#CocaCola
ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በሰበታ ከተማ 100 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የፈጀ የኮካኮላ ምርት ማምረቻ ፋብሪካ ተመርቋል።
ተገንብቶ የተጠናቀቀው የማምረቻ ፍብሪካ ኮካ-ኮላ ቤቭሬጅስ አፍሪካ-ኢትዮጵያን በአመት 100 ሚሊየን በላይ እሽግ ለስላሳ ለማምረት ያስችለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የማምረቻ ግብዓቶችን እንደ የፕላስቲክ ጠርሙስ፣ የፕላስቲክ ጠርሙስ ክዳን እና ሌሎች የምርት ግብአቶችን በማምረት ከውጪ ወደ ሀገሪቷ የሚገቡ ምርቶችን በመቀነስ እንደ " ሚኒት ሜድ ጁስ " የመሳሰሉ አዳዲስ ምርቶችን ሀገር ውስጥ በማምረት ጠቅላላ ምርት ለመጨመር የሚረዳ ነው፡፡
ኮካ ኮላ " ሚኒት ሜድ " የተሰኙ የጁስ ምርቶቹን ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እያመጣ መሆኑ ዛሬ በነበረው የፋብሪካው ምረቃ ስነስርአት ላይ ተሰምቷል።
የሚመረቱት የግብአት ምርቶቹ የሲ.ሲ ቢ.ኤን ፍላጎት ከማሳካት በተጨማሪ ለውጪ ገበያ በማቅረብ የውጨ ምንዛሬን ሀገሪቷ እንድታገኝ እና በዘርፉ ያለውን የምርት እጥረት ለመፍታት ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብም ፋብሪካው እቅድ ይዞ እየሰራ ይገኛል፡፡
መረጃው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ካፒታል ነው።
@tikvahethiopia

ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ተወለደ።
በወላይታ ዞን በገሱባ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዲት እናት ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ትላንት ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ/ም ተገላገለች።
ይህ ክስተት " Natal teeth " ተብሎ እንደሚጠራ የዘርፉ ባለሙያዎች የሚገልፁ ሲሆን ከዚህ በፊት ብዙም ያልተለመደ ቢሆንም አዲስ ከሚወለዱ ከ2000 - 3000 ሕጻናት ውስጥ በአንዱ ላይ ሊከሰት እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
ትላንትና የተወለደው ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ምንም ሳይቸገር ጡት እየጠባ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ የወላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን መረጃ ያሳያል።
በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ሊሰጥ የሚችል ፅሁፍ በዚህ ድረገፅ ማግኘት ይቻላል ፦ https://www.stanfordchildrens.org/en/topic/default?id=natal-teeth-90-P01862
#ወላይታዞንኮሚኒኬሽን #Stanfordchildern

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ህወሃት " የኤርትራ ጦር ጥቃት ከፈተ " በሚል የሚያሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም አሉ። ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ለአል ዓይን አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ነው። ዶ/ር ለገሰ ትንኮሳ ያደረገው ህወሃት ነው ፤ የተመቱትም ራሳቸው የህወሃት ታጣቂዎች ናቸው ብለዋል። በኤርትራና በህወሃት መካከል ግጭት እንዲፈጠር ያደረገው…
#Update #Sheraro
ሮይተርስ ዛሬ ይዞት በወጣው ዘገባ ባለፈው ሳምንት የመጨረሻ ቀናት ላይ የኤርትራ ጦር በሽራሮ ከተማ ላይ በከፈተው ጥቃት አንዲት የ14 ዓመት ታዳጊ መገደሏን እና 18 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን አመልክቷል።
ሮይተርስ ፤ ከሰብዓዊ ድርጅት ተቋማት የተገኘ መረጃ የሰፈረበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) ሰነድ መመልከቱን በመግለፅ ነው ዘገባውን ይዞ የወጣው።
በዚህም የኤርትራ ጦር ቢያንስ 23 ጊዜ ወደ ሽራሮ ከባድ መሳሪያ ተኩሷል።
ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ ግንቦት 20 እና 21 ቀን 2014 ዓ.ም. የኤርትራ ሠራዊት በሽራሮ ከተማ ላይ ከፍቶት ነበረ በተባለው ጥቃት፣ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ተጠልለውበት የነበረ #ትምህር_ቤት ጉዳት ደርሶበታል።
የከባድ መሳሪያ ጥቃት ተፈጽሞባታል የተባለችው ሽራሮ ከኤርትራ ድንበር 11 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቀት ላይ የምትገኝ ናት።
ሰሞኑን ኤርትራ ከፈተች ስለተባለው ጥቃት የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ
https://www.reuters.com/world/africa/eritrean-troops-shell-town-north-ethiopia-un-2022-05-31/

#Tigray, #Mekelle
የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት መቋጫ ያገኝ እና አስተማማኝ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ጥረት እያደረጉ የሚገኙት የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞ ናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ትግራይ ክልል ይገኛሉ።
አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝደንት መቐለ እንደሚገኙ በመግለጽ ከዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ጋር እንደመከሩ ገልጸዋል።
ኦባሳንጆ እና ዶ/ር ደብረፅዮን በቀጠናዊ ጉዳዮች ጋር መምከራቸው የተነገረ ሲሆን ምክክሩን የተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልሆነም።

#MinT
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፈጠራ ባለቤቶችን ለመደገፍና ለማበረታታት የሚያስችል አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑን አሳውቋል።
በሚኒስቴሩ የምርምርና ኢኖቬሽን ዘርፍ ዳይሬክተር ጀነራል ሠላምይሁን አደፍርስ ተከታዩን ብለዋል ፦
" ጀማሪ የፈጠራ ባለቤቶች ሥራዎቻቸው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረገ ነው።
አሁን ላይ ደግሞ ጀማሪ የፈጠራ ባለቤቶች ኢንተርፕራይዝ መሆን እንዲችሉ ማበረታቻዎችን የያዘ አዋጅ እየተዘጋጀ ነው።
አዋጁ ሥራ ላይ ሲውል ውጤታማ የሚያደርግ ነው።
ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ሲሆን አዋጁ ለመጽደቅ የሚያስችሉ አስፈላጊ ሂደቶችን ካለፈ በኋላ ተግባራዊ ይደረጋል።
አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ዜጎች ለመደገፍ ሚኒስቴሩ እያወዳደረ ይገኛል፤ ተወዳድረው ያሸነፉ ፈጣሪዎች የገንዘብ፣ የቴክኒክና የሥልጠና ድጋፎችን እያገኙ ነው።
የልማት አጋሮች አሸናፊ ለሆኑ ኃሳቦች የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉበት ሥርዓትም ተዘርግቷል።
ሚኒስቴሩ አዳዲስ የፈጠራ ኃሳብ ያላቸውን ልጆች ከመደገፍ ባሻገር ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ልጆችም የሚወጡበት ሥርዓት እየዘረጋ ነው "
#ENA

#Update የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የቀጠለ ሲሆን ትላንት ግንቦት 18፣ 17 እና 16 በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክሯል። በትላንት የጉባኤው ውሎ በትግራይ ክልል የሚገኙ አባቶች ያስተላለፉትን መግለጫ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያይቶበታል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ወቅታዊውን ችግር ተከትሎ በትግራይ ክልል የሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሰጧቸውን መግለጫዎች መመልከቱን ቃላቸውንም ከመገናኛ ብዙኃን ማድመጡ ተገልጿል።…
#Update
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የቀጠለ ሲሆን ፤ በግንቦት 23/2014 ዓ/ም ውሎ የደቡብ ክልል ፕሬዝደንት እና ሌሎች የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች በምልዓተ ጉባኤው ተገኝተው ነበር።
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በቤተክርስቲያን ላይ በየጊዜው እየደረሱ ባሉ ችግሮች ዙሪያ ውይይት ለማድረግ ነው ከደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝደንት አቶ ርስቱ ይርዳው ከሌሎች የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደረገው።
ምልዓተ ጉባኤ በሃይማኖታቸው ምክንያት ስለተገደሉ፣ ስለተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናትና ከማምለኪያ ቦታዎች ጋር በተያያዘ ያሉ ችግሮችን በደብዳቤ ንባብ እንዲሁም በክልሉ በሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት አማካይነት የቃል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙም ተጠይቋል።
የክልሉ ፕሬዝደንት የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት አስተዳደሩ እያደረጋቸው ያሉ ጥረቶችን ገልጸው በየደረጃው ለመፍታት እንደሚሠሩ ገልፀዋል።
ምልዓተ ጉባኤው በክልሉ በሚገኙ አንዳንድ ቦታዎች ምላሽ የተሰጠባቸው ጉዳዮችን አንስቶ የክልሉ ፕሬዝደንት በምልዓተ ጉባኤው ተገኝተው ላደረጉት ውይይትና ለሰጡት ምላሽ ምስጋና አቅርቧል።
መረጃውን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዩሴፍን ዋቢ አድርጎ ያሰራጨው የኢኦተቤ መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ስርጭት ድርጅት ነው።

#EU #RUSSIA
የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት በሩስያ የነዳጅ ግብይት ላይ ማዕቀብ ጣሉ።
27ቱ አውሮጳ ህብረት አባል ሃገራት በሩስያ የነዳጅ ግብይት ላይ ማዕቀብ መጣላቸውን ይፋ አድርገዋል።
አባልሃገራቱ በግዙፉ የሩስያ ባንክ ስቤር ባንክንም ከዓለማቀፉ የባንኮች የክፍያ ስረዓት ወይም ስዊፍት ማስወጣታቸውን አስታውቀዋል።
በስምምነቱ መሰረት ወደ አውሮፓ የሚገባው የሩስያ ነዳጅ ሁለት ሶስተኛው እንደሚታቀብ የህብረቱ ፕሬዚደንት ቻርለስ ሚሸል ተናግረዋል።
ማዕቀቡ " የሩስያ የፋይናንስ ምንጭ በከፍተኛ ደረጃ በማንኮታኮት " ሩስያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ገትታ ከሀገሪቱ ለቃ እንድትወጣ ያስገድዳታል " ሲሉ ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል።
የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስም " ስምምነቱ የጋራችን ነው " ብለዋል። ነገር ግን ከሃያ ሰባቱ ሃገራት መካከል ፦
➡️ ሃንጋሪ ፣
➡️ ስሎቫኪያ ፣
➡️ ቼክ ሪፐብሊክ እና ቡልጋሪያ ከሩስያ ነዳጅ ማስገባት #እንደማያቋርጡ አስታውቀዋል።
ይህንኑ በተመለከተ የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን የነዳጅ ማዕቀቡ የህብረቱ አጀንዳ መሆን የለበትም ሲሉም ተቃውሟቸውን አሰምተው እንደነበር የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

" በ5 ወር 27,800 ሰዎች ከአፍሪካ ቀንድ ወደ የመን ተሻግረዋል " - IOM
እንደ ተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ (IOM) ፤ ባለንበት በዚህ ዓመት 2022 (እኤአ) /በ5 ወር/ ቢያንስ 27,800 ሰዎች ከአፍሪካ ቀንድ በጦርነት ወደምትታመሰው ወደ #የመን ተሻግረዋል ፤ ይህ ደግሞ በ2021 ሙሉ ዓመት ከተደረጉት ጉዞዎች ሁሉ የሚበልጥ ነው። (በ2021 ዓመት 27,700 ነበር)
IOM በዚህ ደረጃ ቁጥሩ ከፍ እንዲል ካደረጉት ምክንያቶች መካከል የCOVID-19 እንቅስቃሴ ገደቦች መቃለላቸው ፣ የበለጠ ምቹ የአየር ሁኔታ መኖር እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታ ሁኔታ እና ድርቅ ይጠቀሳሉ ብሏል። (አብዛኞቹ ስደተኞች ከኢትዮጵያ መሆናቸው ተጠቅሷል)
IOM በቅርቡ ከየመን ወደ ኢትዮጵያ በፍቃደኝነት የሚመለሱ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ለመደገፍ የ7.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ጠይቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ከኢትዮጵያና ከሶማሊያ በሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች በየመን በኩል ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመድረስ በማሰብ አደገኛውን የኤደን ባህረ ሰላጤ ያቋርጣሉ።
ስደተኞቹ በዋናነት ዓላማቸው ወደ የመን ሰሜናዊ ጎረቤት ወደሆነችው #ሳዑዲ_አረቢያ ለመድረስ ነው።

ከዓለም ዙሪያ 📣
➡️ #ካሜሮን፦ በካሜሩን መገንጠልን አላማቸው አድርገው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ ታጣቂዎች ናይጄሪያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ መንደር በፈጸሙት ጥቃት በትንሹ 20 ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል። ጥቃቱ ባሳለፍነው እሁድ በደ/ምዕራብ የካሜሩን ክፍል ኦቦኒ ሁለት በተሰኘ መንደር የተፈፀመ ሲሆን ከሞቱ ሰዎች ባሻገር ከ60 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ታጣቂዎቹ ነዋሪዎቹ በየወሩ ገንዘብ እንዲከፍሏቸው ይፈልጋሉ፤ ነዋሪዎቹ ደግሞ ፍቃደኛ አልሆኑም። ለዚህም ነው ጥቃት ያደረሱባቸው ተብሏል።
➡️ #ሜክሲኮ ፦ በደቡባዊ ሜክሲኮ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ በትንሹ 10 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች የገቡበትን ማወቅ እንዳልተቻለ ተሰምቷል።
➡️ #ቻይና ፦ የሻንጋይ ነዋሪዎች ከሁለት ወር በኃላ የኮቪድ-19 የእንቅስቃሴ ገደብ መነሳቱን ተከትሎ ነፃ ሆነዋል። ነዋሪዎች ባለፉት 2 ወር ኮቪድ-19ኝን ለመከላከል በተጣለ የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ከእንቅስቃሴ ርቀው ቆይተዋል።
➡️ #ዩክሬን ፦ የየክሬን ኬርሰን ግዛት በሩስያ ቁጥጥር ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ሁሉንም የግንኙነት መስመሮች እንዲዘጉ ማድረጋቸው ተነግሯል።
➡️ #አሜሪካ ፦ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ሀገራቸው ለዩክሬን 'ቁልፍ ኢላማዎችን' ለመምታት የሚያስችላትን እጅግ የዘመኑ ሮኬቶችን እንደምትልክ አሳውቀዋል።
➡️ #ሶማሊያ ፦ ወደ ባይዶዋ እንደሚሄዱ የተነገረላቸው አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ፕሬዝዳንት ከሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ግዛት መሪ አብዲአዚዝ ሀሰን ሞሀመድ እና ከባህላዊ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። ፕሬዜዳንቱ ወደ ባይዶዋ ያደረጉት ጉዞ ዳግም ፕሬዜዳንት ሆነው ከተመረጡ በኃላ የመጀመሪያቸው ነው።
#ቲአርቲ #ቢቢሲ #ፍራንስ24 #ሲጂቲኤን