TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" Galatoomaa Tour " የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ ወደ በሰኔ እና ሃምሌ ወር 2022 ወደ #ሰሜን_አሜሪካ እና #አውሮፓ እንደሚጓዙ ታውቋል። አመራሮቹ ጉዟቸውን " Galatoomaa Tour " በሚል የሚያደርጉ ሲሆን በተለያዩ ከተሞች ከደጋፊዎቻቸው ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጉዞውን…
#Update

" Galatoomaa Tour "

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሐመድ ጀርመን ይገኛሉ።

ዛሬ በጀርመን ኑርንበርግ በነበረ ህዝባዊ ስበስባ በእስር ላይ በቆዩባቸው ጊዜያት ለሳቸው እና አብረዋቸው ለታሰሩ ሰዎች ከእስር እንዲለቀቁ ደጋፊዎቻቸው አድርገዋል ላሉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

የእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዞ አንደኛው አላማ ምስጋና ለማቅረብ ሲሆን ሌላኛዋ አላማ በብዙ ውጥንቅጥ ውስጥ የምትገኘው ኢትዮጵያ ላይ ሰላም እንዲሰፍን ለማስቻል በሚደረግ ጥረት ውስጥ ደጋፊዎቻቸው የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ለማሳሰብ ነው ተብሏል።

እነ አቶ ጃዋር አሁን ካሉበት ጀርመን በመቀጠል ፈረንሳይ ፣ ኔዘርላንድስ እና ቤልጄም ከመሳሰሉ የአውሮፓ ሀገራት ከደጋፊዎቻቸው ጋር ከተገናኙ በኋላ ወደ ሰሜን አሜሪካ እንደሚያቀኑ ይጠበቃል።

መረጃው የጀርመን ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
#ትኩረት_የሚሻ_የፀጥታ_ጉዳይ 📣

በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ እና በአፋር ተላላክ ወረዳ በአንድ ግለሰብ ሞት ምክንያት የተቀሰቀሰ ግጭት ወደ ተኩስ ልውውጥ ተቀይሮ ለሰዎች ሞት እና መቁሰል ምክንያት ሆኗል።

አሁን ያለው የፀጥታ እጅግ ልዩ ትኩረት የሚፈልግ ነው ተብሏል።

ችግሩ የተከሰተው ባለፈው ማክሰኞ ዕለት ሲሆን አንድ የአፋር ተወላጅ አርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ መድና ከተማ ገበያ ውሎ ሲመለስ መሃል መንገድ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከተገደለ በኃላ ነው።

ባለፉት ተከታታይ ቀናት መዲናን ጨምሮ በበርካታ አካባቢዎች ላይ የተኩስ እሩምታ የሚሰማ ሲሆን የግለሰብ ቤቶችም መቃጠል መጃመራቸው ተነግሯል። እስካሁን ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ ማወቅ አልተቻለም።

ችግሩን ለመፍታት በአፋርም አማራ ክልል በኩልም ብዙ ቢጣርም ውጤት አላመጣም ይልቅም እየባሰ ሄዷል።

በርካቶች ባለው የፀጥታ ችግር ከቄያቸው እየሸሹ መሆናቸውም ተነግሯል።

የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሰኢድ ኢብራሂም አሁን ያለው ሁኔታ ከግለሰብም አልፎ መልኩን ቀይሮ እጅግ አሰቃቂ የሆነና መጥፎ ጉዳት ሊያደርስ በሚችልበት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልፀው የክልሉ መንግስት እና የፌዴራል መንግስት መኃል ገብተው ካላስቆመው ቀጠናው በጣም አስጊ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

ከአፋር ክልል ተላላክ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት እና የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት በኩል ለቪኦኤ ሬድዮ የሰጡት ቃሎች በዚህ ተያይዟል ያንብቡ ⬇️

https://telegra.ph/Attention-06-04-2

#አርጎባ_ብሄረሰብ_ልዩ_ወረዳ #ተላላክ_ወረዳ

#ቪኦኤ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " Galatoomaa Tour " የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሐመድ ጀርመን ይገኛሉ። ዛሬ በጀርመን ኑርንበርግ በነበረ ህዝባዊ ስበስባ በእስር ላይ በቆዩባቸው ጊዜያት ለሳቸው እና አብረዋቸው ለታሰሩ ሰዎች ከእስር እንዲለቀቁ ደጋፊዎቻቸው አድርገዋል ላሉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል። የእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዞ አንደኛው አላማ ምስጋና…
#JawarMohammed

አቶ ጃዋር መሐመድ (የኦፌኮ ም/ሊቀመንበር) በዛሬው የጀርመኑ ህዝባዊ ስብሰባ ወቅት ካነሷቸው ነጥቦች ጥቂቶቹ ፦

➡️ አቶ ጃዋር አጠቃላይ ኢትዮጵያም ሆነ ኦሮሚያ በብዙ ውጥንቅጥ ውስጥ መሆናቸውን ገልፀው ፤ ከዚህ ውጥንቅጥ ተወጥቶ #ሰላም እንዲሰፍን የማድረግ ጥረት መጀመራቸውን ገልፀዋል።

➡️ አቶ ጃዋር ለጀመሩት ሰላም የማስፈን ጥረት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ደጋፊዎቻቸው አብረዋቸው ሆነው ጦርነት እንዲቆም ፣ ሰላም እንዲሰበክ፣ ሰላም እንዲፈጠረ በአንድ እና ሁለት ክልል የተወሰነ ሳይሆን በመላው ሀገሪቱ ሰላም እንዲፈጠር ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

➡️ ኢትዮጵያ ሰላም እንድትሆን በመሰረታዊነት ኦሮሚያ ውስጥ ያለው ችግር ከመሰረቱ መፈታት አለበት የሚል እምነት እንዳላቸው ገልፀው ለዚህም ጦርነት በማቆም ሁሉም ወደ ሰላም የሚመለስበት እድል እንዲፈጠር እሻለሁ ብለዋል።

Credit- መረጃው ስብሰባውን በአካል የተካፈለው የዶቼቨለ ሬድዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ ታምራት ዲንሳ ነው ያጋራው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አዲስ_አበባ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ከለሊቱ 10:30 ጀምሮ የሚዘጉ መንገዶች ! እሁድ ግንቦት 28/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ " በመስዋዕትነታችን የሀገራችን አንድነትና የህዝባችን ሰላም ይረጋገጣል " በሚል መሪ ቃል ለፖሊስ አመራር እና አባላት የምስጋና እና የእውቅና ፕሮግራም በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል። ይህን ተከትሎ ስነ-ሥርዓቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን…
#ማስታወሻ

ውድ የአዲስ አበባ ቤተሰቦቻችን ነገ እሁድ በመስቀል አደባባይ በሚኖር ፕሮግራም ምክንያት መንገዶች ይዘጋሉ።

የሚዘጉ መንገዶችን ሊንኩን በመጫን መለስ ብላችሁ አንብቧቸው : https://t.iss.one/tikvahethiopia/70761

የነገ ውሏችሁን በተመለከተ ፦ የስራ ቀጠሮ ካላችሁ ፣ በግል ጉዳይ የምትንቀሳቀሱ ከሆነ ፣ ስራ የምትገቡም ካላችሁ የሚዘጉትን መንገዶች አውቃችሁ ከመጉላላት እንድትድኑ እና አመራጭ መንገዶችን እንድትጠቀሙ ልናስታውሳችሁ እንወዳለን።

#TikvahFamily❤️

@tikvahethiopia
#ግሪንላይፍ_ስፔሻሊቲ_ዴንታል_ክሊኒክ

🦷 የወለቁ ጥርሶችን  ያለምንም እንከን በኢምፕላንት እንተክላለን ፡፡
🪥በእጅግ ዘመናዊ የብሬስ ህክምና ውስብስብ የሆኑትን ጥርሶችን እናስተካክላለን።
🔬በዓለምአቀፉ  ታዋቂ ከሆኑ ላብራቶሪ ጋር  በመተባበር በዝርኮኒያ ቋሚ ጥርሶችን እንተክላለን ፡፡
👦 ቋሚ የልጆች ጥርስ (በpit & fissure sealant) ማከም

አድራሻ ፦
https://www.facebook.com/GreenLife-speciality-Dental-Clinic-1866888506724080/

https://www.greenlifeethiopia.com

https://t.iss.one/Greenlifedentalclini
#ሰላም

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በጓንጓ ወረዳ እና በቤንሻንጉል ክልል በመተከል ዞን የድባጢና ማንዱራ አጎራባች ወረዳ ቀበሌዎች መካከል የህዝብ ለሕዝብ የሰላም ግንኙነት እየተካሄደ ይገኛል።

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደረር በጓንጓ ወረዳና በመተከል ዞን በድባጢና በማንዱራ ወረዳዎች ስር የሚገኙት የሞጣ፣ የመንታውሀ፣ የአዲስዓለም፣የጨረቃ ፣የሲርበን፣የጎንቻ ላምብቻ፣የዳች ሉምቢያና ባሁስ ቀበሌዎች ሕዝብ በመንታውሀ ቀበሌ የህዝብ ለህዝብ መድረክ እያካሄዱ ይገኛሉ።

በሕዝብ ለሕዝብ መድረኩ የሁለቱም ዞን አጎራባች ወረዳ አስተዳዳራሪዎች፣ የካቢኔ አባላት፣ የጸጥታ አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

ምንጭ፦ አዊ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
" ሰላም ለሁላችን "

በአዊ እና ጉምዝ መካከል ተፈጥሮ የነበረውን የሰላም መደፍስ ተቀርፎ አብሮነትን ለማስቀጠል በዚገም ወረዳ ቅላጅ ከተማ የሰላም መድረክ እየተካሄደ ነው።

ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥና አብሮነትን ለማጠናከር በዚገም ወረዳ ቅላጅ ከተማ ላይ " ሰላማችን ለሁላችን" በሚል መሪ ቃል ነው የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ የሚገኘው።

በመደረኩ የሁለቱም ክልል የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የዚገም ወጣቶች የተገኙ ሲሆን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ወኪሎች ስፍራው ላይ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

"በዚገምና አካባቢው የመጣው ሰላም እንዲቀጥል መንግስት ሀላፊነቱን ይወጣ ፣ ወንድማማችነታችንን ለማጠናከር የህግ የበላይነት ይከበር። " ሲሉ የዚገም ወረዳ ነዋሪዎች ጥሪ አቅርበዋል።

የዚገም ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ አድጎአየሁ ከቅርብ አመታት ወዲህ የሁለቱንም ብሄር ህዝቦች አንድነታቸውን ሲሸረሽሩ ቆይተዋል ያሏቸው 118 ነፍስ ገዳዮችና በአጠቃላይ 218 የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈጽሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በህግ ማስከበር ዘመቻ በህግ ጥላ ስር እንዲውሉ ተደርጓል ሲሉ አሳውቀዋል።

አሁን እየታየ ያለው አንጻራዊ ሰላም እንዲጠናከርና በዚገም ሰማይ ስር የሰላም አየር እስኪነፍአስ የህግ ማስከበር ስራ ይጠናከራል ማለታቸውን የአዊ ኮሚኒኬሽን ፅፏል።

@tikvahethiopia
" በተኩስ ልውውጡ 19 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል " - ፖሊስ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ምዥጋ ወረዳ በክልሉ ልዩ ኃይሎችና በመጋቢት ወር ዕርቅ ፈጽመው ከጫካ በተመለሱ የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የ19 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።

ግንቦት 24/2014 በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ከተገደሉት መካከል የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብደኑ ጀርሞሳ፣ አንድ የአካባቢው ባለሀብትና ልጃቸው ተጠቃሽ ናቸው ተብሏል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ኡመር ሙስጠፋ እንደገለፁት ከሆነ ቀሪዎቹ 16 ሰዎች የጉህዴን ታጣቂዎች ናቸው።

ዋና አስተዳዳሪውን ጨምሮ 3ቱ ግለሰቦች ሕይወታቸው ያለፈው በተኩስ ልውውጥ መሀል በመታቸው ተባራሪ ጥይት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተኩስ ልውወጡ ከመንግሥት ኃይሎች መካከል ሕይወቱ ያለፈ ሰው ስለመኖሩ የተባለ ነገር የለም፡፡

ኮ/ር ኡመር ለተደረገው የተኩስ ልውውጥ ካለፈው 3 ሳምንት ወዲህ ከአቅም በላይ እየሆኑ መጥተዋል ያሏቸውን የጉሕዴን ታጣቂዎች ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

በዕርቁ ከተማ እንዲገቡ የተደረጉት ታጣቂዎች ባለፉት ሳምንታት ዘረፋን ጨምሮ የተለያዩ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ እንደነበር ገልፀው ዕርቅ በመፈጸሙ ምክንያት የክልሉ ኃይሎች እንዲታገሱ ትዕዛዝ ተላልፎ እንደነበር አስረድተዋል። ይሁንና ድርጊቶቹ እየጨመሩ ሲመጡ የክልሉ ኃይሎች "ራሳቸውን እንዲከላከሉ" እንደተናገራቸው አስታውቀዋል፡፡

የረቡዕ ዕለቱ ተኩስ ልውወጥ " በልዩ ኃይል ካምፕ ላይ የመድፈር ሁኔታ ታይቶ ነው " ያሉት ኮሚሽነሩ ታጣቂዎች የመጀመሪያውን ተኩስ በመክፈታቸው ከመንግሥት ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ውስጥ መግባታቸውን አስረድተዋል፡፡

ያንብቡ፦ telegra.ph/RE-06-05-2

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በተኩስ ልውውጡ 19 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል " - ፖሊስ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ምዥጋ ወረዳ በክልሉ ልዩ ኃይሎችና በመጋቢት ወር ዕርቅ ፈጽመው ከጫካ በተመለሱ የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ የ19 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል። ግንቦት 24/2014 በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ከተገደሉት መካከል የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ…
#ካማሺ

በካማሺ ዞን የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ የዞኑ ፀጥታ ምክር ቤት ዓርብ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በካማሺ ከተማ የሰዓት ገደብ ጥሏል።

የፀጥታ ም/ቤቱ " በየአቅጣጫዎች ለማኅበረሰቡ ደኅንነት ሥጋት የሚሆኑ እንቅስቃሴዎች ስላሉ " በሚል በጣለው የሰዓት ገደብ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ እንቅስቃሴ እንዳይደረግ አግዷል፡፡

የመንግሥትም ሆነ የግል ሞተር ብስክሌቶች በከተማ ውስጥም ሆነ ውጪ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይችሉ የተገለፀም ሲሆን ይህንን ተላልፈው በተገኙ አካላት ላይ የፀጥታ ኃይሉ ለሚወስደው ዕርምጃ መንግሥት ኃፊነቱን እንደማይወስድ ማስጠንቀቁን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

ቤተሰብ መስርተዋል?

እንግዲያውስ ባንካችን ለባለትዳራር ጥንዶች ያዘጋጀውን ልዩ የቁጠባ ሂሳብ በመክፈት የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሁኑ!
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ መለያ ስቲከር ፦

• ሙሉ ሰማያዊ ቀለም ያለው መለያ ➡️ ለሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ተሸከርካሪዎች የሚያገለግል ነው።

• በነጭ መደብ የተዘጋጀው መለያ ➡️ በክልል ለሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች የሚያገለግል ነው፡፡

የታለነ የነዳጅ ድጎማ ስርዓት በቅርቡ ተግባራዊ ይሆናል። በዚሁ ስርዓት ተጠቃሚ የሚሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተሸከርካሪዎችን የመለየትና መረጃ የማጥራት ስራ እየተከናወነ ይገኛል

ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia