TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አጭር_ማስታወሻ ነገ ጥዋት በአዲስ አበባ ፤ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ይወጣል፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ አጭር የመረጃ ማስታወሻ ፦ ⮕ ነገ የሚካሄደው የ3ኛ ዙር የ40/60 እና 14ኛ ዙር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ስነስርኣት ነው። ⮕ አጠቃላይ 25 ሺህ 491 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎች በዕጣ ይተላለፋሉ። ⮕ በ20/80 ፕሮግራም 18 ሺ 648 ፤ በ40/60 መርኃ ግብር 6 ሺህ…
ፎቶ ፦ በዛሬው ዕለት በዕጣ ለባለዕደለኞች የሚቀርቡት ቤቶች ከላይ በፎቶ የምትመለከቷቸው ናቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ ቤቶቹ በተሻለ ጥራት ፤ የግንባታ ጥራት ችግሮችን በመቅረፍ በተሻለ ሁኔታ በመገንባት የተዘጋጁ ናቸው ብሏል።

ለዕጣ የቀረቡ ቤቶች የሚገኙባቸው ሳይቶች፣ የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ፦

- አያት 2፤
- ቦሌ በሻሌ፤
- ቡልቡላ ሎት 2

በ20/80 ቤት ልማት ፕሮግራም ፦
- በረከት፤
- ቦሌ አራብሳ (ሳይት 3፤5፤6)፤
- ወታደር፤
- የካ ጣፎ፤
- ጀሞ ጋራ፤
- ጎሮ ስላሴ፤
- ፉሪ ሃና እና ፋኑኤል ናቸው፡፡

ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ አጠቃላይ የዕጣ አወጣጥ ስነስርዓቱን እየተከታተልን ምንልክላችሁ ይሆናል።

Photo Credit : Mayor office of AA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ በዛሬው ዕለት በዕጣ ለባለዕደለኞች የሚቀርቡት ቤቶች ከላይ በፎቶ የምትመለከቷቸው ናቸው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ ቤቶቹ በተሻለ ጥራት ፤ የግንባታ ጥራት ችግሮችን በመቅረፍ በተሻለ ሁኔታ በመገንባት የተዘጋጁ ናቸው ብሏል። ለዕጣ የቀረቡ ቤቶች የሚገኙባቸው ሳይቶች፣ የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ፦ - አያት 2፤ - ቦሌ በሻሌ፤ - ቡልቡላ ሎት 2 በ20/80 ቤት ልማት ፕሮግራም…
#Update

ዛሬ ዕጣ የሚያወጣባቸውን ቤቶች የሚያስተዳድረው ቴክኖሎጂ ሲስተም በአሁኑ ሰአት በይፋ መከፈቱ ተገልጿል።

አ/አ ከተማ አስተዳደር ግልፅነትንና ተጠያቂነትን በሚፈጥር መልኩ ለእጣ ተዘጋጅቷል ፤ የመረጃ መያዣና እጣ ማውጫ ከመበልጸግ ሂደት ጀምሮ ብዙ ሙከራዎች የተካደበት መሆኑ አሳውቋል።

ለዕጣ ማውጣት ስነስረዓቱ ቅድመ-ዝግጅት ለአራት ዙር ሙከራ ተደርጎበት፣ አምስተኛውና የመጨረሻ ዙር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከቆጣቢዎቹ ከተቋማት በተገኙበት ሙከራው ተካሂዶ #ታሽጎ ለዕጣ ማውጣቱ ዝግጁ እንዲሆን ተደርጎ እንደነበር ተገልጷል።

ዛሬ የዘርፉ ባለሙያዎች ፤ገለልተኛ አካላት እንዲሁም ከተመዝጋቢዎች የተወከሉ ታዛቢዎችና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተከፍቶ ለእጣው ዝግጁ ተደርጓል ተብሏል።

የተዘረጋው የጋራ መኖርያ ቤቶች የእጣ አወጣጥና የመረጃ የቴክኖሎጂ ስርዓት የሚለይባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ተብለው የተጠቀሱ ፦

- #እንደከዚህ_ቀደሙ ለተለያየ ህገወጥ ድርጊት እንዳይጋለጥ ለማድረግ ከሰው ንክኪ ነፃ ሆኖ የተሰራ መተግበርያ በመሆኑ አስተማማኝና ግልፅነት እንዲሁም ፍትሃዊ አሰራር የዘረጋ መሆኑ ተገልጿል።

- መተግበርያው በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የበለፀገ ሲሆን ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት የፌደራል ጨምሮ ይሁኝታን ያገኘና በግል ተቋማት ታዛቢዎች ጭምር ታይቶ የተረጋገጠ ነው ተብሏል።

- ሲስተሙ የቅድሚያ ተጠቃሚነት አወሳሰን በፍትሃዊነት የሚተገብር ሲሆን ልዩ ትኩረት የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመመሪያ ቁጥር 3/2011 በተገለጸው መሠረት በመለየት በእጣው ላይ በፍትሃዊነት አካቶ ሊያወጣ በሚችል መንገድ የተሰራ ነው ተብሏል።

- አካል ጉዳተኞች 5 በመቶ ፤ ሴቶች 30 በመቶ ፣ የመንግስት ሠራተኞች 20 በመቶ ስብጥሩን በትክክል ጠብቆ እንዲወጣ ይደረጋል።

- ብቁና ንቁ Eligible ቆጣቢዎችን ከባንክ መረጃ ጋር በመተሳሰር ራሱ በትክክሉ በመለየት በዛው መሰረት እንዲስተናገድ የሚያደርግ ነው።

- በተለይም ደግሞ ፤ የአካል ጉዳተኞች ከዚህ በፊት በእጣ ቢካተቱም ነገር ግን እንደሌሎች ባለእጣዎች ፎቁ የመጨረሻ ወለል ጭምር እየደረሳቸው ለችግር የሚዳረጉበትን ሁኔታ በመቀየር ሲስተሙ ራሱ አካል ጉዳተኞችን በዝቅተኛ ወለል ላይ እጣ በማውጣት ምላሽ መስጠት የቻለ መሆኑ ተገልጿል።

- ሲስተሙ ማንም እንደፈለገ ገብቶ ማስተካከል ሌላ ሰው መጨመር መቀነስም Edit ማድረግ የሚከልክል ሲሆን በተቃራኒው ሂደቱን በመቆጣጠር Audit ደግሞ ስርዓቱን ራሱ ከህገወጥ ድርጊቶች የሚጠብቅ ሲሆን አንዴ እጣው ከወጣ በኋላ ለሌላ ንክኪ እንዳይጋለጥ ራሱን ዝግ የሚያደርግ ሲስተም መሆኑ ተገልጿል።

(የአ/አ ከንቲባ ፅ/ቤት)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ ዕጣ የሚያወጣባቸውን ቤቶች የሚያስተዳድረው ቴክኖሎጂ ሲስተም በአሁኑ ሰአት በይፋ መከፈቱ ተገልጿል። አ/አ ከተማ አስተዳደር ግልፅነትንና ተጠያቂነትን በሚፈጥር መልኩ ለእጣ ተዘጋጅቷል ፤ የመረጃ መያዣና እጣ ማውጫ ከመበልጸግ ሂደት ጀምሮ ብዙ ሙከራዎች የተካደበት መሆኑ አሳውቋል። ለዕጣ ማውጣት ስነስረዓቱ ቅድመ-ዝግጅት ለአራት ዙር ሙከራ ተደርጎበት፣ አምስተኛውና የመጨረሻ ዙር የሚመለከታቸው…
#Update

የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ስነስርዓት መካሄድ ጀመረ።

14ኛው ዙር የ20/80 እና 3ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ስነስርዓት በአሁን ሰዓት እየተካሄደ ይገኛል።

የዕጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ እየተካሄደ የሚገኘው በማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ሲሆን ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች፣ ተመዝጋቢዎች፣ እና እንግዶች ተገኝተዋል።

ይንን ስነሥርዓት በአዲስ ቴሌቪዥን (AMN) በኩል በቀጥታ መከታተል ይቻላል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ የዕጣ አወጣጥ ስነስርዓቱን እየተከታተልን የደረሰበትን እንልክላችኃለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ስነስርዓት መካሄድ ጀመረ። 14ኛው ዙር የ20/80 እና 3ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ስነስርዓት በአሁን ሰዓት እየተካሄደ ይገኛል። የዕጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ እየተካሄደ የሚገኘው በማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ሲሆን ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች፣ ተመዝጋቢዎች፣ እና እንግዶች ተገኝተዋል። ይንን ስነሥርዓት በአዲስ…
#Update

የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት ፦

" ... በዚህ ዙር የ20/80 ነባር ባለ ሶስት (3) መኝታ በ12ኛው ዙር ዕጣ ዝቅተኛ የቁጠባ መጠን ተወስዶ ለማጠናቀቅ የተቻለ በመሆኑ ነባር ባለ 3 መኝታ ብቁ ሆናችሁ የተገኛችሁ በቦርድ ውሳኔ የተቀመጠውን ላለመጣስ በዚህ ዕጣ #የማይካተቱ ሲሆን በቀጣይ በልዩ ሁኔታ ይስተናገዳሉ "

NB. በ20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም የ1997 ተመዝጋቢዎች ብቻ ተሳታፊ ናቸው።

@tikvahethiopia
አንኳር_ጉዳዮች_Executive_Summary_Annual_Human_Rights_Situation_Report.pdf
780.9 KB
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት አንኳር ጉዳዮችን ይፋ አደረገ።

የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. ድረስ ፦

- በተለያዩ የሥራ ክፍሎቹ እና ጽ/ቤቶቹ አማካኝነት ባደረገው ክትትልና ምርመራ፣

- ባከናወናቸው መለስተኛ ጥናቶች፣

- የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች፣

- በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደውን ጦርነት ተከትሎ ባካሄዳቸው ምርመራዎች፣

- በውትወታ እና በሌሎች ተግባራቶቹ አማካኝነት ከተገኙ መረጃዎች የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጾልናል።

ኢሰመኮ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በላከው እና በዓይነቱ የመጀመሪያ በሆነው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት መንግሥት በማናቸውም ጊዜ የሰዎችን መብት እንዲጠብቅ፣ እንዲያከብርና እንዲያረጋግጥ አሳስቧል።

ይህ ሪፖርት በዓመቱ የነበረውን አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን፣ የተገኙ ቁልፍ እመርታዎችን፣ ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮችን፣ ተግዳሮቶችን እና ምክረ-ሃሳቦችን ያካትታል

(ሙሉ ሪፖርቱ በPDF ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ ዕጣ የሚያወጣባቸውን ቤቶች የሚያስተዳድረው ቴክኖሎጂ ሲስተም በአሁኑ ሰአት በይፋ መከፈቱ ተገልጿል። አ/አ ከተማ አስተዳደር ግልፅነትንና ተጠያቂነትን በሚፈጥር መልኩ ለእጣ ተዘጋጅቷል ፤ የመረጃ መያዣና እጣ ማውጫ ከመበልጸግ ሂደት ጀምሮ ብዙ ሙከራዎች የተካደበት መሆኑ አሳውቋል። ለዕጣ ማውጣት ስነስረዓቱ ቅድመ-ዝግጅት ለአራት ዙር ሙከራ ተደርጎበት፣ አምስተኛውና የመጨረሻ ዙር የሚመለከታቸው…
#Update

ዛሬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የሚወጣበት ሲስተም ፦

- ዕጣ ሲወጣ በቀጥታ የአሸናፊዎችን ሙሉ መረጃ እና የቤት መረጃ ያሳያል።

- የዕጣ አወጣጥ ሲጠናቀቅ የአሸናፊዎችና የቤታቸውን መረጃ ያለ ሰው ንክኪ በቀጥታ ያሳያል ፤ ለህትመትም ያዘጋጃል።

- ዕጣ የወጣላቸው እድለኛ መሆን አለመሆናቸውን #በኦንላይን ማረጋገጥ ይችላሉ።

ውድ ቤተሰቦቻችን የ20/80 እንዲሁም 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ስነስርዓት መካሄዱን የቀጠለ ሲሆን በቀጣይም ያለውን ሂደት ተከታትለን እናሳውቃችኃለን።

@tikvahethiopia