TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray #Mekelle

ተጨማሪ ፎቶዎች፦ ዛሬ በመቐለ ከተማ ለፌዴራል መንግስት ልዑካን ቡድን የተደረገለት አቀባበል።

Photo Credit : Tigrai Television & Demtsi Weyane

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #Mekelle ተጨማሪ ፎቶዎች፦ ዛሬ በመቐለ ከተማ ለፌዴራል መንግስት ልዑካን ቡድን የተደረገለት አቀባበል። Photo Credit : Tigrai Television & Demtsi Weyane @tikvahethiopia
#Mekelle

መቐለ የሚገኘው የፌዴራል መንግስት ልዑክ ፦

- በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጨፎ የተመራ ነው።

- ልዑኩ ከ50 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን ሚኒስትሮች፣ የፌደራል መስርያ ቤት ዋና ኃላፊዎች እና ዲፕሎማቶች ይገኙበታል።

- በልዑካን ቡዱኑ የጠ/ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ፣ #የኢትዮ_ቴሌኮም ዋና ስራ ስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሪት ፍሬህይወት ታሙሩ ፤ #የባንክ_ኃላፊዎች በርካታ ሚኒስቴሮች ይገኙበታል።

- የፌዴራሉ መንግሥት ልዑክ ፤ ዛሬ መቐለ መግባቱ የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊነት እንደሚያጠናክረው ታምኗል።

Credit : Demtsi Weyane

@tikvahethiopia
#safaricom

በቴሌኮም ዘርፍ የተሰማራዉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎቶቹን ለማስተዋወቅ በመላዉ አዲስ አበባ ለ 10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የመንገድ ላይ ትርዒት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ትርዒቱ የተለያዩ መዝናኛዎችን ያካተተና ሲምካርድ ለሚገዙ ደንበኞቹ የተለያዩ ስጦታዎችን አዘጋጅቷል። ተቋሙ አዲሱን የሳፋሪኮም ኔትወርክ  እንዲቀላቀሉ ጥሪውን  ለደምበኞቹ ያቀርባል።

ታህሳስ 18ና 19/2015 በሳፋሪኮም ሱቆች አካባቢ የመንገድ ላይ ትርዒቱ የሚከናወን ሲሆን ታህሳስ 19/2015 ዝግጅቱ ፍፃሜውን ያገኛል።

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle መቐለ የሚገኘው የፌዴራል መንግስት ልዑክ ፦ - በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጨፎ የተመራ ነው። - ልዑኩ ከ50 በላይ አባላት ያሉት ሲሆን ሚኒስትሮች፣ የፌደራል መስርያ ቤት ዋና ኃላፊዎች እና ዲፕሎማቶች ይገኙበታል። - በልዑካን ቡዱኑ የጠ/ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ፣ #የኢትዮ_ቴሌኮም…
" በክልሉ ትልቅ ችግር የሆነው የባንክ አገልግሎት በቅርቡ ይፈታል " - አቤ ሳኖ

ዛሬ ወደ መቐለ ያመራው የፌደራሉ መንግስት ልኡክ በክልሉ ያለው የባንክ ችግር በቅርቡ እንደሚፈታ ለክልሉ ህዝብ ማረጋገጡ ተገልጿል።

ልዑኩ ለትግራይ ህዝብ እንዳረጋገጠው ከሆነ  በክልሉ ትልቅ ችግር የሆነው የባንክ አገልግሎት በቅርቡ መፍትሄ ያገኛል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 18 ባለሞያዎችን ወደ መቐለ እንዳሰማራም በዛሬው ዕለት ተገልጿል።

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ " ባንኩ የሚስተካከሉ የሲስተምና የኦዲት ሥራዎችን በዚህ ሳምንት አጠናቆ አገልግሎት ለማስጀመር እየሰራ ነው " ብለዋል።

" በትግራይ የባንክ አገልግሎት በመቋረጡ ምክንያት ህብረተሰቡ  ለከፋ ችግር እንደተዳረገ እንረዳለን " ያሉት አቤ " ይህንን ችግር  በአጭር ጊዜ ለመፍታት ከዛሬ ጀምሮ ባለሞያዎቻችን ወደ ስራ ገብተዋል " ሲሉ አሳውቀዋል።

የሰላም ጅምሩ እንዲፀና ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ የባንኩ ፕሬዝዳንት መጠየቃቸውንም ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ታህሳስ19

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የኃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓልን ለማክበር ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅ/ገብርኤል ገዳም አምርተዋል።

ቅዱስነታቸው ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን ዛሬ ድሬዳዋ ከተማ ሲደርሱ በከተማው ከንቲባ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በሌላ በኩል ፤ ታህሳስ 19/2015 ዓ/ም በቁልቢ እንዲሁም በሀዋሳ በድምቀት ለሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል የፀጥታ መዋቅሮች በዓሉ ደህንነቱ የተረጋገጠና ሰላማዊ እንዲሆን አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውን ለመስማት ችለናል።

Photo Credit : EOTC

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

#ቅዱስ_ገብርኤል

የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ መንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም (ቤተመንግሥት ቅዱስ ገብርኤል) በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል።

በዓሉን በደማቅ መልኩ ለማክበር የገዳሙ አስተዳደር ጽ/ቤት ከፀጥታ አካላት ከአከባቢው ምዕመናን ጋር ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ፅ/ቤቱ የፓርኪንግ ችግር ፈፅሞ እንጋይገጥም አዲሱ የቤተመንግስት ፓርኪንግ መፈቀዱንም አመልክቷል።

ምእመናን ለበዓሉ ሲመጡ መታወቂያ ከእጃቸው ላይ እንዳይለይ መሳሰቢያ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ፤ መንግስት በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ በአገር ውስጥ ባንኮች በውጭ አገራት ገንዘብ የሂሳብ ደብተር የሚከፍቱበትን የዲያስፖራ አካውንት ህግና የአሠራር ስርዓት በመጣስ የተለያዩ ግለሰቦች በህገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው መገኘታቸውን የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ባካሄደው ክትትል ማረጋገጥ መቻሉን አስታወቀ።

በዚሁ መሠረት አገልግሎቱ እስካሁን ባደረገው ክትትል፣ የትንተናና ማጣራት ስራዎች 85 ግለሰቦች የተሰታፉበት እና መጠኑ 20,226,583 ዶላር (ሃያ ሚሊየን ሁለት መቶ ሃያ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሰማኒያ ሶስት ዶላር) የውጭ አገር ገንዘብ በባንክ እንዲታገድ በማድረግ ለወንጀል ምርመራ መተላለፉን አመልክቷል።

ወንጀሉ እንዴት ተፈፀመ ?

-  አንደኛ ፦ ውጭ አገር ሳይሄዱ ውጭ አገር ሄደው የተመለሱ በማስመሰል ሀሰተኛ ዲክላራሲዮን በማቅረብና በመጠቀም፣

- ሁለተኛ ፦ ከውጭ አነስተኛ የውጭ ምንዛሪ ይዘው በመግባት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ይዘው እንደገቡ በማስመሰል ቀሪውን በህገ-ወጥ መንገድ ከጥቁር ገበያ ላይ በመሰብሰብና ሀሰተኛ ሰነድ/ዲክላራሲዮን በማቅረብ፣

- ሶስተኛ ፦ የሌላውን ሰው ዲክላራሲዮን የራስ አስመስለው በመጠቀም፣

- አራተኛ ፦ ህጉ ከሚፈቅደው ውጪ በተለያዩ ባንኮች የዲያስፖራ አካውንት በመክፈትና በመጠቀም በአጠቃላይ ሌሎች ሀሰተኛ ዲክላራሲዮን በመጠቀም የወንጀል ተግባራት መፈጸማቸውን መረዳት ተችሏል።

(የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Mekelle #EthioTelecom

" በአጭር ጊዜ ማለት ምን ማለት ነው ? ስንት ነው ? " - የመቐለ ነዋሪ

" ... በሌሎች ከተሞች ይደርሳል፣ ይመጣል ሳይባል መጥቶ እንዳስደሰትናችሁ ይህንኑ እናደርጋለን " - ፍሬህይወት ታምሩ (የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ)

ዛሬ ወደ #መቐለ ሄደው የነበሩ የፌዴራሉ መንግስት ልዑካን ከክልሉ አመራሮች እና ከመቐለ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

በውይይቱ ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ የቴሌኮም አገልግሎት በአጠረ ጊዜ ለማስጀመር ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህም ወቅት ፤ የመድረኩ አንድ ተሳታፊ እንዲህ ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል ፦

" የቴሌኮሙኒኬሽን መሰረተ ልማት መዘርጋት ነው ወሳኙ መብራት ኃይል ቀድሞ ስለተዘረጋ ብዙ ነገሮችን የፈታ ይመስለኛል።

የቴሌ በአጭር ጊዜ መፍትሄ ያገኛል የሚል ነገር ሰምተናል ፤ በአጭር ጊዜ ማለት ምን ማለት ነው ? ስንት ነው ?

አጭር ጊዜ የሚለው ወሳኝ ነው ፤ የትግራይ ህዝብ ለሁለት ለሶስት አመታት በተለያዩ ችግሮች ሲጠቃ የቆየ ለብዙ ችግሮች የተዳረገ ነው ፤ ስለዚህ የታመቀ ህመምና ጉዳት አለው ከዚህ ጉዳት ለመውጣት አሁን የደረስንበት ነገር ዛሬ መሆን የሚችል ከሆነ ለምን ነገ እናደርገዋለን ?

ዛሬ መደረግ ያለበትን ነገር የምናደርግ ከሆነ አጭር ጊዜ ማለት ስንት ነው ? የሚለውን መግባባት አለብን።

እናውቃለን መሰራት ያለባቸው ነገሮች አሉ ፤ አሁንም መልስ ማግኘት ይፈልጋል የትግራይ ህዝብ አጭር ጊዜ ማለት ስንት ነው ? "

ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ፦

" ... በመቐለ ላይ ያሉ ልጆቻችን ከዚህ ስብሰባ በኃላ ልናገኛቸው ነው (ይሄን ያሉት ቀን ላይ ከነዋሪዎች ጋር በነበረው ስብሰባ ነው) እነሱ በሰጡን መረጃ እየዋለን፤ ከፍተኛ የሚባል ጉዳት እንዳልደረሰበት ገልፀውልናል (በመቐለ ያለው መሰረተ ልማት) ፤ ነገር ግን ወደ #አዲስ_አበባ መገናኘት ስላለበት ፋይበሮች መጠገን አለባቸው።

የሆነው ሆኖ ግን ያ የቤት ስራ የእናተ ሳይሆን የኛ ሆኖ በአጠረ ጊዜ ውስጥ ያልነው የትኛውንም አጋጣሚና አማራጮችን ተጠቅመን አገልግሎት እናስጀምራለን።

በዛ በኩል ያለውን ጥገና ስናከናውን ስለቆየን ይሄ የሚፈጥን ይመስለኛል። አንድም ሁለትም ቀንም ሊሆን ይችላል ፤ ከመቐለ ወደ አብዓላ መንገድ ያለው ወደ 50 ኪ/ሜ 1.4 ነው ትላንት ባለኝ መረጃ የቀረን ከመቐለ ያለው ቡድናችን እየሰራ ስላለ በአጠረ ጊዜ ብዬ የተናገርኩበት ምክንያት ዛሬ ያልቃል ብለን በጣም በጉጉት የሚጠበቅ አገልግሎት እንደመሆኑና ለረጅም ጊዜ ግንኙነት ሳያዳርግ የቆየ ማህበረሰብ ከመጓጓቱ የተነሳ ዛሬ ይደርሳል ብለን ባይደርስ ከፍተኛ disappointment ይፈጠራል ያ እንዲሆን አንፈልግም።

ስለዚህ በሌሎች ከተሞች ይደርሳል፣ ይመጣል ሳይባል መጥቶ እንዳስደሰትናችሁ ይህንኑ እናደርጋለን ብለን እየሰራን ነው። "

@tikvahethiopia
T-MAX FLASH

በጣም ፍጥነት ያለውን T-MAX USB Flash Disc ለገበያ  አቅርበናል።
💎 ጫፉ የማይሸራረፍ ባለ ብረት
💎 ፍጥነቱ በጣም ጥሩ የሆነ
💎 ከተጠቀሙ በኋላ ወደ ውስጥ የሚሰበሰብ ዲዛይን
💎 ከጀርባው ህትመት/Logo ለማስቀመጥ ምቹ

🔔በፈለጉት መጠን በተመጣጣኝ ዋጋ እናቀርባለን
➭ 8 GB /16 GB/32 GB /64 GB/128 GB
ስልክ፦ 0933111111 /  0911676767
T-Max Electronics ምርቶችን ለማየት ተከታዩን ሊንኩን ይጠቀሙ፦
https://linktr.ee/tmaxelectronics

📍አድራሻ፦ መርካቶ ይርጋ ኃይሌ ህንጻ ሱቅ ቁጥር G-96 Ground Floor
www.tmaxelectronics.com

ቴሌግራም : https://t.iss.one/tmaxelct
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበል ጀምረዋል። አንዳንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከቀናት በኃላ መሰጠት የሚጀምረውን 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎችን ዛሬ መቀበል ጀምረዋል። ተቋማቱ ከወዲሁ ፤ ተፈታኝ ተማሪዎች ከገቡ በኃላ ፈተናው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከተፈቀደላቸው የተቋሙ ሰራተኞች እና ፈተና አስፈፃሚዎች በስተቀር ተፈታኞች ባሉባቸው…
#Update

2ኛው ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው።

ፈተናው ከዛሬ ታህሳስ 18 ጀምሮ እስከ ታህሳስ 21/2015 ዓ/ም በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

ተቀባይነት ባገኙ ምክንያቶች በመጀመሪያው ዙር ፈተናውን መውሰድ ያልቻሉ በሁሉም ክልል የሚገኙ ተማሪዎች በሁለተኛው ዙር ለፈተና ይቀመጣሉ።

በሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና የማህበራዊ ሳይንስ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።

የ12ኛ ክፍል የብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ትላንት የግንዛቤ ማስጨበጫ (Orientation) ተሰጥቷቸዋል።

More : @tikvahuniversity