#Repost
የካራማራ ድል !
የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ/ም የሱማሊያን ዚያድባሬ ጦር ለመመከት በካራማራ ጀግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የህይወት መሰዋዕትነት ከፍለው ወራሪውን ጦር ከሀገር ያባረሩበትና የሀገራቸውን ሰንደቅ ያውለበለቡበት ቀን ነው።
ዘንድሮ ይህ ድል 45ኛ አመት ሞልቶታል ቀኑም እየታሰበ ነው።
ከጦርነቱ በፊት ለረጅም ጊዜ የሶማሊያ ጦር በሶቪዬት ኅብረት ይደገፍ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ከአሜሪካ ጋር ወዳጅነት ነበረው። በወቅቱ አሜሪካ እና የሶቪየት ህብረት በቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ ነበሩ።
በቅድሚያ በሶቪየት ህብረት ከፍተኛ ድጋፍ የመጣው የዚአድባሪ ጦር የእናት ሀገር ጥሪ እያለ በተሰበሰበው የኢትዮጵያ ጦረኛ ካራማራ ላይ ድባቅ ተመትቶ ወደ መጣበት ተመልሶል፡፡
በጦርነቱ መጀመሪያ ሶማሊያን ስትደግፍ የነበረችው ሶቪየት ህብረት ወደ ኢትዮጵያ አዘንብላ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ እገዛ አድርጋለች ፤ አሜሪካ ደግሞ ወደ ሶማሊያ ፊቷን አዙራለች።
በጦርነቱ ኩባ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመንና ምሥራቅ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች አገራት አጋርነታቸውን ለኢትዮጵያ አሳይተዋል።
ከ16 ሺ በላይ የኩባ ወታደሮች በውጊያው እንደተሳተፉ መዛግብት ያሳያሉ። ደቡብ የመንም ጦሯን ለኢትዮጵያ አሰልፋ ነበር።
በተለያየ የፖለቲካ የትግል ሁኔታ፣ በተለያየ ቅራኔ ውስጥ የነበሩ የኢትዮጵያ ሀይሎች ሁሉ ስለ ሀገር አንድ ሆነው የዚያድባሬን ጦር የመከቱበት የካራማራ ጦርነት የኢትዮጵያ አንድነት ዳግም በጉልህ የታየበት ስለመሆኑ ይነገርለታል፡፡
በየአመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰበው የ " ካራማራ ድል " ዘንድሮም ለ45ኛ ጊዜ እየታሰበ ይገኛል፡፡
https://telegra.ph/Ethiopia-03-05
@tikvahethiopia

' ሰላተል ኢስትስቃ '
ነገ በመላ ሀገሪቱ "ሰላተል ኢስ ትስቃ" እንዲሰገድ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጥሪ አቅርቧል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቦረና ዞን በዝናብ እጥረት ምክንያት የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ " ሰላተል ኢስ ትስቃ " እንዲሰገድ ለመላው ምዕመን ጥሪ አድርጓል።
ነገ ሰኞ በመላው ሀገሪቱ እንዲሰገድ ጥሪ የቀረበው " ሰላተል ኢስትስቃ " ዝናብ በሚርቅበት ጊዜ የሚሰገድ ሰላት መሆኑን ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በሌላ በኩል ፤ ጠቅላይ ም/ቤቱ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን ዕርዳታ የሚውል ድጋፍ ማሰባሰቢያ የባንክ ቁጥሮችን ይፋ አድርጎ ድጋፍ እያሰባሰበ እንደሆነ ተሰምቷል።
ጠቅላይ ም/ቤቱ ይፋ ያደረጋቸው የባንክ ቁጥሮች ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 5582 ፣ ዳሸን ባንክ ሂሣብ ቁጥር 795571270973፣ ዘምዘም ባንክ ሂሣብ ቁጥር 222255፣ ሂጅራ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 308010 ፣ ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ቁጥር 1000093406226 ናቸው።

" ለእኛም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ይድረሱልን " - የዳዋ ዞን አስተዳደር
በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን አስተዳደር ባጋጠመ ድርቅ በርካታ እንስሳት የሞቱ ሲሆን የሰዎች ሕይወትም አደጋ ላይ መውደቁ ተገልጿል።
የዞኑ አስተዳደር ያለው ሁኔታ ከአቅም በላይ መሆኑን አስታውቋል።
ከኦሮሚያ የቦረና ዞን ጋር የሚዋሰነው ዞኑ፣ በድርቅ የተነሳ ከሚሞቱ እንስሳት አልፎ ሰዎች #ለሆስፒታል እየተዳረጉ መሆኑን ገልጿል፡፡
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሀቢቻ ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦
" የድርቁ ጉዳት ከዞኑ አቅም በላይ ነው።
ዞናችን ከቦረና ጋር በሁለት ወረዳዎች በኩል ይዋሰናል፡፡ ወደ 700 ሺሕ የሚጠጋ አርብቶ አደር ነዋሪ ያለው ሲሆን፣ ለ3 ተከታታይ ዓመታት የደረሰው ድርቅ ከብቱን በሙሉ ጨርሶበታል።
በክልሉ አደጋ ሥጋት ቢሮና በተለያዩ የዕርዳታ ድርጅቶች ርብርብ ዘንድሮ ለድርቁ ተጎጂዎች ዕርዳታ እየቀረበ ነው ይሁን እንጂ ዕርዳታው በቂ አይደለም። ችግሩም ከአቅም በላይ ነው።
በኦሮሚያ ክልል ለሚገኘው ለአጎራባቻችን ቦረና ዞን በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንዳለው ሁሉ፣ ለእኛም የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ይድረሱልን። "
ዳዋ ዞን በሥሩ ሞያሌ፣ ሙባረክ፣ ካደዱማና ሁደት የተባሉ አራት ወረዳዎች ያሉት ሲሆን ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ዝናብ ባለማግኘቱ ትልቁ የዳዋ ወንዝ ጭምር ደርቋል።
ድርቅ የሚቋቋሙ ግመሎችን ጨምሮ ከብቶችና ፍየሎች በከፍተኛ ቁጥር ማለቃቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ATTENTION
" ለሕዝቡ አስቸኳይ ዕርዳታ ካልደረሰለት አደጋው ከአሁኑ ሊብስ ይችላል "
በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ሀቢቻ ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦
" ሕዝቡ የሚኖረው በከብቶቹ ላይ ተመሥርቶ ነው፡፡ ድርቁ እስከ መቼ እንደሚቀጥል አይታወቅም፡፡
ለሕዝቡ አስቸኳይ ዕርዳታ ካልደረሰለት አደጋው ከአሁኑ ሊብስ ይችላል።
የሞተውን የእንስሳት ሀብት ቁጥር ገና እየተጠና ነው፤ በሰዎች ላይ የደረሰውንም ጉዳት እየተገመገመ ነው።
ስለጉዳቱ የተጣራ አኃዝ ባይኖረንም በምግብ እጥረት ችግር ወደ ሆስፒታል የገቡ ሰዎች መረጃ አለን። "
NB. አምና በሶማሌ ክልል ካሉ 11 ዞኖች በአሥሩ ከባድ የድርቅ አደጋ ደርሶ #ከአንድ_ሚሊዮን ያላነሱ እንስሳትን ገድሏል። የዳዋ ዞን ገና ከዚህ አደጋ ያላገገመ ሲሆን ዘንድሮም ከባድ አደጋ ገጥሞታል።
Credit : #Reporter

" ሌላ አዲስ ማሽን ካልመጣ በስተቀር አንድም ተጠግኖ ስራ ላይ የሚውል አንድ ብሎን እንኳን የለም " - አቶ ካሳሁን ፎሎ
ከሰሞኑን የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አመራሮችን ያቀፈ የልዑካን ቡድን በትግራይ ክልል፣ በጦርነት ምክንያት የወደሙ የኢንቨስትመንት ተቋማትን በአካል ተገኝተው ተመልክተዋል።
ልዑኩ ከጎበኛቸው የወደሙ ተቋማት መካከል የ " ሸባ ሌዘር ኢንዱስትሪ " እና " ሰማያታ እምነበረድ ፋብሪካ " ይገኙበታል።
ከጉብኝቱ በኃላ በመቐለ ውድመት ከደረሰባቸው የኢንቨስትመንት እና ኢንድስትሪ ተቋማት ሰራተኞች ጋር ውይይት ተደርጓል።
በዚህ መድረክም በጦርነቱ የደረሰው ውድመት፣ በሰራተኞች ላይ ስለደረሰው ጉዳት ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ምክክር ተደርጓል።
የኢሰማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በጉብኝታቸው የተመለከቱን እንዲህ ሲሉ ገልፀዋል ፥
" ሙሉ በሙሉ 100% የወደሙ ሌላ አዲስ ማሽን ካልመጣ በስተቀር አንድም ተጠግኖ ስራ ላይ የሚውል አንድ ብሎን የለም "
አቶ ካሳሁን ይህንን በመቐለ አካባቢ ባደረጉን ጉብኝት መመልከታቸውን አስረድተዋል።
" ሌሎቹ ስለራቁብን ብቻ ሳይሆን አንዳንዶቹ ቦታዎች ላይ የማንደርስባቸው አሁንም ጥሩ ያልሆኑ አካባቢዎች አሉ በደንብ ያልተፈቱ ጉዳዮች አሉ፤ ሁሉም ነገር ያላለቀለት እዛም ችግሮች አሉ ። " ያሉት አቶ ካሳሁን " ከምዕራብ ትግራይ ተፈናቅለው ከወልቃይት ስኳር ፋብሪካ፣ ህይወት እርሻ ሜካናይዜሽን ተፈናቅለው ያሉትን ዞረን ያሉበትን ቦታ አይተናል በምን ደረጃ ላይ እንዳሉም ተመልክተናል ፤ ይሄ የጦርነት ውጤት ነው ፤ በቃላት ከምንገልፀው በላይ በአይናችን አይተናል " ሲሉ አስረድተዋል።
" ችግሩ በሰላም በውይይት እንዲፈታ ፣ ወንድም ወንድሙን አይግደል ፣ ኢትዮጵያውያን ነን እየተገዳደልን ያለነው ፣ ከጦርነት ማንም የሚያተርፍ የለም እያልን መግለጫ ስናወጣ ነው የቆየነው " ሲሉም ፕሬዜዳንቱ አስታውሰዋል።
በትግራይ ክልል በተቋማት ላይ የደረሰው ውድመት እንዲሁም ሰራተኞች ያሉበት ሁኔታ የከፋ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ኢሰመኮ ያለውን አቅም ተጠቅሞ ያሉትን ችግሮች መፍታት እንዲቻል ከመንግስት እና ከአጋር አካላት ጋር በመሆን ጥረት እንዲያደርግ ለሰራተኞችም ትኩረት እንዲሰጥ ከትግራይ ሰራተኞች ተጠይቋል።
አቶ ካሳሁን ፎሎ በትግራይ ያለው ችግር ከባድ መሆኑን አንስተው ችግሮችን መፍታት ለአንድ ወገን ብቻ የሚሰጥ ስራ ባለመሆኑ ከክልል ፣ ከፌዴራል ከአጋር ተቋማት ጋር በመሆን ኢሰማኮ ችግሮች እንዲፈቱ ጥረት እንደሚያደርግ ማሳወቃቸውን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
#NB. ሼባ ሌዘር ፦ 100% ውድመት ደርሶበታል። ተጠግኖ እንኳን ስራ ላይ የሚውል ንብረት እንዳይቀር ተደርጎ ነው የወደመው። ሼባ ሌዘር 1200 ሰራተኞች ነበሩት ውድመት ከደረሰበት በኃላ ሰራተኛው ደመወዝ አጥቶ ፣ ተቸግሮ ተፈናቅሏል።

#እናት_ፓርቲ
እናት ፓርቲ ትላንት እሁድ በአዲስ አበባ ጠቅላላ ጉባኤውን እንዳያደርግ መከልከሉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ገልጿል።
ፓርቲድ " ክልከላ በእሳት ፈትኖ እንደ ብረት ቢያጠነክረን እንጂ ሸብረክ እንድንል አያደርገንም " ብሏል።
ከመግለጫው የተወሰደ ፦
" በቅድሚያ 6 ኪሎ የሚገኘው በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሥር የሚተዳደረው የስብሰባ ማዕከል አዳራሽ ይሁንታ አግኝተን በመንግሥት ክልከላ ተደርጎብናል፡፡
ቀጥሎም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትልቁ አዳራሽ በአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት በኩል አስይዘን ስለነበር ወደዚያ ቀይረን እንዲሁ ለጉባኤው ከ48 ሰዓት በታች ሲቀር በድጋሚ ክልከላ ተደርጎብናል፡፡
#የግድ መደረግ ያለበት በመሆኑ ሦስተኛ አማራጭ ከብዙ ድካም በኋላ የቅ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የሰርግ አዳራሽ ሕጋዊ ሂደቶችን አሟልተን፣ ክፍያ ፈጽመን፣ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን አስገብተንና ትላንት ጠዋት ከሀገራችን 4ቱም ማዕዘናት ከመጡ ከ700 በላይ አባላት ተገኝተው፣ የተጋበዙ የሌሎች ፓርቲዎች አመራሮች፣ መገናኛ ብዙኃን፣ የምርጫ ቦርድ ተወካዮች፣ ተጋባዥ እንግዶች ጋር በመሆን ወደአዳራሽ ስናመራ “ከመንግሥት የመጣ ትዕዛዝ” በሚል ወደውስጥ እንዳንገባ ታግደናል፡፡
በዚህ መሐል የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሓላፊ ለወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ጉዳዩን አስረድተን ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም፣ በተዋረድ ካሉ የጸጥታ ተቋማት ሓላፊዎች ጋር ቢደወልም መፍትሔው ሊቀርብ አልቻለም፡፡
ፓርቲያችንም ከ3 (ሦስት) ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደረገበት ጉባኤ ሳይከናወን አባላትን ለከፍተኛ እንግልት ዳርጎብናል፤ እንደፓርቲም ከፍተኛ የገንዘብ ኪሣራና የሥነልቡና ጉዳት አድርሶብናል፡፡ "
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#MoE
" የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቅድሚያ የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ ይኖርባቸዋል " - ትምህርት ሚኒስቴር
የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን አሀዱ ዘግቧል።
በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ95 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች ከ50 በመቶ በታች ውጤት ማምጣታቸው ይታወቃል፡፡
ከሀምሳ በመቶ በታች ካመጡት ተማሪዎች መካከል በልዩ ሁኔታ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለ4 ወር የአቅም ማሻሻያ ትምህርት ሪሜዲያል እንዲወስዱ የተወሰነ ሲሆን ከመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተጨማሪ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መውሰድ እንደሚችሉ የትምህርት ሚንስቴር የህዝብ ግንኙት ሃላፊ ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል ገልፀዋል፡፡
ትምህርት ሚንስቴር ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ያደረገ ሲሆን ይህን የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መስጠት የሚፈልጉ የግል ከፍትኛ የትምህርት ተቋማትም በዚሁ መሰረት ተማሪዎች ተቀብለው ማስተማር የሚችሉ ሲሆን በቅድሚያ ግን የመዘገቧቸውን ተማሪዎች ለትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን ማሳወቅ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የልህቀት ማእከል ተብለው በተለዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በኩል የተዘጋጀ የአቅም ማሻሻያ ሪሜዲያል ትምህርት ማስተማሪያ ተዘጋጅቶ ለሁሉም የመንግስት እና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መላኩን ጠቁመዋል፡፡
አያይዘውም የማስተማሪያ ሰነዱ ለተማሪዎቹ ከ 9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ትምህርት አጠቃሎ የያዘ ሲሆን ሁሉም የትምህርት ተቋማት ማስተማር የሚችሉት ይሄንን በመጠቀም መሆን እንዳለበት ለአሀዱ በሰጡት ቃል አመላክተዋል፡፡
Credit : #Ahadu