TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የዕጣ ማውጣት ሂደቱ ተጀምሯል። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ማውጣት ሂደትን ከሲስተም ባለሞያዎች ጋር በመሆን እያካሄዱ ነው። (ውድ ቤተሰቦቻችን ፦ ዕጣው ወጥቶ ሲጠናቀቅ ሙሉ ዝርዝሩን እንልክላችኃለን) @tikvahethiopia
#Update

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የማውጣት ሂደት ቀጥሏል።

ከዛሬው የዕጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ የ20/80 ባለሶስት መኝታ ቆጣቢዎች ጥያቄ እየተነሳ ይገኛል።

በ20/80 የባለ ሶስት መኝታ ቤት ያልተካተተው በ12ኛ ዙር በልዩ ሁኔታ ታይቶ እስከ 1500 ብር ቁጠባ ድረስ የተካተቱና በቦርድ ውሳኔ ባለሶስት መኝታ በወቅቱ የተዘጋ በመሆኑ ነው ተብሏል።

ቆጣቢዎቹ ተስፋ ባለመቁረጥ ቁጠባቸው በመቀጠላቸው በዛሬው ዕጣ ባይካተቱም ከተማ አስተዳደሩ ወደፊት በልዩ ሁኔታ ይስተናገዳሉ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

(የዛሬው ዕጣ አወጣጥ እንደተጠናቀቀ ዝርዝሩን እንልክላችኃለን)

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሽንዞ አቤ ተገደሉ።

የቀድሞ የጃፓን ጠ/ሚ ሺንዞ አቤ በጥይት ተመተው ተገደሉ።

ሺንዞ አቤ በምዕራባዊ ጃፓን በሚገኝና ናራ በተባለ ከተማ ጎዳና በአንድ ዕጩ ፖለቲከኛ ቅስቀሳ ላይ ንግግር በማድረግ ላይ ሳሉ ከበስተጀርባቸው በተተኮሰ ሁለት ጥይት ተመተው ነበር።

በኃላ ወደ ሆስፒታል ቢገቡም ህይወታቸዉን መታደግ አልተቻለም።

በቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ላይ ተኩስ ከፍቶ ህይወታቸው እንዲያልፍ ያደረገው የ41 ዓመት ግለሰብ ሲሆን በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋሉም ተዘግቧል።

Video Credit : Mia

@tikvahethiopia
የዒድ አል-አድሃ በዓል ነገ ይከበራል።

ነገ የሚከበረውን 1443ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ምክንያት በማድረግ ከንጋቱ 12፡00 ላይ 9 ጊዜ መድፍ የሚተኮስ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

የዒድ አል-አድሃ በዓል የሶላት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፡-

- ከቦሌ አየር መንገድ ፣ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ወይም ኦሎምፒያ አደባባይ አካባቢ

- ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ ለገሃር እንዲሁም ከቦሌ መድሃኔአለም ፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ

- ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት

- ከፒያሣ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቸርችል ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ

- ከተክለ ኃይማኖት ፣ በሜትሮሎጂ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ

- ከተክለ ኃይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ

- ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ

- ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ

- ከባሻ ወልዴ ችሎት ፣ በኦርማ ጋራዥ ወደ ፍል ውሃ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት

- ከጎፋ ፣ በቂርቆስ ቤተ-ክርስቲያን ወደ ለገሃር አዲሱ መንገድ የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛው ላይ

- ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ

- ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ፡፡ ከሳሪስ በጎተራ ወደ ለገሃር የሚመጡ ከባድ ተሽከርካሪዎችም ከአጎና ሲኒማ ማለፍ እንደማይችሉ ተገልጿል።

(አዲስ አበባ ፖሊስ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የስም ዝርዝር ጉዳይ !

ዛሬ የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለዕድለኞች ታውቀዋል።

ጥዋት በነበረው የዕጣ አወጣት ስነስርዓት ባለዕድለኞች አዲስ በተዋወቀ ሲስተም አማካኝነት ነው የተለዩት።

ከዕጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ በኃላ ተመዝጋቢዎች የቤት ዕጣ ደርሷቸው እንደሆነ እና እንዳልሆነ ለማወቅ የስም ዝርዝሩን ሲጠባበቁ ነበር ፤ ነገር ግን ይፋ አልሆነም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባላቱን ጥያቄ ይዞ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንን ጠይቆ ምላሽ አግኝቷል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በሰጠን ቃል ፤ የባለዕድለኞች ስም ዝርዝር ይበልጥ ታማኝነት እንዲኖረው ይፋ ከሆነበት ሰዓት ጀምሮ ኦዲት (Audit) እየተደረገ ነው ብሏል።

ታማኝነቱ ፣ ግልፅነቱ ሁሉም ያየው ጉዳይ ነው ሲስተሙ ምንም አይነት የእጅ ንክኪ ስለሌለው በፊት ከነበሩት የዕጣ አወጣጦች ሁሉ ልዩ ያደርገዋል ሲልም ገልጿል። የዕጣ አወጣጡንም በአካል ተገኝተው ከተመዝጋቢዎች ታዝበዋል ፤ በሰዓቱ ታትሞ በወጣው ወረቀት ላይም ፈርመዋል ሲል አክሏል።

የባለዕድለኞች የስም ዝርዝር በእራሱ በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ድረገፅ እና በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ ይወጣል ሲልም ኮርፖሬሽኑ አሳውቆናል።

መቼ ? ለሚለው ጥያቄም እጅግ በጣም በተቻለው ፍጥነት እየተሰራ ነው ፤ በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ እንዲወጣም እጥፍ ክፍያ ተከፍሎም ቢሆን ለማሰራት ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል።

ዛሬ ካለቀ ነገ ቅዳሜ ፤ እና ከነገ በስቲያ እሁድ አልያም ሰኞ ዕለት የባለዕድለኞችን ስም ዝርዝር ይፋ እናዳርጋለን ሲል ገልጿል።

(ውድ ቤተሰቦቻችን ተከታትለን እናሳውቃለን ፤ ዛሬ ለህዝብ ከታዩት መካከል #ጥቂቱን ከላይ አያይዘናል ተጨማሪ - ይመልከቱ telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-08-2)

@tikvahethiopia
#አረፋ

(Tikvah 🕌 Family)

የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በሀገራችን #ኢትዮጵያ እንዲሁም በተለያዩ ሀገራት ነው የተከበረ የሚገኘው።

በዚሁ አጋጣሚ የእስልምና ተከታይ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለበዓሉ አደረሳችሁ ፤ አደረሰን እያልን በዓሉን ስናከብር በፀጥታ ችግር ፣ በጦርነት ፣ በሰላም እጦት የሚወዱትን የተነጠቁ ፣ በሀዘን ውስጥ ሆነው በዓሉን የተቀበሉትን ወገኖቻችን እያሰብን እንዲሆን አደራ እንላለን።

በተጨማሪ እንደሁል ጊዜው በዓሉን ካጡት ጋር ተካፍለን፣ የታመሙትን በመዘየር ፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም እና ደህንነት ፣ ህዝባችንም ከሰቆቃ፣ ከችግር ያርፍ ዘንድ ፈጣሪያችንን እየተማፀንን እንድናከብረው አደራ እንላለን።

በድጋሚ በዓሉ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ እንዲሁም የአንድነት ይሆን ዘንድ እንመኛለን!!

በኢትዮጵያና በተለያዩ ሀገራት የበዓሉን ድባብ የሚያሳዩ ፎቶዎችን በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ 👇
https://t.iss.one/+Rx7P5YHQp_G16wyX

@tikvahethiopia
#እናት #መኢአድ #ኢሕአፓ

" መንግስት በቅጡ ሐዘናችንን እንድንወጣ ባያውጅልንም በራስ ተነሳሽነት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በመጪው ሰኞ፣ ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ/ም ጥቁር ልብስ በመልበስ በቅርቡ በወለጋ፣ ቤኒሻንጉል እና ጋምቤላ ለተጨፈጨፉ ወገኖቻችን የተሰማችሁን ሐዘን እንድትገልጹ ጥሪያችንን እያስተላለፍን በዕለቱ ከቀኑ 6:30 ላይ ዅላችሁም በያላችሁበት የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት እንድታደርጉ፣ መገናኛ ብዙኃንም ዕለቱን በሙሉ ሐዘናችሁን ከመላው የኢትዮጵያውያን ጋር እንደሚገባው እንድትገልጹ እንጠይቃለን። " - ኢሕአፓ፣ መኢአድ እና እናት

ኢሕአፓ ፣ መኢአድ እና እናት ፓርቲዎች ትላንት ያወጡት መግለጫ ሙሉ ቃል ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሽንዞ አቤ ተገደሉ። የቀድሞ የጃፓን ጠ/ሚ ሺንዞ አቤ በጥይት ተመተው ተገደሉ። ሺንዞ አቤ በምዕራባዊ ጃፓን በሚገኝና ናራ በተባለ ከተማ ጎዳና በአንድ ዕጩ ፖለቲከኛ ቅስቀሳ ላይ ንግግር በማድረግ ላይ ሳሉ ከበስተጀርባቸው በተተኮሰ ሁለት ጥይት ተመተው ነበር። በኃላ ወደ ሆስፒታል ቢገቡም ህይወታቸዉን መታደግ አልተቻለም። በቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ላይ ተኩስ ከፍቶ ህይወታቸው እንዲያልፍ ያደረገው…
#Update

ትላንት አርብ በአደባባይ በአንድ የፖለቲካ ቅስቀሳ ላይ ንግግር ሲያደርጉ በጥይት ተመተገው የተገደሉት የቀድሞ የጃፓን ጠ/ሚ ሺንዞ አቤ አስክሬናቸው ቶክዮ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ገብቷል።

አስክሬናቸው ቶኪዮን መኖሪያ ቤታቸው ሲደርስ ፤ የገዢው ፓርቲያቸው አባላት LDP ጥቁር በጥቁር ለብሰው የተቀበሉ ሲሆን የአሁኑ ጠ/ሚ ፉሚዮ ኪሺዳ ከሰዓት በኃላ ወደ ሺንዞ አቤ ቤት ይመጣሉ ተብሏል።

ትላንት ግድያውን የፈፀመው የ41 አመት ዕድሜ ያለው ቴሱያ ያማጋሚ የተባለ ሰው ሲሆን ለፖሊስ በሰጠው ቃል ግድያውን በቤት ውስጥ በተሰራ መሳሪያ መፈፀሙን አምኗል።

ፖሊስ ለምን ግድያውን እንደፈፀመ እና ከጀርባው ሌላ አካል ይኖር እንደሆነ የማጣራት ስራ እየሰራ ሲሆን በወቅቱ ሺንዞ አቤ ላይ ከተኮሰ በኃላ የማምለጥ ሙከራ አለማድረጉን አመልክቷል።

ግድያውን የፈፀመው ግለሰብ ቤት ውስጥ በተሰራ መሳሪያ ሲሆን በኃላ ላይ ፖሊስ ቤቱን ሲበረብር ሌሎች ከእጅ የተሰሩ መሳሪያዎች እና ተቀጣጣይ ነገሮችን ማግኘት ችሏል።

ጃፓን እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የመሳሪያ ቁጥጥር ያለባት ሀገር ስትሆን በመሳሪያ ሰዎች የሚገደሉበት እድል እጅግ ጠባብ ነው።

@tikvahethiopia