TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Peace
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ምን አሉ ?
የፕሪቶሪያ ስምምነትና የዛሬው ናይሮቢ ስምምነት ተፈፃሚ እንዲሆን ለማድረግ በሙሉ ቁርጠኝነት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።
ጀነራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ?
የዛሬው ስምምነት በትግራይ ውስጥ በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ ያስወግዳል የሚል ተስፋ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።
ኡሁሩ ኬንያታ ምን አሉ ?
ኡሁሩ ኬንያታ በዛሬው መግለጫ ስምምነቱ በጦር ወንጀሎች ላይ " ተጠያቂነትን " ያጠቃልል እንደሆነ ለተጠየቀ ጥያቄ ምላሽ ሰጥተው ነበር።
ኡሁሩ ኬንያታ ይህ " የመሳሪያ ድምፅ ፀጥ ሲል እና አስከፊው የሰብአዊ ሁኔታ ሲስተካከል " እንደሚመጣ ተናግረዋል።
" በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግፍ የሚፈጽም አካል ላይ ከባድ ማዕቀብ ይጣልበታል " ብለዋል።
@tikvahethiopia

#Peace ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ምን አሉ ? የፕሪቶሪያ ስምምነትና የዛሬው ናይሮቢ ስምምነት ተፈፃሚ እንዲሆን ለማድረግ በሙሉ ቁርጠኝነት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል። ጀነራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ? የዛሬው ስምምነት በትግራይ ውስጥ በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ ያስወግዳል የሚል ተስፋ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል። ኡሁሩ ኬንያታ ምን አሉ ? ኡሁሩ ኬንያታ በዛሬው መግለጫ ስምምነቱ በጦር…
#Update
በደቡብ አፍሪካ ፤ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የኢትዮጵያ መንግስትን ወልክለው ፊርማቸውን ያኖሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከዛሬው የናይሮቢው ስምምነት በኃላ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።
አምባሳደር ሬድዋን ፤ ከዛሬው የቀጠለ ውይይት (በወታደራዊ ኃላፊዎች መካከል) የዛሬ ወር ገደማ (mid-December) በትግራይ ክልል መዲና #መቐለ ላይ ሊደረግ እንደሚችል ጠቁመዋል።
ዋናውና የውይይቶቹ ፍፃሜ ደግሞ በፈረንጆቹ አዲስ አመት #አዲስ_አበባ ላይ ሊደረግ እንደሚችል ገልፀዋል።
የናይሮቢው ውይይት በተጀመረበት ዕለት ኡሁሩ ኬንያታ ፤ " በፕሪቶሪያ ጀመርን፣ መንገዳችን እየተጠጋ ፤ አሁን ናይሮቢ ነን ፣ በሚቀጥለው ጊዜ ስብሰባችን መቐለ እንደሚሆን ተስፋ አድርጋለሁ ፤ በመጨረሻም አዲስ አበባ ላይ አብረን እናከብራለን። ይህ ጸሎታችን ፣ ተስፋ የምናደርገው እና የምንፈልገው ነው። " ማለታቸው አይዘነጋም።
በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው ፤ የናይሮቢው ውይይት የተደረገው በፕሪቶርያ የተደረገውን ስምምነትን መሰረት አድርጎ መሆኑን ገልፀዋል።
ነገር ግን በዚህ ውይይት የውጭ ኃይሎች ጉዳይ " sticking point " እንደነበር እና ውይይቱ በዛ ሁኔታ የተካሄደ እንደነበር አስረድተዋል።
(አምባሳደር ሬድዋን እና አቶ ጌታቸው ቃላቸውን የሰጡት በዛው ኬንያ፣ ናይሮቢ ለሚገኘው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ነው )

#የፀጥታ_ጉዳይ
" የክልል እና የፌደራል የጸጥታ ሀይል እንዲገባልን አመልክተናል " - አቶ ውብሸት አበራ
ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከሌሊት 8 ሰዓት ጀምሮ ተኩስ እንደከፈቱ ተሰምቷል።
ለአል ዓይን ኒውስ የደራ ወረዳ፤ ጉንዶ መስቀል ከተማ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ፤ መንግስት በአሸባሪነት የፈረጀው የኦነግ ሸኔ ቡድን ታጣቂዎች ወደ ከተማዋ ዘልቀው በመግባት ከባድ ጥቃት እያደረሱ ነው።
ነዋሪዎቹ በቅድሚያ ጥቃቱ በገጠር ቀበሌዎች ላይ መጀመሩን አመልክተው ማለዳ ሶስት ሰዓት ላይ ወደ ጉንዶመስቀል ከተማ በመግባት ተኩስ መክፈታቸውንና የመንግስት እና የግለሰብ ንብረቶችም እየተዘረፈ ነው ብለዋል።
በጉንዶ መስቀል ከተማ ዙሪያ ላይ ባሉት ቀበሌዎች የሚኖሩ ዜጎችም መኖሪያ ቤቶች በታጣቂዎቹ እየተቃጠለ እና ከብቶቻቸው እየተወሰዱባቸው እንደሆነ ነዋሪዎቹ አመልክተዋል። በስፍራው ላይ የመንግስት የጸጥታ መዋቅር እንደሌለም አክለዋል።
የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ውብሸት አበራ በሰጡት ቃል ፤ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ደራ ወረዳ ዋና ከተማ ጉንዶመስቀል መግባታቸውን ገልጸዋል።
" ታጣቂዎቹ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በከተማዋ ባሉ ባንኮች፣ የመንግስት ተቋማት እና የግለሰቦችን ንብረት እየዘረፉ ነው " ያሉት አስተዳዳሪው የክልል እና የፌደራል የጸጥታ ሀይል እንዲገባላቸው ማመልከታቸውን ለአል አይን ኒውስ ገልጸዋል።

#Update በደቡብ አፍሪካ ፤ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የኢትዮጵያ መንግስትን ወልክለው ፊርማቸውን ያኖሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከዛሬው የናይሮቢው ስምምነት በኃላ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር። አምባሳደር ሬድዋን ፤ ከዛሬው የቀጠለ ውይይት (በወታደራዊ ኃላፊዎች መካከል) የዛሬ ወር ገደማ (mid-December) በትግራይ ክልል መዲና #መቐለ ላይ ሊደረግ እንደሚችል ጠቁመዋል። ዋናውና የውይይቶቹ ፍፃሜ…
#Update
በኬንያ ናይሮቢ ከህወሓት አመራሮች ጋር ውይይት ላይ የቆየው እና በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራው የመንግስት ልዑክ ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ወደ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃል ተከታዩን ብለዋል ፦
- የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የተፈራረመውን የሰላም ስምምነት ለመተግበር ቁርጠኛ ነው።
- ለሰላም እና ለህዝቡ ስንል የተፈራረምንባትን #እንፈፅማለን ፣ ለተግባራዊነቱም #እንታገላለን።
- በውይይቱ በተሻለ ሁኔታ መግባባት ላይ ተደርሷል።
- ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ ኢትዮጵያ ብዙ ፈተናዎች ተፈትናለች ፤ ተገድዳ ወደ ጦርነት ገብታለች ፤ በተደረገው ውግያም በርካታ ውድመቶች ደርሰዋል።
- በርካታ የሰላም አማራጮች አምልጠዋል ፤ ከቅርብ ታሪኮቻችንን ተጠቅመን ወደ ቀደመ ሰላማችን ለመመለስ ዛሬ የተገኘውን የሰላም ንግግር ወደ ተግባር ለማውረድ ትልቅ ጥረት እየተደረገ ነው።
- ከዚህ በኋላ ይህን #ጦርነት ለመሸከም እንደ ኢትዮጵያ ማንም ጫንቃ የለም።
- የተበላሹ ነገሮች ወደ ነበሩበት እንዲመጡ መሠረት የጣለው የፕሪቶሪያው ስምምነት እና በናይሮቢ የተደረሰው ስምምነት የጋራ መግባባትን እንዲፈጠር ያደረገ ነው።
Credit : ኤፍቢሲ እና ኢብኮ

#የፀጥታ_ጉዳይ " የክልል እና የፌደራል የጸጥታ ሀይል እንዲገባልን አመልክተናል " - አቶ ውብሸት አበራ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከሌሊት 8 ሰዓት ጀምሮ ተኩስ እንደከፈቱ ተሰምቷል። ለአል ዓይን ኒውስ የደራ ወረዳ፤ ጉንዶ መስቀል ከተማ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ፤ መንግስት በአሸባሪነት የፈረጀው የኦነግ ሸኔ ቡድን ታጣቂዎች ወደ ከተማዋ ዘልቀው በመግባት ከባድ…
#ትኩረት
በሰሜን ሸዋ ፤ ደራ ወረዳ ያለው ሁኔታ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚያስፈልገው በወረዳው ቤተሰቦቻቸው የሚኖሩ የቲክቫህ አባላት አመልክተዋል።
" ንፁሃን በጭንቀት ውስጥ ነው ያሉት " ሲሉ የገለፁት የቤተሰብ አባላቶቻችን ዛሬ በጉንዶ መስቀል ከተማ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ እሩምታ ሲሰማ እንደነበር እና ነዋሪውም #ለደህንነቱ_በመስጋት በየቤቱ ተቀምጦ እንደነበር ተናግረዋል።
በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ #ጉዳት መድረሱን አመልክተው አፋጣኝ እንዲሁም አስተማማኝ መፍትሄ እንዲፈልግ ድምፃቸውን አሰምተዋል።
የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ውብሸት አበራ ዛሬ ለአል ዓይን ኒውስ በሰጡት ቃል ፤ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ወደ ደራ ወረዳ ዋና ከተማ ጉንዶ መስቀል መግባታቸውን ገልፀዋል።
ከጠዋት ጀምሮ በከተማዋ ባሉ ባንኮች፣ የመንግስት ተቋማት እና የግለሰቦች ንብረት ላይ ዘረፋ ሲፈፀም እንደነበር ጠቁመው ወረዳው የክልል እና የፌደራል የጸጥታ ሀይል እንዲገባለት ማመልከቱን አሳውቀዋል።

" አንዳንድ የተፈጠረውን ሰላማዊ ሁኔታ የማይቀበሉ አሉ "
የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፤ የተፈጠረውን ሰላማዊ ሁኔታ (ከህወሓት ጋር ማለታቸው ነው) የማይቀበሉ እንዳሉ በመጠቆም ፤ እነዚህ ሰላማዊ ሁኔታውን አይቀበሉም ያሏቸው አካላት " በዛም በዚህም " ያሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ትላንት ከናይሮቢ ሲመለሱ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ፤ " አንዳንድ የተፈጠረውን ይሄን ሰላማዊ ሁኔታ የማይቀበሉ አሉ። በዛም በዚህም አሉ፤ ይሄ ትግል ይፈልጋል፤ ሰላም አልፈልግም የሚል እና ሰላም የሚፈልግ ትግል ከገጠመ ሰላም የማይፈልግ ሰው አሸንፎ አያውቅም ብለን እናስባለን " ሲሉ ተደምጠዋል።
ኢታማዦር ሹሙ እነዚህ " በዛም በዚህም " አሉ ሲሉ የገለጿቸው ሰላም አይፈልጉም ያሏቸው አካላትን በግልፅ ከመናገር ተቆጥበዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በኢትዮጵያ መንግስት / በመከላከያ በኩል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ለመፈፀም " በመሉ ልብ ዝግጁ ነን " ሲሉ አሳውቀዋል።
" ዝግጁ የሚያደርገን (ለስምምነቱ ተፈፃሚነት) ለኢትዮጵያ ህዝብ ብለን ነው። " ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ " የትግራይ ህዝብ ህዝባችን ነው። እዛ የደረሰውን ችግር፣ ውድመት አይተናል፣ ይበቃዋል፤ ከዚህ በላይ በእሱ ላይ መፍረድ ህሊናቢስነት ነው። ሀገራችንም ይበቃታል፤ ወደ ተጀመረው ልማት ፣ ብልፅግና ብትሸጋገር ይሻላል የሚል ሀሳብ ይዘን ነው በዚህ ድርድር የተደራደርነው የተፈራረምነው አፈፃፀሙንም የተግባባነው " ሲሉ ተናግረዋል።
የመጣው የሰላም ዕድል ጥሩ ዕድል መሆኑን የገለፁት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፤ " የተቻለንን ያህል ተግባራዊ እንዲሆንና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እና #ሁሉም ወደነበረበት ወደሰከነበት እንዲመለስ እንመኛለን " ብለዋል።

" የተለያዩ ግለሰቦች በተለይ በቲክቶክ የሚያካሂዷቸው ሎተሪዎች ህገ-ወጥ ናቸው " - ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ በ" ቲክቶክ " የተለያዩ ግለሰቦች የሎተሪ ጨዋታ እያካሄዱ መሆኑን እንደደረሰበትና ይህ ድርጊታቸው ህገወጥ ስለሆነ እንዲታቀቡ ካልሆነ ግን ለህግ እንደሚያቀርባቸው አስጠንቅቋል።
አስተዳደሩ ፤ በማህበራዊ ሚዲያዎቹ የሚካሄደው ሎተሪ ግለሰቦች እንዲያካሂዱት ፈቃድ ያልተሰጠው ህገ-ወጥ ጨዋታ ነው ያለ ሲሆን " በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ማቋቋሚያ ደንብ በቁጥር 160/2001 በአንቀጽ 20 በተደነገገው መሰረት ህገ-ወጥ ሎተሪ የሚያካሂድ ማንኛውም ሰው ከብር 50 ሺህ እስከ 100 ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮና ከ3 እስከ 5 ዓመት በሚደርስ #እስራት እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡ " ብሏል።
በማቋቋሚያ ደንቡ አንቀጽ 12 መሰረት አስተዳደሩ የገንዘብ ሎተሪዎችን ጨዋታ ለማካሄድ ብቸኛ መብት እንዳለው አስገንዝቦ በአዋጁ መሰረት አስተዳደሩ ፈቃድ ሰጥቷቸው መካሄድ የሚችሉት ፦ የዕድል ጨዋታዎች የፕሮሞሽን ሎተሪ፣ የቶምቦላ ሎተሪ፣ የኮንቪንሽናል ቢንጎ ሎተሪ እና የስፖርት ውርርድ ሎተሪዎች መሆናቸውን አስረድቷል።
በመሆኑን የተለያዩ ግለሰቦች በተለይም " ቲክቶክ " በተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ የሚያካሂዷቸው ሎተሪዎች ህገ-ወጥ በመሆናቸው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቦ ከዚህ ህገወጥ ድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆኑ ለህግ እንደሚያቀርባቸው አስጠንቅቋል።

#AddisAbaba • ከወራት በፊት "በቅርብ ቀናት በድጋሚ ይወጣል። " ሲባል የነበረውን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ለማውጣት ሂደቶች እየተጠናቀቁ ነው ተብሏል። • ትክክለኛው የዕጣ መውጫው ቀን እስካሁን አይታወቅም። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰረዘውን የ40/60 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ለማውጣት ሂደቶች እየተጠናቀቁ ሲል አሳውቋል። የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤…
#Update
የተሰረዘው የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ነገ ይወጣል።
በቅርቡ በተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ምክንያት ተሰርዞ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ በነገው ዕለት እንደሚወጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
በጉዳዩ ላይ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ ያስሚን ወሀቢረቢ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሽመልስ ታምራት ዛሬ በሰጡት መግለጫ የተናገሩት ፦
- ነገ 25 ሺህ 791 የ40/60 እና 20/80 ቤቶች ዕጣ ይወጣባቸዋል።
- በነገው እጣ 146 ሺህ 892 እስከ የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በቂ ቁጠባ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ይሳተፋሉ።
- በነገው እጣ አወጣጥ ነባርና በ2005 ዓ.ም በባለሶስት መኝታ ቤት የተሰሩ 300 ቤቶችም ይተላለፋሉ።
- በእጣ አወጣጡ ላይ ከዚህ ቀደም የገጠሙ ችግሮች እንዳይደገሙ አዲስ የእጣ አወጣጥ ስርዓት ተዘርግቷታ።
- የመረጃ ማጥራት እና ማደራጀት ስርዓቱ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ተከናውኗል።
- የእጣ ማውጫ መተግበሪያውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ያለማው ሲሆን ከፌደራል ተቋማት እና ከከተማ አስተዳደሩ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
- የእጣ አወጣጡ በቆጣቢዎች የቅድመ ግምገማ ወይም የእጣ አወጣጥ ሙከራ የተካሄደበት ነው።
- ነገ ከሰዓት ላይ የሚካሄደው የእጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓቱም በቴሌቪዠን #በቀጥታ_ስርጭት ይተላለፋል።
Credit : ኤፍ ቢ ሲ

#Update የተሰረዘው የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ነገ ይወጣል። በቅርቡ በተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ምክንያት ተሰርዞ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ በነገው ዕለት እንደሚወጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል። በጉዳዩ ላይ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ ያስሚን ወሀቢረቢ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሽመልስ…
#AddisAbaba
በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ ያስሚን ወሀቢረቢ የተናገሩት ፦
" ... በ20/80 18,930 ቤቶች እና በ40/60 6,843 ቤቶች በድምሩ 25, 791 ቤቶች እጣ ይወጣባቸዋል።
ቀደም ብሎ ከፍተኛ የሆነ ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረውን የባለ ሶስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎችን ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ 300 መቶ ቤቶችን ቀሪ ስራዎችን በማከናወን ለነባር እና ለአዲሰ ተመዝጋቢዎች በእጣ ለማስተላለፍ ዝግጁ ተደርጓል። "
#AMC

ከህወሓት በኩል በፕሪቶሪያና ናይሮቢ የሰላም ድርድር ላይ ሲካፈሉ የነበሩት የፖለቲካና ወታደራዊ አመራሮች ወደ ትግራይ መዲና መቐለ መመለሳቸው ተሰምቷል።
የፖለቲካና ወታደራዊ አመራሮቹ በደ/ አፍሪካ ፕሪቶሪያ እና በኬንያ ናይሮቢ በተካሄዱ የሰላም ንግግሮችን ላይ መካፈላቸው ፤ በኃላም በተደረሱ #የስምምነት ሰነዶች ላይ ፊርማቸውን ማኖራቸው ይታወቃል።
ትላንት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሚመራው የኢትዮጵያ መንግሥት ተደራዳሪዎች ቡድን ከኬንያ፣ ናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ መመለሱ ይታወሳል።
ፎቶ ፦ ከናይሮቢ የተወሰደ (ሮይተርስ)

#AddisAbaba በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ ያስሚን ወሀቢረቢ የተናገሩት ፦ " ... በ20/80 18,930 ቤቶች እና በ40/60 6,843 ቤቶች በድምሩ 25, 791 ቤቶች እጣ ይወጣባቸዋል። ቀደም ብሎ ከፍተኛ የሆነ ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረውን የባለ ሶስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎችን ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ 300 መቶ ቤቶችን ቀሪ ስራዎችን በማከናወን ለነባር እና…
#AddisAbaba
ነገ የሚወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ...
የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት የተናገሩት ፦
" በእጣው ብቁ የሚሆኑት የ20/80 (ስቱዲዮ ፣ ባለ 1 እና ባለ 2) ነባር ተመዝጋቢዎች (1997) በመመሪያው መሠረት ዝቅተኛውን የ60 ወራት ቁጠባ መጠን እንዲሁም የባለ 3 መኝታ ነባርና አዲስ ተመዝጋቢዎች (2005) ዝቅተኛውን የ84 ወራት ቁጠባ መጠን ያሟሉ።
የ40/60 ተመዝጋቢዎች ከ40% እና ከዚያ በላይ ቁጠባ ያላቸው ለእጣ ውድድር ብቁ የሆኑ እስከ የካቲት 21/2014 ዓ.ም ድረስ (ማለትም መረጃ መውሰጃ የመጨረሻ ቀን - cut off period)፣ መሰረት መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም. ከባንክ በተገኘው መረጃ ላይ ተመስርቶ የመረጃ ማጥራት ኮሚቴው ባጠራውና ባደራጀው የመጨረሻ ሰነድ መሰረት።
በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም 93,352 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም 53,540 በአጠቃላይ 146,892 ተመዝጋቢዎች ለዕጣ ብቁ ሆነው በመገኘታቸው በዚህ ዙር ዕጣ ተካትው የቤት እድለኛ ለመሆን የሚወዳደሩ ይሆናል። "
Via Mayor Office of AA