TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፕሬዜዳትን ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ኤርትራ ይገኛሉ።

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ በኤርትራ የሁለት ቀን የስራ ጉብኝት እያደረጉ መሆኑ ታውቋል።

ፕሬዜዳንቱ ትላንት አስመራ ኤርፖርት ሲደርሱ በፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ሩቶ በኤርትራ የስራ ጉብኝት ላይ የሚገኙት በፕሬዜዳንት ኢሳያስ ግብዣ ሲሆን ትላንት ከቀትር በኃላ የሁለትዮሽ ውይይት ከፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር አድርገዋል።

የተደረገው ውይይት ሰፊ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ውይይቱ ያተኮረው የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እና ቀጠናዊ አጋርነትን ማጠናከር ላይ እንደበር ከኤርትራ መንግስት በኩል ተሰምቷል።

ፎቶ ፦ Yemane G. Meskel

@tikvahethiopia
" ዎላይታ ታይምስ " ፤ የተሰኘው ሚዲያ ከመንግስት አካል ይደርስብኛል ባለው ጫና ሥራ ማቋረጡን ገልጿል።

በኢትዮጲያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በሚዲያ ሥራ ለመሰማራት ሕጋዊ ፈቃድ ወስዶ በዞናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ የነበረው "ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ" በደረሰበት ጫና ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ሥራ ማቆሙን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላከው መረጃ ያሳያል።

የሚዲያው መስራች የሆነው ጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ በሥራው በተደጋጋሚ ለእስርና ለእንግልት፣ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት መዳረጉን ጠቅሶ በቅርቡም ከቀን 19/03/2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት ላይ ጥላቻና ሀሰተኛ መረጃ አሰራጭቷል በሚል ተጠርጥሮ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደነበር ተናግሯል።

ጋዜጠኛው ፤ በዎላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስሮ ከቆየበት ትላንት 28/3/2015 ዓ.ም በሰላሳ ሺ (30,000) ብር ዋስትና መለቀቁን ተናግሯል።

ተመሳሳይ አይነት ጫና በመኖሩም ሌሎች የሚዲያው ጋዜጠኞችም ማስፈራሪያና ዛቻ እየደረሰባቸው በመሆኑ ሥራው ተቋርጦ ቢሮው መዘጋቱን አክሎ ገልጿል፡፡

ሚዲያው እየደረሰበት ያለውን ከፍተኛ ጫና ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ጨምሮ ለሚመለከታቸው አካላት " በደብዳቤ ጭምር " ማስታወቁን የገለጸ ቢሆንም ምንም አይነት ምላሽ አለማግኘቱን ጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Wolaita-Times-12-10
#ዓለም_ዋንጫ

አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ደማቅ አዲስ ታሪክ ፅፋለች !

በአሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ የሚመራው የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በየሱፍ ኤል ነስሪ ብቸኛ ግብ ፖርቹጋልን በመርታት ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

⚽️ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫው ታሪክ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል የቻለች ቀዳሚዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆናለች።

⚽️ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በኳታሩ የዓለም ዋንጫ #በተጋጣሚ_ቡድን #ተጫዋች አንድም ግብ ከመረብ አላረፈባቸውም።

⚽️ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን 196 ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል።

⚽️ የሱፍ ኤል ነስሪ በዓለም ዋንጫው ሶስት ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ በታሪክ የመጀመሪያው #ሞሮካዊ ተጫዋች ሆኗል።

https://t.iss.one/tikvahethsport

@tikvahethiopia
#ፌርማታ

በፋና ላምሮት ፡ በፋና ቀለማት እና በፋና 90 የሚታወቀው ጋዜጠኛ አዳነ አረጋ በአዲስ Reality show እና ቲዩብ መምጣቱን ገልጿል “Entoto Tube”

“ፌርማታ ሾው” ሁሉንም ሰው የሚያሳትፍ ሾው ሲሆን ዘውትር እሁድ በፋና ቲቪ ይተላለፋል በEntoto tube” ታገኙታላችሁ።

በEntoto Tube ሌሎችንም አዳዲስ ልዩ የመዝናኛ ሾዎች ለየት ባለ መልኩ በቅርቡ ወደእናንተ ይደርሳሉ SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ https://www.youtube.com/@entototube
" በዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር ለጊዜው ተቀርፏል " - ኢኦተቤ

ቅዳሜ ታሕሣሥ  2 /2015 ዓ.ም  ታጣቂዎች ወደ ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ገብተው ነበር።

የገዳሙ አበምኔት መምህር አባ ገብረሕይወት የተከሰተውን ክስተት በተመለከተ ለኢኦተቤ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፤ ታጣቂዎች የገዳሙን መነኮሳት የሞባይል ስልኮች የጥበቃ መሣሪያዎች እና ሦስት መነኮሳትን አርብሮብ ወደ ተባለ ቦታ ከወሰዱ በኋላ  በሰላም እንደለቀቋቸውና የወሰዱትን ንብረት መመለሳቸውን ገልፀዋል።

" ታጣቂዎቹ የመንግሥት ተቃዋሚዎች " ይሆናሉ  የሚል ግምት እንዳላቸው የገለጹት አበምኔቱ በገዳሙ በአሁኑ ሰዓት ሰላማዊ እንቅስቃሴ መቀጠሉን ገልጸውዋል።

@tikvahethiopia
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

በተለያዩ የሀገራችን ፊልሞች ላይ በድንቅ ብቃት በመተወን በተለይ ደግሞ በወጣቶች ዘንድ እጅግ የሚወደደው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ለማረጋገጥ ተችሏል።

አርቲስት ታሪኩ (ባባ) አርባ ያህል ፊልሞች ላይ የተወነ ሲሆን በህመም ምክንያት ህይወቱ ማለፉን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) ከአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች ለማረጋገጥ መቻሉን አሳውቋል።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ የአንድ ልጅ አባት ነበረ።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ፦
- ወጣት በ97፣
- ወንድሜ ያዕቆብ፣
- ላውንድሪ ቦይ፣
- ማርትሬዛ፣
- ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2 ፣
- ሞኙ የአራዳ ልጅ 4፣
-  አንድ ሁለት ፣
- ብር ርርር፣
- ወደው አይሰርቁ፣
- ወፌ ቆመች፣
-  እንደ ቀልድ ፣
- ወቶ አደር ፣
- አባት ሀገር
- የሞግዚቷ ልጆች፣
- ይዋጣልን ፣
- ዋሻው፣
- ወሬ ነጋሪ እና ሌሎችም ፊልሞች ላይ ተውኗል።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የቤኒሻንጉል ሕዝብ ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ታጣቂ ቡድን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት መፈራረሙና ወደ ሀገር መግባቱ ዛሬ ክልሉ አሳውቋል።

የቤሕነን ታጣቂ ቡድን እና የቤኒሻንጉሙዝ ክልል መንግሥት የሰላም ስምምነት ላይ የደረሱት በሱዳን #ካርቱም መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ቡድኑ የሰላም አማራጮችን በመከተል ወደ ክልሉ ተመልሷል ተብሏል።

በሰላም ስምምነቱ መሠረት የቡድኑ አባላት ትጥቃቸውን ፍትተው ተሃድሶ በመውሰድ በክልሉ የሰላም እና የልማት ሥራዎች ላይ እንደሚሰማሩ ክልሉ ገልጿል።

(የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሚኒኬሽን)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። በተለያዩ የሀገራችን ፊልሞች ላይ በድንቅ ብቃት በመተወን በተለይ ደግሞ በወጣቶች ዘንድ እጅግ የሚወደደው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ለማረጋገጥ ተችሏል። አርቲስት ታሪኩ (ባባ) አርባ ያህል ፊልሞች ላይ የተወነ ሲሆን በህመም ምክንያት ህይወቱ ማለፉን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) ከአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች ለማረጋገጥ…
#Update

የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ ፤ ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ ፤ በታዋቂው እና ተወዳጁ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ህልፈት ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል።

በመግለጫው ፤ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በህይወት በነበረበት ወቅት የዓይን ባንኩ አምባሳደር እንደነበርና ህልፈት በሚያጋጥምበት ጊዜ የዓይን ብሌኑን ለመለገስ ቃልገብቶ እንደነበር ጠቁሟል።

አርቲስቱ በገባው ቃል መሰረትም በቤተሰቦቹ እና በጓደኞቹ ቀና ትብብር ቃሉ ተፈፃሚ መሆኑን ባንኩ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ዓይን ባንክ ፤ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) " ስሙንም ብርሃኑንም ከመቃብር በላይ ህያው አድርጎ ያለፈ መልካም አርቲስት " ሲል ጠርቶታል።

በሌላ በኩል ፤ የአርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ)ን ስርዓተ ቀብር ለማስፈፀም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየሰራ ሲሆን ይኸው ኮሚቴ የአርቲስቱ ስርዓተ ቀብር ነገ ታህሳስ 3 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት እንደሚፈፀም ገልጻል።

ከስርዓተ ቀብሩ ቀደም ብሎ ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮዽያ ብሔራዊ ቴአትር ሽኝት ይደረጋልም ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የክቡር ዶ/ር ቄስ በሊና ሳርካ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ይፈፀማል።

ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አገልጋይ የነበሩት ቄስ ዶ/ር በሊና ሳርካ ባለፈው ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ማረፋቸው ይታወሳል።

የእኚህ በቤተከርስቲያንም ሆነ በአገር ደረጃ ተወዳጅ የነበሩት አባት አሸኛኘት አገልግሎት ዛሬ ሰኞ ታህሣሥ 3 ቀን 2015 ዓ/ም ይካሄዳል ፤ ከአሸኛኘት ስነ ስርዓቱ በኃላ ስርዓተ ቀብራቸው ይፈፀማል።

ለቄስ ዶ/ር በሊና ሳርካ የቀብር ስርዓትን ለማስፈፀም በወጣውና በተመለከትነው መርሃ ግብር መሰረት ፦ በአሁን ሰዓት (እስከ 4:00 ድረስ) አስክሬናቸው ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ እንጦጦ ማህበረ ምዕመናን እየተሸኘ ነው።

ከ4:00 - 6:00 የአስክሬን ሽኝት በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እንጦጦ ማ/ምዕመናን ይደረጋል።

በተጨማሪ በወጣው መርሃግብር መሰረት በወዳጅነት አደባባይ ሽኝት የሚደረግ ሲሆን ከዚህ በኃላ ከ9:00 - 10:00 አስክሬናቸው በጴጥሮስ ወ. ጳውሎስ መካነ መቃብር በክብር ያርፋል።

ፎቶ ፦ የክቡር ቄስ ዶ/ር በሊና ሳርካ የሽኝት ኘሮግራም በመኖሪያ ቤታቸው

@tikvahethiopia