TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ላለፉት ቀናት በኬንያ፣ ናይሮቢ ሲካሄድ የነበረው የመንግስት እና የህወሓት የሰላም ንግግር (ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እና የፖለቲካ ተደራዳሪዎች የተገኙበት) የተደረሰበት ደረጃ እና ስምምነትን በተመለከተ በአሁን ሰዓት መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ፣ ኡሁሩ ኬንያታ ፣ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ በመድረኩ ላይ ተሰይመዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ይጠብቁ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአሁን ሰዓት በናይሮቢ እየተሰጠ ባለው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ወታደራዊ አመራሮች ባለፈው በደቡብ አፍሪካ፣ ለተፈረመው የሰላም ስምምነት ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል። ተጨማሪ መረጃዎችን ይጠብቁ። @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#BREAKING

በናይሮቢ ሳምንት ያህል የፈጀውን ውይይት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ከፍተኛ የጦር አዛዦች #ጦርነቱን_ለማቆም የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ፤ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በዘላቂነት ግጭት እንዲቆም ስምምነት መፈረማቸው ይታወሳል ዛሬ ወታደራዊ አመራሮቹ በናይሮቢ ስምምነቱን ለማስፈጸም የሚያችል ስነድ ተፈራርመዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃ ይጠብቁ።

Video Credit : Ruud Elmendrop

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በሰላም ስምምነቱ መሠረት የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበት ዝርዝር ዕቅድ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አዛዥና የሕወሐት ታጣቂዎች አዛዥ በናይሮቢ መክረዋል።

በሰላም ስምምነቱ በተያዘው የጊዜ ገደብ ትጥቅ የሚፈታበትንና መከላከያ ወደ መቐለ የሚገባበትን ዕቅድ ላይም #ተስማምተዋል። ዕቅዱም በቀጣይ ተግባራዊ ይደረጋል።

ለዕቅዱ ተግባራዊነት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በስምምነቱ መሠረት የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መንግሥት ማሳሰቡን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ከናይሮቢው ስምምነት በኃላ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Africa አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦ " ዛሬ የተፈረመው ስምምነት #የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካውያን ይፈታሉ የሚለውን እሳቤ እንዲጸና ያደረገ ነው ። " #ENA @tikvahethiopia
#Update

ዛሬ በናይሮቢ #በተፈረመው_ስምምነት መሰረት ፤ በሚቀጥሉት 7 ቀናት ወታደራዊ ሀላፊዎቹ ለወታደሮቻቸው ኦረንቴሽን እንደሚሰጡና ከዛም የፌደራል ባለስልጣናት በትግራይ ኃላፊነታቸውን እንደሚረከቡ ይገልፃል።

የከባድ መሳርያዎች ትጥቅ አፈታትም በትግራይ ክልል ያሉ የውጭ ኃይሎች እና ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ ያሉ ኃይሎች ከክልሉ መውጣት ጋር በአንድ ግዜ እንደሚፈፀም ይገልጻል።

የቀላል መሳርያዎች ትጥቅ አፈታትን ለማሳለጥ ከሁለቱም ወገን የተውጣጣ ኮሚቴ እንደሚቋቋምም የስምምነት ሰነዱ ላይ ሰፍሯል።

(Credit : ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

@tikvahethiopia