TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የክብር ዶክተር አርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን ዛሬ ቢሾፍቱ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ወደ አዲስ አበባ ተሸኝቷል። በአሁን ሰዓት ከቢሾፍቱ ከተማ የተነሳው የክብር ዶ/ር አርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ደርሶ ወደ ወዳጅነት አደባባይ እየተሸኘ ነው። በወዳጅነት አደባባይ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች የክብር እና የጀግና ስንብት ከተደረገለት በኋላ አስክሬኑ ወደ ድሬዳዋ የሚሸኝ እንደሆነ…
ፎቶ ፦ የአንጋፋው የኢትዮጵያ አርቲስት የክቡር ዶክተር አሊ ቢራ የቀብር ሥነ ስርዓት በድሬዳዋ ከተማ ተፈፅሟል።

ከስርዓተ ቀብሩ ቀደም ብሎ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ እና በድሬዳዋ ከተማ የክብር የሽኝት ስነርስርዓት ተካሂዶ ነበር።

የፎቶ ባለቤት ፦ የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት፣ የድሬዳዋ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ፤ የቃሊቲ ቱሉ ዲምቱ ቀለበት መንገድ ግንባታ ለማስጨረስ የኤግዚም ባንክ ብድር እስከሚለቀቅ ድረስ ከመንግስት በጀት በብድር መልክ ክፍያ እየተፈፀመ ፕሮጀክቱ እንዲጠናቀቅ ዛሬ ውሳኔ አሳለፈ።

የአዲስ አበባ ካቢኔ በ2ኛ አመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

ውሳኔዎቹ ፦

- የጥቁር ህዝቦች ነፃነት እና የጀግንነት ማሳያ አርማ የሆነው የአድዋ ሙዚየም የኪነጥበብ (Art) ስራ ላይ ተወያይቶ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ተወክለው  ግብአቶችን እንዲሰጡበት አቅጣጫ አስቀምጧል።

- የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ የቆየውን የግንባታ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን 1044 ፕሮጀክቶች በአብዛኛው #የመኖርያ_ቤቶች በመሆናቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የግንባታ ጊዜያቸው #እንዲራዘምላቸው ወስኗል፡፡

በሌላ በኩል ቢሮ ለሌላቸው 11 ወረዳዎች በፈጣን የግንባታ ስልት  11 ህንፃዎች እንዲገነቡ ወስኗል፡፡

- የቃሊቲ ቱሉ ዲምቱ ቀለበት መንገድ ግንባታ ለማስጨረስ የኤግዚም ባንክ ብድር እስከሚለቀቅ ድረስ ከመንግስት በጀት በብድር መልክ ክፍያ እየተፈፀመ ፕሮጀክቱ እንዲጠናቀቅ ወስኗል፡፡

ምንጭ ፦ የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፦

(የፀጥታ ጉዳዮች)

ከቀናት ለፊት በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ቤተሰቦቻችን በተለይ በወለጋ አካባቢዎች በፀጥታ ችግር ከፍተኛ ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን ፣ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ባሉ ችግሮች ንፁሃንን ሰለባ እየሆኑ እንደሚገኙ ፣ ሚማሩበት ዩኒቨርሲቲ የጠራቸው ተማሪዎች መንገድ በመዘጋቱ በእግር ለመጓዝ እንደተገደዱ መግለፃቸው አይዘነጋም።

በእርግጥ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ያለው የፀጥታ ችግር ዘላቂ እና አስተማማኝ መፍትሄ ሳያገኝ የበርካታ ንፁሃንን ህይወት እየቀጠፈ እንሆ አመታት አልፈዋል ፤ አሁንም ቀጥሏል ፤ በፀጥታ ችግሩ ሳቢያ ኢኮኖሚው ተጎድቷል፣ ገበሬዎች ማረስ እንዳችሉ ሆነዋል በርካቶች የሰው እጅ ጠባቂ ሊሆኑ ተገደዋል።

ከሰሞኑን ደግሞ የፀጥታ ችግሩ እስከ ትልቋ የነቀምቴ ከተማ ደርሶ ነበር።

ባለፈው እሁድ ዕለት በከተማይቱ መንግስት 'ሸኔ' ሲል በሽብርተኝነት የፈረጀው እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ወደ ከተማይቱ ዘልቆ በመግባት ከመንግስት የፀጥታ ኃይል ጋር #የተኩስ ልልውጥ አድርጎ ነበር።

በዕለቱ የደረሱ ጉዳቶች ስለመኖራቸው (ትክክለኛውን ለመግለፅ ቢያስቸግርም) ፣  ነገር ግን ሁኔታውን የፀጥታ ኃይሉ መቆጣጠር እንደቻለ ከቤተሰቦቻችን ተገልጾልናል።

ይህን ያህል በትልቅ ከተማ ውስጥ የተኩስ ልውውጥ እስኪደረግ የፀጥታና ደህንነት ኃይሉ ምን ይሰራ ነበር የሚለው " ትልቁ ጥያቄያቸው " እንደሆነ ቤተሰቦቻችን ነግረውናል።

የነቀምቴ ከተማ አስተዳደር ለማህበረሰቡ እና ለመላ ለአገልግሎት ሰጪዎች ባሰራጨው አጭር መልዕክት ፤ በቅርቡ ነቀምቴ ከተማ ውስጥ በሸኔ ቡድን የፀጥታ ችግር ተፈጥሮ እንደነበር ገልጾ ችግሩ በፀጥታ ኃይሉ ቅንጅት ፣ በከተማው ህዝብ ተሳትፎ እንዲረጋጋ መድረጉን አመልክቷል።

ነቀምቴ ከተማ አሁን ላይ ሰላም በመሆኗ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ የአገልግሎት ሰጪዎች (የትራንስፖርት ፣ ባንክ ...የመሳሰሉ) ወደ ስራ ተመልሰው አገልግሎት እንዲሰጡ የከተማው አስተዳደር አሳስቧል።

                                 --------

በአ/አ - ሀዋሳ ፈጣን መንገድ ላይ " መቂ " አካባቢ ምንድነው የሆነው ?

ከትናንትና በስቲያ ምሽት 2 ሰአት አከባቢ ከአ/አ ወደ ሃዋሳ በሚወስደው ፈጣን መንገድ ላይ መቂ አከባቢ ሲጓዙ በነበሩ ተሳፋሪዎች ላይ በታጣቂዎች ተኩስ ተከፍቶ የሰዎች ህይወት ስለማለፉ አንድ የቤተሰባችን አባል ገልጿል።

ይህንን ክስተት የገለፀው የሻሸመኔ፤ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ " ወንድም እና እህት መሞታቸውን አረጋግጫለሁ " ብሏል።

በወቅቱ ከተሳፋሪዎቹ አንዷ የእሱ #እህት እንደነበረች በመግለፅ በጥቃቱ ሳቢያ የቆሰሉ ሰዎች እንደነበሩ አመልክቷል።

ሟቾቹ የሻሸመኔ ከተማ 04 ቀበሌ ውሃ ልማት አካባቢ ነዋሪዎች እንደሆኑ ጠቁሟል።

የኸው ቤተሰባችን በዚያው ሰአት ከአዲስ አበባ እቃ ጭነው ሲመጡ የነበሩ ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን እንደሰማ ገልጿል።

እስካሁን በዚህ ጉዳይ ከመንግስት በኩል የተባለ ነገር የለም።
 
                                 --------

በአሶሳ ምንድነው ያለው ?

" አሶሳ ፍፁም ሰላም ነች "

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዋና ከተማ አሶሳ ከተማ ከሀሙስ ከሰአት ጀምሮ ኔትዎርክ፣ ሲስተም ፣ መብራት ጠፍቶ ነበር።

ትላንት ከሰዓት ኔትወርክ / ሲስተም የተመለሰ ሲሆን ይህ መልዕክት እስከተላከበት ሰዓት መብራት የለም።

አንድ የአሶሳ የቤተሰባችን አባል በላከው መልዕክት ፤ " ስለጉዳዩ ከመንግስት በኩል የተነገረ ምክንያት የለም " ያለ ሲሆን " አሶሳ ከተማ ግን ባለፉት 6 ቀናት ከባንኮች መዘጋት በስተቀር  እጅግ ሰላማዊና መደበኛ የስራ እንቅስቃሴዎች አንዳሉ ናቸው። " ብሏል።

በኔትወርክ መጥፋት ምክንያት የተጨነቁ ቤተሰቦችም ሁሉም ነገር ሰላም ስለሆነ ጭንቀት እንዳይገባቸው መልዕክት አስተላልፏል።

ከሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል " ምዕራብ ወለጋ " አካባቢ ካለው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ በአሶሳ ኔትዎርክ መቋረጡ ያሳሰባቸው በርካቶች ሲሆኑ አሶሳ ከተማና አካባቢው ላይ ኔትዎርክ ከመቋረጥ በዘለለ / አሁን ላይ ኔትዎርክ ተመልሷል / ሁሉም ነገር #ሰላም ነው።

በሌላ በኩል፦ በአሶሳ ዞን #ባንባሲ ወረዳ ከወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር በተያያዘ (ወረዳው የስጋት ቀጠና በመሆኑ ምክንያት) ከቀናት በፊት የታወጀው የሰዓት እላፊ ተግባራዊ እየሆነ ነው።

ለማስታወስ ያህል ፦

- እግረኞች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ምንም እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም።

- ሞተር ሳይክሎችና 3 እግር ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 1:00 - ንጋቱ 12:00 ሰዓት ምንም እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም።

- ማንኛውም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሻይ ቡና፣ ምግብ ፣ ሪስቶራንት፣ መጠጥ ቤቶች እና ወ.ዘ.ተ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም።

በተጨማሪ ፦ ማንኛውም የጸጥታ አካል ከተመደበው #መደበኛ_ሠራዊት_ውጪ የተጣለውን የሰዓት እላፊ ገደብ አልፎ ሲንቀሳቀስ ከተገኘ በቁጥጥር ስር ይውላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፦ (የፀጥታ ጉዳዮች) ከቀናት ለፊት በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ቤተሰቦቻችን በተለይ በወለጋ አካባቢዎች በፀጥታ ችግር ከፍተኛ ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን ፣ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ባሉ ችግሮች ንፁሃንን ሰለባ እየሆኑ እንደሚገኙ ፣ ሚማሩበት ዩኒቨርሲቲ የጠራቸው ተማሪዎች መንገድ በመዘጋቱ በእግር ለመጓዝ እንደተገደዱ መግለፃቸው አይዘነጋም። በእርግጥ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች…
" ዛሬ ላይ ሁሉንም ነገር ማመን ነው ያቃተኝ "

ከትላንት በስቲያ ምሽት በአዲስ አበባ - ሀዋሳ ፈጣን መንገድ ላይ መቂ አካባቢ በታጣቂዎች ተኩስ እህት እና ወንድም መገደላቸው እና ሌሎችም መቁሰላቸውን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከሻሸመኔ ማሳወቃቸው ይታወቃል።

ከደቂቃዎች በፊት አንድ የቤተሰባችን አባል ሟቾች አብሮ አደጎቹ እንደሆነ ገልጿል።

" አብሮ አደጎቼ ናቸው ፤ ዛሬ ላይ ሁሉንም ነገር ማመን ነው ያቃተኝ " ያለው ይኸው ቤተሰባችን " የዚህ አይነት አስደንጋጭ ድርጊቶች ዜጎች በሰላም እና ደህንነታቸው ላይ ማስተማመኛ እንዳይኖራቸው እንደሚያደርግ ገልጿል።

" መንግስት መቼ የዜጎችን ህይወት እንደሚታደግ አምላክ ይወቀው " ሲልም ሀዘኑን እና በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የዜጎችን ህይወት መታደግ ባለመቻሉ እና ብዙ ተስፋ ያላቸውን ሰዎች እየነጠቁ ባሉ ጥቃቶች እየደረሰ ያለውን ጉዳት ማስቆም ባለመቻሉ ያደረበትን ቅሬታ ገልጿል።

ከዚህ ቀደም ፤ በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ታጣቂዎች በሚፈፅሙት ጥቃት የበርካታ ንፁሃን ሰዎች ህይወት መጥፋቱ የሚታወቅ ሲሆን መንግስት የፀጥታ ችግር ባላባቸው ቀጠናዎች ንፁሃን እንዳይገደሉ ፣ ንብረት እንዳይዘረፍ ፣ ዜጎች ከቄያቸው እንዳይፈናቀሉ፣ ንብረት እንዳይወድም የደህንነት ስጋት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ዘላቂ መፍትሄ እና እርምጃ እንዲወስድ ቤተሰቦቻችን ሲጠይቁ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia
በኮንሶ_ዞን፣_በሦስት_ልዩ_ወረዳዎች_የሚገኙ_የሀገር_ውስጥ_ተፈናቃዮች_የሰብአዊ_መብቶች_አያያዝ_ላይ_የተከናወነ.pdf
987.6 KB
#EHRC : የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርት ፦

ኢሰማኮ በደቡብ ክልል ፤ በኮንሶ ዞን እና በአጎራባች 3 ልዩ ወረዳዎች ማለትም በአሌ ልዩ ወረዳ፣ በዲራሼ ልዩ ወረዳ እና በአማሮ ልዩ ወረዳ ለሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በቂ፣ ወቅቱን የጠበቀ እና ተደራሽ የሰብአዊ ድጋፍ ሊቀርብ ይገባል ብሏል።
 
መንግሥት በኮንሶ ዞን እና በአጎራባች ልዩ ወረዳዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች የተደራጀ የምዝገባ ሥርዓት ማከናወን፣ የወሳኝ ኩነት አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች ሰነዶችን ማግኘት እንዲችሉ ማድረግ፣ እንዲሁም በክልሉ ለተደጋጋሚ መፈናቀል መንስዔ ለሆኑ ጉዳዮች ዘላቂ መፍትሔ ሊያፈላልግ እንደሚገባ አስገንዝቧል።

(የኢሰመኮ ሙሉ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ሰላም

"ለስምምነቱ ለተግባራዊነት ጠንክረን እንሰራለን"

ትግራይ ክልል ያሉ የሃይማኖት ተቋማት በፕሪቶሪያ የተፈፀመውን የሰላም ስምምነት እንደሚደግፉና ለተግባራዊነቱ እንደሚሰሩ አሳውቀዋል።

ይህን ያሳወቁት በሃይማኖት ተቋማቱ ጉባኤ በኩል በሰጡት መግለጫ ነው።

የሃይማኖት ተቋማቱ፤ ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው ያሉ ሲሆን፥ በባለፈው ጊዜ በጦርነት በደረሰው ጥፋት/ጉዳት፣ በወደመው መሰረተ ልማት እንደሚያዝኑ ገልፀው በደቡብ አፍሪካ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።

ስምምነቱንም እንደሚደግፉ እና ለተፈፃሚነቱም ጠንክረው እንደሚሰሩ አሳውቀዋል።

የሃይማኖት ተቋማቱ ጦርነት የጭንቅ እንጂ የመጀመሪያ ሆነ የመጨረሻ አማራጭ ሊሆን እንደማይገባው አስገንዝበው " ጦርነት የማይተካውን የሰው ህይወት የሚበላ፣ ሀብት እና ንብረትን አውዳሚ እንደሆነ ሁሉም ቢገነዘበው አይደለም ጦርነት ወዳዛ የሚገፋፋና ከአንዳንድ ግለሰቦች የሚወጣው መርዛማ ቃላት አስፈላጊ አልነበሩም " ብለዋል።

እስካሁን በጦርነት የጠፋውን በጀት ለሰላም እና ለልማት ቢውል በሀገሪቱ ምን ያህል ለውጥ ሊያመጣ ይችል ነበር ? ብለን ማሰብ አለብን ያሉት የሃይማኖት ተቋማቱ ወደፊትም ችግሮች ቢያጋጥሙ በጦርነት ሳይሆን በሰላማዊ ውይይት፣ በትዕግስት፣ በመቀራረብ፣ በህግ ብቻ ሊፈቱ ይገባል ብለዋል።

የሃይማኖት ተቋማቱ ከአሁን በኃላ ጦርነት እና ወደጦርነት የሚገፋፉ ነገሮች ሊኖሩ እንደማይገባና ሁሉም ያለአንዳች እንቅፋት ለሰላም ለልማት፣ ለሀገር እድገት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበው ከአሁን ሰዓት ጀምሮ የኤርትራ ሰራዊት ከትግራይ መሬት እንዲወጣ ሲሉ አሳስበዋል።

የሃይማኖት ተቋማቱ በመግለጫቸው ከአሁን በኃላ ከሁሉም አጎራባች ክልሎች እንዲሁም ከሀገራት ጋር ስለ #ሰላም እንደሚወያዩ አመልክተዋል።

@tikvahethiopia