TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሶማሌ_ክልል
አልሸባብ የሽብር ቡድን ዳግም ድንበር አቋርጦ ለመግባት ሞክሮ በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል መታቱ ታውቋል።
የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ሰራዊት ዛሬ ድንበር አቋርጦ ለመግባት የሞከረውን አሸባሪውን የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን መደምሰሱን የክልሉ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።
ልዩ ሀይሉ የሽብር ቡድኑን ታጣቂዎች ከመደምሰስ ባለፈ በርካታ የጦርና የመገናኛ መሣሪያዎችን መያዝ ችሏል።
ወደ ውስጥ ለመግባት ከሞከሩ ታጣቂዎች መካከል የተማረኩም አሉበት።
አልሸባብ ከሶማሊያ ሂራን ግዛት ተነስቶ ነው ድንበር አቋርጦ ወደ ሸቤሌ ዞን ፌርፌር ወረዳ ለመግባት የሞከረው።
ነገር ግን በሶማሌ ልዩ ኃይል በደረሰበት ምት ኤል ቁዱን በምትባል ቦታ ላይ ተደምስሷል።
ከጥቂት ቀን በፊት ይህ የሽብር ቡድን ድንበር ጥሶ ሊገባ ቢሞክርም በሶማሌ ልዩ ኃይል ደረሰበት ከፍተኛ ምት ከ100 በላይ ታጣቂዎቹን እንዳጣ አይዘነጋም።
በሌላ በኩል የሶማሌ ክልል ህዝብ ለልዩ ኃይሉ እያደረገ ያለው ድጋፍና እገዛ እንደቀጠለ መሆኑን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ገልጿል።
@tikvahethiopia

#AddisAbaba የ8ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ተደረገ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል። ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 63.9 ፐርሰንት ተማሪዎች 50 እና በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ይህም ካለፉት አመታት ከተመዘገቡት ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ውጤቶች አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ውጤት ሆናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ…
" የተቀመጠው አድራሻ በአግባቡ ስለማይሰራ ውጤታችንን ማየት አልቻልንም " - ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘንድሮው የስምንተኛ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን አሳውቋል።
ቢሮው ተማሪዎች ውጤታቸውን https://aaceb.gov.et/%e1%8b%a88%e1%8a%9b-%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%88%8d-%e1%8b%89%e1%8c%a4%e1%89%b5/ ወይም aaceb.gov.et ላይ በመግባት ማየት እንደሚችሉ ገልጾ ነበር።
ነገር ግን ቢሮው ይፋ ያደረገው ውጤት መመልከቻ አድራሻ በትክክል ስለማይሰራ ውጤት ለማየት እንዳልቻሉ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች አሳውቀዋል።
በመሆኑም ፤ የከተማው ትምህርት ቢሮ አድራሻው ላይ ያለውን ችግር እንዲያርም /እንዲያስተካክል እንዲሁም ለህዝብ ይፋ ከመደረጉ በፊት ተገቢውን ፍተሻ ማለፉን ሊያረጋግጥ ይገባል ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 29 /2014 ዓ/ም በተሰጠው የ8ኛ ክፍል ፈተና ከ71 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።
በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ይፋ በተደረገው መረጃ ለፈተናው ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 63.9 ፐርሰንት ተማሪዎች 50 እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፤ 85.5% ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል ለመዛወር ችለዋል።

#ሐምሌ19
በየዓመቱ ሐምሌ19 የሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል ንግሥ በአል በደመቀና በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቁን የምስራቅ ሐረረርጌ ዞን ፖሊስ ገልጿል።
በበዓለ ንግሱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከአገር ውስጥና ከወጭ የመጡ ምዕመናን እና ሌሎች አንግዶች ታድመው ነበር።
በዘንድሮ ንግስ በዓል የስርቆት ወንጀል በፈፀመ ተጠርጣሪ ላይ በስፍራው የተቋቋመው ጊዜያዊ ፍርድ ቤት የሁለት አመት እስራት መወሰኑን ፖሊስ ገልጿል።
ዘንድሮ የተፈፀመው ስርቆት ወንጀል ከባለፉት ዓመታት ከተፈፀሙ የወንጀል ድርጊት እጅግ ማነሱን የፖሊስ ሪፖርት አመልክቷል።
በመንገድ ትራፊክ በኩልም ምንም ዓይነት የትራፊክ አደጋ አልደረሰም።
በሌላ በኩል ፤ በሀዋሳ ሐምሌ19 የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።
በዓሉ ከወትሮው በተለየ ከፍተኛ የሰው ቁጥር የተገኘበት ነው።
በበዓሉ በርካታ ቁጥር ያላቸው ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር የመጡ ጎብኚዎች፣ ታላላቅ የሀይማኖት አባቶች እና የቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣ የክልልና የሐዋሳ ከተማ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የተከበረው።
እንደ ፖሊስ ሪፖርት በዓሉ ያለአንዳች የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሯል።
ከወንጀል ጋር በተያያዘ አንዲት የበዓሉ ታዳሚ ላይ የሞባይል ስርቆት የፈጸመ ተጠርጣሪ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተይዞ በጊዜያዊነት በተቋቋመው ችሎት ማስረጃ ቀርቦበት የ2 ዓመት እስራት ቅጣት ተላልፎበታል። የተሰረቀውን ሞባይል ለግለሰቧ ማስመለስ መቻሉን ፖሊስ ገልጿል።
Photo Credit : የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ ENA

#MyMusicShop
🎼 Box Guitar, Lead Guitar, Bass guitar.
🎼 Keybord for Bigginers, for Stage & Midi keybord.
🎼 Home/Studio/recording equipments.
🎼 Different kinds of musical instruments & accessories are avial with us!
ለበለጠ መረጃ፦ 0911192909 or 0939854210 ወይም በቴሌግራም ቻናላችን https://t.iss.one/dagmusical
Join በማድረግ ይጎበኙን ! @dagmusical
አድራሻ፦📍መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ #325 ላይ እንገኛለን

የቅዱስነታቸው የአሜሪካ ጉዞ !
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወደ አሜሪካ ጉዞ ላይ ናቸው።
ከጥቂት ቀናት በፊት ለህክምና ጉዳይ ከሀገር እንደሚወጡ ገልፀው የነበሩት ቅዱስነታቸው ትላንት ምሽት ነው የአሜሪካ ጉዟቸውን የጀመሩት።
ትላንት ምሽት ከኢትዮጵያ የተነሱት ቅዱስነታቸው ዛሬ ማክሰኞ #ምሽት ቨርጂንያ ዳላስ ኤርፖርት ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የቅዱስነታቸው የአሜሪካ ጉዞ ! ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወደ አሜሪካ ጉዞ ላይ ናቸው። ከጥቂት ቀናት በፊት ለህክምና ጉዳይ ከሀገር እንደሚወጡ ገልፀው የነበሩት ቅዱስነታቸው ትላንት ምሽት ነው የአሜሪካ ጉዟቸውን የጀመሩት። ትላንት ምሽት ከኢትዮጵያ የተነሱት ቅዱስነታቸው ዛሬ ማክሰኞ #ምሽት ቨርጂንያ ዳላስ…
" አጠቃላይ ሂደቱ ህግን የተከተለ ነበር "
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ትላንት ምሽት የአሜሪካ ጉዟቸውን ለማድረግ በአዲስ አበባ ኤርፖርት በተገኙበት ወቅት " ከቅዱስነታቸው ጋር ሕገ ወጥ ቅርስ ከሀገር ሊሸሽ ሲል ተያዘ " እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ተገልጿል።
ቅዱስነታቸው ሁለት ጽላቶችን ፣ 3 የብር የእጅ መስቀሎችን (የግል ንብረታቸውንና ስማቸው የተፃፈባቸውን) ፣ 5 አዲስ እትም የግእዝ መጽሐፍ ቅዱስ እና አንድ ሊትር ቅብዓ ሜሮን ይዘው ለመሄድ ለቦሌ ኤርፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዳቤ ጥያቄ ቅርቦ ነበር።
አጠቃላይ ሂደቱም ህግን የተከተለ እንደነበር ተገልጿል።
ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እና ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ተፈቅደው በአድራሻ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የተጻፈ ሕጋዊ ደብዳቤ ያለ እና ሂደቱ ትክክለኛ ነው።
ስለሂደቱ ሕጋዊነት ሚገልፁ የሰነድ ማስረጃዎችም አሉ።
ይህ ሆኖ ሳለ በተለያዩ ማኅበራዊ ድኅረ ገጾች በሰበር ዜና እየተላለፈ የሚገኘው " በአባቶች ሻንጣ ውስጥ ተደብቀው የነበሩ ቅርሶች ተያዙ " የሚሉ መረጃዎች መሰረተ ቢስ መሆናቸው ተገልጿል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአገልግሎት ይዘዋቸው የሚጓዙ ንዋያተ ቅድሳት ሲሆኑ ህጋዊ ሰነዶች የተዘጋጁላቸው ናቸው።
Credit : TMC

" አጠቃላይ ሂደቱ ህግን የተከተለ ነበር " ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ትላንት ምሽት የአሜሪካ ጉዟቸውን ለማድረግ በአዲስ አበባ ኤርፖርት በተገኙበት ወቅት " ከቅዱስነታቸው ጋር ሕገ ወጥ ቅርስ ከሀገር ሊሸሽ ሲል ተያዘ " እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ተገልጿል። ቅዱስነታቸው…
#ነገ_መግለጫ_ይሰጣል !
በቅዱስ ፓትርያርኩ ጉዞ ላይ በቦሌ ኤርፖርት በተፈፀመው አሳዛኝ ድርጊት ጋር ተያይዞ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነገው ዕለት ቀን 8:30 መግለጫ እንደሚሰጡ ታውቋል።
ብፁዕነታቸው ስለተፈፀመው ድርጊት መረጃውን እንደሰሙትና እንዳሳዘናቸው በመግለጽ ወጡ የተባሉት ጽላትና ንዋያተ ቅድሳት በሕጋዊ መንገድ መውጣታቸውንና ለዚህም ሕጋዊ ፍቃድ መያዛቸውን ተናግረዋል።
ብፁዕነታቸው አክለውም ይህ ለአዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትም ሆነ ድርብ ለሚፈልጉ አብያተ ክርስቲያናት በሀገረ ስብከታቸው ጥያቄ መሰረት በመንበረ ፓትርያርክ ፍቃድ የሚሰጥ አስቀድሞ የነበረ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አሠራር ነው ብለዋል።
#EOTC_TV

#ትውልድእንገንባ
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በጦርነት ሳቢያ ተቋርጦ የቆየው ዓመታዊው የመማሪያ መፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ በዚህ ዓመት እየተካሄደ ይገኛል።
የዚህኛው ዓመት የመማሪያ መፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ትኩረቱን በአዲስ አበባ ያደረገ ሲሆን ከ5ኛው ዓመት የተቋረጠ ነው። እስካሁን ባለው በርከት ያሉ የቤተሰባችን አባላት መፅሀፍ አስረክበዋል።
በሌላ በኩል ፤ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትን የ5ኛ ዓመት ጉዞን ምክንያት በማድረግ በመላው ቤተሰቡ ስም በመጀመሪያ ዙር ግምቱ 25 ሺህ ብር የሆነ 521 መደበኛ እና 192 አጋዥ መፅሀፍ ማበርከት ተችሏል።
ዓመታዊው የመማሪያ መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ የሚቀጥል ሲሆን እንዳለፉት ዓመታት ስራዎች መፅሀፉ የሚበረከተው ከከተማ ወጣ ባሉ የገጠር ት/ቤቶች ነው።
ቤታችሁ ውስጥ ያሉትን የመማሪያ መፀሀፍ (ከKG - 12ኛ ክፍል) መስጠት የምትፈልጉ የአዲስ አበባ ቤተሰቦቻችን በያላችሁበት አካባቢ እየመጣን መፅሀፉን የምንረከባችሁ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎች @tikvahuniversity ላይ እንዲሁም @tikvahethmagazine / @tikvahethiopiaBOT ላይ ታገኛላችሁ።
@tikvahethiopia
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በጦርነት ሳቢያ ተቋርጦ የቆየው ዓመታዊው የመማሪያ መፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ በዚህ ዓመት እየተካሄደ ይገኛል።
የዚህኛው ዓመት የመማሪያ መፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ትኩረቱን በአዲስ አበባ ያደረገ ሲሆን ከ5ኛው ዓመት የተቋረጠ ነው። እስካሁን ባለው በርከት ያሉ የቤተሰባችን አባላት መፅሀፍ አስረክበዋል።
በሌላ በኩል ፤ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትን የ5ኛ ዓመት ጉዞን ምክንያት በማድረግ በመላው ቤተሰቡ ስም በመጀመሪያ ዙር ግምቱ 25 ሺህ ብር የሆነ 521 መደበኛ እና 192 አጋዥ መፅሀፍ ማበርከት ተችሏል።
ዓመታዊው የመማሪያ መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ የሚቀጥል ሲሆን እንዳለፉት ዓመታት ስራዎች መፅሀፉ የሚበረከተው ከከተማ ወጣ ባሉ የገጠር ት/ቤቶች ነው።
ቤታችሁ ውስጥ ያሉትን የመማሪያ መፀሀፍ (ከKG - 12ኛ ክፍል) መስጠት የምትፈልጉ የአዲስ አበባ ቤተሰቦቻችን በያላችሁበት አካባቢ እየመጣን መፅሀፉን የምንረከባችሁ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎች @tikvahuniversity ላይ እንዲሁም @tikvahethmagazine / @tikvahethiopiaBOT ላይ ታገኛላችሁ።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የቅዱስነታቸው የአሜሪካ ጉዞ ! ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወደ አሜሪካ ጉዞ ላይ ናቸው። ከጥቂት ቀናት በፊት ለህክምና ጉዳይ ከሀገር እንደሚወጡ ገልፀው የነበሩት ቅዱስነታቸው ትላንት ምሽት ነው የአሜሪካ ጉዟቸውን የጀመሩት። ትላንት ምሽት ከኢትዮጵያ የተነሱት ቅዱስነታቸው ዛሬ ማክሰኞ #ምሽት ቨርጂንያ ዳላስ…
#Update
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወደ ሰሜን አሜሪካ ደርሰዋል ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓመተ ምሕረት በወሰነው መሠረት ለሕክምና ሐምሌ 18 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ሰሜን አሜሪካን የተጓዙት ብፁዕ ወቅዱስነታቸው በትናንትናው ዕለት በሰላም ገብተዋል።
የሕክምና ክትትላቸውንም በተያዘው መርሐ ግብር መሠረት በዛሬው ዕለት የሚጀምሩ ሲሆን ከሕክምናው ጋር ተያያዥ የሆኑ ዝርዝር ጉዳዮችን በተመለከተ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በቀጣይ ይገለፃል ተብሏል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት