TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ምናልባትም በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ወይም በሚቀጥለው ሳምንት አጋማሽ ላይ የሰብአዊ እርዳታ እንዲገባ ሊደረግ እንደሚችል የኢትዮጵያ መንግስት ተደራዳሪ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለጋዜጠኞች መናገራቸውን ኤፒ አስነብቧል። የህወሓት ተደራዳሪ አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው የዕርዳታ አቅርቦት መቀላጠፍ በሰላም ንግግሩ እና ስምምነቱ ላይ እምነት እንዲጨምር…
" ... መገናኛ ብዙሃን ጦርነትን ማራገብን ትተው ሰላምን እና መረጋጋትን መዘገብ ይገባቸዋል " - አምባሳደር መለስ አለም
የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሃት ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች በናይሮቢ እያደረጉ የሚገኙት ምክክር አሁንም መቀጠሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ፤ የተለያዩ ሀገራት በሰላም ስምምነቱ ላይ ያላቸውን ደስታ እየገለፁ መሆኑን ገልፀው ወዳጅ ሀገራት የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ ንበረቶችን ወደ አገልግሎት ለመመለስ ፍላጎታቸውን እያሳዩ ነው ብለዋል።
ቃል አቀባዩ ፤ በስምምነቱ ላይ እንደተገለፀው መገናኛ ብዙኃን ስም ማጥፋትን እና ጦርነትን ማራገብን ትተው ሰላምን እና መረጋጋትን መዘገብ ይገባቸዋል ያሉ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ሁሉም አስተዋፅኦ ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
Credit : AMC
Photo : Citizen TV Kenya
@tikvahethiopia

#የፀጥታ_ችግር ሰሞኑን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ አሶሳ ከተማ 96 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ማና ሲቡ ፤ መንዲ ከተማ (ምዕራብ ወለጋ) እና አካባቢው ላይ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መኖሩና ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል። አንድ በአካባቢው ላይ ቤተሰቦቹ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል፤ ከትላንት ወዲያ ሰኞ ታጣቂዎች ከማለዳ ጀምሮ ቶክስ በመክፈት ወደመንዲ…
#Oromia
በኦሮሚያ ክልል፣ በምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ቤተሰቦቻቸው ያሉ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በግጭት ቀጠናዎች ሰዎች ህይወታቸው እያለፈ መሆኑን፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም መንገድ በማጣታቸው ባሉበት ለመሆን መገደዳቸውን፣ በአንዳንድ ከተሞችም መሰረታዊ አገልግሎት ሰጪዎች መመዘጋታቸውን በመግለፅ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርበዋል።
አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል፤ እናት እና አባቱ በምዕራብ ወለጋ ውስጥ እንደሚኖሩ ገልጾ በፀጥታው ችግር ሳቢያ ሊያገኛቸው እንዳልቻለ አመልክቷል።
ከታጣቂዎች ጋር ያለው ግጭት የአየር ጥቃትንም ያካተተ እንደሆነ በመግለፅ በግጭቱ ንፁሃን ሰለባ እየሆኑ እንዳለ አመልክቷል።
ባለው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ መናሩንና ዜጎች ሰላም ፍለጋ ቄያቸውን ለቀው እንዳይወጡ እንኳን መንገድ መዘጋቱን ትራንስፖርትም ማግኘት አዳጋች መሆኑን ገልጿል።
ላለፉት ዓመታት በኦሮሚያ ክልል ያለው የፀጥታ ችግር ይህ ነው የሚባል ዘላቂ መፍትሄ ሳያገኝ ቆይቷል፣ ህዝቡ ሰለምን ተርቧል ፣ ገበሬው ማረስ፣ መላው የወለጋ ህዝብ እድገትን ይሻል፣ ሁሌ የግጭት ቀጠና ሆኖ መቀጠል ለህዝቡ አይገባም አስቸኳይ መፍትሄ ይፈለግ ሲል ይኸው የቤተሰባችን አባል ጥሪ አቅርቧል።
ከጥቂት ቀናት በፊት በምዕራብ ወለጋ በተለይ መንዲና አካባቢው ላይ የፀጥታ ችግር መኖሩን በዚህም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ እንደሆኑና ከአሶሳ - መንዲ የህዝብ ትራንስፖርት እንደተቋረጠ በክስተቱ ንፁሃን ሰለባ እየሆኑ እንዳለ ቤተሰቦቻችን መግለፃቸው ይታወሳል።
የፀጥታ ችግር ባለባቸው የወለጋ አካባቢዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እና የህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ብሎ የፈረጀው " ሸኔ " እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ በሚጠራው የታጠቀ ቡድን መካከል ግጭቶች መሆናቸውን ለማውቅ ችለናል።

Photo
#Oromia
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ም/ ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ በኦሮሚያ ያለው ጦርነት በዜጎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል አሉ።
አቶ ጃዋር ፤ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በጮቢ እና በሜታ ወልቂጤ (ምዕራብ ሸዋ)፣ በነቀምቴ (ምስራቅ ወላጋ)፣ ቢላ፣ ናጆ፣ ማንዲ (ምዕራብ ወለጋ) በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎች ተገድለዋል ብለዋል።
ንፁሃን በሚደረገው የተኩስ ልውውጥ ከሚደርስባቸው ጉዳት በተጨማሪ ያለ ልዩነት በሚፈፀመው የአየር ጥቃት የንፁሃንን ጉዳት በከፋ ሁኔታ እየጨመረው ነው ሲሉ ገልፀዋል።
አቶ ጃዋር ካለንበት የፖላቲካ ቀውስ ልንወጣ የምንችለው በኃይል አይደለም ያሉ ሲሆን ይህ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ አልሰራም፤ ዛሬ ወይም ነገ አይሰራም ይልቅ ነገሩን የበለጠ ያባብሰዋል ብለዋል።
በኦሮሚያ የእርስ በርስ ጦርነት መንስኤው የፖለቲካ ልዩነት ነው ሲሉ የገለፁት ምክትል ሊቀመንበሩ የሚፈታው መሪዎች በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው ለመወያየት እና በጋራ ተቀባይነት ያለው ስምምነት ላይ ሲደርሱ ብቻ ነው ብለዋል።
በአንድ የሀገሪቱ ክፍል ሰላም አምጥቶ ሌላው ጥግ እየደማ ዘላቂ ሰላም ሊመጣ ይችላል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው ብለው ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ሰላም ያስፈልጋታል ሲሉ አስገንዝበዋል።

#Oromia የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ም/ ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ በኦሮሚያ ያለው ጦርነት በዜጎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል አሉ። አቶ ጃዋር ፤ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በጮቢ እና በሜታ ወልቂጤ (ምዕራብ ሸዋ)፣ በነቀምቴ (ምስራቅ ወላጋ)፣ ቢላ፣ ናጆ፣ ማንዲ (ምዕራብ ወለጋ) በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎች ተገድለዋል ብለዋል። ንፁሃን በሚደረገው የተኩስ…
#ተጨማሪ
አቶ ጃዋር መሀመድ ከኢትዮጵያ ቀውስ ጋር በተያያዘ ‘ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ’ ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ እየመረጡ መጮሃቸው ነው ብለዋል።
" ባለፉት አራት አመታት በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የጦር ወንጀሎች እና የዓለም አቀፍ የሰብአዊ ህግ ጥሰቶች በተደጋጋሚ ተፈጽመዋል " ያሉት አቶ ጃዋር ፤ በዓለም አቀፉ ህበረሰብ ምንም አይነት ትኩረት አልተሰጠም ፤ ሌላው ቀርቶ የተለመደውን ‘ በጣም ያሳስበናል ’ የሚሉ ነገሮችን አይሉም " ሲሉ ነቅፈዋል።
" አልፎ አልፎ ሽፋን ይሰጡ የነበሩትም አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂውማን ራይትስ ዎች እንኳን ተስፋ የቆረጡ ይመስላሉ " ሲሉ ገልፀዋል።
" እየመረጡ መጮህ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም አያመጣም። " ያሉት አቶ ጃዋር መሀመድ " ወይ ለአጠቃላይ ሀገራዊ የሰላም ሂደት እንሰራለን ወይም ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ሆነው ሲቀጥሉ እንመለከታለን። " ብለዋል።

" የሰላም ስምምነቱ በጎ ጅምር ሆኖ ሳለ ለህዝብ ስለሂደቱ በዝርዝር እና በግልፅነት እንዲያውቅ አላመደረጉ ያሳስበናል " - እናት ፓርቲ
ከእናት ፓርቲ የተላከ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
ከእናት ፓርቲ የተላከ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
#Tigray , #Mekelle
የፕሪቶሪያውን #የሰላም_ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ በምግብ እና ሸቀጦች ላይ ቅናሽ እየታየ መሆኑን ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል።
የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ስለታየው ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ቅናሽ በ " ቀዳማይ ወያነ ገበያ " ያሉ ነጋዴዎች እና ሸማቾች ቃላቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ሰጥተዋል።
አለቃ አረጋዊ ጨርቆስ የተባሉ ነጋዴ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፦
- ሰርገኛ ጤፍ 11 , 000 ብር ይሸጥ የነበረው አሁን ከ6000 እስከ 6500 እየተሸጠ ነው።
- ነጭ ጤፍ 14,000 እስከ 13,500 ይሸጥ የነበረው አሁን 10,000 ብር እየተሸጠ ነው።
" ይህ የሚመጣው ከመኸኒና ከአካባቢው ብቻ ሲሆን አላማጣ ዝግ ነው፣ ጨርጨር ዝግ ነው። መንገድ በምዕራብ አቅጣጫ በሽረ በኩል ዝግ ነው ፤ ወቅቱ ጥቅምት እና ህዳር ቢሆንም በሁሉም አቅጣጫ መስመር ቢከፈት ይቀንሳል።
ሰላሙን ተከትሎ ከመሃል ሀገር ቢመጣ ደግሞ በደንብ ይቀንስ ነበር።
በተለይ ነዳጅ ቢገባ አሁን ውድ የሆነው ትራንስፖርት ይቀንስ ነበር። አንድ ሊትር ነዳጅ በጥቁር ገበያ 350 ብር እየተገዛ ሲሆን ከነዳጅ ማደያ የሚገዛ ነዳጅ ቢኖር ኖሮ በደንብ ይቀንስ ነበር " ብለዋል።
በመቐለ የስንዴ ዋጋ በኩንታል ከ10 ሺህ ብር ወደ 7 ሺህ ብር ቀንሷል።
ሰመሃል ኪዳኔ የተባለች የበርበሬ ነጋዴ ደግሞ ለአንድ ኪሎ ግራም 700 ብር የነበረው በርበሬ አሁን 500 ብር ገብቷል ይህ የሆነው በሰላሙ ስምምነት ተስፋ በማድረግ ነጋዴው ይቀንሳል ብሎ ስላመነ የያዘውን በቅናሽ እየሸጠ በመሆኑ ነው ብላለች።
" ህዝባችን ተጨቁኗል፣ በጣምም ተርቧል፣ አጥቷል #ሰላም በመሆኑ ተጠቃሚ ነን ፤ በጦርነት ኪሳራ እንጂ ልማት የለም ፤ ድርድርን ተከትሎ ባንክ ቢከፈት የቴሌኮም አገልግሎት ቢጀመር እንዲሁም ነዳጅ እንዲገባ ነው #ተስፋችን " ብላለች።
ቃላቸውን ለሬድዮ ጣቢያው የሰጡ ሩፋኤል የተባሉ ሸማች ፤ ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የሸቀጦች ዋጋ በጣም ወርዶ ማግኘታቸውን ገልፀዋል። ሙሉ በሙሉ ቀንሷል ባይባልም ለውጦች እየታዩ መሆኑን አመልክተዋል።
ዘይት 1,700 እና 1,800 የነበረው ወደ 1,400 ዝቅ ማለቱን ገልፀዋል። ፉርኖ ዱቄት በኩንታል እስከ 13,000 ብር የነበረው ወደ 9,000 ብር ወርዷል (እንደየጥራቱ)።
ነጭ ጤፍ ከአንድ ወር በፊት 13,000 ብር እንደገዙ አሁን ግን 3,000 ብር ቀንሶ በ10,000 ብር እንደገዙ ገልፀዋል፤ ከዚህም ይቀንሳል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ሰርገኛ ጤፍ ፣ ቀይ ጤፍ ላይም መቀነስ እንዳሳየ አስረድተዋል።
በሩዝ ፣ በመኮሮኒ ዋጋዎች ላይም ከፍተኛ የሆነ ቅናሽ መመዝገቡን እኚሁ ሸማች ለሬድዮው ተናግረዋል።
#በአስቸኳይ መሰረታዊ አገልግሎቶችን በመክፈት ህዝቡ የመግዛት አቅም እንዲኖረው ቢደረግ ጥሩ መሆኑን የገለፁት ሸማቹ የመሰረታዊ አገልግሎት መከፈት ፣ የንግድ ቀጠናዎች ትራንስፖርት ቢከፈት አሁን ካለው ዋጋም እንዲቀንስና ገበያው እንደሚረጋጋ ገልፀዋል።
መሀመድ ካህሳይ የተባሉ ነጋዴ ለሬድዮው በሰጡት ቃል ፥ " ሰላምን ምንም የሚወዳደረው ነገር የለም ፤ ጥፋት ጥፋት ነው ሁልጊዜ ሰላም ግን ሰላም ነው ፤ አሁን ሰላም ከተጀመረ ጀምሮ 5 ሊትር ዘይት 2,100 የነበረው በአንድ ጊዜ ወደ 1,500 እና 1,450 ብር ገብቷል።
የበለጠ መኪና/ትራንስፖርት ሲከፈት ባንኩ ሲከፈት በጣም ቆንጆ ነገር ይሆናል ።
ባንክ ሳይከፈት ዋጋው እንደዚህ የሆነ ባንክን ጨምሮ መሰረታዊ ነገር ሲከፈት ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል በጣም ደስ ይላል። ስኳርም አንድ ኪሎ 270 የነበረ 160 ገብቷል በጣም ደስ ይላል።
መድሃኒትም ይሁን ጥራጥሬ ከመጣ ሁሉም ነገር ወደቦታው እየተስተካከለ ይመጣል ሱቁም ይሞላል ፣ ትራንስፖርትም 24 ሰዓት የሚሰራ ከሆነ በጣም ቆንጆ ነው።
መንግሥት ቶሎ ብሎ አስተካክሎ ካደረገው በጣም ደስ ይለናል። "
በመቐለ ገበያ ፤ ከሳምንት በፊት 2,700 ብር ሲሸጥ የነበረ የ25 ኪሎግራም መኮሮኒ አሁን 1800 ብር እየተሸጠ ነው። አንድ ፓስታ ከ130 ብር ወደ 60 ብር ቀንሷል። 1 ኪሎ ኦቾሎኒ ከ370 ብር ወደ 160 ብር ቀንሷል። ሽኩርት ፣ ቲማቲም ፣ ድንች ዋጋ ላይ ለውጥ የለም።
Credit : ጋዜጠኛ ሙልጌታ አፅብሃ (ቪኦኤ ፌድዮ)
የፅሁፍ ዝግጅት ፦ Tikvah Family

#Tigray , #Mekelle የፕሪቶሪያውን #የሰላም_ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ በምግብ እና ሸቀጦች ላይ ቅናሽ እየታየ መሆኑን ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል። የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ስለታየው ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ቅናሽ በ " ቀዳማይ ወያነ ገበያ " ያሉ ነጋዴዎች እና ሸማቾች ቃላቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ሰጥተዋል። አለቃ አረጋዊ ጨርቆስ የተባሉ ነጋዴ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፦ - ሰርገኛ…
#Tigray , #Mekelle
የፕሪቶሪያውን #የሰላም_ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ በምግብ እና ሸቀጦች ላይ የታየው ቅናሽ (በቀዳማይ ወያነ ገበያ) ፦
- ሰርገኛ ጤፍ 11,000 ብር ይሸጥ የነበረው አሁን ከ6,000 እስከ 6,500 እየተሸጠ ነው።
- ነጭ ጤፍ 14,000 እስከ 13,500 ይሸጥ የነበረው አሁን 10,000 ብር እየተሸጠ ነው።
- የስንዴ ዋጋ በኩንታል ከ10 ሺህ ብር ወደ 7 ሺህ ብር ቀንሷል።
- ለአንድ ኪሎ ግራም 700 ብር የነበረው በርበሬ አሁን 500 ብር ገብቷል።
- ዘይት 1,700 እና 1,800 የነበረው ወደ 1,400 ቀንሷል። 5 ሊትር ዘይት 2,100 የነበረው በአንድ ጊዜ ወደ 1,500 እና 1,450 ብር ገብቷል።
- ፉርኖ ዱቄት በኩንታል እስከ 13,000 ብር የነበረው ወደ 9,000 ብር ወርዷል (እንደ የጥራቱ)።
- ስኳር አንድ ኪሎ 270 የነበረ 160 ገብቷል።
- 25 ኪሎግራም መኮሮኒ 2,700 ብር ሲሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን 1,800 ብር እየተሸጠ ነው።
- አንድ ፓስታ ከ130 ብር ወደ 60 ብር ቀንሷል።
- አንድ ኪሎ ኦቾሎኒ ከ370 ብር ወደ 160 ብር ቀንሷል።
(ሽኩርት ፣ ቲማቲም ፣ ድንች ዋጋ ላይ ለውጥ የለም።)