#AddisAbaba
" ስፖኪዮ የተሰረቀባችሁ ማስረጃ በማቅረብ ንብረታችሁን መውሰድ ትችላላችሁ "
የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ፤ በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ ከ200 በላይ የተሽከርካሪ ስፖኪዮ ጉድጓድ ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን አስታውቋቃ።
ስፖኪዮዎቹን እየተቀበሉ በማከማቸት የተጠረጠሩ 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛልም ብሏል።
ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ አሜሪካን ግቢ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ በአካባቢው በላስቲክ ተወጥሮ በተሰራ መኖሪያ ቤት ውስጥ ጉድጓድ ቆፍረው በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ በርካታ የመኪና ስፖኪዮዎችን አከማችተው የተገኙ ናቸው።
ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማና ፖሊስ ባደረገው ክትትል 2 ግለሰቦችን ከነኤግዚቢቶቹ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ የገለፀው ፖሊስ በተከናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ የተሰረቁ ተጨማሪ ስፖኪዮዎች በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ጎላ ሚካኤል ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ እንደተመለሱ እና በአጠቃላይ 202 ስፖኪዮዎች ከነመፍቻዎቹ እንደተያዙ አሳውቋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በተለያዩ ጊዜያት ስፖኪዮ የተሰረቀባቸው ባለንብረቶች ማስረጃዎቻቸውን በማቅረብና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል እየቀረቡ ንብረታቸው ስለመኖሩ አረጋግጠው እንዲረከቡ መልዕክቱን አስተላልፏል።
(አዲስ አበባ ፖሊስ)
@tikvahethiopia

ፎቶ ፦ በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ ዞን ከወልድያ ወደ ቆቦ በሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኘው የ " አለውሃ " ወንዝ የብረት ድልድይ ስራ ተጠናቆ ዛሬ ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ/ም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (ERA) አሳውቋል።
Credit : https://telegra.ph/ERA-12-10
@tikvahethiopia
Credit : https://telegra.ph/ERA-12-10
@tikvahethiopia
የት ገቡ ?
(በባይሽ ኮልፌ)
#እስካሁን_አልተገኙም !
👉 ወጣት አብርሀም በየነ ከ3 ዓመት በፊት ከሚኖርበት ሀዋሳ ወደ ወልቂጤ ሚቄ የሚባል ቦታ መጥቶ ወረዳ ውስጥ ስራውን እየሰራ መስከረም 25 " እናቴ ናፍቃኛለች አይቻት ልምጣ " ብሎ ለጓደኞቹ ነግሮ ከቢሮና ከተከራየበት ቤት ቢወጣም እናቱ ጋር ሳይደርስ ወደ ቤቱም ሳይመለስ የት እንደገባ ጠፍቶ 2 ወር አልፎታል። በየቀኑ ይደውልላት የነበረው እናት " የምሄድበት ግራ ገባኝ ምን ልሁን? " እያለች ቤተክርስቲያን እየዞረች በፀሎት እያነባች ነው 😭 ስልኳ-0985132283 (እልፍነሽ-እናት)
👉 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግራውንድ ቴክንሽያን ዳዊት ምትኩ ከሚኖርበት አምባሳደር ኮንዶሚኒየም አካባቢ ድንገት እንደወጣ ሳይመለስ 24 ቀናት ተቆጥረዋል። እናትና አባት እንዲሁም እህቱ እያለቀሱ መንገድ ለመንገድ እየተንከራተቱ ነው። (0941213747-የእህቱ ስልክ)
👉 የ2 ህፃናት አባት በሙያው ጎበዝ ሼፍ የሆነው ዘሪሁን ቢሰጥ ሀያት አካባቢ የሚከፈት አዲስ ሆቴል ውስጥ ስራ ሊጀምር እንደሆነ ለባለቤቱ ነግሯት ሰኞ ህዳር 12 ዓ/ም በስራው ዙሪያ ለመነጋገር ቀጠሮ እንዳለውና በዛውም ኬጂ የምትማረው የመጀመሪያ ልጁን ኮተቤ የሚገኘው አፕል አካዳሚ ላድርሳት ብሎ እንደወጣ ሳይመለስ ቀርቷል። 18 ቀናት ተቆጥረዋል ፤ ባለቤቱ "መቋቋም አቃተኝ፣ አመመኝ ድፍን ያለነገር ሆነብኝ " እያለች ነው። (0920181284-ሰብለ ባለቤቱ)
መልዕክቱን ሼር በማድረግ ያፋልጉን !
(ባየሽ ኮልፌ)

ፕሬዜዳትን ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ኤርትራ ይገኛሉ።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ በኤርትራ የሁለት ቀን የስራ ጉብኝት እያደረጉ መሆኑ ታውቋል።
ፕሬዜዳንቱ ትላንት አስመራ ኤርፖርት ሲደርሱ በፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ሩቶ በኤርትራ የስራ ጉብኝት ላይ የሚገኙት በፕሬዜዳንት ኢሳያስ ግብዣ ሲሆን ትላንት ከቀትር በኃላ የሁለትዮሽ ውይይት ከፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር አድርገዋል።
የተደረገው ውይይት ሰፊ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ውይይቱ ያተኮረው የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እና ቀጠናዊ አጋርነትን ማጠናከር ላይ እንደበር ከኤርትራ መንግስት በኩል ተሰምቷል።
ፎቶ ፦ Yemane G. Meskel

" ዎላይታ ታይምስ " ፤ የተሰኘው ሚዲያ ከመንግስት አካል ይደርስብኛል ባለው ጫና ሥራ ማቋረጡን ገልጿል።
በኢትዮጲያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በሚዲያ ሥራ ለመሰማራት ሕጋዊ ፈቃድ ወስዶ በዞናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ የነበረው "ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ" በደረሰበት ጫና ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ሥራ ማቆሙን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላከው መረጃ ያሳያል።
የሚዲያው መስራች የሆነው ጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ በሥራው በተደጋጋሚ ለእስርና ለእንግልት፣ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት መዳረጉን ጠቅሶ በቅርቡም ከቀን 19/03/2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት ላይ ጥላቻና ሀሰተኛ መረጃ አሰራጭቷል በሚል ተጠርጥሮ በዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደነበር ተናግሯል።
ጋዜጠኛው ፤ በዎላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስሮ ከቆየበት ትላንት 28/3/2015 ዓ.ም በሰላሳ ሺ (30,000) ብር ዋስትና መለቀቁን ተናግሯል።
ተመሳሳይ አይነት ጫና በመኖሩም ሌሎች የሚዲያው ጋዜጠኞችም ማስፈራሪያና ዛቻ እየደረሰባቸው በመሆኑ ሥራው ተቋርጦ ቢሮው መዘጋቱን አክሎ ገልጿል፡፡
ሚዲያው እየደረሰበት ያለውን ከፍተኛ ጫና ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ጨምሮ ለሚመለከታቸው አካላት " በደብዳቤ ጭምር " ማስታወቁን የገለጸ ቢሆንም ምንም አይነት ምላሽ አለማግኘቱን ጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።
ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Wolaita-Times-12-10

Telegraph
Wolaita Times
"ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ" ከመንግስት አካል ይደርስብኛል ባለው ጫና ሥራ ማቋረጡን ገለጸ። በኢትዮጲያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በሚዲያ ሥራ ለመሰማራት ሕጋዊ ፈቃድ ወስዶ በዞናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ የነበረው "ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ" በደረሰበት ጫና ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ሥራ ማቆሙን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላከው መረጃ ያሳያል። የሚዲያው መስራች ጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ በሥራው በተደጋጋሚ…
#ዓለም_ዋንጫ
አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ደማቅ አዲስ ታሪክ ፅፋለች !
በአሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ የሚመራው የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በየሱፍ ኤል ነስሪ ብቸኛ ግብ ፖርቹጋልን በመርታት ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።
⚽️ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫው ታሪክ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል የቻለች ቀዳሚዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆናለች።
⚽️ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በኳታሩ የዓለም ዋንጫ #በተጋጣሚ_ቡድን #ተጫዋች አንድም ግብ ከመረብ አላረፈባቸውም።
⚽️ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን 196 ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል።
⚽️ የሱፍ ኤል ነስሪ በዓለም ዋንጫው ሶስት ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ በታሪክ የመጀመሪያው #ሞሮካዊ ተጫዋች ሆኗል።
https://t.iss.one/tikvahethsport

#ፌርማታ
በፋና ላምሮት ፡ በፋና ቀለማት እና በፋና 90 የሚታወቀው ጋዜጠኛ አዳነ አረጋ በአዲስ Reality show እና ቲዩብ መምጣቱን ገልጿል “Entoto Tube”
“ፌርማታ ሾው” ሁሉንም ሰው የሚያሳትፍ ሾው ሲሆን ዘውትር እሁድ በፋና ቲቪ ይተላለፋል በEntoto tube” ታገኙታላችሁ።
በEntoto Tube ሌሎችንም አዳዲስ ልዩ የመዝናኛ ሾዎች ለየት ባለ መልኩ በቅርቡ ወደእናንተ ይደርሳሉ SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ https://www.youtube.com/@entototube