TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ ፦ የጸሎተ ሐሙስ ሥነ ሥርዓት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በከፊል።

የጸሎተ ሐሙስ የተለያዩ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓቶች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተክርስቲያናት እና ገዳማት ተካሂዷል።

በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በነበረው መርሐ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን ጨምሮ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት እና ምዕመናን ተገኝተው ነበር።

ፎቶ ፦ ዲ.ን ሙሉዓለም ዐሥራት (EOTC TV)

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኤርትራ ዜጎች ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ መንግስት አለመከልከሉን አስታውቋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ " የኤርትራ ዜጎች ከኢትዮጵያ እንዳይጡ ይከለከላሉ " በሚል ለቀርበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ዲና መንግስት ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ ተከልክለዋል ስለተባሉት እና የኤርትራ ፓስፖርት የያዙ የውጭ ሀገር ቪዛ ያላቸውን ጉዳይ በጥንቃቄ ይመረምራል ሲሉ ተናግረዋል።

በኤርትራውያን በኩል የሚነሳ ቅሬታ ሚኒሰቴር መ/ቤታቸው በተለያየ መልኩ እንደሚሰማ ያነሱት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ " ጉዳዩ በዋናነት ከህግ፣ ከሰነድ እንዲሁም ከደህንነት ጋር የሚያያዝ በመሆኑ መንግስት ነገሮችን በተጠና መልክ ለመስራት እየጣረ ነው " ብለዋል።

" የሀገሪቱ ህግ እና ሂደቶች በሚጣረስ መልኩ ኢትዮጵያን ለቆ ለመውጣትና የመቻኮል (እዚህ ሀገር ካልሄድን ወዘተረፈ የሚሉ) ሁኔታዎች ቢኖሩም፤ ሁሉም ነገር ግን በህጉ መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል " ሲሉ አምባሳደር ዲና አሳውቀዋል።

የኢፌድሪ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አገልግሎት መረጃ እንደሚያመለክተው አሁን ላይ ፦

👉 324 ሺህ የደቡብ ሱዳን ፣
👉 217 ሺህ የሚገመቱ የኤርትራ፣
👉 200 ሺህ የሶማልያ ፣
👉 67 ሺህ የሱዳን
👉 5 ሺህ የኬንያ ስደተኞች በኢትዮጵያ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ 1 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ስደተኞችን በማስተናገድ በአፍሪካ ከኡጋንዳ እና ሱዳን ቀጥላ በ3ኛ ደረጃ ተቀምጣለች።

ምንጭ፦ አልዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
#Russia

ሩስያ ተጨማሪ አሜሪካውያንን ' ወደ ሀገሬ ድርሽ እንዳይሉ ስትል " እገዳ ጣለች።

ሩስያ በዛሬው ዕለት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ፣ የፌስቡክ (Facebook) መስራች ማርክ ዙከርበርግን ጨምሮ 29 የአሜሪካ ባለስልጣናት ፣ የንግድ ሰዎች እና ጋዜጠኞች ወደ ሀገሯ እንዳይደርሱ እገዳ ጥላባቸዋለች።

በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ በተደረገው የማዕቀብ ዝርዝር ከምክትል ፕሬዜዳንት ካማላ ሃሪስ እና ከፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ በተጨማሪ ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ካትሊን ሂክስ እና የፔንታጎን ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ ይገኙበታል።

ሚኒስቴሩ ይፋ ባደረገው ዝርዝር ላይ ፤ " እነዚህ ግለሰቦች ላልተወሰነ ጊዜ ወደ ሩሲያ ፌዴሬሽን እንዳይገቡ ተከልክለዋል " ብሏል።

@tikvahethiopia
#USA #ETHIOPIA

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 313 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እየሰጠች መሆኑ አስታውቃለች።

አሜሪካ ፤ በ #USAID በኩል በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ግጭት ሳቢያ የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት ወደ 313 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ተጨማሪ እርዳታ እየሰጠች መሆኑን ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በአፋር ፣ በአማራና በትግራይ ክልሎች እየተካሄድ ያለው ግጭት ወደ 9 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ያጋላጠቸው ሲሆን ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ እንዲፈናቀሉ ማድረጉንም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

በትግራይ ክልል ብቻ 90 % የሚሆነው የክልሉ ህዝብ እርዳታ የሚሻ ነው ያለው መግለጫው በ3ቱም ክልሎች ወደ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በሚቀጥለው ሰኔ ከፍተኛ ረሀብ ለመሰለ አደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ ብሏል።

ዛሬ ይፋ የተደረገው አዲሱ እርዳታ ወደ 7 ሚሊዮን ለሚጠጉ ሰዎች አስቸኳይና የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ የሚያደርግ ሲሆን የማህበረሰባዊ ጤና ተቋማትን ለማጠናከር የሚውል መሆኑም ድርጅቱ መግለፁን ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#COVID19Ethiopia - Health Worker Training Platform

ኮቪድ-19 ሰልጠና ሰርተፍኬትዎን አሁኑኑ በሰልክዎ ባለው መተግበሪያ መውሰድ ይችላሉ።

የኮቪድ-19 ስልጠና ወስደው ሰርተፍኬትዎን መውሰድ እንዴት እንደሚችሉ ለማወቅ ከላይ ቪድዮውን ይመልከቱ።

https://bit.ly/3apv5J2 ይህንን ማስፈንጠርያ በመጫን አፕልኬሽኑን ያዘምኑ።
" ስቅለት "

በክርስትና አስተምሮ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለ በደል ያለ ጥፋት ንጹሕ እና ጻድቅ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰቀሉበት ዕለት ነው።

ዕለቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ዂሉ መድኀኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የሚታሰብበት ታላቅ ቀን ነው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በስግደትና በጾም የሚታሰብ ሲሆን በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትም በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ታስቦ ይውላል፡፡

በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከንጋታው ጀምሮ እስከ ማምሻው በዕለቱ የተፈጸሙትን ክስተቶች በሰዓት ከፍላ በልዩ መንፈሳዊ ሥርዓትና በስግደት ታከብረዋለች ፦

ዓርብ ጠዋት

ዓርብ ጠዋት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በፍርድ አደባባይ መቆሙ ይታሰባል። የካህናት አለቆችና ሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት በኢየሱስ ላይ ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት ፥ ለገዢው ለጰንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።

በ3 ሰዓት

ጲላጦስ በወቅቱ በነበረው ሕዝብ ግፊት መሠረት ወንጀለኛውን በርባንን ከእስር አስፈትቶ በምትኩ ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠበት፤ አካሉ እስኪያልቅም 6,666 የገረፉት ከሊቶስጥራ - ቀራኒዮ እርጥብ መስቀል አሸክመው የወሰዱበት ነው።

በ6 ሰዓት

ኢየሱስ ክርስቶስን እጆቹን እና እግሮቹን ቸንክረው በቀራንዮ ጎልጎታ ተራራ በ2 ወንበዴዎች መካከል የተሰቀለበት ነው።

በ9 ሰዓት

በእምነቱ አስተምሮ ይህ ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ከሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ የለየበት ወደ ሲዖል ወርዶም የታሠሩትን ሁሉ ያስፈታበት ነው።

11 ሰዓት

ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብር እና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር የቀበሩበት ነው።

@tikvahethiopia
#በዓላትና_ትራንስፖርት

በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ቅሮታን እያስነሳ መፍትሔ ያላገኘው የበዓል ሰሞን የትራንስፖርት አገልግሎት አሁንም እንደቀጠለ ነው።

መጪው የትንሳኤ በዓልን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት ትራንስፖርት የለም በማለት በደላላ ትኬት የመሸጥ እና ከመደበኛ ዋጋ እጥፍ ወይም ከፍ አድርገው እየሸጡ ይገኛሉ።

በተላይ ሰሞኑን በርካታ ሰዎች ከአዲስአበባ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በዓል ለማክበር ወደ ቤተሰብ ጋር ለመሄድ በዚህ የትራንስፖርት ዘርፍ ብልሹ አሰራር ምክንያት እየተጉላሉ እና ለከፍተኛ ወጭ እየተዳረጉ ይገኛሉ።

በዚህ በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ በሚታየው ብልሹ አሰራር በስምሪት ላይ የሚሰሩ የተለያዩ አካላት ፣ አንድ አንድ ብልሹ ስነምግባር ያላቸው የትራፊክ ፖሊሶች እና ደላሎች በተጨማሪም የትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ተሳታፊ መሆናቸው ችግሩን መፍትሔ አልባ አድርጎታል።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ችግሩን ለመፍታት የመፍትሔ ስራ በመስራት ለማስተካከል ቢሰሩ መልካም ነው ብለዋል ትራንስፖርት ለመጠቀም በመጠበቅ ላይ ያሉ ተሳፋሪዎች።

#ጋዜጠኛ_ነፃነት_ጌታቸው

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT