TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Professor

11 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ተሰጣቸው።

አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ11 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል።

በዩኒቨርሲቲ የውስጥና ውጭ ገምጋሚዎች በጥልቀት ተመርመሮ ፣ በኮሌጆች የአካዳሚክ ኮሚሽኖች ተፈትሾ ፣ በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ታይቶና ይሁንታ አግኝቶ የቀረበለትን መረጃ ከተመለከተ በኋላ የየኒቨርሲቲው የሥራ አመራር ቦርድ ለ11 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል።

የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው፦

1. ዶ/ር ቁምላቸው የሺጥላ፣  
2. ዶ/ር ሽመልስ አሰፋ፣  
3. ዶ/ር መንግስቱ ለገሰ፣
4. ዶ/ር ጉታ ዘነበ፣
5. ዶ/ር ፋሲል አሰፋ፣  
6. ዶ/ር ጥልዬ ፈይሳ፣
7. ዶ/ር ብሩክ ላምቢሶ፣  
8. ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ አለሙ፣  
9. ዶ/ር ዘበነ ክፍሌ፣  
10. ዶ/ር ተረፈ ደገፋ እና
11. ዶ/ር ንጉሴ ደየሳ መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ምሁራኑ የ #ሙሉ_ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው
በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማኅበረሰብ ዐቀፍ እና ሙያዊ አገልግሎት የነበራቸው አበርክቶ ተገምግሞ መሆኑ ታውቋል።

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
#Kombolcha

#ሙሉ_በሙሉ የግንባታ ወጭው በውጭ ሀገራት በሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች የሚሸፈን መልቲ ጀነራል ሆስፒታል የመሰረት ድንጋይ የቀመጠ።

ሆስፒታሉ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ የሚገነባ ሲሆን ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ይሆንበታል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ በ1 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን ወጪው ሙሉ በሙሉ በውጭ ሀገራት በሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚሸፈን ነው።

በወረዳው ለሚገነባው ሆስፒታል የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ጀማል ዪስፍ፣ የኮምቦልቻ ወረዳ አስተዳደር አቶ አልዪ ኢብራሂም እና የዲያስፖራ ተወካይ አቶ ፈረሃን አህመድ የመሰረት ድንጋዩን አስቀምጠዋል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አድማስ_ዲጅታል_ሎተሪ ! የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የአድማስ  ድጅታል ሎተሪ የአንደኛ ዙር ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ/ መውጣቱን ገልጿል። የወጡ ዕድለኛ የሚያደርጉ ቁጥሮች ፡- 👉 የ1ኛ ዕጣ የ1.5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር -002031699514 👉 2ኛ ዕጣ  የ800 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር -002294990063 👉 3ኛ ዕጣ የ350 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር…
#DigitalLottery

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስጀመረው " አድማስ " የተሰኘው ድጂታል ሎተሪ የመጀመሪያው ዙር እጣ ትላንት ማውጣቱን አሳውቋል

የዲጂታል ሎተሪ ዕጣው ቀጣይነት እንዳለው የገለፀው አስተዳደሩ የሁለተኛ ዙር  ዕጣው  መስከረም 11 ቀን 2015 የሚወጣ መሆኑን ገልጿል።

የአድማስ ዲጅታል ሎተሪ በአንደኛ ዕጣው 1.5 ሚሊዮን ብር፣ በሁለተኛ 800 ሺህ ብር፣ በሶስተኛ 350 ሺህ ብር ጨምሮ ሌሎችም የገንዘብ ዕጣዎችን ያካተተ ነው።

ከብሄራዊ የሎተሪ አስተዳደር እንዳገኘነው መረጃ ዕጣው በ605 ላይ ማንኛውም ፊደል በመላክ ወይም በቴሌብር ወደ *127# በመደወል በ3 ብር ነው የሚቆረጠው።

(ከላይ በትላትናው ዕለት የወጣው የመጀመሪያ ዙር ዕጣ #ሙሉ የባለዕድለኞች ቁጥር ተያይዟል)                            

@tikvahethiopia