TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሰቆጣ ከተማ ጤና ጣቢያ "ብፁዕ አቡነ በርናባስ ጤና ጣቢያ " ተብሎ እንዲጠራ የከተማው ም/ቤት አጸደቀ።

የሰቆጣ ከተማ ም/ቤት ባካሔደው አስቸኳይ ጉባኤ ነው የሰቆጣ ከተማ ጤና ጣቢያን " በብፁዕ አቡነ በርናባስ ጤና ጣቢያ" በሚል ስያሜ እንዲፀድቅ ያደረገው።

ጤና ጣቢያው በብፁዕ አቡነ በርናባስ የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ስም እንዲሰየም የተደረገበትን ዋነኛ ዓላማ ለም/ቤቱ የተብራራ ሲሆን በዚህም፦

- ብፁዕነታቸው ባለፈው ዓመት ማኅበረሰቡ በጦርነት ምክኒያት ተፈናቅሎ በነበረበት ወቅት ያበረከቱት አስተዋጽኦና መልካም ሥራቸው ሕያው ሆኖ እንዲቀጥል፤

- ብፁነታቸው ሙስሊም፣ ክርስቲያን ዘርና ቋንቋ ሳይለዩ ሁሉም እናቶች፣ ሕጻናት፣ አረጋዊያንና ማኅበረሰብ የሚበሉትና የሚጠጡት አጥተው ሲቸገሩ ካለው ለምነው የሌለው በመስጠት፣ መንግስት ሠራተኞች ለዐራት ወራት ያህል ደሞዝ በመቋረጡ ምክኒያት ሲቸገሩ ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ከባለሃብቱና ከበጎ አድራጊዎች ገንዘብ አፈላልገው በመስጠት ታሪክ የማይረሳው ሥራ በመሥራታቸው፤

- ከሕዝባቸውና ማኅበረሰባቸው ጋር ችግሩን ሁሉ ተጋፍጠው በየቦታው ገንዘብ እያሰባሰቡ፣ ቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ላይ ለምዕመናን ትምህርት በመስጠትና በማጽናናታቸው፤

- የጤና ተቋማት እንዳይዘነጉ እና አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ከ160 በላይ እናቶች በጤና ተቋም እንዲወልዱ በማድረጋቸው፤ ያበረከቱትን ሕያው ሥራ እውቅና ለመስጠትና ትውልዱ ከመልካምና ከማይሞት ሥራቸው እንዲማርና የእሳቸውን ፈለግ እንዲከተል፣ በጤና ተቋም አገልግሎት የሚያገኙ አካላት እንዲዘክሩ የሰቆጣ ከተማ ጤና ጣቢያ የሚለው ስም" ብፁዕ አቡነ በርናባስ ጤና ጣቢያ" ተብሎ እንዲሰየም ተደርጓል።

መረጃው የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ነው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማንኛውም የቋሚ ንብረት ሥም ዝውውር አገልግሎት፤ ከትናንት ኀዳር 29 ቀን 2015 ጀምሮ በጊዜያዊነት መታገዱ ተገልጿል።

አገልግሎቱ የታገደው በከተማዋ ህገ ወጥነትን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ሒደት ውጤታማ ለማድረግ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።

ለሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ለሚመለከታቸው አካላትም የተላለፋው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲሆን ትዕዛዝ መሰጠቱንም የከተማ አስተዳደሩን ዋቢ አድርጎ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExam የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ  ፦ " የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ የቀን ፣ የማታ እና የርቀት መርሀ ግብር ተመራቂዎች ይሰጣል። ከዚህ ዓመት ጀምሮ  በመንግስትና ግል ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ የሚደረገውን የመውጫ ፈተና #በኦንላይን ለመስጠት ታቅዷል ። በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመሠረተ ልማት አቅሞቻቸውን ከወዲሁ በማረጋገጥ ለፈተናው…
#MoE

• መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።

• 200, 000  ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።

መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚገኙ  ተማሪዎች በአንድ ጊዜ እንደሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ገልጸዋል።

መሪ ስራ አስፈጻሚው ኤባ ሚጀና ( ዶ/ር )  በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ አውደጥናት ላይ  እንደገለጹት መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ  ወር ለሁሉም ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች  በአንድ ጊዜ ይሰጣል።

የመጀመሪያው ፈተና በሰኔ  ወር ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ የመውጫ ፈተና ከ6 ወራት  በኋላ እንደሚሰጥም ዶ/ር ኤባ  አስረድተዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው ፈተናውን ለ200, 000 የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ፈተናው ለሁሉም ተማሪዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ የጠቀሱት አቶ ሰይድ " ይህ የፈተና ስርቆትን ለመከላከል የተሻለ አማራጭ  በመሆኑ ነው " ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱም ሆኑ ተፈታኝ  ተማሪዎች ፈተናው በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው #ከወዲሁ_ዝግጅት እንዲያደርጉ አቶ ሰይድ አሳስበዋል።

በመውጫ ፈተና ብቃትና የፈተና ኮርሶች ልየታና የተገቢነት ማረጋገጥ ዙሪያ በተዘጋጀው አውደጥናት ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውም ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

(ትምህርት ሚኒስቴር)

@tikvahethiopia
" ሰሞኑን ባምቢሲ ወረዳ በሚገኝ መጠለያ ጣቢያ ብቻ 16 ሺህ ሰላማዊ ሰዎች ገብተዋል " - የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ሰላምን ፍለጋ እና ህይወታቸውን ለማትረፍ እየሸሹ ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ባምቢሶ ወረዳ የሚገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ዶቼ ቨለ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ምዕራብ ወለጋ ዞን ቆንዳላ ፣ ቤጊ ፣ መንዲ አካባቢ በሚደረጉ ግጭቶችና በዘር ላይ ባነጣጠሩ ጥቃቶች በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል ፤ በርካቶችም ከቄያቸው ተፈናቅለዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለዶቼ ቨለ በሰጠው ቃል ፤ ከግጭትና ጥቃቱ አምልጠዉ ሰሞኑን ባምቢሲ ወረዳ በሚገኝ መጠለያ ጣቢያ ብቻ 16 ሺህ ሰላማዊ ሰዎች ገብተዋል።

ኮሚሽኑ ከባለፈው ዓመት ህዳር 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከምዕራብ ወለጋ ሰዎች ወደ ባምባሲ መፈናቀላቸውን አመልክቶ ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ከዞኑ ማናስቡ ወረዳ፣ ቤጊና ቆንዳላ ወረዳዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ባምባሲ መፈናቀላቸውን ገልጿል።

በዚህም በወረዳው ያለው የተፈናቃይ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የገለፀው ኮሚሽኑ ፤ በወረዳው 16 ሺህ በላይ ከምዕራብ ወለጋ እና ማኦ ኮሞ ወረዳ ተፈናቅለው በመጠለያ ይገኛሉ ሲል ለሬድዮ ጣቢያው አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Tigray #Afar

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሎጅስቲክስ ክላስተር ትብብር ወሳኝ የሆኑ ህይወት አድን ድጋፎችን በአየር መቐለ መድረሳቸውን አሳውቋል።

መቐለ በአየር ከደረሰው ህይወት አድን ድጋፍ መካከል የUNICEF ክትባቶች እና በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለተጎዱ እናቶች እና ህፃናት የሚውል የዓለም ምግብ ፕሮግራም ድጋፍ የተካተተበት ነው።

UNICEF ይፋ ባደረገው መረጃ 1.4 ሚሊዮን ዶዝ ክትባቶችን መቐለ ደርሷል። ክትባቶቹ በክልሉ 50,000 ህጻናትን እና እናቶችን ለመከተብ እንደሚውሉ የሚውሉ ናቸው ተብሏል። መቐለ ከደረሱት ክትባቶች አሁን ላይ በክልሉ ላሉ ጤና ጣቢያዎች እየተከፋፈሉ መሆኑ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ በዩናይትድ ኪንግደም ድጋፍ በሰሜን ምዕራብ አፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የምግብ እርዳታ የያዙ ተሽከርካሪዎች ስለመንቀሳቀሳቸው ተሰምቷል።

እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች በዓለም ምግብ ፕሮግራም በኩል እንዲደረስ በዩናይትድ ኪንግደም የተሰጠው ወሳኝ የሆኑ ህይወት አድን ድጋፎችን የያዙ 54 ተሽከርካሪዎች መሆናቸው ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#ሀበኑ_ሞባይል

ኦርጅናል አይፎ እና ሳምሰንግ ስልኮችን ከሙሉ መለዋወጫ እና የ 1አመት ዋስትና ጋር ይዘን ቀርበናል።

እጆት ላይ ያለውን ስልክም በጥሩ ዋጋ ስለምንወስድሎ ለበለጠ መረጃ በአካል ይምጡ አልያም በስልክ ቁጥራችን ይደውሉ በተጨማሪም ለድርጅቶች ታብሌት እና ላፕቶፖችን በብዛት እናቀርባለን።
ስልክ ፦0924537515 ፣ 0925061718
📍አድራሻ ቦሌ ኤድናሞል ሬድዋን ህንፃ አጠገ
#STEMPower  #EIPA

ስቴም ፖወር በተለያዩ ዙር ባሰለጠናቸው ወጣቶች እንዲሁም በትምህርት ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ በሚገኘው ማምረቻ ቦታው የተሰሩ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎችን የባለቤትነት መብት ጥበቃ እንዲያገኙ ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

የሁለቱ ተቋማት ስምምነት በተለይ ወጣቶች የሚሰሯቸው የፈጠራ ውጤቶች በሌሎች እንዳይቀሙ እና አቅማቸውን አጎልብተው ወደገበያ እንዲወጡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞም የተለያዩ ሥልጠናዎች ለወጣቶቹ እንደሚሰጡ ተጠቁሟል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" ስፖኪዮ የተሰረቀባችሁ ማስረጃ በማቅረብ ንብረታችሁን መውሰድ ትችላላችሁ "

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ፤ በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ ከ200 በላይ የተሽከርካሪ ስፖኪዮ ጉድጓድ ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን አስታውቋቃ።

ስፖኪዮዎቹን እየተቀበሉ በማከማቸት የተጠረጠሩ 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛልም ብሏል።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ አሜሪካን ግቢ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ተጠርጣሪዎቹ በአካባቢው በላስቲክ ተወጥሮ በተሰራ መኖሪያ ቤት ውስጥ ጉድጓድ ቆፍረው በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ በርካታ የመኪና ስፖኪዮዎችን አከማችተው የተገኙ ናቸው።

ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማና ፖሊስ ባደረገው ክትትል 2 ግለሰቦችን ከነኤግዚቢቶቹ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ የገለፀው ፖሊስ በተከናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ የተሰረቁ ተጨማሪ ስፖኪዮዎች በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ጎላ ሚካኤል ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ እንደተመለሱ እና በአጠቃላይ 202 ስፖኪዮዎች ከነመፍቻዎቹ እንደተያዙ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በተለያዩ ጊዜያት ስፖኪዮ የተሰረቀባቸው ባለንብረቶች ማስረጃዎቻቸውን በማቅረብና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል እየቀረቡ ንብረታቸው ስለመኖሩ አረጋግጠው እንዲረከቡ መልዕክቱን አስተላልፏል።

(አዲስ አበባ ፖሊስ)

@tikvahethiopia