TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#GurageZone የጉራጌ ዞን መንግስት የኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ ቡድን መሪ አቶ ፈቃዱ ዘለቀ ለብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬድዮ ጣቢያ የተናገሩት ፦ " ... የጉራጌ ዞን በክልልነት ለመዋቀር ለፌደሬሽን ም/ቤት የቀረበውን ጥያቄ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ነው። የህዝቡ ጥያቄ በክልልነት ለመዋቀር ነዉ ይሄንንም ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቅርበናል ምላሹን እየጠበቅን ነው። የዞኑ ም/ቤት እስካሁን በአዲሱ አደረጃጀት…
" ማንኛውንም ኢ-መደበኛና ህገወጥ እንቅስቃሴ አልታገስም " - የደቡብ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ

የደቡብ ክልል መንግስት ከአደረጃጀት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የሚፈፀም ማንኛውንም ኢ-መደበኛና ሕገ -ወጥ እንቅስቃሴን አልታገሰም ሲል አስጠነቀቀ።

ጉራጌ ዞንን የሁከትና የብጥብጥ ቀጠና ለማድረግ የሚደረገውን እንቅስቃሴን መንግስት አይታገስም ብሏል።

ዛሬ በጉራጌ ዞን ወቅታዊ ፀጥታ ሁኔታ ላይ የክልሉ የፀጥታ ሴክተር፣ የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት አመራርና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች በወልቅጤ ከተማ ውይይት አድርገው ነበር።

በዚህም ወቅት በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሠ መስተዳድር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር ዘርፍ አስተባባሪና የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ ፥ በጉራጌ ዞን የሕዝብን የመዋቅር ጥያቄ ሽፋን በማድረግ የሚደረግ ኢ-መደበኛ እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም፤ ይህንኑ ሕገ ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በዛሬው መድረክ ፤ ሁሉም አካባቢዎች በክልል ለመደራጀት ጥያቄዎችን ማቅረባቸው ተገልጾ " ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታን ባገናዘበና የሕዝብን የአብሮነት፣ የልማትና የጋራ ተጠቃሚነት ብሎም በሁሉም ዘርፍ በቅርበት ለሕብረተሰቡ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል መልኩ መዋቅሩ እየተሰራ ይገኛል " ተብሏል።

የጉራጌ ዞንም ከሌሎች አጎራባች ወንድም ሕዝቦች ጋር ለሀገር ግንባታ፣ ለኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ለጋራ ብልፅግና እንዲያመች በአንድ ላይ መሆን እንደሚገባው በመድረኩ ተጠቁሟል።

ለዚህም አመራሩ ሕብረተሰቡን በቅርበት በማወያየትና ከአደረጃጀት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በዞኑ የሚፈጠር ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንዳይኖር በከፍተኛ ትኩረት መስራት ይኖርበታል ተብሏል።

ያንብቡ : telegra.ph/Gurage-Zone-08-03

@tikvahethiopia
ክረምት በመጣ ቁጥር በሌላም ጊዜ በተመቻቸ መንገድ እጦት ምክንያት የሚሰቃዩ፣ ስራቸው የሚስተጓጎል፣ ለክህምና ቶሎ መድረስ ሳይችሉ ቀርተው ህይወታቸው አደጋ ላይ የሚወድቅ ዜጎች ብዙ ናቸው።

ከዚህም በተጨማሪ በሀገር ኢኮሮኖሚ እና በዜጎች ኑሮ መሻሻል ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖም ከባድ ነው።

በሀገራችን በርካታ መንገዶች ቢገነቡም ገና እጅግ ብዙ መስራት ይቀራል። ብዙ ሊታዩ የሚግባቸው እጅግ በጣም ወሳኝ ቦታዎችም አሉ።

በተለይም ከፍተኛ የሰዎች እንቅስቃሴ ባሉባቸው አካባቢዎች በመንገድ እጦትና ብልሽት ብዙ እንግልት ይፈጠራል።

የሚሰሩ መንገዶች መጓተት፣ የጥራት ጉድለት ፣ በጊዜው አለማለቅ፣ ሲበላሽ አለመጠገን፣ ወሳኝ ቦታዎች ላይ የመንገዶችን አለመስራት ችግሮች በመንገድ ምክንያት ለሚፈጠረው እንግልት እንደምክንያት ይጠቀሳሉ።

ከላይ በፎቶ እና ቪድዮ የተያያዘው ከኦሮሚያ ክልል (ከቲክቫህ አባላት)ና ከአማራ ክልል (ከአሚኮና አዊ ኮሚኒኬሽን) የተገኙ ሲሆን ብዙ ቦታ የለውን የመንገድ ችግር ማሳያ ነው።

በዚሁ አጋጣሚ፦

ከከሳ- ግምጃቤት - አምበላ የጠጠር መንገድ ጥገና እየተደረገለት ይገኛል ተብሏል። ጥገናውን መንገዱን ወደ አስፋልትነት ለማሳደግ የተረከበው የቻይናው ccecc ተቋራጭ እያከናውነው መሆኑን ተገልጿል።

የወልድያ-ጋሸና መንገድም ጥገናውን ለማክናወን (1.1 ቢሊዮን ብር) የተቋራጭነት ስራው በአማራ መንገድ ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ ተይዞ የነበረ ሲሆን ስራው እየተሰራ በጦርነት ሳቢያ ተቋርጦ ነበር ተብሏል።

ተቋራጩ ያቀረባቸው ንብረቶች በመዘረፉ ወደ ስራ ለመግባት አስቸጋሪ እንደነበር ተገልጾ አሁን ላይ የመንገዱ አገልግሎት እንዳይቋረጥ የሚያስችል ጥገና ለማድረግ ስምምነት ላይ መደረሱን አሚኮ ዘግቧል።

ፎቶ /ቪድዮ ፡ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት፣ አሚኮ፣ አዊ ኮሚኒ.

@tikvahethiopia
#GujiZone

• " እስከ ሃምሌ 15 ቀን 2014 ባለው ጊዜ የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ቁጥሩ ግን ሊጨምር ይችላል " - የሰባ ቦሩ ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ

• " የሞቱት ዜጎች ምናልባት በፀጥታ ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል " - የጉጂ ዞን ኮሚኒኬሽን

በኦሮሚያ ክልል፣ በጉጂ ዞን ፤ ሰባ ቦሩ ወረዳ በድርቅ ምክንያት የወገኖቻችን ህይወት እያለፈ መሆኑ ተገለፀ።

በኦሮሚያ ክልል፣ በጉጂ ዞን በሰባ ቦሩ ወረዳ ረሃብ ተከስቶ 12 ሰዎች መሞታቸውን የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ቢሮው፤ እስከ ሃምሌ 15 ቀን 2014 ዓ/ም ባለው ጊዜ ብቻ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን ገልጾ ቁጥሩ ግን ሊጨምር እንደሚችል አሳውቋል።

በወረዳው 35,442 ዜጎች አስቸኳይ ምግብ እርዳት ያስፈልጋቸዋል የተባለ ሲሆን እነዚህ ዜጎች በንሳ ፣ በደጋላልቻ ፣ ሰባሎሌማሞ ፣ በኡቱሉ፣ ኦዴ ፣ ሀራጌሳ ቀበሌዎች ያሉ ናቸው ተብሏል።

የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት መኮና ሀጤሳ ፤ ለወረዳው አልፎ አልፎ የምግብ እርዳታ ቢመጣም ምግብ ከሚያስፈልጋቸው ዜጎች ጋር የሚመጣጠን አይደለም ብለዋል።

በወረዳው የሟቾች ቁጥር በየቀኑ #እየጨመረ ሲሆን ባለፉት 2 ወራት የምግብ እና መሰል እርዳታቸዎች መቋረጣቸው ማህበረሰሙ ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጡን ገልፀዋል።

የጉጂ ዞን የኮሚኒኬሽን ቢሮ በበኩሉ ፤ በዞኑ ቆላማ አካባቢዎች 5 ወረዳዎች ድርቅ ተከስቷል ብሏል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ኦልኮ፤ " በረሃብ ምክንያት ስለሞቱ ሰዎች መረጃ የለኝም " ብለዋል። ነገር ግን " በአካባቢው የፀጥታ ችግር አለ " ሲሉ መግለፃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Guji-Zone-08-04

@tikvahethiopia
#ሀዋሳ #ድሬዳዋ #ባህርዳር

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የማለዳ በረራ ጀመረ።

አየር መንገዱ ከሀዋሳ ፣ ከድሬዳዋ እና ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ማለዳ 1:00 የሚነሱ እለታዊ በረራዎች መጀመሩን አሳውቋል።

#EthiopianAirlines

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ደቡብ ክልል ? በደቡብ ክልል ስር ያሉ 10 የዞን እና 6 ልዩ ወረዳ ምክር ቤቶች ክልሉን በሁለት ክላስተር ለማደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አፅድቀዋል። እስካሁን በአዲስ ክልል ለመደራጀት ስምምነት ላይ ደርሰዋል በም/ቤቶቻቸውም አፅድቀዋል የተባሉት ፦ - የወላይታ ዞን፣ - የጋሞ ዞን፣ - የጎፋ ዞን፣ - የደቡብ ኦሞ ዞን፣ - የኮንሶ ዞን - የጌዲኦ ዞን - የአማሮ ልዩ ወረዳ፣ - የቡርጂ…
#Update

" 10 ዞኖች እና 6 ልዩ ወረዳዎች ጥያቄያቸውን አቅርበዋል "

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ክልል ያሉ 10 ዞኖችና 6 ልዩ ወረዳዎች በሁለት ክልል የመደራጀት ጥያቄአቸውን እንዳቀረቡለት ገለፀ።

ዞኖቹ እና ልዩ ወረዳዎቹ በክልል የመደራጀት ጥያቄአቸውን ለፌደሬሽን ምክር ቤት ያቀረቡት ዛሬ መሆኑ ተገልጿል።

የፌደሬሽን ም/ ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ጥያቄውን መቀበላቸውም ተነግሯል።

ም/ቤቱ ውሳኔውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳውቃል ብለዋል።

በአንድ ላይ በክልልነት እንደራጅ ብለው ጥያቄያቸውን ያቀረቡት 10 ዞኖች እና 6ቱ ልዩ ወረዳዎች እነማን ናቸው ?

- ወላይታ፣
- ጋሞ፣
- ጎፋ፣
- ኮንሶ፣
- ደቡብ ኦሞ፣
- ጌዴኦ ዞኖች
- ደራሼ፣
- ባስኬቶ፣
- ኧሌ፣
- አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች በአንድ ላይ በክልል እንደራጃለን በማለት በየምክር ቤቶቻቸው በማጽደቅ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ፦

- ስልጤ ፣
- ከምባታ ጠምባሮ፣
- ሀዲያ ፣
- ሀላባ ዞኖች
- የም ልዩ ወረዳ በአንድ ላይ በመሆን አንድ ክልል ለመመስረት በምክር ቤቶቻቸው አፅድቀው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
#ተመዝገቡ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በመመዝገብ ላይ ይገኛል።

የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ፤ የሃይማኖት ድርጅቶች አስተምህሮታቸውን በመገናኛ ብዙኃን እንዲያደርሱ የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከሰኔ 27/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በመመዝገብ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ማንኛውም የሃይማኖት የቴሌቪዥን ጣቢያ እስከ #ነሐሴ_13_ቀን_2014 ዓ.ም ድረስ https://www.eservices.gov.et/ በሚለው ፖርታል ውስጥ በመግባት ወይም #በአካል_በመቅረብ ማመልከትና ፈቃድ መውስድ እንዳለበት ባለሥልጣኑ አሳስቧል።

Via @EthMediaAuth