TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#MayDay በዓለም ለ133ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ47ኛ ጊዜ የሚከበረውን የላብ አደሮች ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል። የሠራተኞች መብት አለመጠበቅ፣ የኑሮ ውድነትና ሰራተኞች የሚያገኙት ደሞዝ አለመጣጣም፣ ከጊዜ ወደጊዜ ግጭቶች መከሰት ፣ ዲሞክራሲ በፈተና ውስጥ መግባትና ሌሎች ችግሮች እንዲፈቱ ተጠይቋል። በዕለቱ ከተላለፉት መልዕክቶች ፦ 🪧 " ሠራተኛው መልካም አስተዳደርን…
" መንግስት የገባውን ቃል አያጥፍም " - ወ/ሮ ሙፍሪያት ካሚል

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፍሪያት ካሚል ፥ መንግሥት የሠራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ለመወሰን የገባውን ቃል እንደማያጥፍ ገልፀዋል።

ይህን የገለፁት ትላንት በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የዓለም የላብ አደሮች ቀን (ሜይዴይ) ሲከበር ባሰሙት ንግግር ነው።

" መንግሥት የሠራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ለመወሰን የገባውን ቃል አያጥፍም፡፡ ነገር ግን ጉዳዩ በጥልቅ ጥናት ታይቶ ሊሠራ የሚገባው ስለሆነ ጥናቶች እየተከናወኑ ነው " ብለዋል፡፡

ወ/ሮ ሙፍሪያት ፤ እየተሠሩ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እንደተጠ ናቀቁ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ እንሸጋገራለን ብለዋል።

" የሠራተኛውን ጥያቄ ለመመለስ መንግሥት ወደ ኋላ አይልም ፤ ሠራተኛው የተለያዩ ጥያቄዎች እንዳሉት እናውቃለን፡፡ ጥያቄዎቹን ለመመለስ ከሠራተኞች እና ከአሠሪዎች ኮንፌዴሬሽኖች ጋር የበለጠ ተቀራርበን እንሠራለን " ሲሉ ተደምጠዋል።

በሠራተኛው እና በኮንፌዴሬሽኑ በኩል የተጠየቁ ጥያቄዎች አብዛኞቹ ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት የሚፈልጉ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ኢፕድ

@tikvahethiopia
#ቴስት_ኦፍ_አዲስ

ቴስት ኦፍ አዲስ የምግብ ፌስቲቫል ተመልስዋል::የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ ግንቦት 14 እና 15 በ ግዮን ሆቴል በሚዘጋጀው በዚህ አስደሳችና አዝናኝ ፕሮግራም ላይ በከተማችን የሚገኙ የተለያዩ ሬስቶራንቶች እና ኬክ ቤቶች ተወዳጅ የሆኑ ጣፋጭ ምግቦቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፤  የጊዜያችን ምርጥ የባንድ እና የዲጄ ሙዚቃዎችን እያጣጣሙ ከቤተሰብዎ ጋር ይዝናኑ:: የመግቢያ ዋጋ 200 ብር:: 

አዘጋጅ ብሉ ሚድያ
@TasteofAddisFams
ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ ሚያዚያ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ዓ.ም በአዲስ አበባ የዒድ ሶላት ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቀ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት፡-

🛣 ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ ስታዲዩም የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባቢ፤

🛣 ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ፤

🛣 ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት፤

🛣 ከፒያሣ አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቸርችር ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ፤

🛣 ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ ወደ ስታዲየም የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፤

🛣 ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ፤

🛣 ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀኛ፤

🛣 ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፤

🛣 ከባሻ ወልዴ ችሎት በኦርማ ጋራዥ ወደ ፍል ውኋ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት፤

🛣 ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ፤

🛣 ከጦር ኃይሎች፣ ልደታ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ፤

🛣 ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ መንገዱ የሚዘጋ ሲሆን

ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ከሳሪስ እና ከጎተራ ወደ አዲስ አበባ ስታዲዩም ለሚመጡ ከባድ ተሸከርካሪዎች መንገዱ አጎና ሲኒማ ጋር የሚዘጋ ይሆናል፡፡

ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ነገ የሚከበረውን 1 ሺህ 443ኛው ዓመተ ሂጅራ የዒድ አል-ፈጥር በዓልን በማስመልከት ነገ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ መድፍ የሚተኮስ መሆኑን መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tikvahethiopia
" ዒድ አልፈጥር "

ውድ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለ1443ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ። ዒድ ሙባረክ !

በዓሉ የሰላም ፣ የአንድነት ፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሆንልን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስታከብሩ የተቸገሩት ፣ ያጡትን ፣ በድርቅ ምክንያት በችግር ላይ የወደቁትን ፤ በሰላም እጦት የሚሰቃዩትን ፣ በጦርነት እና በግጭት ወገን ዘመዶቻቸውን ከጎናቸው የተነጠቁትን ፣ ከሞቀው ቄያቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የቀሩትን ወገኖቻችን በማሰብ ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።

ሀገራችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን!!
መልካም በዓል !

#TikvahFamily ❤️

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ የዒድ አልፈጥር በዓል !

ዛሬ ጥዋት በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ላይ የዒድ ሶላት ተከናውኖ ነበር። አ/አ ከነበረው ችግር ውጭ ሁሉም ቦታ በሰላም ነው የተካሄደው።

በጎንደር ግን፤ ሕዝበ ሙስሊሙ ለሶላት አደባባይ ሳይወጣ ቀርቷል፤ ይህ የሆነው የደኅንነት ስጋቶች በመኖራቸው የጎንደር ከተማ ኡለማ ም/ቤት ሕዝበ ሙስሊሙ በየመኖሪያ ቤቱ በዓሉን እንዲያሳልፍ ጥሪ በማስተላለፉ ነው።

በአ/አ የነበረው ዒድ ሶላት እጅግ ከፍተኛ ምእመን የተገኘበት ነበር።

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እንደገለፁት፤ የዛሬው መርሃግብር አብዛኛው በድምቀት የተጠናቀቀ ሲሆን ሰላቱ እንደተጀመረ በሀያት ሪኤጀንሲ ሆቴል በኩል በተተኮሰ አስለቃሽ ጭስ እና ይህ ተከትሎ በተፈጠረ ግርግር ከዚያም በተከታታይ በተተኮሰ አስለቃሽ ጭስና የህዝብ ግፊት ሰላት ተረብሾ፣ ሰጋጁም ላይ ጉዳት አጋጥሟል።

ግርግሩ በተስፋፋበቸው አካባቢዎችም ጉዳት ደርሷል።

ሁኔታውን በተመለከተ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በዒድ ሰላት ወቅት የተከሰተው ክስተት በክርስቲያኑና በሙስሊሙ መካከል የተፈጠረ እንዳልሆነ አረጋግጧል።

አንዳንድ አካላት ችግሩን ከመንግስት ጋር ለመሰያያዝ መሞከራቸውም የተሳሰተ ነው ብሏል።

የተፈጠረው ችግር ምን እንደሆነ በስፍራው የነበሩ በጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎች እንደገለፁት በአንድ ፌደራል ፓሊስ ድንገት በተተኮሰ አስለቃሽ ጭስ ምክንያት ግርግር ተፈጥሮ ጉዳት እንደደረሰ ነው።

የም/ቤቱ መረጃ telegra.ph/AA-05-02-5

የአዲስ አበባ ፖሊስ በበኩሉ፤ በኢድ ሶላት ላይ ጥቂት ግለሰቦች ባስነሱት ረብሻ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ነው የገለፀው ፤ ፖሊስ የረብሻውን መነሻና ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሌሎች ጉዳዮችን ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

የፎቶ ባለቤት ፦ አቤል ጋሻው

@tikvahethiopia
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል የቀጠሮ እስረኛ የነበሩት ሜ/ጄነራል ገ/መድህን ፍቃዱ (ወዲ ነጮ) በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል።

በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ይፋ በተደረገው መረጃ ሜ/ጄነራል ገ/መድህን ከረፋዱ 3፡30 አካባቢ በቤተሰብ ጥየቃ ሠዓት ባለቤታቸው እና ልጃቸው አስጠርተዋቸው እያወሩ እያለ በድንገት ይወድቃሉ።

ወዲያውኑ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ህክምና ቦታ ቢወሰዱም ህይታቸው ማለፉ ነው የተገለፀው።

ለሞመታቸው ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ አስከሬናቸው ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ህክምና ተቋም የተላከ ሲሆን ውጤቱ እንደታወቀ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ዛየን_ፊዚዮቴራፒ

ዛየን የፊዚዮቴራፒ ህክምና ልዩ ክሊኒክ
በማንኛውም የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎች ለሚያጋጥማቸው የጡንቻ ፣ የነርቭ ፣ የጅማት ፣ የአጥንት ፣ የመገጣጠሚያ ህመሞች ፣ ለፊት መጣመም ፣ ለራሰ ምታት ፣ ለስትሮክ ፣ ለዲስክ መንሸራትና ተመሳሳይ ችግሮች ብቁ ባለሙያዎችንና ዘመናዊ የህክምና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የፊዚዮቴራፒ ህክምና አገልግሎት እንሰጣለን።

4ኪሎ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ፊት ለፊት ቅዱስ ፕላዛ ህንፃ ፡- 0969696924/ 0111265926
ፌስቡክ : WWW.FACEBOOK.COM/ZIONPHYSIOTHERAPY/
ቴሌግራም @zionclinic2012
#Tigray

• በሚያዚያ ወር 170 ተሽከርካሪዎች ትግራይ በሰላም ደርሰዋል።

• እስካሁን 158 ተሽከርካሪዎች ተመልሰዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፤ ከትላንት በስቲያ ተጨማሪ 27 ተሽከርካሪዎች የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ትግራይ፣ መቐለ ማድረሳቸውን ገልጿል።

ድርጅቱ ፥ በሚያዚያ ወር ውስጥ 170 ተሽከርካሪዎች መግባታቸውን የገለፀ ሲሆን ይህም በምግብ ተደራሽ ለማድረግ ካቀደው ህዝብ ውስጥ 8 በመቶ የሚሸፍን መሆኑን አመልክቷል።

ዛሬም የሰብዓዊ ድጋፍ የያዘ ኮንቮይ ወደ ትግራይ ጉዞ እንደሚጀምር አሳውቋል።

ሚያዚያ ወር ላይ ትግራይ ከገቡ 170 ተሽከርካሪዎች መካከል ይህ መረጃ ክፋ እስከሆነበት ሰዓት ድረስ 158 ተሽከርካሪዎች መመለሳቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ የዒድ አልፈጥር በዓል ! ዛሬ ጥዋት በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ላይ የዒድ ሶላት ተከናውኖ ነበር። አ/አ ከነበረው ችግር ውጭ ሁሉም ቦታ በሰላም ነው የተካሄደው። በጎንደር ግን፤ ሕዝበ ሙስሊሙ ለሶላት አደባባይ ሳይወጣ ቀርቷል፤ ይህ የሆነው የደኅንነት ስጋቶች በመኖራቸው የጎንደር ከተማ ኡለማ ም/ቤት ሕዝበ ሙስሊሙ በየመኖሪያ ቤቱ በዓሉን እንዲያሳልፍ ጥሪ በማስተላለፉ ነው። በአ/አ የነበረው…
#AddisAbaba

የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ፤ በአዲስ አበባ በሁከትና ብጥብጥ በግንባር ቀደምትነት ተሳትፈዋል ያላቸውን 76 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ግብረ ኃይሉ ፤ " ከሀይማኖታዊ ሥርዓቱ ውጭ ሌላ የሁከትና ብጥብጥ ዓላማ ያላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ለብጥብጥ መነሻ በማይሆን ምክንያት ከስታዲየም ውጭ በተለምዶ ' የቀይ ሽብር ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም ' አጠገብ ሆነው ባስነሱት ረብሻና ብጥብጥ በጸጥታ ኃይሎችና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል " ሲል አሳውቋል።

በዚህም 76 ግንባር ቀደም የሆኑ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ግብረ ኃይሉ የሁከት እና ግርግሩ መንስኤ እያጣራ መሆኑን ገልጾ ውጤቱን ለህዝብ ይፋ አድርጋለሁ ብሏል።

ግብረ ኃይሉ ፤ የተፈጠረውን ችግር መስዋዕትነት ከፍሎ መቆጣጠር መቻሉን ገልፆ " በበዓሉ ታዳሚዎች ላይ የሞትም ሆነ የአካል ጉዳት አልደረሰም " ብሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Addis-Ababa-05-02

@tikvahethiopia