TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #የከተራ_በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል። መልካም በዓል ! Photo Credit : Mayor Office of AA & Gondar Communication @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ከጊዜ ወደ ጊዜ የቀደመው ሰላማዊ ድባብ እየተመለሰባት በምትገኘው ትግራይ፤ በደቡባዊ ዞን ከተማ ማይጨው የጥምቀት ዋዜማ በድምቀት እየተከበረ ነው።

በማይጨው እጅግ በርካታ ምዕመን መታደሙን ለማወቅ ተችሏል።

በተለያዩ ከተሞች ያለውን የበዓል ድባብ በ @tikvahethmagazine ላይ መመልከት ትችላላችሁ።

Photo Credit : Demtsi Weyane

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ከውጭ የሚገቡ ሆነ ሀገር ውስጥ የሚመረቱ #የኤሌክትሪክ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፣ የቤት አውቶሞቢሎችና የእቃ መጫኛ ተሽከርካሪዎች ላይ ዝቅተኛ የጉምሩክ ታሪፍ የሚጣልባቸው ሲሆን ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከኤክሳይዝ ታክስና ከሱር ታክስ #ነፃ መደረጋቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል። የታክስ ማሻሻያው በርካታ ዓላማዎች ያሉት ሲሆን ከዓላማው አንዱ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በተመጣጣኝ…
ቁጥሮች ...

(ኢትዮጵያ - የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች)

[ ሪፖርተር ጋዜጣ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ በርኦ ሐሰንን ቃለ መጠይቅ አድርጎ ካወጣው ዘገባ የተወሰደ ]

• መስከረም ወር ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር ካደረገው በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች የታክስ ማሻሻያ በኋላ ከ7,000 በላይ ተሽከርካዎች አገር ውስጥ ገብተዋል።

• ከብሔራዊ ባንክ ጋር የኤሌክትሪክ አውቶብሶች እንዲጉ መግባባት ላይ ተደርሶ እንቅስቃሴዎች የተጀመረ ሲሆን በቅርቡ 1,300 የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ወደ አገር ቤት ይገባሉ።

• የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የአሥር ዓመት ዕቅድ 48,000 የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ የኤሌክትሪክ አውቶብሶች ፤ በተጨማሪም 148,000 የኤሌክትሪክ #አውቶሞቢሎችን አገር ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ ነው።

#ማስታወሻ

በመስከረም ወር ይፋ የሆነው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነፃ ማስገቢያ ማሻሻያ ፦

1ኛ. ሙሉ በሙሉ ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ አውቶሞቢሎች ከጉምሩክ ቀረጥ፣ ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ ናቸው።

2ኛ. በከፊል ተበትነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የሚገጣጠሙ የኤሌክትሪክ የቤት አውቶሞቢሎችን 5 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ ናቸው።

3ኛ. ሙሉ ለሙሉ ተገጣጥመው ያለቀላቸው የኤሌክትሪክ አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ሲገቡ 15 በመቶ የጉምሩክ ቀረጥ ብቻ የሚጣልባቸው ሲሆን ከኤክሳይዝ ታክስ፣ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሱር ታክስ #ሙሉ_በሙሉ_ነጻ ናቸው።

@tikvahethiopia
#ጥምቀት

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ #በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ።

መልካም የጥምቀት በዓል!
Baga Ayyaana Cuuphaa Nagaan Geessan! Ayyaana Gaarii
ርሑስ በዓል ጥምቀት !

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የ #ጥምቀት_በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እየተከበረ ይገኛል።

Photo Credit : EPA & EBC

@tikvahethiopia
#Photo

የጥምቀት በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የዘንድሮው የጥምቀት በዓል ያለውን ገፅታ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን ከተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች በማሰባሰብ ልከንላችኃል።

ፎቶዎቹ ከአዲስ አበባ ፣ ጎንደር ፣ መቐለ ፣ ኣክሱም ፣ ላሊበላ፣ ደሴ ፣ ወልድያ ፣ ሀዋሳ ፣ ሐረር ፣ ድሬዳዋ ፣ አሶሳ ፣ ጋምቤላ ፣ ቡሌሆራ ...ከሌሎችም ከተሞች የተሰባሰቡ ናቸው።

ፎቶ : https://telegra.ph/Timket-2015-01-19

© ሁሉም ፎቶዎች #ምንጫቸው የተገለፀበት ነው።

@tikvahethiopia
ባንካችን አቢሲንያ ከሳፋሪኮም ጋር በአጋርነት መሥራት ጀመረ፡፡

የባንካችን ደንበኞች የሳፋሪኮም አየር ሰዓት በአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ ካሉበት ሆነው ወይም አቅራቢያዎ በሚገኙት የባንካችን ቅርንጫፎች መሙላት ይችላሉ፡፡

#BankofAbyssinia #Abyssinia #Banking #BankingService #MobileBanking #Digital #DigitalEthiopia #DigitalPayment #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
TIKVAH-ETHIOPIA
ሚኒስትሮቹ ወዴት ነው የተሸኙት ? ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፦ - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞግስ፤ - የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፤ - የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን፤ - የጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ተፈሪ ፍቅሬን ዛሬ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት መሸኛታቸውን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አሳውቋል።…
#ሹመት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች በመስጠት የህ/ተ/ም/ቤት ሹመቱን እንዲያፀድቅላቸው ጠይቀዋል።

በዚህም መሰረት፦

1.  ዶክተር ዓለሙ ስሜ - የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር፣

2.  ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ - የማዕድን ሚኒስትር፣

3.  ዶክተር ግርማ አመንቴ - የግብርና ሚኒስትር

እንዲሁም ከጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ፦

1.  አቶ ማሞ ምሕረቱ - የብሔራዊ ባንክ ገዢ፣

2.  ወይዘሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር፣

3. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት - የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር፣

4.  አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ - የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር እና

5.  አቶ መለሰ አለሙ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት  ግንባታ ማስተባበሪያ የዘርፍ አስተባባሪ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ተሹመዋል፡፡

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የገንዘብ ድጋፍ በሚያስገኝ ውድድር ይሳተፉ!

ትምህርት ሚኒስቴር እና ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና ከብሪታንያ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (UKaid) ጋር በመተባበር የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር (University Industry Linkage) ላይ መሰረት ያደረጉ ችግር ፈቺ እና ወደ ኢንዱስትሪው ሊሸጋገሩ የሚችሉ የተጠናቀቁ የምርምር ውጤቶችን አወዳድሮ ወደ ገበያ እንዲገቡ የፋይናንስ ድጋፍ የሚያደርግ ውድድር ይፋ አድርገዋል፡፡ 

በዩኒቨርሲቲዎች፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት፣ በምርምር ማዕከላት እንዲሁም በኢንዱስትሪዎች ውስጥ ወደ ምርትና አገልግሎት ሊቀየሩ የሚችሉ እና ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ የምርምር ውጤቶች ያላችሁ እና የመወዳደሪያ መስፈርቱን የምታሟሉ ተመራማሪዎች እና የፈጠራ ባለሙያዎች በውድድሩ መሳተፍ ትችላላችሁ።

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ የካቲት 11/2015 ዓ.ም

ለማመልከት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ፦

https://forms.gle/ESk1iYwf9bYhJo879

ለበለጠ መረጃ፦ 0948862349  ወይም 0912612679

E-mail፦
[email protected]
[email protected]

@tikvahuniversity