TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ ፤ ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ ፤ በታዋቂው እና ተወዳጁ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ህልፈት ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል። በመግለጫው ፤ አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በህይወት በነበረበት ወቅት የዓይን ባንኩ አምባሳደር እንደነበርና ህልፈት በሚያጋጥምበት ጊዜ የዓይን ብሌኑን ለመለገስ ቃልገብቶ እንደነበር ጠቁሟል። አርቲስቱ በገባው ቃል መሰረትም በቤተሰቦቹ እና…
#Update
ከአርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ስርዓተ ቀብር ጋር በተያያዘ #ካሜራ ይዘው ቪድዮ ለመቅረፅ እና በየማህበራዊ ሚዲያው ለማስራጨት የሚሞክሩ ከድርጊታቸውን እንዲታቀቡ ስርዓተ ቀብሩን ለማስፈፀም የተቋቋመው ኮሚቴ አሳስቧል።
ከኮሚቴው አባላት አንዱና የአርቲስቱ የቅርብ ወዳጅ ዲጄ ቢቢ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ሬድዮ በሰጠው ቃል ፤ " ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር በተለይም ፌክ ኒውስ፣ የተለያዩ ቪድዮ እየቀረፁ ፣ ፎቶዎችን እያነሱ ርዕስ እየሰጡ የሚለጥፉ አሉ ወጣቶቻችን ፤ ታናናሾቻችን በዚህ ላይ ጥንቃቄ ያድርጉ። " ብሏል።
ትላንት የስርዓተ ቀብሩ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በአርቲስት ታሪኩ (ባባ) መኖሪያ ቤት በነበሩበት ሰዓት ካልተጠበቁ ሰዎች ቪድዮ ተቅርፆ ርዕስ እየሰጡ በቲክቶክ ...በማህባዊ ሚዲያ ላይ ሲለጥፉ እንደነበር ፤ ይህም የአካባቢውን ልጆች ፣ አብሮ አደጎቹንና የኮሚቴውን አባላት እንዳስደነገጠ ገልጿል።
ወጣቶች እንዲያህ ያለውን ነገር እንዳያደርጉ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።
የአርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ስርዓተ ቀብር ለማስፈፀመው በወጣው መርሃ ግብር ዛሬ ጥዋት 5:00 ላይ በብሄራዊ ትያትር አዳራሽ የሽኝት ፕሮግራም ይኖራል ፤ ፕሮግራሙ ላይ የሞያ አጋሮቹ፣ ጓደኞቹ ፣ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ይገኛሉ።
ከዚህ በኃላ ከቀኑ 9:00 ሰዓት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ይፈፀማል።
@tikvahethiopia

#ተጠንቀቁ
• " የአንድ ብሩን ሳንቲም በሺዎች በሚቆጠር ገንዘብ እንገዛለን ከሚሉ አጭበርባሪዎች ራሳችሁን ጠብቁ " - ብሄራዊ ባንክ
• " ድርጊቱ በህግ የሚያስጠይቅ ነው " - ፖሊስ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ " የአንድ ብሩን ሳንቲም በሺዎች በሚቆጠር ገንዘብ እንገዛለን " ከሚሉ አጭበርባሪዎች ኅብረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጠው ቃል ፤ ከሰሞኑ በተለያዩ ማኅበራዊ ድረገፆች " አራት የግዕዝ ፊደላት ያሉትን የአንድ ብር ሳንቲም በ2 ሺህ ብር እና ከዚያም በላይ እንገዛለን " የሚሉ ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች በስፋት ተስተውለዋል ብሏል።
ማስታወቂያዎቹ ኅብረተሰቡን ለማጭበርበር እየተነገሩ ያሉ እና ከእውነት የራቁ በመሆናቸው ፤ ኅብረተሰቡ ራሱን ከአጭበርባሪዎች ሊጠብቅ እንደሚገባ ገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ በበኩሉ፣ ድርጊቱ በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን ገልጾ በዚህ ማጭበርበር ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ግለሰቦች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ ማስጠንቀቁን ቴሌቪዥን ጣቢያው ዘግቧል።

Photo
ፎቶ ፦ የአርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (#ባባ) ሥርዓተ ቀብር በዛሬው እለት ቤተሰቦቹ ፣ አብሮ አደጎቹ ፣ የስራ ባልደረቦቹ ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
Credit : ETHIOPIA PRESS AGENCY
@tikvahethiopia
Credit : ETHIOPIA PRESS AGENCY
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
የክቡር ዶ/ር ቄስ በሊና ሳርካ ስርዓተ ቀብር ተፈፅሟል።
ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አገልጋይ የነበሩት የቄስ ዶ/ር በሊና ሳርካ አስክሬን በጴጥሮስ ወ. ጳውሎስ መካነ መቃብር በክብር ያርፏል።
ከስርዓተ ቀብሩ ቀደም ብሎ በመኖሪያ ቤታቸው ፣ በእንጦጦ ማህበረ ምዕመናን እንዲሁም በወዳጅነት አደባባይ ሽኝት ተደርጓል።
Credit : Entoto Mekane Yesus

Addis Ababa University- Cisco Networking Academy,
@CiscoExams www.netacad.com www.cisco.com
Cisco CCNA Professional Network Engineering Training & Certification Preparation.
Class start date: Dec 17, 2022.
CCNA trainees will receive 3 international certificate of training completion, 3 digital badge & 58% discount voucher for the international exam.
Phone #: 0902-340070 OR 0935-602563 OR 0945-039478:
Follow our telegram channel: @CiscoExams

#USA
ዛሬ የሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የ49 አገራት መሪዎች እንዲሁም አፍሪካ ህብረት የሚሳተፉበት ሁለተኛው የአሜሪካ- አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ይጀመራል።
ለዚሁ ጉባኤ ዶ/ር ዐቢይን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አሜሪካ ላይ ተሰባስበዋል።
ለሦስት ቀናት የሚካሄደው ይኸው የመሪዎች ጉባኤ ዓለማችንን እየፈተኗት ያሉ ተግዳሮቶች ፦
- የአየር ንብረት ቀውስ፣
- መልካም አስተዳደር፣
- የምግብ ዋስትና እና የዓለም ጤናን የሚጨምር ሲሆን፣ እንዲሁም የአሜሪካ-አፍሪካ የንግድ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማጠናከር ላይ ያተኩራል።
አሜሪካ ጉባዔው አፍሪካ ቁልፍ የጂኦፖለቲካል ተጫዋች እንደሆነች ዕውቅና በመስጠት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ገልጻለች።
በአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ፕሬዝዳንት ባይደን በቡድን 20 ውስጥ የአፍሪካ ኅብረት ቋሚ ቦታ እንዲያገኝ ድጋፍ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
በተጫማሪም የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ከአፍሪካ አገራት መካከል " ቋሚ አባል እንዲያካትት " ድጋፍ መስጠትን ጨምሮ ማሻሻያ እንዲያደርግ ፕሬዝዳንት ባይደን ቁርጠኛ እንደሆኑ ተነግሯል።
በሌላ በኩል ፤ አሜሪካ ለአፍሪካውያን አገራት ከቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት ዕድል (#አጎዋ) ጋር በተያያዘ ከተጠቃሚ አገራቱ ንግድ ሚኒስትሮች ጋር የሚካሄደው ጉባኤ ዛሬ ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን ቢቢሲ ዘግቧል።
#DrAbiyAhmed - " አፍሪካ ፡ የዓለም አቀፍ ንቅናቄ አጣዳፊነት " በሚል መሪ ሀሳብ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ አቺቭመንትና ግሎባል ሆፕ ኮአሊሽን የተሰኙት ተቋማት በዋሽንግተን ዲሲ በጋራ ባዘጋጁት ልዩ ዝግጅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄን አስመልክቶ ላሳዩት አመራር ‘የአፍሪካ የላቀ አመራር’ ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

በአዲስ አበባ የትምህርት ቤቶች ጉዳይ የከተማው አስተዳደር፣ ትምህርት ቢሮ ፣ ፖሊስ ፣ ወላጆች ምን ይላሉ ?
የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፦
" ሲጀመር አዲስ አበባ አፋን ኦሮሞ የምታስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልነበራትም መምህራኖች ታውቃላችሁ ይሄንን እውነት።
ያኔ ቀርቶ እስካሁንም አፋን ኦሮሞ ወይም ቋንቋዎች የምናስተምርበት ስርዓተ ትምህርት አልጨረስንም አላፀደቅንም።
ስርዓተ ትምህርት ከኦሮሚያ ተዋስን አፋን ኦሮሞ የሚሰጠው ኦሮሚያ ነው ይህ በዘመነ ኢህአዴግ ነው።
እዛ ላይ ስርዓተ ትምህርቱ ላይ ምን አለ ትምህርት ክፍል ከመጀመሩ በፊት የክልሉ መዝሙር ይዘመራል፤ የክልሉ ባንዲራ ይሰቀላል የሚል አለ።
ይህን ሙሉ ስርዓተ ትምህርቱን በመተግበር ነው 4 ትምህርት ቤቶች (አ/አ ያሉ) የጀመሩት። በውቅቱ አጀንዳ ያደረገውም የለም። በዚህ ምክንያት በተለየ ሁኔታ ኦሮሞ ይጠቀማል ተብሎ የታሰበ ነገር አልነበረም።
ከዛ ተማሪዎች እያደር እየሰፉ መጡ ፣ ከየአካባቢው ፍላጎት ያላቸው ፣ በየአካባቢው ተመዝጋቢ እየበዛ መጣ ኦሮሞም የሆነ ያልሆነ መማር የሚፈልግ እየተመዘገበ መጣ።
እና እንዴት አድርገን ነው የካ ላይ የተመዘገበን ሄደህ ኮልፌ ላይ ነው የምትማረው የምንለው ? ለምን በአካባቢው ላይ ባለ ት/ቤት ክፍል የማንከፍትለት ?
በአካባቢው ትም/ቤት ላይ ፤ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መማር እንዲችሉ ትምህርት ቤት እየተከፈተ (በ403 ትምህርት ቤት ውስጥ) በአፋን ኦሮሞ መማር ተጀመረ ሲጀመር ይኸው ካሪኩለም / ስርዓተ ትምህርት ነው አብሮ እየሄደ ያለው።
መማህራኖች፣ ትምህርት ቤቶች እጃቸው ላይ ያለው ስርዓተ ትምህርት እሱ ነው ስርዓተ ትምህርቱን ተግብሩ ተብሎ ስለተሰጣቸው ስርዓተ ትምህርቱ ላይ ያለውን ሙሉ ነገር እየተገበሩ መጡ ይኸው ነው። "
የአ/አ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፦
" የሆኑ ት/ቤቶች ላይ ይሄንን ቋንቋ አንሰማም የሚል ይህ መዝሙር መዘመር የለበትም የሚል ጥያቄ ያነሳ አለ። ሌላ ትምህርት ቤቶች ላይ በተለይ አፋን ኦሮሞ ተማሪዎች የሚበዙበት ላይ ሌላ ጥያቄ።
በአማርኛ የሚማሩ/ የአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች ቁጥር ባነሰበት በባንዲራ መዝሙር አላማው አንድ ያደረገ ግን በተለያየ ስትራቴጂ መጥቶ የከተማውን ሰላማዊ መማር ማስተማር ማደፍረስ ነው። "
ወላጆች እና ተማሪዎች የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ምን ይላሉ ?
ደስ ታቲሌስ ፦
" ... ትምህርት በ ' #አፍ_መፍቻ_ቋንቋ ' መማር እና የአንድ ክልልን ባንዲራን መስቀልና መዝሙር ማዘመር በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው።
ለምሳሌ ያህል ፦ አብዛኛዎችን የትምህርት አይነቶች የምንማረው በእንግሊዘኛ ነው። ነገር ግን የእንግሊዝን መዝሙር አልዘመርንም ፣ ባንዲራቸውም በትምህርት ቤቶቻችን ላይ አልተሰቀለም።
ይህንን ያልኩት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወይንም በመንግስት የተገነቡት ትምህርት ቤቶች ላይ ነው።
የግል ትም/ቤትን አይጨምርም። አሁን ግን የኦሮሚያ ክልል መዝሙር እየተዘመረ እና ባንዲራው እየተሰቀለ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በራሱ ወጪ በሰራቸው ትምህርት ቤቶች ላይ ነው።
ሲቀጥል ቋንቋውን ማስተማርም ካስፈለገ የሌላውን ክልል መዝሙር እንዲዘምሩ በማስደረግ መሆን የለበትም።
በከተማው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲማሩ እኮ የአማራ ክልል ባንዲራ አልተሰቀለም ፤ የአማራ ክልልን መዝሙር አልተዘመረም።
አሁን ላይ እየታየ ያለው ነገር እና ለድርጊቱ የከተማ አስተዳደር እየሰጠ ያለው መልስ ፍፁም የተለያየ ነው። "
ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/ADDIS-ABABA-12-13

Telegraph
ADDIS ABABA
#ADDIS_ABABA በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ጋር በተያያዘ ባለፈው ዓመት ከኦሮሚያ ክልላዊ ባንዲራ እና መዝሙር ጋር ተያይዞ የነበረው ሁኔታ ዘንድሮ በተለይም ደግሞ ከሰሞኑን ተባብሶ ነበር። ይኸውም ችግር በተለያዩ ወገኖች እና በመንግስት አካላት የተለያየ ማባራሪያ እየተሰጠበት ነው። ወላጆችም የሚሉት አላችሁ። ነዋሪዎች ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር…
ሀሰተኛ የትምህርት መረጃ ...
(በዳውሮ ዞን)
በዳውሮ ዞን ፤ ከጪ በተባለው ወረዳ ለመጀመሪያ ዙር በተደረገ ማጣራት ከ264 የትምህርት መረጃ 127 #ሀሰተኛ ሆኖ መገኘቱ ተሰምቷል።
ሀሰተኛ ሆኖ ከተገኘው የትምህርት መረጃ መካከል 6ቱ #የአመራርና ቀሪው #የመንግስት_ሰራተኞች ነው።
የሁለተኛ ዙሪ የማጥራት ስራ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
በዚሁ ዞን ፤ ቶጫ በተባለው ወረዳ በመጀመሪያ ዙር ከተደረገው ማጣራት ከ565 የትምህርት መረጃ የ218 ሰዎች #ሀሰተኛ ሆኖ ተገኝቷል።
መረጃቸው ወደ ግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተልኮ ከተጣራው ከ565 የመንግስት ሰራተኞች መካካል የ210 ባለሙያዎችና የ8 #አመራሮች የትምህርት መረጃ ነው ሀሰተኛ ሆኖ የተገኘው።
ይኸው የማጣራት ስራ ይቀጥላል ተብሏል።
መረጃው ከዳውሮ ኮሚኒኬሽን የተገኘ ነው።