TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia

በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ የ44 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሬታ ሰዋሰው እና የልማት ባንኩ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ልማትና የቢዝነስ አቅርቦት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱል ካማራ ናቸው።

የመጀመሪያው የ40 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በምስራቅ አፍሪካ ፈተናዎችን በመቋቋም የምግብ ዋስትና ማረጋገጥን አላማ ላደረገ መርሃ ግብር ተፈጻሚነት የሚውል ነው።

የተቀረው 4. 4 ሚሊዮን ዶላር የማክሮኢኮኖሚ አስተዳደር አቅምን የማጠናከር ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ እንደሚውል የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

#ENA

@tikvahethiopia
ልጆቻችን እየመጡ ነው❤️

በአትሌቲክሱ ዘርፍ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ከፍ ያደረጉት ያስከበሩት የሀገራችን ልጆች ዛሬ ምሽት ኢትዮጵያ ይገባሉ።

የአትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድናችን ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 20/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

በስካይ ላይት ሆቴልም ያርፋል።

ነገ ሀሙስ ሐምሌ 21/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ ካረፈበት ስካይላይት ሆቴል ተነስቶ ፦ በእስጢፋኖስ ፣ 4 ኪሎ ፣ ፒያሳ ፣ ቸርችል አድርጎ በለገሀር ወደ መስቀል አደባባይ በመሄድ ደስታቸውን ለህዝቡ ይገልፃሉ።

በመቀጠልም በቤተ መንግስት ከፍተኛ የሀገሪቱ መሪዎች በተገኙበት የእውቅናና የማበረታቻ ፕሮግራም ይደረጋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እፀገነትን የገደሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ! የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ የነበረችውን ወ/ሮ እፀገነት አንተነህን የገደሉ ሦስት #ተጠርጣሪዎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ወ/ሮ እፀገነት አንተነህ መስከረም 6 ቀን 2012 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 12 ሰዓት 30 አቃቂ ቃሊት ክፍለ ከተማ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ወደ ስራ ለመሄድ ትራንስፖርት በመጠበቅ ላይ እንዳለች ሦስቱ ተጠርጣሪዎች ወንጀል…
#ተፈርዶባቸዋል

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ የነበረችውን ወጣት እፀገነትን አንተነህ የገደሉ 3 ወንጀለኞች የ13 ዓመት ፅኑ እስራት እንደፈረደባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ግለሰቦቹ ከልዩ ከህዝባዊ መብቶቻቸው በተለይ ፦
- በምርጫ ላይ ተካፋይ ከመሆን ፣
- ለህዝብ አገልግሎት ስራ ከመመረጥ ፣
- በሰነድ ወይም የውል ስምምነት ላይ ምስክር ከመሆን ፣
- በቤተ ዘመድ ካለው መብት በተለይም የወላጅነት ስልጣን ከመያዝ ችሎታ ፣
- ከሞግዚትነት እና የንግድ ፈቃድ የሚያስፈልገውን የሙያ ፣
- የኢንዱስትሪ ወይም የንግድ ስራ ከመስራት መብታቸው ለአምስት ዓመት እንዲሻሩ ፍርድ ቤት እንደወሰነባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

የእፀገነት ጉዳይ ጉዳይ ለማስታወሻ ፦
👉 https://t.iss.one/tikvahethiopia/39362
👉 https://t.iss.one/tikvahethiopia/39871

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ዶሮ እና የዶሮ ውጤቶችን ያለ ስጋት መጠቀም ይቻላል " - የኢትዮጵያ የዶሮ አርቢዎች እና አቀናባሪዎች

ተከስቶ የነበረው የዶሮ በሽታ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ ተጥሎ የነበረው ገደብ ተነሳ።

በኢትዮጵያ በተከሰተው የዶሮ በሽታ ምክንያት በዶሮና የዶሮ ውጤቶች ላይ ተጥሎ የቆየው ገደብ መነሳቱን የኢትዮጵያ የዶሮ አርቢዎች እና አቀናባሪዎች ማህበር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ባለፉት ወራት በአንዳንድ የሃገራችን ክፍሎችና በአንዳንድ የዶሮ እርባታዎች ላይ የዶሮ በሽታ ተከስቶ እንደነበር ይታወቃል።

ይህንንም ተከትሎ የግብርና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማህበር ጋር እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በሽታውን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡

በሽታውን ለመቆጣጠር ያስችል ዘንድ በጊዜያዊነት በዶሮና የዶሮ ምርቶች ላይ ጊዜያዊ የግብይትና የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎም ቆይቷል።

በአሁኑ ወቅት በሽታው በቁጥጥር ስር በመዋሉ የዶሮ ውጤቶች (እንቁላልና የዶሮ ስጋ) ላይ በግብርና ሚኒስቴር ተጥሎ የነበረው በግብይትና እንቅስቃሴ ገደብ ተነስቷል ተብሏል፡፡

ማህበረሰቡ ሆነ ዶሮ አርቢዎች ምርቶቹን መገበያየትና ያለ ምንም ሥጋት መጠቀም ይችላሉ ሲል የኢትዮጵያ የዶሮ አርቢዎች እና አቀናባሪዎች አሷውቋል።

በግብርና ሚኒስቴር በኩል እካሁን ድረስ ይፋዊ መግለጫ አልተሰጠም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነገ_መግለጫ_ይሰጣል ! በቅዱስ ፓትርያርኩ ጉዞ ላይ በቦሌ ኤርፖርት በተፈፀመው አሳዛኝ ድርጊት ጋር ተያይዞ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነገው ዕለት ቀን 8:30 መግለጫ እንደሚሰጡ ታውቋል። ብፁዕነታቸው ስለተፈፀመው ድርጊት መረጃውን እንደሰሙትና እንዳሳዘናቸው በመግለጽ ወጡ የተባሉት ጽላትና ንዋያተ ቅድሳት በሕጋዊ መንገድ…
ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፦

"... ቅዱስነታቸው ሊወስዷቸው የነበሩ ታቦታት በቤተክርስቲያኗ እውቅና ቅዱስ ፓትር ያርኩ በሰጡት መመሪያ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላላ ጽ /ቤት ትዕዛዝ በቅርፃ ቅርፅ ክፍል ተዘጋጅቶ ይዘውት እንዲሄዱ የተዘጋጀ የተለመደና ሕጋዊ አሠራርን የተከተለ ነው።

በጉዞው ወቅት ቅርጻ ቅርጽ የሚለውን "ቅርሳ ቅርስ" በማለት የተፈጠረው ውዝግብ አግባብ አይደለም።

በየምክንያቱ የቤተክርስቲያንን ክብር መንካት በየተቋማቱ እየታየ በመሆኑ የቤተ ክርስቲያኗን ጥንታዊነት ለሀገር ያበረከተችውን አስተዋዖ በማስብ ክብር ሊጠበቅ ይገባል "

#EOTC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የተቀመጠው አድራሻ በአግባቡ ስለማይሰራ ውጤታችንን ማየት አልቻልንም " - ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘንድሮው የስምንተኛ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን አሳውቋል። ቢሮው ተማሪዎች ውጤታቸውን https://aaceb.gov.et/%e1%8b%a88%e1%8a%9b-%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%88%8d-%e1%8b%89%e1%8c%a4%e1%89%b5/…
" ውጤታችሁን በየት/ቤታችሁ ማየት እና መወሰድ ትችላላችሁ " - ትምህርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸድን በየትምህርት ቤታቸው ማየት እና መውሰድ ይችላሉ ብሏል።

ቢሮው " ይፋ በተደረገው የውጤት መመልከቻ ሊንክ #በኔትዎርክ_መጨናነቅ ምክንያት ውጤታችሁን ያላያችሁ ተማሪዎች በየት/ቤታችሁ ማየት እና መውሰድ ትችላላችሁ " ብሏል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን እንዲያዩ ይፋ የተደረገው አድራሻ እስካሁን እየሰራ እንዳለሆነ ለማወቅ ችለናል።

@tikvahethiopia
" በቤታችን የሚላስ የሚቀመስ እህል የለም ፤ በረሃብ እየተቸገርን ነው " - አርሶ አደሮች

የቡርጂ ልዩ ወረዳ አርሶ አደሮች ለበልግ የተዘሩ ሰብሎች የዝናብ እጥረት በመከሰቱ በረሃብ እየተጎዱ መሆናቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

የወርዴያ ድንባቾ ቀበሌ አርሶ አደር የሆኑት ወ/ሮ ሃብቦ ዳቶ እንዳሉት ፤ ለበልግ የዘሩት ሰብል በዝናብ እጥረት ሙሉ በመሉ መውደሙን ተናግረዋል።

" በቤታችን የሚላስ ፥ የሚቀመስ እህል የለም፤ በረሃብ እየተቸገርን ነው" ያሉት ወ/ሮ ሃብቦ "መንግስት እና ለጋሽ ድርጅቶች እጃቸውን እንዲዘረጉ እንጠይቃለን " ብለዋል።

ሌላኛው አርሶ አደር ህርቦ ሻሬና ሣህዶ በዘንድረ በልግ 10 ሄክታር ማሳ ላይ የተለያዩ ሰብሎችን ዘርተው እንደነበርና በዝናብ እጥረት ሁሉም ሰብሎች መድረቃቸውን ገልፀዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት በቂ ዝናብ ባለመጣሉ ዝቅተኛ ምርት አግኝተው እንደነበረ የሚናገሩ አርሶአደሮቹ የዘንድረው ግን የከፋ በመሆኑ ና አፈጣኝ እርዳት ያስፈልገናል ብለዋል።

ለቀጣይ መኸር የዘር፥ የግብዓት አቅርቦት እና ሌሎች ድጋፎችን መንግስት እንዲያቀርብ አርሶአደሮቹ ጠይቋል።

የልዩ ወረዳው ግብርና ጽ/ቤት በዘንድሮው ምርት ዘመን 85 ሺ6 መቶ 96 ሄክታር መሬት በሰብል ተሸፍኖ እንደነበር ገልጾ በዝናብ እጥረት 53 ሺ4 መቶ 90 ሄክታር ላይ ተዘርቶ የነበረው የተለያየ የሰብል ምርት ሳይሰጡ በድርቅ መጥፋቱን አሳውቋል።

ፅ/ቤቱ በምግብ እጥረት እየተቸገሩ ያሉ አርሶ አደሮች የእህል እርዳታ እንዲያገኙ ሪፖርት መደረጉን ገልጿል።

ለክልሉ በቀረበው ሪፖርት ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የገለፀው ፅ/ቤቱ ባለው ነባራዊ ሁነታ ድጋፉ በቂ ስላልሆነ የምስል እና ሌሎች መረጃዎችን ለሚመለከተው አካል ለማድረስ ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል።

(የቡርጂ ልዩ ወረዳ ኮሚኒኬሽን)

@tikvahethiopia
የ2005 የ20/80 ባለ3 መኝታ ተመዝቢዎች ፦

" ... በ14ኛው ዙር የዕጣ አወጣጥ የከተማ አስተዳደሩ ቤቶች በቴክኖሎጂ ሆነ በማኑዋል ዕጣ የማውጣት ሂደቶች በሚፈጠሩ ችግሮች ሊወጣለት ከሚገባው ባለእድለኛ ወጪ ለሌላ ለማይመለከተው አካል እንዳይተላለፉ የሄደበትን ርቀት እናደንቃለን፡፡

ነገር ግን ይህ ቁርጠኝነት በባለ3 መኝታ 2005 ዓ.ም የ20/80 ተመዝቢዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲገለጽ እንፈልጋለን፡፡

በቅርቡ የተሰረዘውን የ14ኛው ዙር የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓትን አስመልክቶ በዋዜማውና ከዛ በኋላ በተሰጡ መግለጫዎች ባለ3 መኝታ የኮንዶሚኒየም ቤት ዕጣ ውስጥ እንደማይገባ የተሰጠው መግለጫ ግልጽነት የጎደለውና ማብራሪያ የሚሻ ሆኖ አግኝተነዋል።

ይህ ሁኔታ የ2005 የ20/80 ባለ3 መኝታ ተመዝቢዎችን በእጅጉ ያሳዘነ፣ ያስደነገጠና ግራ ያጋባ ሆኗል፡፡

ይህን አስመልክቶ በከተማ አሰተዳደሩ የተለያየ የስራ ኃላፊዎች በቅርብ ጊዜያት በተለያዩ ሚዲያዎች በሚሰጡት መግለጫዎችና ማብራሪያዎች ላይ የ20/80 ባለ3 መኝታ የ2005 ተመዝቢዎችን አቤቱታና ቅሬታዎችን በግልጽ ከመመለስ ይልቅ ሆን ተብሎ በሚመስል መልኩ ቸል በማለትና በማድበሰበሰ እየታለፈ በመሆኑ በመንግሥት ላይ ያለንን እምነት እየሸረሸረ ይገኛል። "

የ2005 የ20/80 ባለሶስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች አሉን ያሏቸውን ጥያቄዎች በዝርዝር በመፃፍ ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

(ሙሉ ጥያቄያቸው በዝርዝር ተገልጿል)

@tikvahethiopia