TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የካቢኔ አባል የተደረጉት የቀድሞ የአልሸባብ ከፍተኛ አመራር ማንናቸው ?

በትላንትናው ዕለት የሶማሊያ ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ 26 አባላት ያሉትን ካቢኔ ይፋ አድርገዋል።

ጠ/ሚስትሩ በጠ/ሚኒስትርነት ከተሾሙ በኃላ ካቢኔያቸውን የሚያሳውቁበት ቀን በሶማሊያውያን ዘንድ በብዙ ሲጠበቅ ነበር።

ትላንት ይፋ ባደረጉት የካቤኔ አባላት ዝርዝር ግን አንድ የቀድሞ የአልሸባብ ከፍተኛ አመራርን ማካተታቸው የሚዲያዎችን ትኩረት ስቧል።

የሶማሊያ ካቢኔ ሹመት ያገኙት መክታር ሮቦው ናቸው።

ሙክታር ሮቦው፤ የቀድሞ የአልሸባብ ምክትል መሪ የነበሩ ሲሆን አሁን የሀይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር ተደርገው ነው በካቢኔው የተካተቱት።

ሮቦው ከ3 ዓመታት በላይ በሶማሊያ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ኤጀንሲ (NISA) በቤት ውስጥ የቁም እስረኛ ሆነው አሳልፈዋል፤እንሆ ከ3 ዓመት በኃላ ወደ ንቁ የፖለቲካ ተሳትፎ መመለሳቸው ነው የተነገረው።

በአንድ ወቅት አሜሪካ ሮቦውን ለጠቆማት 5 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ ገልፃ ነበር።

ሮቦው በታህሳስ 2018 በቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ሞሀመድ (ፋርማጆ) አስተዳደር ሊታሰር ችሏል።

የቀድሞው የአልሸባብ መሪ በሶማሊያና በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች (AU) ጥምረት ነው በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በNISA የቤት ውስጥ እስረኛ ሆነው ቆይተዋል።

በጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ የካቢኔ አባል ተደርገው የተመረጡት ሮቦው የአልሸባብ ታጣቂዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመዋጋት መንግስትን ይረዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፕ/ት ሀሰን ሼክ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የአልሸባብ ታጣቂዎችን በብቃት ለመታገል ቃል መግባታቸው ይታወቃል።

NB : የካቢኔ አባላቱ ሹመት ወደፓርላማ ቀርቦ አፀደቀም። መቼ ፓርላማው እንደሚያፀድቀው አልታወቀም።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ

በኢትዮጵያ ያሉ የነዳጅ ኩባንያዎች፣ ነዳጅ አመላላሽ ቦቴ ተሽከርካሪዎቻቸው ከጂቡቲ ነዳጅ ሲቀዱ ከዚህ በፊት የጫኑት ነዳጅ መዳረሻው ደርሶ ስለመራገፉ የርክክብ ሰነድ እንዲያመጡ ካልሆነ ግን ከነገ ከሐሙስ ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ነዳጅ መጫን እንዳይፈቀድላቸው የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ትዕዛዝ ማስተላለፉን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ከዚህ በተጨማፊ ቦቴዎቹ ነዳጅ ቀድተው ሲወጡ ስለመዳረሻቸው ሙሉ መረጃ ለጥፈው መውጣት እንዳለባቸው በባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰሃረላ አብዱላሂ ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ተፈርሞ የወጣውና ለኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የተጻፈ ደብዳቤ ያሳያል።

የኩባንያዎቹ ቦቴዎች የርክክብ ሰነድ የሚያገኙት በየማደያው አካባቢ ካሉ የወረዳ ንግድ ቢሮዎች ሲሆን፣ ይህም የሚሆነው የንግድ ቢሮዎች ባለሙያዎች ቦቴዎቹ ነዳጁን ለማደያዎች ሲያስረክቡ እዚያው ማረጋገጫቸውን በመስጠት ነው።

ስለቀጣይ መዳረሻዎቻቸው ሙሉ መረጃ በመስጠትና በመለጠፍ ይቀዳሉ ተብሏል።

የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በመመርያው ይህን እንዲያስቀድም የታዘዘ ሲሆን የነዳጅ ኩባንያዎቹ ይህን አውቀው የማይታዘዙ ከሆነ መጫን እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው ተብሏል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ " ይህን ካላደረጉ ዳግም ነዳጅ ለመጫንና ሥምሪት ለማድረግ አይችሉም " ብሏል።

የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ተግባራዊ እንዲያደርግ ያዘዘው ደብዳቤ ዓላማ፣ ባለፈው ወር የወጣውን የነዳጅ ውጤቶች የሥርጭት፣ ርክክብና ሽያጭ አፈጻጻም መመርያ ተግባራዊ ለማድረግ ታስቦ ሲሆን በዚህም #ከጂቡቲ እስከ #ማደያ ድረስ ይፈጸማል የሚባለውን የኮትሮባንድ ንግድ ለማስቀረት ከፍተኛ አስተዋጾኦ እንደሚኖረው ታምኗል፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-08-03-2

Credit : ሪፖርተር

@tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል የተባለው ዝርፊያ !

በአዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ ወጪ በተሠሩ የመንገድ ዳር መብራቶች ላይ እየተፈፀመ ያለው ዝርፊያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን " በምሽት የሚኖረውን የህብረተሰቡን እና የትራፊክ እንቅስቃሴ ደህንነትና ምቾት ለማስጠበቅ አይነተኛ ሚና ያላቸው የመንገድ ዳር መብራቶች ላይ የሚፈፀም ስርቆት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል " ብሏል።

ባለስልጣኑ ፤ መንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች ጎን ለጎን የመንገድ ዳር መብራት ተከላና ጥገና ስራዎችን በስፋት እያከናወነ መሆኑን ገልጾ ነገር ግን በከፍተኛ ወጪ በተሠሩ የመንገድ ዳር መብራቶች ላይ በተደጋጋሚ እየደረሰ በሚገኘው የስርቆት ወንጀል የተነሳ በተለያዩ አካባቢዎች የመንገድ መብራት የአገልግሎት መቆራረጥ እያጋጠመ ይገኛል ብሏል።

የመንገድ ዳር መብራት አገልግሎት መቆራረጥ በምሽት ክፍለ ጊዜ የሚኖረውን የትራፊክ ፍሰት ከማስተጓጎሉ በተጨማሪ ለወንጀል ድርጊቶች እና ለአደጋዎች መጨመር አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል ሲል ገልጿል።

ችግሩን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝም የገለፀው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ይህንን ህገ-ወጥ ተግባር ለማስቆም ዋነኛው የመንገድ ባለቤት ሕብረተሰቡ በመሆኑ የመንገድ ዳር መብራቶችን ከጉዳት እንዲከላከልና እንዲጠብቅ መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
" እድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል "

ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ህገወጥ የጦር መሣሪያ ታጥቆ ጫካ በመግባት የወንጀል ድርጊት ስፈጽም ቆይቷል የተባለ ግለሰብ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ።

ውሳኔውን ያሳለፈው በሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቴፒ ምድብ ችሎት ሀምሌ 25 /2014 ባስቻለው ችሎት ነው ፤ ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ማስረጃ በማረጋገጥ ነው ውሳኔውን ያሳለፈው።

ግለሰቡ " ባቤ ጌታቸው " የሚባል ሲሆን በሸካ ዞን የኪ ወረዳና ቴፒ ከተማ ላለፉት ዓመታት የተከሰተውን የፀጥታ ችግር እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም በህገወጥ መንገድ የጦር መሣሪያ በመታጠቅ ፦
- ሰው መግደሉ
- ተሽከሪካሪዎችን በማቆም የዘረፋ ወንጀል መፈጸሙ
- በሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።

በፈፀመው ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ እንደተፈረደበት ከዞኑ ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሀሰተኛ ዜና ነው " - ታይዋን የታይዋን መከላከያ የቻይና የጦር ጄቶች PLA Su-35 " የታይዋንን አየር ክልል ጥሰው ገቡ " ተብሎ በኦንላይን ሚዲያዎች የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰተኛ_ዜና ነው አለ። በታይዋን ያለውን ጉዳይ የሚከታተሉ ትክክለኛው የመከላከያ ድረገፅ ብቻ እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተለልፏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ነዋሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩትን ሀሰተኛ መረጃዎች ለሌሎች እንዳያጋሩ…
#Update

ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝታቸውን አጠናቀው ታይዋንን ለቀው ወጥተዋል።

የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና በሀገሪቱ የስልጣን እርከን ሶስተኛ ሰው የሆኑት ናንሲ ፔሎሲ ታይዋን ጎብኝተዋል።

ትላንት ታይዋን ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ብዙ ሲባልለት የነበረ እና በአሜሪካ እና ቻይና መካከል የፈጠረው ከፍተኛ ውጥረት ዓለምን ያሰጋ ነበር።

ቻይና ፔሎሲ ወደታይዋን እንደሚመጡ ከሰማች ጊዜ አንስታ ስታስጠነቅቅና እስከወታደራዊ እርምጃ ድረስ እንደምትወስድ ፤ አሜሪካም ትልቅ ዋጋ እንደምትከፍል ስትዝት ነበር።

ነገር ግን ፔሎሲ ወደ ታይዋን ገብተው ጉብኝትም አድርገው ፤ ማግኘት ያለባቸውን አካላት ባለስልጣናት አግኝተው ዛሬ ታይዋንን ለቀው ወጥተዋል።

ቻይና ጉብኝቱን ለማስቆም የወሰደችው ምንም እርምጃ ባይኖርም በአካባቢው ላይ ግን ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ስለመኖራቸው ታውቋል።

ትላንት የቻይና የጦር ጄቶቿ ወደ ታይዋይን የአየር ክልል ዘልቀው መግባታቸው በኦንላይ ሚዲያ ቢሰራጭም መረጃው ውሸት እንደነበር የታይዋን መከላከያ ማሳወቁ ይታወሳል።

ቻይና " ታይዋን " የራሷ ግዛት አድርጋ ነው የምታስባት ፤ #ወደ_እናት_ሀገሯ መመለስ አለባትም ብላ ታምናለች ለዚህም ታይዋንን የሚደግፉ ሁሉ በሀገር አንድነት ላይ አደጋ ያመጡ አድርጋ ነው የምትወስዳቸው።

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

እንደስማችን ብርሃን ነው ስራችን ! Access your funds 24/7

Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
#DrAbiyAhmed

ዛሬ ከሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን በአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ መክሯል።

እንዲሁም የአረንጓዴ ዐሻራ ክንውን ያለበትን ደረጃ አንስቷል።

በተጨማሪም የ2015 የበጀት ዓመት ዕቅድ የትኩረት አቅጣጫን መቃኘቱን የጠ/ሚ ፅ/ቤት አሳውቋል።

ዶ/ር ዐቢይ ስብሰባውን በተመለከተ ፤" ባለፈው ዓመት የሚያበረታታ የወጪ ንግድ አፈጻጸም፣ ቀጥተኛ የውጭ ሙዓለ ነዋይ ፍሰት መጨመር ታይቷል። ባለፉት ሁለት ወራት የዋጋ ግሽበት መቀነስ፣ ከፍተኛ የአረንጓዴ ዐሻራ ክንውን፣ የበጎ ፈቃደኝነት ተግባራት፣ የሬሚታንስ ጭማሪ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥራ ክንውን የተመዘገቡበት እንደ ሆነ አረጋግጠናል። በዚህ ዓመት የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ መቀጠል በእጅጉ አስፈላጊ ነው። " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝታቸውን አጠናቀው ታይዋንን ለቀው ወጥተዋል። የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እና በሀገሪቱ የስልጣን እርከን ሶስተኛ ሰው የሆኑት ናንሲ ፔሎሲ ታይዋን ጎብኝተዋል። ትላንት ታይዋን ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ብዙ ሲባልለት የነበረ እና በአሜሪካ እና ቻይና መካከል የፈጠረው ከፍተኛ ውጥረት ዓለምን ያሰጋ ነበር። ቻይና ፔሎሲ ወደታይዋን እንደሚመጡ…
#US #CHINA

" ቻይና ማንንም መከልከል አትችልም " - ፔሎሲ

" ሀገሬን የሚዳፈሩ ሁሉ ይቀጣሉ " - ቻይና

በአሜሪካ በስልጣን እርከን 3ኛዋ ሰው ናንሲ ፔሎሲ ከታይዋን ጉብኝታቸው በኋላ " ቻይና የዓለም መሪዎችን ወይም ማንንም ወደ ታይዋን እንዳይጓዙ መከልከል አትችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

ቻይና ፤ ከፔሎሲ ጉብኝት በፊት ጉብኝቱ እንዳይደረግ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያና ዛቻ ብታሰማም ፔሎሲ ወደ ታይዋን ገብተው ፤ ጉብኝት አድርገው ባለስልጣናትን አነጋግረው ሄደዋል።

ምንም እንኳን የፔሎሲ ጉብኝት ቢጠናቀቅም በቻይና እና አሜሪካ መካከል ያለው ውጥረት የቀጠለ ሲሆን ቻይና " ሀገሬን የሚዳፈሩ ሁሉ ይቀጣሉ " ስትል ዝታለች።

በሌላ በኩል ወደ ታይዋን ትልክ የነበረውን የተፈጥሮ አሸዋ መላክ ያቆመች ሲሆን ፍራፍሬና የዓሣ ምርቶችን ከታይዋን ማስገባት አቁማለች።

ታይዋን አካባቢ አሁንም የቻይና ወታደራዊ እንቅስቃሴ መቀጠሉ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#China

ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ እና ሱዳን ስለ ቻይና-ታይዋን ጉዳይ ምን አሉ ?

#ኢትዮጵያ

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰሞኑን የቻይና-ታይዋን ጉዳይ የተከሰተውን ውጥረት በትኩረት እየተከታተለች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ለኢዜአ ተናግረዋል።

አምባሳደር መለስ ፤ ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ስታራምድ የቆየችውን የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋሟን እንዳጸናች መሆኑን ተናግረዋል።

" የኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋም ዛሬ የተጀመረ አይደለም ያሉት " አምባሳደር መለስ፤ " ከቻይና ጋር በነበረን ግንኙነት ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስታት አፅንተው የያዙት አቋም ነው " ብለዋል።

አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያ ለ #አንድ_ቻይና ፖሊሲ ፅኑ አቋም አላት ያሉ ሲሆን ፖሊሲውን ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው የተመድና የአፍሪካ ህብረት የሚያራምዱት አቋም መሆኑን ገልፀዋል።

#ሱዳን

ሱዳን ለአንድ ቻይና መርህ ድጋፏን እንደምትሰጥ አሳውቃለች። ታይዋንም የቻይና ግዛት አካል መሆኗን ገልጻለች።

ሱዳን ፤ ቻይና ሉዓላዊነቷን እና የግዛት አንድነትዋን በመጠበቅ ረገድ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደምትደግፍም አስታውቃለች።

#ኤርትራ

ኤርትራ የአሜሪካ አፈጉባዔ ወደ ታይዋን ያደረጉት ጉዞ ከዓለም አቀፍ ህግና መርህ ያፈነገጠ ነው ብላለች።

የአፈጉባኤዋ ድርጊት የቻይና መንግስት ሉዓላዊነት ደንቦችን እና ድንጋጌዎች እንዲሁም " የአንድ-ቻይና " ፖሊሲ የሚጻረር እና የቻይናውያን ውህደት ሂደትን የሚያደናቅፍ ነው ስትል ገልፃለች።

ኤርትራ፤ አሜሪካ ቻይናን ለመቆጣጠርና ለመያዝ ጥረት እያደረገች ነው ብላ ድርጊቱ አጸያፊ ነው ብላለች።

#CGTN #ENA #AlAIN #Shabait

@tikvahethiopia