊያደርግ እንደማይገባ ም/ቤቱ እንደሚያምን ማስታወቁን ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በሲዳማ እና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ ካለፈው ሳምንት እሁድ ጀምሮ የፀጥታ ችግር ተቀስቅሶ የሰዎች ህይወት መጥፋቱን ዜጎችም ከቄያቸው መፈናቀላቸውን የአካባቢው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጥቆማ ማድረሳቸው ይታወሳል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቪኦኤ የአማርኛ ክፍል ባሰራጨው የሬድዮ ዘገባ ፤ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ ጉቦሄማና ቦጨሳ በተቀሰቀሰ ግጭት እስካሁን 12 ሰዎች መገደላቸውን ፤ አሁንም ግን አስክሬን እየተፈለገ መሆኑና አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር እንዳልተለየ የተጎጂ ቤተሰቦች ገልጸዋል።

አንድ የተጎጂ ቤተሰብ ሁለት ወንድማቸው እንደተገደለባቸው ገልጸዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ጥቃት እንደፈፀሙ የገለጿቸው የምዕራብ አርሲ ዞን የነንሴቦ ወረዳ ሚሊሻዎች እና ቢጤኔሳ/በታኝ የተሰኘ ኢመደበኛ ቡድን ነው።

በሁለቱም በኩል ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች አመልክተዋል ያለው የሬድዮ ዘገባው ከታች እስከ ላይ ያሉ የመንግስት ኃላፊዎች ስለጉዳዩ አስተያየት እንዲሰጡ ለማድረግ ጥረት ቢደረግም አንዳንዶቹ " ስብሰባ ላይ ነን " በማለት ሌሎቹ ስልክ ባለማንሳታቸው ሊሳካ አልቻለም። የነሴቦ ወረዳ አስተዳደሪ አቶ ኡመር ጠና " በዚህ ጉዳይ ላይ መናገር አልፈልግም " ብለዋል።

አንድ የጭሪ ወረዳ የጤና ጣቢያ ሰራተኛ የስራ ኃላፊ በጥይት ተመተው የመጡ ተጎጂዎችን ስለማከማቸው እና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ወደ ሀዋሳ እና ቦና ሆስፓታል መላካቸውን ገልጸዋል።

የጤና ባለሞያው 28 ሰው ተጎድቶ መምጣቱን ከነዚህ ውስጥ 11 ሪፈር እንደተደረጉ አስረድተዋል፤ በጤና ተቋም ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች መኖሩን የሚገልፁት እኚሁ የጤና ባለሞያና የስራ ኃላፊ በየጫካው ህይወታቸው ያለፈውን እንዳልተቆጠረ ገልጸዋል።

የሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ተጎጂዎችን በተመለከተ ቅዳሜ እና እሁድ የቀዶ ጥገና ክፍል እድሳት ላይ ስለነበር ቁስለኛ እንዳልተቀበለ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሀዋሳ ቅርጫፍ በሲዳማ እና ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢ ስላለው ሁኔታ መረጃው እንዳለው ገልጾ በቅርብ ቀን በሪፖርት ይፋ አደርጋለሁ ሲል ለቪኦኤ የአማርኛው ክፍል ተናግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሲዳማ እና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ ካለፈው ሳምንት እሁድ ጀምሮ የፀጥታ ችግር ተቀስቅሶ የሰዎች ህይወት መጥፋቱን ዜጎችም ከቄያቸው መፈናቀላቸውን የአካባቢው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጥቆማ ማድረሳቸው ይታወሳል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቪኦኤ የአማርኛ ክፍል ባሰራጨው የሬድዮ ዘገባ ፤ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ ጉቦሄማና ቦጨሳ በተቀሰቀሰ ግጭት እስካሁን 12 ሰዎች መገደላቸውን…
#Update

የሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልል አዋሣኝ ከሆነው ከምዕራብ አርሲ ዞን ነሰቦ ወረዳ የተፈናቀሉ ዜጎች የሚመለከተው የመንግሥት አካል ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው መጠየቃቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ተፈናቃዮቹ በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው ያለው ዘገባው፤ ይኖሩበት በነበረው የምዕራብ አርሲ ዞን ነሰቦ ወረዳ - ቦርጮሳ ቀበሌ ባለፈው ዓርብ መሣሪያ የታጠቁ ሰዎች ግድያ መፈጸማቸውን ተከትሎ ወደ ሲዳማ ክልል ጭሪ ወረዳ ሸሽተው መጠለላቸውን ገልጿል።

የወረዳዎች መስተዳድር ባለሥልጣናት በበኩላቸው ነዋሪዎቹን በአጭር ጊዜ ወደ ቦታቸው ለመመለስ በቅንጅት እየሠራን እንገኛለን ብለዋል።

ተጎጂዎች እንዳሉት ከሆነ ዓርብ መሣሪያ የታጠቁ ሰዎች ለስብሰባ በተጠራው ነዋሪ ላይ ተኩሰው 12 ከገደሉና ሌሎች 38 ሰዎችን ካቆሰሉ በኋላ አብዛኛው የቀበሌ ነዋሪ በፍርሃት አካባቢውን ለቆ ወጥቷል።

ከግድያ በተጨማሪ የመኖሪያ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን በዚህም በርካቶች ሸሽተው የሲዳማ ክልል ጭሪ ወረዳ መገባታቸውና በትምህርት ቤቶችና በቀበሌ ጽህፈት ቤቶች ቅጥር ግቢ የተቀሩት ደግሞ በየዘመዶቻቸው ቤት ተጠግተው እንደሚገኙ ተመላክቷል።

ተፈናቃይ ወገኖች ፤ የኢትዮጵ ቀይ መስቀል ማህበር ውስን የዕለት ድጋፍ እንዳቀረበለቸው ከዚህ በስተቀር ግን የደገፋቸው አካል እንደሌለ በመግለፅ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በምዕራብ አርሲ ዞን የነሰቦ ወረዳንና በሲዳማ ክልል የጭሪ ወረዳ አመራሮች  የጋራ ምክክር ተደርጎ መግባባት ላይ እስኪደረስ የተናጠል መግለጫ እንዳይሰጥ ስምምነት በመኖሩ ዝርዝር ማብራሪያ ለመስጠት እንደሚቸገሩ እንደገለፁ ሬድዮ ጣቢያው አመልክቷል።

አሁን ላይ አመራሮቹ ከመንደራቸው ለቀው የወጡ ነዋሪዎችን በአጭር ጊዜ ወደቦታቸው ለመመለስ ከመግባባት ላይ መድረሳቸውንና ሂደቱ እንደተጠቃለለ የጋራ መግለጫ እንደሚሰጥ እንዳሳወቁ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በዘገባው ጠቅሷል።

@tikvahethiopia
ቁጥሮች ...

በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ከባድ ድርቅ በከፍተኛ ሁኔታ ዜጎቻችንን እየጎዳ ነው። እንስሳት እንደቅጠል ረግፈዋል ፤ አሁንም እየረገፉ ነው ፤ ዜጎችም በምግብ እጥረት ለተለያዩ የጤና ችግሮች እየተጋለጡ ነው።

እነዚህን ቁጥራዊ መረጃዎች ይመልከቱ ፦

▪️ደቡብ ክልል፤ ደቡብ ኦሞ ዞን ፦

- ከባድ ድርቅ የተከሰተው በ6 ወረዳዎች በደቡብ ኦሞ ከሚገኙ 13 ወረዳዎች (ማሌ፣ በና ጸማይ፣ ሐመር፣ ዳሰነች፣ ኛንጋቶም ፣ ስላማጎ) ።

- በድርቅ ምክንያት 14 ሺህ ከብቶች አልቀዋል።

- ከ337 ሺህ በላይ ሕዝብ ለምግብ እጥረት ተጋልጧል።

-  2.3 ሚሊዮን ከብቶች ክፉኛ በመዳከማቸው መንቀሳቀስ ሳይችሉ ባሉበት ቦታ ሆነው መኖ እየቀረበላቸው ይኛል።

- 303 ሺህ ለሚሆን ሕዝብ ለአንድ ወር የሚሆን የመጀመሪያ ዙር እርዳታ በመንግሥት አማካይነት ተደርጓል። ግን ችግሩ አሁንም እየሰፋ እየሄደ ነው በዚህም ለምግብ ክፍተት ሊጋለጡ የሚችሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው የሚሄደው።

- ዝናብ እየዘነበ አይደለም። አርሶ አደሮች ከብቶቻቸው እየሞቱ ነው። ሰው ወደ እርሻ ሥራው እየገባ አይደለም።

- ለተቸገሩት ሰዎች እርዳታ ማድርግ ያስፈልጋል።

▪️ሶማሌ ክልል ፦

- በሶማሌ ክልል ባለፉት 3 ዓመታት በቂ ዝናብ ባለመጣሉ በተለይ ደግሞ በዳዋ፣ አፍዴራ እና ሊበን ዞኖች ከባድ ድርቅ ተከስቷል።

- በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የቤት እንስሳት ሞተዋል።

- በዳዋ ዞን በ92 መጠለያ ጣቢያዎች ከ52 ሺህ በላይ ተፈናቃይ የቤተሰብ አባላት ተጠልለው ይገኛሉ።

- በዳዋ ዞን ብቻ ግመል፣ ከብት እና ፍየልን ጨምሮ ወደ 334 ሺህ እንስሳት ሞተዋል። 420 ሺህ በላይ እንስሳት ደግሞ ወደ ሞት እየተቃረቡ ነው።

- ከዳዋ ውጪ ባሉት ዞኖች የእንስሳት ሞት አልጀመረም።

- በሶማሌ ክልል ድርቅ በተከሰተባቸው በሶስት ዞኖች በቂ ባይሆንም ለሰው እና ለእንስሳት ምግብ እና መኖ ተከፋፍሏል፤ በዳዋ ተፈናቅለው ለሚገኙት ጨምሮ በአፍዴራ እና ሊበን ዞኖች ሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀል ባለመጀመራቸው ባሉበት ቦታ ድጋፍ እየቀረበ ነው።

መረጃው የደቡብ ኦሞ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤት እንዲሁም የሶማሌ ክልል ሕዝብ ግንኙነት ቢሮ ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ክፍል ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopia