TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
* አዲስ አበባ

ከ8,500 በላይ መምህራን የሞያ ብቃት ምዘና ይወስዳሉ።

ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ 8,588 መምህራን የሞያ ብቃት ምዘና መውሰድ እንደሚጀምሩ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል።

በዘንድሮው ዓመት በሚያስተምሩት የትምህርት ዘርፍ ብቃታቸው የሚመዘነው መምህራን ከዚህ ቀደም ከነበረው ከፍተኛ ነው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ስንታየሁ ማሞ በሰጡት ቃል ፥ " ግንቦት 25 ሀሙስ በስምንት ክ/ከተሞች ላይ ምዘና ይካሄዳል። እዚህ ምዘና ላይ የግል ትምህርት ቤቶች ተመዝግበው በየትምህርት ቤቶቻቸው ስም ዝርዝራቸው ተለጥፏል " ብለዋል።

አክለው ፤ " በሀሙስ 8,588 መምህራን ፤ በአንደኛ ደረጃ 6,569 በሁለተኛ ደረጃ 2,672 መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች በዚህ ውስጥ ያልፋሉ " ሲሉ ገልፀዋል።

የመምህራንን የሞያ ብቃት መለካት የመጨረሻው ግብን በተመለከተ ወ/ሮ ስንታየሁ ፤ " ብቃት የሌላቸው መምህራን ከዚህ በኃላ ወደፊትም በዚህ ስታንዳርድ አልፎ ብቁ ያልሆነ መምህር መምህር ሆኖ መቀጠል የለበትም የሚል አቋም ይዘናል " ሲሉ ለሸገር ኤፍ ኤፍም ሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #UNICEF

ስለምስራቅ አፍሪካ ድርቅ እና በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ ስላሳደረው ተፅእኖ ምን ያህል እናውቃለን ?

(የተመድ የህጻናት ተራድኦ ድርጅት - UNICEF)

➤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ምስራቅ አፍሪቃን የመታው ድርቅ ከ10 ሚሊየን በላይ #ህጻናት ለአስከፊ የምግብ እጥረት ዳርጓል። እስካሁን በርሃም አደጋው የሞተ ሰው አላጋጠመም።

➤ በኢትዮጵያ ባጋጠመው 3 ተከታታይ የዝናብ ወቅቶች የዝናብ እጥረት በዓመታት አስከፊ የድርቅ ሁኔታ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል፤ አስከፊው ድርቅ ለበርካታ እንስሳት ሞት ፣ የውኃ ምንጮችም ተሟጠው እንዲደርቁ መንስኤ ሆኗል።

➤ በ4 ክልሎች (ሶማሊ፣ ኦሮሚያ ፣ አፋር፣ ደቡብ ) ድርቅ በሰፊው የተከሰተባት ኢትዮጵያ ከችግሩ ለመላቀቅ ቢያንስ 5 ዓመታት ያስፈልጓታል።

➤ በኢትዮጵያ አራት ክልሎች (ኦሮሚያ፣ ሶማሊ፣ አፋርና ደቡብ) ድርቁ 10 ሚሊየን ህዝብ ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ አሳርፏል። ከዚህ ውስጥ 1.5 ያህሉ ለተመጣጠነ የምግብ እጥረት የተዳረጉ ህጻናት ናቸው፡፡ 

➤ በኢትዮጵያ ያለው ድርቅ 1.75 ሚሊየን ህዝብን ከመኖሪያ ቀዬው አፈናቋል።

➤ በሶማሊ ክልል ከ5 ዓመት በታች የሆኑ 220 ሺ ህጻናት ገደማ የተመጣጠነ ምግብ እጦት አለባቸው፡፡ ከ150 ሺህ በላይ አጥቢና እርጉዝ እናቶች በቂ ምግብ የማያገኙ ናቸው።

➤ ባለፈው ዓመት በችግሩ ሳቢያ ከ400 ሺ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተቆራርጠዋል፡፡ ይህ ደግሞ ያለዕድሜ ጋብቻን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ ምስቅልቅሎችን አሳርፏል።

➤ በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ሳቢያ የናረው የስንዴና ሌሎች መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ የድርቅ ተፅእኖውን ምላሽ የመስጠት ጥረቶችን አዳጋች አድርጎታል።

#UNICEF #ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የቀጠለ ሲሆን ፤ በግንቦት 23/2014 ዓ/ም ውሎ የደቡብ ክልል ፕሬዝደንት እና ሌሎች የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች በምልዓተ ጉባኤው ተገኝተው ነበር። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቤተክርስቲያን ላይ በየጊዜው እየደረሱ ባሉ ችግሮች ዙሪያ ውይይት ለማድረግ ነው ከደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት አቶ ርስቱ ይርዳው ከሌሎች የክልሉ…
#Update

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መካሄዱን የቀጠለ ሲሆን ዛሬ በተካሄደ ምርጫ ጉባኤው ፤ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ጴጦሮስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በማድረግ መሾሙን ከኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ ከወራት በፊት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ የሾመቻቸው አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በቅርቡ (ከሰኔ በፊት) ከስልጣናቸው ሊለቁ ነው። ከስድስት ወር ላነሰ ጊዜ በልዩ መልዕክተኛነት ያገለገሉት ሳተርፊልድ ከስልጣናቸው ሲለቁ ምክትል ልዩ መልዕክተኛ ፔይቶን ኖፕፍ ቦታውን እንደሚረከቡ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸድ ምንጮች መስማቱን ሮይተርስ ዘግቧል። በቅድሚያ የአምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በቅርቡ…
#NewsAlert

አሜሪካ አዲስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሾመች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ፤ በአምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ምትክ አምባሳደር ማይክ ሀመር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው እንደሚሾሙ አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ አምባሳደር ሳተርፊልድ በስልጣን ቆይታቸው ላበረከቱት አስተዋፆ ምስጋናቸውን አቅርበው አዲሱ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሀመር አሜሪካ በቀጠናው የጀመረችውን ዲፕለማሲያዊ ጥረት እንደሚያስቀጥሉ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

የአምባሳደር ሀመር መሾም አሜሪካ በአካባቢው እያደረገች ያለችውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት መጠናከር መንግሥታቸው ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ብሊንከን አመልክተዋል።

" ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ሰላም የሚወስደውን ሁሉን አካታች የሆነ የፖለቲካ ሂደት፣ የጋራ ደኅንነትና የመላ ኢትዮጵያዊያንን ብልጽግናን የሚደግፍ ነው " ብለዋል ብሊንከን።

አስተዳደራቸው " መላ ትኩረቱን ግጭት እንዲቆም፣ ሰብዓዊ ድጋፍ ባልተገደበ ሁኔታ እንዲደርስ፣ በሁሉም ወገኖች በተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችና ጥቃቶች ላይ ግልፅ ምርመራ እንዲደረግና ለግጭቱ መፍትሄ ለማምጣት ድርድር እንዲካሄድ ያደርጋል " ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ።

ከዚህ ቀደም የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከሰኔ በፊት ከስልጣናቸው እንደሚለቁ መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ 6710 ከA/B/C/D ወደ " OK " መቀየሩን አሳውቆናል።

በኢትዮ ቴሌኮም ድጋፍ ለልብ ሕሙማንን የሚለገስበት 6710 አጭር የፅሁፍ መልዕክት ከዚህ በፊት ከ1 ብር እስከ 100 ብር ድጋፍ የሚደረግበት A/B/C/D አማራጭ ወደ “OK” ተቀይሯል።

አሁን ላይ አንድ ጊዜ ብቻ " OK " ብሎ ወደ 6710 በመላክ እና በመመዝገብ በቀን አንድ ብር ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ፡፡

#6710_OK📨
#አንድ_ብር_ለአንድ_ልብ!💖

ይህንን መልዕክት በማጋራት ለብዙሃን ያድርሱ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#US በየጊዜው በርካቶች በታጣቁ ሰዎች በሚከፈት ተኩስ የሚገደሉባት ሀገረ አሜሪካ ትላንትም እጅግ በጣም ዘግናኝ የሚባል ጥቃት ተፈፅሞ 2 አዋቂዎችን ጨምሮ 19 ሕጻናት ተገድለዋል። በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት አንድ የ18 ዓመት ወጣት በከፈተው የተኩስ እሩምታ 2 አዋቂዎችን ጨምሮ 19 ሕጻናት መገደላቸውን ተዘግቧል። ድርጊቱ የተፈፀመው በደቡብ ቴክሳስ ግዛት፣ ዩቫልዲ ከተማ ሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት…
#አሜሪካ

በአሜሪካ ኦክላሆማ ግዛት ቱልሳ በተሰኘች ከተማ ሆስፒታል ውስጥ በተከፈተ ተኩስ አራት ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ትኩስ እንደከፈተ የተጠረጠረው እና ጠመንጃ እና ሽጉጥ ታጥቆ የነበረው ግለሰብ መሞቱንም ፖሊስ አረጋግጧል።

ፖሊስ ጥቃቱ በተሰነዘረበት ቅዱስ ፍራንሲስ ሆስፒታል በሦስት ደቂቃ የደረሰ ሲሆን በጥቃቱ የሚጎዱ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ በስፍራው በአስቸኳይ መድረሱ ተገልጿል።

ትላንት ረቡዕ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት በርካቶች መቁሰላቸውንም ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል።

የቱልሳ ከተማ ምክትል የፖሊስ ኃላፊ ኤሪክ ዳላግሊሽ " አሁን ላይ አራት ሲቪል ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ ጥቃት አድራሹም ሞቷል " ብለዋል።  

እስካሁን ማንነቱ ያልተለየው ጥቃት አድራሽ እራሱ ሳያጠፋ እንዳልቀረ ተገምቷል።

ተጠርጣሪው ሁለት መሳሪያዎችን ታጥቆ የነበረ ሲሆን " አንደኛው ረዝም ያለ፣ ሌላኛው ደግሞ የእጅ ሽጉጥ ነው በስፍራው የተገኘው " ብለዋል የፖሊስ ኃላፊው። 

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia
Audio
#Olusegun_Obasanjo

ከቀናት በፊት ትግራይ ክልል ፤ መቐለ የነበሩት እና ከዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር ምክክር ያደረጉት በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት መቋጫ እንዲያገኝ እንዲሁም ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ እየተደረገ ያለውን ጥረት በተመለከተ ከBBC Focus on Africa ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ ከላይ በድምፅ ተያይዟል።

(3.3 MB)

@tikvahethiopia
#ባሌ_ሮቤ

በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለሥራ ጉብኝት ባሌ ሮቤ ገብቷል።

በጉብኝቱ ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪ ፦

➡️ ሰሞኑን ትግራይ ክልል መቐለ የነበሩት የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣

➡️ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣

➡️ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኡስማን ዲዮን እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ናቸው።

የልዑካን ቡድኑ በባሌ ዞን እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ሥራዎችን ተዘዋውሮ ይመለከታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ችሎት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፤ " ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት " ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር ላይ በሚገኘው በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የምርምራ ጊዜውን የፈቀደው የተከሳሽ ጠበቃ ያቀረቡትን መከራከሪያ እና የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ነው። የምርመራ ጊዜው ከግንቦት 19 ቀን…
" የግራ ዓይኑ ስር አብጦ የለበሰው ቲ-ሸርት ተቀዶ አግኝተነዋል " - ታሪኩ ደሳለኝ (የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም)

በእስር ላይ የሚገነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለለኝ ደብደባ እንደተፈፀመበት ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ገልጿል።

የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም የሆነው ታሪኩ ደሳለኝ ፤ ዛሬ ግንቦት 25/2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ፖሊስ በተለምዶ 3ተኛ ወንድሙን ጋዜጠኛ ተመስገንን ለመጠየቅ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝቶ እንደነበር ገልጿል።

" በዚህ እስር ቤት በታሳሪና በጠያቂ መካከል በሁለት ሾቦ የተጋረደ ከ10 ሜትር የሚበልጥ ርቀት አለ " የሚለው ታሪኩ " በታሳሪና በጣያቂ መካከል ባለው ርቀት የተነሳ፣ ንግግር ለማድረግ እጅግ አዳጋች ነው። አጠቃላይ ነገሩ መጯጯህ ነው " ብሏል።

" ጋዜጠኛ ተመስገን ከዚህ በፊት በእስር ቤት እያለ ባጋጠመው በጆሮ ህመም ምክኒያት በዚህ ግር ግር ውስጥ ጆሮው ለመስማት ያዳግተዋል " ሲል አክሏል።

ይሄ በመሆኑ ጋዜጠኛ ተመስገን ለፖሊሶቹ " ትንሽ ቀረብ ብሎ ቢያወራኝ " ሲለው ፖሊሱ በእጁ የማመናጨቅ ምልክት እንዳሳየው ተመስገንም ድጋሜ ለማስረዳት ሲሞክር አንዱ ፖሊስ ከነበረበት ከጠያቂ ቦታ ሌላው ፓሊስ ከእስረኛቹ መቆሚያ ደረጃ ላይ በመውረድ ለሁለት ተመስገንን አብረውት ከቆሙት እስረኞች መካከል ጎትተው በማውጣት በቦክስ፣ በጫማ ጥፊ ለሁለት እንደደበደቡት ታሪኩ አስረድቷል።

" ይህ ሲሆን የሌሎች እስረኛ ጠያቂ ቤተሰቦችና እስረኞችም አይተዋል። " ያለው ወንድሙ ታሪኩ " ድብደባውን እየፈፀሙ ወደ እስራኛ ክፍል ሳይሆን ወደ ሌላ ቦታ ይዘውት ሄደዋል "ብሏል።

ከቆይታ በኃላ በቢሮ ውስጥ ጋዜጠኛ ተመስገንን እንዳገኘው የሚገልፀው ታሪኩ " የግራ ዓይኑ ስር አብጦ የለበሰው ቲ-ሸርት ተቀዶ አግኝተነዋል " ሲል ሁኔታውን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ባሌ_ሮቤ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለሥራ ጉብኝት ባሌ ሮቤ ገብቷል። በጉብኝቱ ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪ ፦ ➡️ ሰሞኑን ትግራይ ክልል መቐለ የነበሩት የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ ➡️ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ➡️ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኡስማን ዲዮን እንዲሁም የፌደራል…
#Update

ለስራ ጉብኝት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ባሌ ሮቤ የሚገኙት የቀድሞው የናይጄሪያው ፕሬዝደንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በሲናና ወረዳ በ3 ሺህ 200 ሔክታር መሬት ላይ በክላስተር የለማውን የሥንዴ ሰብል ጎብኝተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነች የሚገኘው ስራ አበረታች እና ለበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ መሆን የሚችል ተግባር መሆኑን ኦባሳንጆ በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት ሰጥተው ከሰሩ የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ባሻገር ምርታቸውን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያቸውን ሊያሻሽሉ እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡

በወረዳው በዘንድሮ የበልግ እርሻ 42 ሺህ 901 ሔክታር መሬት በስንዴ ሰብል መሸፈኑን ከሲናና ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

(የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ)

@tikvahethiopia
#Germany #Ethiopia

ጀርመን በኢትዮጵያ መንግሥት ጥያቄ ከቀረበላት አገራዊ የምክክር ሂደቱን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አሳውቃለች።

ሀገሪቱ ይህን ያሳወቀችው ኢትዮጵያ በሚገኙት አምባሳደሯ ነው።

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፋን አወር ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፤ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር የአገሪቷን መሰረታዊ ችግሮች ለመፍታት ጥሩ የመፍትሔ አማራጭ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ጥያቄ ከቀረበላት የፌዴራል ስርዓት የምትከተለው ጀርመን በሚቻለው አቅም ሁሉ አገራዊ የምክክር ሂደቱን ለመደገፍ ዝግጁ ናት ሲሉ አረጋግጠዋል።

" በኢትዮጵያ የሚስተዋሉትን ውስጣዊ ችግሮች በመፍታት መፍትሔ ለማበጀት በጋራ መምከር ያስፈልጋል " ያሉት አምባሳደሩ " ኢትዮጵያ የምታካሂደው አገራዊ ምክክር ሁሉንም አሳታፊና አካታች ሆኖ ሲካሄድ ልዩነቶችን በመነጋገርና በመፍታት በቀላሉ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር ያስችላል " ብለዋል።

በአገራዊ ምክክሩ ለጋራ ችግሮች መንስኤ የሆኑ ጉዳዮች ምንድን ናቸው? የሚለውን ቁልፍ ጥያቄ በማንሳትና በግልጽ መነጋገር የጋራ መፍትሔ ማምጣት ይቻላል ሲሉም አክለዋል።

አምባሳደር ስቴፈን ፤ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የምክክር ሂደቱን ሁሉን አቀፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

#ENA

@tikvahethiopia