TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ፦ ቅዱስ ፓትርያርኩ መቐለ ገቡ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት በሰላም መቐለ ገብተዋል።

ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና ሊቃውንትን አስከትለው መቐለ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

Photo : Social Media

@tikvahethiopia
" ገዳዮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው "

ከሰሞኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ያሳለፈው አዲስ አደረጃጀት በጉጂ ዞን በተለያዩ ቦታዎች ተቃውሞ እንደገጠመው የቲክቫህ አባላት ከየአካባቢው አሳውቀዋል።

ትላንት ከዚህ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በቦሬ ማቲ በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ የኃይል እርምጃ የሰው ህይወት ስለመጥፋቱ ተሰምቷል።

አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል " መንግስት በሰላማዊ ተቃውሞ ላይ የሚወስደው የሃይል እርምጃ ሊቆም ይገባዋል " ሲል አሳስቧል።

" በቦሬ ማቲ የምስራቅ ቦረና ዞን አወቃቀርን ተቃውመው ባዶ እጃውን ሰልፍ ወጥተው የነበሩ ሶስት ሰዎች (2ቱ ተማሪዎች ናቸው/ሌላ አንድ ነዋሪ) በፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ እርምጃ ተገድለዋል " ሲል አስረድቷል።

" ያልተመጣጠነ የሃይል እርምጃ መቆም አለበት " ያለው ይኸው የቤተሰባችን አባል "ገዳዮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው" ሲል አሳስቧል።

በዛሬው ዕለት ከአዲሱ አወቃቀር ጋር በተያያዘ በሻኪሶ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

አንድ ስለጉዳዩ የጠየቅናቸው የቤተሰባችን አባል ፥ " ክልሉ ውሳኔውን ሲያሳልፍ ከህዝብ ጋር አለመከረም፣ ህዝቡ ውሳኔ እንዲሰጥበትም አልተደረገም " ሲሉ ተናግረዋል።

እስካሁን ጉዳዩን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም አልተሳካም።

በአዲሱ አደረጃጀት የምስራቅ ቦረና ዞን በአዲስ መልክ የተደራጀ ሲሆን የጉጂ ዞን ዋና ከተማ አዶላ ሬዴ ሆኖ የቦረና ዞን ዋና ከተማ ደግሞ ያቤሎ ከተማ እንዲሆን ተወስኗል።

ከዚህ ባለፈ ደግሞ ቡሌ ሆራ እና ሻኪሶ ከተሞች ተጠሪነታቸው ለክልሉ መንግስት እንዲሆን ተወስኗል፡፡

የክልሉ ም/ቤት ያሳለፈው የአደረጃጀት ውሳኔ ምንድነው ? በዚህ ያንንቡ https://t.iss.one/tikvahethiopia/76667

@tikvahethiopia
ለመላው የኢትዮጵያ ልጆች የቀረበ ጥሪ !

የ " ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር " በድርቅ ምክንያት ለጉዳት የተጋላጡ ወገኖችን ለመርዳት የሚያስችል የድጋፍ ማሰባሰቢያ ጥሪ አቅርቧል።

ማህበሩ ከቅርብ አመታት ወዲህ በደቡባዊና ደቡብ ምስራቃዊ አካባቢዎች የተከሰተው የድርቅ አደጋ በሰውና በእንስሶች ላይ ያስከተለውና እያስከተለ ያለው ጉዳት #እጅግ_አስከፊ መሆኑን ገልጿል።

ማኅበሩ እ.አ.አ በ2022 ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባባር ፦
- በደቡብ ክልል ከንባታ ጠንባሮና ጋሞ ዞኖች፣
- በኦሮሚያ ክልል ቦረና፣ ባሌ፣ ምስራቅ ባሌ እና ምስራቅ ጉጂ ዞኖች፣
- በሶማሌ ክልል ሸበሌ፣ ፋፈን እና አፍዴር ዞኖች ከዚህ በተጨማሪ ሞያሌ አካባቢ በድርቅ አደጋ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ 14,530 አባዎራዎችን ህይወት ለመታደግ ከ104 ሚሊዮን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

በአሁኑ ወቅትም በተለይም #በኦሮሚያ እና #ሶማሌ ክልሎች እንዲሁም ሞያሌ አካባቢ በ206.3 ሚሊዮን ብር መሰል ድጋፍ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው።

ድርቁ በሰውም ሆነ በእንስሶች ላይ እያስከተለ ካለው ጉዳት አንፃር እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ማህበሩ የተጎጂዎችን ህይወት ለመታደግ እያደረገ ያለውን ጥረት መላው ኢትዮጵያውያን በአይነትም ሆነ በገንዘብ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል።

እንዴት ድጋፍ ማድረግ ይቻላል ?

1ኛ. #የአይነት_ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ አዲስ አበባ ስቴዲየም አካባቢ በሚገኘው የማህበሩ ዋና መ/ ቤት ግቢ ድረስ በማምጣት መለገስ ይችላሉ።

2ኛ. የገንዘብ ልገሳ ማድረግ የሚፈልጉ በ #ቴሌ_ብር ሂሳብ ቁጥር 0907 ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ።

3ኛ. ለቦረና ድርቅ ምላሽ ተብሎ በተከፈት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 👉 1000529766916 እንዲሁም 907 አጭር የሂሳብ ቁጥርን በመጠቀም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ በዳሽን ባንክ፤ በአቢሲኒያ ባንክ፤ በአዋሽ ባንክ እና በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይቻላል።

4ኛ. የእጅ ስልክ በመጠቀም በ9400 ላይ OK ብሎ በመላክ 1 ብር መለገስ ይቻላል።

#EthiopianRedCrossSociety
#ETHIOPIA🇪🇹

@tikvahethiopia
የ2015 ዓ/ም ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆኗል።

በዚህ አመት የተዘጋጀው መቁረጨ ነጥብ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተሰላ በመሆኑ የሚያገለግለው ለ2015 ዓ.ም የስልጠና ዘመን ብቻ መሆኑን ተገልጿል።

በ2013/2014 የሥልጠና ዘመን በተለየየ ምክንያት ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ያልገቡ ተማሪዎች የሚስተናገዱት በ2014 ዓ.ም በነበረው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ይሆናል ተብሏል።

(የ2015 ዓ/ም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ውጤት ከላይ ተያይዟል)

ምንጭ፦ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

በሆቴሎች፤ በሱፐርማርኬቶች እና በቅርንጫፎቻችን በሚገኙት የፖስ ማሽኖቻችን የቪዛና ማስተር ካርድዎን ተጠቅመው ግብይትዎን ያቅልሉ፡፡

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !

Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ

እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
#TEKLEHAIMANOT_GENERAL_HOSPITAL

ማርች 8 የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 6 የእርግዝና ክትትል ለሚጀምሩና ለሚወልዱ ነፍሰጡር እናቶች ልዩ ልዩ ስጦታዎችን እስከ ወሊድ ጊዜያቸዉ የሚቆይ 25% በሁሉም አገልግሎቶች ላይ ማድረጋችንን ስንገልፅ በደስታ ነው::

#ከ1993_ጀምሮ
ስልክ ፦ 0940333333 / 8175
እስከዛሬ ምላሽ ያልተገኘለት የኮቪድ-19 መነሻ !

" FBI የወረርሽኙ መነሻ በቤተ ሙከራ ውስጥ ያጋጠመ ክስተት ሊሆን እንደሚችል ገምግሟል " - ክርስቶፈር ውሬይ

የአሜሪካ የወንጀል ምርመራ ቢሮ (FBI) የኮቪድ 19 መነሻ የቻይና መንግሥት የሚቆጣጠረው ላብራቶሪ ሊሆን ይችላል ብሎ እንደሚያምን የተቋሙ ዳይሬክተር ክርስቶፈር ውሬይ ተናገሩ።

ዳይሬክተሩ ለፎክስ ኒውስ በሰጡት ቃል " FBI የወረርሽኙ መነሻ በቤተ ሙከራ ውስጥ ያጋጠመ ክስተት ሊሆን እንደሚችል ገምግሟል " ብለዋል።

" ቻይና የዓለም አቀፍ ወረርሽኙን ምንጭ ለማወቅ የሚደረገውን ጥረት ለመከላከልና ለማድበስበስ እየሞከረች ነው። ይህም በጣም የሚያሳዝን ነው " ሲሉ ወቅሰዋል።

FBI ወረርሽኙ እንዴት እንደተቀሰቀሰ ውስን ድምዳሜ ላይ ሲደርስ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።

ቻይና ከዚህ ቀደም ወረርሽኙ በዉሃን ከሚገኝ ቤተ ሙከራ አምልጦ የወጣ ነው መባሉን የተቃወመች ሲሆን የቀረበባትን ውንጀላም " #ስም_ማጥፋት " ነው ብላ ነበር።

ከዚህ በፊት ወረርሽኙ ከቤተ ሙከራ አምልጦ ስለመውጣቱ በስፋት ውድቅ የተደረገ ሲሆን ከፍተኛ የጤና ባለሠልጣናትም "ቫይረሱ ከማምለጡ በፊት በቤተ ሙከራ የተፈጠረ ሊሆን ይችላል" መባሉን በይፋ አጣጥለውታል።

የዓለም ጤና ድርጅት ከቤተ ሙከራ አምልጦ ወጥቷል መባሉን " የማይሆን ነው "  ያለ ሲሆን ነገር ግን በምርመራው ላይ ከፍተኛ ትችት ከደረሰበት በኋላ የተቋሙ ዳይሬክተር ጀኔራል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም አዲስ ምርመራ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ፤  " ሁሉም መላ ምቶች ቀርበዋል ተጨማሪ ጥናት ግን ያስፈልጋል " ብለው ነበር።

ኮቪድ 19 በ2019 መጨረሻ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ ሲሆን ወደ 7 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

@tikvahethiopia
#NEBE

ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል በሚገኙ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች የተካሄደውን የህዝበ ውሳኔ ውጤት ይፋ አድርጓል።

እነዚህ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል እንዲደራጁ የነጭ እርግብ ምልክት የተወከለ እና በአንድ ክልል መደራጀቱን አልደግፍም ለሚለው የጎጆ ምልክት ተወክሏል፡፡

ውጤቱን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት ወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳ ተከታዩን መረጃ ሰጥተዋል።

- የወላይታ ዞን ህዝበ ውሳኔ #እንዲደገም በመወሰኑ እና በሌሎች ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ያልተካተቱ 81 የምርጫ ጣቢያዎች ሳይካተቱ፥ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ መራጮች በአንድ ክልል እንደራጅ የሚለውን ምልክት መርጠዋል።

- በህዝበ ውሳኔው 78 ሺህ 970 መራጮች በአንድ ክልል መደራጀቱን ያልደገፉ ናቸው።

- በውጤቱ ያልተካተቱ የ81 ጣቢያዎች ውጤት በዞኖቹ አጠቃላይ ውጤት ላይ ሊያመጡ የሚችሉት ተጽዕኖ ባለመኖሩ ሳይካተቱ ቀርተዋል።

- የወላይታ ዞን ሙሉ በውጤቱ ያልተካተተው በአጠቃላይ የህዝበ ውሳኔው ውጤት ላይ ተጽእኖ ሊፈጥር የሚችል በመሆኑ #ድጋሚ ህዝበ ውሳኔ ይደረግበታል።

- የምርጫ ውጤታቸው በውጤቱ ያልተካተቱት የምርጫ ጣቢያዎች የወላይታ ዞን ሙሉ በሙሉ እና ኮንሶ 4 የምርጫ ጣቢያ፣ ደቡብ ኦሞ 4 ምርጫ ጣቢያ፣ ጋሞ 21የምርጫ ጣቢያዎች ፣ ጌዴኦ 23 የምርጫ ጣቢያዎች ፣ ጎፋ 10 የምርጫ ጣቢያዎች ፣ ቡርጂ ልዩ ወረዳ 2 የምርጫ ጣቢያዎች፣ አሌ ልዩ ወረዳ 3 የምርጫ ጣቢያዎች ፣ አማሮ ልዩ ወረዳ 7 እና ደራሼ ልዩ ወረዳ 7 የምርጫ ጣቢያዎች ነው።

Credit : #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
የገዛ ልጁን የደፈረው አባት በ15 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት ተቀጣ።

በራሱ ልጅ ላይ #በተደጋጋሚ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው አባት በፅኑ እስራት ተቀጥቷል።

የድርጊቱ ፈፃሚ ሃይማኖት ስዩም የሚባል ሲሆን ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው አለም ባንክ ስላሴ ማሪያም ቤተክርስቲያን ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው።

ይኸው ግለሰብ ከታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2014 ዓ.ም ባሉ የተለያዩ ቀናት በራሱ ልጅ ላይ በተደጋጋሚ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈፅሟል።

ተከሳሹ የአስገድዶ መድፈር የፈፀመው በ15 ዓመት ልጁ ላይ ሲሆን ልጁን በማስገደድ በተደጋጋሚ ጊዜ የግብረ ስጋ ግንኙነት የፈጸመባት እና በዚሁ ምክንያትም ተበዳይ ያረገዘች በመሆኑ በፈጸመው የአስገድዶ መድፈር እና በዘመዳሞች መካከል የሚፈጸም የግብረ ስጋ ግንኙነት ወንጀል ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶበት ክርክር ሲያደርግ ቆይቷል።

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራኒዮ ሴቶች እና ህጻናት ምድብ ችሎት የቀረበው ተከሳሽ የክሱ ዝርዝር በችሎት ተነቦለት የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈጸሙ ሲጠየቅ ድርጊቱን አንድ ጊዜ ብቻ በማስገደድ የፈጸመ መሆኑን አምኖ ነገር ግን እርግዝናውን እንደማይቀበል ክዶ ተከራክሯል።

ዐቃቤ ህግ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች ዐቅርቦ ክሱን በበቂ ሁኔታ ያስረዳ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም የመከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለቱ የመከላከል መብቱ ታልፎ የጥፋተኝነት ፍርድ ተወስኖበታል፡፡

በዚሁ መሰረት ፍርድ ቤቱ የካቲት 14/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ በ15 ዓመት ከ8 ወራት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ከፍትሕ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ምንጭ፦ የፍትሕ ሚኒስቴር

More @tikvahethmagazine