TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትግራይ

በሰላም ስምምነቱ መሰረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋሚያ ኮንፈረንስ በዚህ ሳምንት ለሁለት ቀናት ተካሂዷል።

በኮንፈረንሱ የተለያዩ ውሳኔዎች መተላለፋቸው ተገልጿል።

የኮንፈረንሱ ውክልና አስተዳደር፣ የሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ተልዕኮ፣ የአስተዳደሩ አደረጃጀትና የስልጣን ክፍፍል ላይ ውይይት እንደተደረገበት እና ስምምነት ላይ እንደተደረሰባቸው ተገልጿል።

ወደ ጦርነት ያስገቡ የትግራይ ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች በሰላም ምላሽ እንዲያገኙ ሁሉም የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተመላክቷል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በሁለቱም ተደራዳሪዎች ስምምነት ፀድቆ ወደ ተገባር የሚገባ ሲሆን አስተዳደሩ ከ6 ወር እስከ 1 ዓመት ይቆያል ተብሏል።

ኮንፈረንሱ 11 ነጥብ ያለው የአቋም መግለጫ በማውጣት የተጠናቀቀ ሲሆን የትግራይ ህዝብ ፍላጎት የሚሟላበት፣ የጦርነት ሰለባዎች ትኩረት የሚያገኙበት፣ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው የሚመለሱበት፣ በትግራይ ያጋጠሙ ሁለንተናዊ ችግሮች የሚፈታ እንዲሆን ሁሉም ለሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና የኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቁን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ጀነራል ታደሰ ወረደ ከቀናት በፊት ኮንፈረንሱ ሲካሄድ እንደተናገሩት ከሆነ የሚቋቋመው ጊዚያዊ አስተዳደር፦
👉 30 % ከህወሓት
👉 25 % ከትግራይ ታጣቂ ሐይሎች
👉 30 % የሲቪል ተቋማት
👉 15 % ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የያዘ ነው።

ለ2 ቀናት ከተደረገው ኮንፈረንስ ጋር በተያያዘ ከዓሲምባ በስተቀር በክልሉ ያሉ የተቃዋሚ ኃይሎች እንዳልተካፈሉ በስፋት ተነግሯል።

ያንብቡ: https://telegra.ph/TG-03-03

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
መንግስት ምን አለ ? የኢፌዴሪ መንግስት በኮሚኒኬሽን አገልግሎት በኩል ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ፤ 127ኛው የዓድዋ በዓል በብሔራዊ ደረጃ በአዲስ አበባ ፣ በመላው ሀገሪቱ እንደአመቺነቱና እንደ ሁኔታው #በድምቀት ፣በታቀደለት ልክ ተከብሯል ብሏል። አገልግሎቱ ዛሬ በምንሊክ አደባባይ ስለነበረው ሁኔታም በመግለጫው አብራርቷል። በምኒልክ አደባባይ የሚደረገውን በዓል ለመረበሽ የፈለጉ አካላት ሁከት ለመቀስቀስ…
ትላንት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በተከሰተው ጉዳይ ቤተክርስቲያን መግለጫ ሰጠች።

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ የአ/አ ሀገረ ሰብከት በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አማካኝነት ተፈጽሟል ባለው ሕገ ወጥ ድርጊትን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

የቅ/ጊዮርጊስ ክብረ በዓል ለማክበር ህዝቡ ከየቤቱ ተሰባስቦ ከጠዋቱ 3:15 ላይ በሰሜን በኩል ከመንግሥት የጸጥታ አካላት 2 ጊዜ በተተኮሰ አስለቃሽ ጭስና በቅጥሩ በተፈጠረው ረብሻ እስከአሁን ባለው መረጃ የ1 ምዕመን "በአስለቃሽ ጭስ ታፍነው" ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል።

በተጨማሪም አገልጋይ ካህናት፣ምእመናንና ምእመናት ከፍተኛ የሆነ አካላዊ እና ሥነ ልቡናዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ከ15 ያላነሱ የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋይ ተማሪዎች በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተጠቅሷል፡፡ 

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ በዓሉን አስመልክቶ በዕለቱ ያወጣውን መግለጫም ከነበረው እውነታ በእጅጉ የራቀ በሚል የተገለጸ ሲሆን መንግሥት ችግሩን ለማረምና መፍታት ፍላጎት የሌለው መሆኑን ያመለከተ ነውም ብለዋል።

መንግሥት የቤ/ክርስቲያንን ክብርና ልዕልና በሚዳፈር መልኩ በተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ላይ የተሳተፉና ይህን ድርጊት የፈጸሙና ያስፈጸሙ፤እንዲፈፀም ያዘዙ የመንግሥት ኃላፊዎችን በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለይቶ በሕግ እንዲጠየቁ እንዲያደርግ" ተጠይቋል።

በተለመደው የሀሰት ውንጀላ በዓላችንን በማክበር ላይ እያሉ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በፈፀሙት ሕገ ወጥ ተግባር ምክንያት በተፈጠረው ግርግር መነሻነት የታሰሩ ምእመናንን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፤ ይህ የማይሆን ከሆነ ቤ/ክርስቲያን መብቷን ለማስከበር ወደ ቀጣይ እርምጃዎች እንደምትገባ ገልጻለች።

(ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ትላንት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በተከሰተው ጉዳይ ቤተክርስቲያን መግለጫ ሰጠች። በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ የአ/አ ሀገረ ሰብከት በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አማካኝነት ተፈጽሟል ባለው ሕገ ወጥ ድርጊትን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። የቅ/ጊዮርጊስ ክብረ በዓል ለማክበር ህዝቡ ከየቤቱ ተሰባስቦ ከጠዋቱ 3:15 ላይ በሰሜን በኩል ከመንግሥት የጸጥታ አካላት…
"ድርጊቱን የፈጸሙ የፀጥታ ኃይል አባላት ሊጠየቁ ይገባል" - ኢሰመኮ

127ኛው የዓድዋ ድልን ለማክበር በምኒልክ አደባባይ በተሰበሰቡ ነዋሪዎች ላይ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ድብደባ፣ አስለቃሽ ጭስ፣ የፕላስቲክ እንዲሁም እውነተኛ ጥይቶችን መተኮሳቸውን ኢሰመኮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ኢሰመኮ የፀጥታ ኃይሎች ሰጥተውታል ባለው ከልክ ያለፈ ምላሽ በእድሜ ገፋ ያሉ እና ሕፃናትም ጭምር ለእንግልት መዳረጋቸውን ገልጿል። በዚህም ቢያንስ የአንድ ሰው ሕይወት እንደተቀጠፈና፣ በርካቶችም የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል።

የፀጥታ ኃይሎች የሕዝብን ደኅንነት መጠበቅና የሁሉንም ሰው ሰብዓዊ መብቶች ማስጠበቅ ቀዳሚ ኃላፊነታቸው መሆን እንደነበረበትም ኢሰመኮ አስታውሷል።

ድርጊቱን የፈጸሙ የፀጥታ ኃይል አባላትም ሊጠየቁ እንደሚገባ ያስታወሰው የኢሰመኮ መግለጫው “የሕግ አስከባሪዎች መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ በበቂ ሁኔታ ሥልጠና ሊሰጣቸው ይገባል”ብሏል።

ቢቢሲ የሟች ዘመድን ጠይቆ በሰራው ዘገባ በክብረ በዓሉ ወቅት ሕይወቱ የጠፋው ሚሊዮን ወዳጅ በዳግማዊ ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የሲቪክስ መምህር መሆኑን ዘግቧል።

ሟች ከመሞቱ በፊት በስልክ ሲደዋወሉ እንደነበር የገለጸው የሟች ሚሊዮን ዘመድ የሆነው አዲስ፥ ሚሊዮን ፒያሳ ምኒልክ አደባባይ አካባቢ በጥይት ከተመታ በኋላ ሕይወቱ አልፎ አብነት ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ስለአሟሟቱ ሁኔታ የጤና ባለሙያዎችን መጠየቁን ይገልጻል።

“አሟሟቱን ስንጠይቅ በጥይት ተመትቶ በጎኑ የገባው ጥይት በሌላኛው ጎኑ እንደወጣ ነገሩን። ከዚያ ውጪ ዝርዝር መረጃ ለፖሊስ እንጂ ለእናንተ አንሰጥም አሉን” በማለት ተናግሯል። የሟችን አስክሬን ወደ ትውልድ አካባቢው ደቡብ ጎንደር ንፋስ መውጫ ይዘው መጓዛቸውንም በወቅቱ ለቢቢሲ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" 100 ሚሊዮን ብር ለግሻለሁ " - የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት ለድርቅ ተጋላጭ ለሆኑ የቦረና ወገኖቻችን 100 ሚሊየን ብር መለገሱን አሳውቋል። ባንኩ በላከው መልዕክት ፤ ከሠራተኞቹ ጋር በመሆን የማህበረሰብ ተቆርቋሪነት እሴቱን እየኖረ እንደሆነ ማሳየቱን መቀጠሉን ገልጿል። @tikvahethiopia
" 30 ሚሊዮን ብር ለግሻለሁ " - አዋሽ ባንክ

አዋሽ ባንክ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች 30 ሚሊዮን ብር መለገሱን አሳውቋል።

ባንኩ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተፈጥሯዊና ሰዉ ሰራሽ ችግሮች ለተለያዩ ጉዳቶች ለሚጋለጡ ዜጎች ድጋፍ ሲያደርግ እንደነበር አስታውሶ አሁን ደግሞ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።

አዋሽ ባንክ ባለፈዉ ዓመት በቦረና ጉጂ ዞኖች  በድርቅ ለተጎዱ ወገኖችና 60 ሚሊዮን ብር መለገሱን ፤ በተመሳሳይ በምዕራብ ኦሮሚያ ተከስቶ በነበረዉ የእርስ በርስ ግጭት ተፈናቅለዉ ለነበሩ ዜጎችና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለዉ ከባድ ዝናብ ቤት ለፈረሰባቸዉ አባወራዎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ለቲክቫህ በላከው መልዕክት አስታውሷል።

@tikvahethiopia
#ትኩረት

በኦሮሚያ እና በሲዳማ ክልል አዋሳኝ አከባቢዎች [ቦጬሳ ቀበሌ - ጭሬ] ካለፈው እሁድ ረፋድ ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዎች ህይወት መጥፋቱ እንዲሁም በዜጎች ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን በአከባቢው የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰቦች አስታውቋል።

ግጭቱ በተቀሰቀሰባቸው ቦታዎች በርካታ ዜጎች መፈናቀላቸውን ገልጸው #መንግስት ለአከባቢው በቂ የሆነ ትኩረት እንዲሰጥ ፤ የዜጎችንም ደህንነት እንዲያስጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።

በአካባቢው ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እየተከታተልን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray

በሽረ ከተማ የሚገኘው መናኸሪያ መቐለ ጨምሮ ወደ ተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተገልጋዮችን እና የመናኸሪያውን የስራ ኃላፊዎች ዋቢ በማድረግ ኢዜአ ዘግቧል።

ተጓዦች በጦርነቱ ምክንያት የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ በመቆየቱ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠው እንደነበር ገልጸዋል።

የፌደራል መንግስት ከህወሓት ጋር የሰላም ስምምነት መድረሱን ተከትሎ ግን መቐለን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መጀመሩን አስረድተዋል።

የተፈጠረው ሰላም ከፍተኛ እፎይታና ደስታ እንደፈጠረላቸው ጠቁመዋል።

የሽረ ከተማ መናኸሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ተክላይ ገብረየሱስ  በበኩለቸው ፤ የሽረ መናኸሪያ መቐለን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የትግራይ ክልል ከተሞች ለሚንቀሳቀሱ የህዝብ ማመላለሻ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ መኪኖች ስምሪት እየሰጠ ነው ብለዋል።

የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መጀመሩ አሽከርካሪዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ፣ ተሳፋሪዎች ደግሞ ወደ ሚፈልጉት ከተማ እንዲንቀሳቀሱ ማስቻሉን አንስተዋል።

የትራንስፖርት አገልግሎቱን ለማሳለጥ መንግስት ነዳጅ እያቀረበ መሆኑን ጠቁመው፥ በቀጣይ ለህብረተሰቡ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የጀመሩትን ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ይደረጋል ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ኢትዮጵያ ውስጥ የቴሌግራም፣ ፌስቡክ ፣ ዩትዩብ መሰል የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ምክንያቱ ግልፅ ባልተደረገበት ሁኔታ ገደብ ከተደረገባቸው ዛሬ 19ኛ ቀን ተቆጥሯል። የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ " ለምን ገደብ እንደተጣለ " እንዲሁም " ገደቡ መቼ እንደሚነሳ " በየትኛውም አካል በኩል ለህዝብ ማብራሪያም ሆነ ገለፃ ያደረገ የለም። ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ እና ሌሎችም የማህበራዊ መገናኛዎች…
" መንግስት በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ የጣለውን ገደብ ያንሳ " - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ም/ቤት

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት መንግሥት በኢንተርኔት ግንኙት ላይ የጣለው ገደብ ሚዲያዎች ስራቸውን በአግባቡ ለህዝቡ ተደራሽ  እንዳያደርጉ እንቅፋት እየፈጠረ በመሆኑ ገደቡ እንዲነሳ መጠየቁን ለቲክቫህ በላከው መግለጫ አሳውቋል፡፡

ከሰሞኑን መንግስት በአንዳንድ የኢንተርኔት የግንኙነት መተግበሪያዎች ላይ የጣለው ገደብ መገናኛ ብዙሃን መረጃ የማሰባሰብ፤ የማደራጀትና ተደራሽ የማድረግ ላይ ተግዳሮት ከመፍጠሩ ባሻገር የሰበሰቡትን መረጃ በሀገርና በውጭ ሀገር ለሚገኙ ተደራሲያን ኢንተርኔትን እንደ ዋነኛ የመረጃ ማሰራጫ የሚጠቀሙ መገናኛ ብዙሃን ስራቸውን በአግባቡ ለመከወን መቸገራቸውን በመግለጫው ተመላክቷል።

በመሆኑም ሰሞኑን  በሀገሪቱ ከተፈጠረው ኃይማኖታዊ አለመግባባቶች ጋር በተያያዘ የችግሩን ስፋትና ክብደት ከግምት በማስገባት ሊቀለበስ የማይችል አደጋን ምክንያት በማድረግ ካልሆነ በስተቀር ሕግን መሰረት በማድረግ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ መንግስት ገደብ ሊያደርግ እንደማይገባ ምክር ቤቱ እንደሚያምን አሳውቋል።

ከዚህ አንፃር በአንዳንድ የኢንትርኔት መረጃ ማስተላለፊያ መተግበሪያዎች ላይ የተጣለው ገደብ ሶስት ሳምንታትን ያስቆጠረ ከመሆኑም በላይ ገደቡ የተደረገበትን ምክንያት የሚመለከተው መንግስታዊ አካል የሰጠው ግልጽ  ማብራሪያ ባለመኖሩ የጠቅላላ ህዝቡን መረጃ የማግኘትና የማሰራጨት መብት ላይ ገደብ ለመጣል የሚያበቃ አማራጭ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ም/ቤት ገልጿል።

ም/ቤቱ ገደቡ እንዲነሳ በይፋ ጥሪ አቅርቧል።

#NB. በማህበራዊ መገናኛዎች (ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ ዩትዩብ...) ላይ ገደብ ከተጣለ ዛሬ 24ኛ ቀን ሆኗል።

More : @tikvahethmagazine
#ብርሃን_ባንክ

የገንዘብ እንቅስቃሴዎን ቀላል እና ምቹ ለማድረግ የቪዛ እና ማስተር ካርድዎን እንዲሁም የብርሃን ባንክ ካርድዎን ይጠቀሙ!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
#ነፃ_የትምህርት_ዕድል

ጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግል ከፍለው መማር ለሚቸገሩና የመግቢያ መስፈርቱን ለሚያሟሉ የኢመርጀርሲ ሜዲካል ቴክኒሽያን ባለሙያ ደረጃ 4 ውስን ሰልጣኞችን ተቀብሎ የነጻ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማመቻቸቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በላከው መልዕክት አሳውቋል።

የመግቢያ መስፈርቶች ፦

1. ከ2011 - 2013 ባለው የትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁና ውጤታቸው ለወንዶች ከ293 በላይ ለሴቶች ከ278 በላይ  ያመጡ፡፡

2. የ2014 ዓ.ም (በ2015 ዓ.ም ) ፈተና ለወሰዱ
ሀ.ለተፈጥሮ ሳይንስ  ተማሪዎች ለወንዶች ከ158 በላይ ለሴቶች ከ157 በላይ፤

ለ. ለሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ለወንዶች 149 በላይ ለሴቶች ከ145 በላይ ውጤት ያለቸው

3. ዕድሜ ከ30 ዓመት ያልበለጠ/ያልበለጠች፡፡

4. የኮሌጁን መግቢያ ፈተና  ማለፍ  የሚችል/የምትችል፡፡

5. ከፍለው ለመማር  የማይችሉ  መሆኑን   የሚገልጽ  ከሚኖሩበት ቀበሌ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

6. ለሴት ተወዳዳሪዎች ቅድሚያ ይሰጣል

7. ስልጠናውን ለ20 ወራት በመደበኛ ፕሮግራም የሚሰጥ በመሆኑ ሙሉ ጊዜውን ለስልጠናው ለመጠቀም ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች፡፡

የምዝገባ ጊዜ ከየካቲት 27 - መጋቢት  2/2015 ዓ.ም ድረስ ከላይ መስፈርቱን በሟሟላት በጠብታ ፓራሜዲክ ኮሌጅ በመገኘት መመዝገብ ትችላላችሁ። ( 👉 አድራሻውን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ)

ለምዝገባ ሲመጡ 4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ትራንስክሪፕት፤ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ  በ8035 ወይም 0943302400 /0923514151 በስራ ሰዓት መደወል ይቻላሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የንግድ ሱቆች ጨረታ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል "

በአዲስ አበባ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ ለጨረታ ከቀረቡ 5,397 የንግድ ቤቶች ውስጥ ከሰነድ ሽያጭ ብቻ 21.5 ሚሊየን ብር መሰብሰቡ አሳወቀ።

በ11 ሳይቶች በሚገኙ 5397 የንግድ ሱቆች ሽያጭ 52,614 የጨረታ ሰነድ የተሸጠ ሲሆን ከሰነድ ሽያጭ ብቻ 21.5 ሚሊየን ብር ተሰብስቧል ተብሏል።

ከሱቆቹ ሽያጭ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ይገኛል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ገንዘቡ ከተማ አስተዳደሩ ለግንባታ ወጪ ያለበትን የቦንድ ብድር የሚቀንስበት እንደሚሆን ተገልጿል።

በአዲስ አበባ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለ9 የስራ ቀናት ተጫራችች በተገኙበት ሲከፍት የቆየውን የንግድ ሱቆች ጨረታ ትላንት በ24/06/2015 ዓ.ም አጠናቋል።

የንግድ ሱቆች ጨረታ ውጤቱን በቅርቡ በጋዜጣ እና በተቋሙ ማህበራዊ ሚዲያ ይፋ የሚያደርግ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
አቢሲንያ ባንክ ፦

ውድ ደንበኞቻችን !

በአቢሲንያ ባንክ ስም በተከፈተ ሀሰተኛ ድረ ገፅ አማካኝነት፣ ባንካችን ያለ መያዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝና፣ ብድር ፈላጊዎች አስቀድመው ገንዘብ በማስገባት የብድር ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገፆች መረጃ እየተላለፈ ይገኛል፡፡

ነገር ግን ይህ ሀሰተኛ መረጃ በመሆኑ ከዚህ እና ከመሰል የተሳሳቱ መረጃዎች እንዲሁም ማጭበርበሮች እንድትጠነቀቁ እያሳሰብን፣ የባንካችንን ትክክለኛ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን የሚከተሉት እንደሆኑ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

የአቢሲንያ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች
Website: https://www.bankofabyssinia.com/
Telegram: https://t.iss.one/BoAEth
Facebook: https://www.facebook.com/BoAeth/
Instagram: https://www.instagram.com/abyssinia_bank/
Twitter: https://twitter.com/abyssiniabank
TikTok: https://www.tiktok.com/@abyssinia_bank
YouTube: https://www.youtube.com/@abyssinia_bank
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/