TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA
የኢትዮጵያ መንግስት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ የሚገኘው ‘’ የሩሲያ ኤምባሲ የውትድርና ምልመላ ቅጥር አውጥቷል ’’ የሚል መሰረተ ቢስ ወሬን ኤምባሲው ውድቅ ማድረጉን እንደሚደግፍ አሳውቋል።
ኤምባሲው ምንም አይነት የቅጥር ማመልከቻ እንደማይቀበል እና በፈረንጆቹ 1961 የቪየና የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ስምምነትን እንደሚያከብር ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት ከኤምባሲው ጋር በመሰል አግባብ በሌላቸው የቅጥር ጉዳዮች ላይ ተስማምቶ ከተገኘ የቪየና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ስምምነትን የሚጥስ ሲሆን ፥ ይህም የዲፕሎማቲክ ሚሲዮንን ተግባር እንደሚጻረር ይታወቃል።
ስምምነት ከመጣሱም ባሻገር የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች የአገርን ህግና ደንብ አለማክበር እንደሆነም ነው የተመለከተው፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ኤምባሲው ለወሰደው ፈጣን እርምጃ አድናቆቱን ገልጿል።
ምንጭ ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tikvahethiopia

የበዓል ገበያው እንዴት ይዟችኃል ?
በየጊዜው እየታየ ያለው የዋጋ ንረት የበዓሉን ድባብ እንደሚያቀዘቅዘው እሙን ነው።
ምን ያህሎቻችን ባለው የዋጋ ንረት ሳቢያ ኑሮ ፈተና እንደሆነብን እናውቀዋል፤ ምንም ያህል የዋጋ ንረቱ በአስፈሪ ሁኔታ ቢያሻቅብም በዓል ነውና በአቅም ሸምቶ ለማሳለፍ የሚሮጠው ብዙ ነው።
የዘንድሮው ገበያ ግን ከአምናውም በእጅጉ የተለየ ነው።
በተለይም በሀገራችን አንዳድን አካባቢዎች የእንስሳት ግብይት ዋጋ የማይቀመሥ ሆኗል። በርካቶችም ባለው የዋጋ ውድነት ሳቢያ ገዝቶ ከቤተሰብ ጋር ተደስቶ በዐል ለማሳለፍ ፈተና ሆኖባቸዋል።
ለአብነት ዛሬ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ ያለውን ውድነት እንመልከት ፤ በባለፈው ዓመት በበዓል ገበያ 20 ሺህ ብር ይሸጥ የነበረ በሬ በዘንድሮው ዓመት ከእጥፍ በላይ ጨምሮ በ45 ሺህ ብር ተሽጧል።
በባለፈው ዓመት የበዓል ገበያ አንደኛ ደረጃ በሬ 42 ሺህ 667 ብር የተሸጠ ሲሆን ዘንድሮው የበዓል ዋዜማ ገበያ በአማካኝ 59 ሺ 333 ብር ተሸጧል። የ16 ሺህ 666 ብር ጭማሪ አሳይቷል።
የበግ ሙክትን ባለፈው ዓመት የበዓል ገበያ 4 ሺህ 766 ብር የተሸጠ ሲሆን በዘንድሮው ዓመት የበዓል ዋዜማ ገበያ 8 ሺህ ብር ተሸጧል። ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በበግ የ3 ሺህ 234 ብር ጭማሪ አሳይቷል።
የደጀን ወረዳ ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት ፤ የዋጋ ጭማሪው መንስኤ የእንስሳት መኖ እጥረት እንደሆነ ማስረዳቱን ከደጀን ወረዳ ኮሚኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ውድ ቤተሰቦቻችን በአካባቢያችሁ ያለው የበዓል ገበያው እንዴት ይዟችኃል ? ዘይቱ ፣ እንቁላሉ ፣ ዶሮው ፣ በጉ ፣በሬው ስንት እየተባለ ነው - በ @tikvahethiopiaBOT መልዕክታችሁ አኑሩ።

#BalderasParty
አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም የባልደራስ አመራሮች አርባ ምንጭ ከተማ መታሰራቸውን ፓርቲው አስታወቀ።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ፕሬዝዳንቱ አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አመራሮች በፖሊስ እንደታሰሩበት አስታውቋል።
ፓርቲው አመራሮቹ የታሰሩበት አርባ ምንጭ ከተማ መሆኑን ገልጿል።
አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም የፓርቲው ልዑካን ዛሬ ወደ አርባምንጭ ያቀኑ ሲሆን ወደ አርባ ምንጭ የሄደቱ በደቡብ ክልል የፓርቲውን የሀገር አቀፍ ፊርማ ንቅናቄ ለማስጀመር እንደሆነ ተገልጿል።
ፓርቲው የፊርማ አሰባሰቡን ንቅናቄ ለማስጀመር በአርባ ምንጨ እና በወላይታ ሶዶ ህዝባዊ ስብሰባዎች ለማድረግ ጠይቆ ከተፈቀደ ቦኃላ፣ " ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው " በሚል ስብሰባዎቹ እንዳይደረጉ እንደተከለከሉበት አስረድቷል።
ከዚህ በኃላ ነው ፓርቲው ፕሬዜዳንቱን ጨምሮ ወደ አርባ ምንጭ የሄዱት ልዑካን በፖሊስ መታሰራቸውን ያሳወቀው።
ባልደራስ እስሩ ያለምንም ምክንያት የተፈፀመ ነው ብሏል።

#IMF
ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ፥ የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገትን ዝግ እንደሚያደርገው ትላንት ይፋ ባደረገው ሪፖርት አሳውቋል።
IMF ፤ የዓለም ምጣኔ ሀብት እ.አ.አ. ባለፈው 2021 በ6.1 ከመቶ ማደጉን አስታውሶ ዘንድሮ ግን ዕድገት የሚኖረው በ3.6 % ብቻ እንደሚሆን ተንብዩዋል።
" ጦርነቱ በምጣኔ ሀብት ላይ ያሳደረው አንድምታ ራቅ እያለም አድማሱንም እያሰፋ ነው " ሲል ገልጿል።
IMF የውጭ ንግድ የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎችን በማስተጓጎል እንዲሁም የነዳጅ እና የምግብ ዋጋ ንረት በማስከተል የዓለም ኢኮኖሚ ወደ አሉታዊ አቅጣጫ እንዲያመራ አድርጓል ሲል አመልክቷል።
ዋናው የIMF ኢኮኖሚስት ፒየር ኦልቪዬ ጉሪንቻስ በጻፉት የዓለም ኢኮኖሚ ትንበያ ሪፖርቱ መግቢያ ፦
" በዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ምክንያት ተንኮታኩቶ የነበረው የዓለም ኢኮኖሚ ጠንከር ብሎ ሊያንሰራራ ተቃርቦ ነበር።
ጦርነቱ መጣና በቅርብ ጊዚያት የተገኙ አብዛኞቹን ስኬቶች ጠራርጎ የሚያጠፋ ሁኔታ ፈጠረ።" ሲሉ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ፤ IMF ከዚህ ቀደም ለዓለም አገራት በሰራው ትንበያ የገደፈውን የኢትዮጵያን ምጣኔ ሐብት የተመለከቱ መረጃዎች በትላንት ሪፖርቱ አካቷል።
እኤአ 2022 የኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብት 3.8 በመቶ ያድጋል ሲል ተንብዩዋል። በ2023 የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ 5.7 በመቶ ያድጋልም ብሏል።
በሸማቾች የዋጋ ግሽበት መለኪያ (Consumer Prices) ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ 26.8 በመቶ የነበረው የሸቀጦች ዋጋ ንረት በተያዘው ዓመት ወደ 34.5 በመቶ እንደሚደርስ የIMF ትንበያ ያሳያል። ይኸ እኤአ 2023 በአንጻሩ 30.5 በመቶ ይሆናል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/IMF-04-20 (VOA, DW, IMF)

#BalderasParty አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም የባልደራስ አመራሮች አርባ ምንጭ ከተማ መታሰራቸውን ፓርቲው አስታወቀ። ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ፕሬዝዳንቱ አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አመራሮች በፖሊስ እንደታሰሩበት አስታውቋል። ፓርቲው አመራሮቹ የታሰሩበት አርባ ምንጭ ከተማ መሆኑን ገልጿል። አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎችም የፓርቲው ልዑካን…
#Update
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የፓርቲውን ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮልን ጨምሮ ሌሎች አባላት በአርባ ምንጭ፤ ሴቻ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣብያ ታስረው እንደሚገኙ አሳውቋል።
ፓርቲው አመራሮቹ የታሰሩት ዛሬ ምሽት ካረፉበት ሆቴል ውስጥ በየመኝታ ክፍላቸው በነበሩት ጊዜ መሆኑን ገልጿል።
በአሁን ጊዜ ፕሬዚደንቱ አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ የድርጅቱ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው እና የካሜራ ባለሙያው ሱራፌል አንዳርጌ እስር ላይ ይገኛሉ ሲል አስረድቷል።
ፓርቲው ፤ በአርባ ምንጭ ከተማ የመንግሥት ደህንነት መሥሪያ ቤት ባልደረባ እና የገዢው ፓርቲ ካቢኔ አባል መሆናቸውን ገለፁ ያላቸው ግለሰብ " የምናስራችሁ እንቅስቃሴያችሁ ስላልተመቸን ነው" ሲሉ መናገራቸውን ጠቁሟል።
ፓርቲው የግለሰቡን ስም ያልጠቀሰ ሲሆን ነገር ግን በእኚሁ ግለሰብ ትዕዛዝ በ3 'ፒክ አፕ' መኪኖችና ቁጥራቸው ባልታወቀ ሞተር ብስክሌቶች የመጡ በርካታ ፖሊሶች እነ አቶ እስክንድር ያረፉባቸውን የሆቴል ክፍሎች ገለባብጠው በርብረዋል ብሏል።
በብርበራው ያገኟቸውን የአዳዲስ የፓርቲ አባላት ማስፈረሚያ ቅፆችንም ወስደዋል ሲል ገልጿል።
እነ አቶ እስክንድር ነጋ በአሁኑ ጊዜ በአርባ ምንጭ ሴቻ ክ/ከተማ ፖሊስ ጣብያ ውስጥ ይገኛሉ ብሏል።
ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ ፤ ለእነ አቶ እስክንድር ነጋ የታክሲ አገልግሎት ሲሰጡ የዋሉ 2 ወጣቶች መታሰራቸውን ፓርቲው አመልክቷል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#COVID19Ethiopia - Health Worker Training Platform
ኮቪድ-19 ሰልጠና ሰርተፍኬትዎን አሁኑኑ በሰልክዎ ባለው መተግበሪያ መውሰድ ይችላሉ።
የኮቪድ-19 ስልጠና ወስደው ሰርተፍኬትዎን መውሰድ እንዴት እንደሚችሉ ለማወቅ ከላይ ቪድዮውን ይመልከቱ።
https://bit.ly/3apv5J2 ይህንን ማስፈንጠርያ በመጫን አፕልኬሽኑን ያዘምኑ።

#Update ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የፓርቲውን ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮልን ጨምሮ ሌሎች አባላት በአርባ ምንጭ፤ ሴቻ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣብያ ታስረው እንደሚገኙ አሳውቋል። ፓርቲው አመራሮቹ የታሰሩት ዛሬ ምሽት ካረፉበት ሆቴል ውስጥ በየመኝታ ክፍላቸው በነበሩት ጊዜ መሆኑን ገልጿል። በአሁን ጊዜ ፕሬዚደንቱ አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ የፓርቲው የአደረጃጀት…
#Update
የባልደራስ አመራሮች ተፈቱ።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) በእስር ላይ የነበሩት አመራሮቹና ልዑካን ፣ ከእስር መፈታታቸው አሳውቋል።
እስሩ አለአግባብ የተፈፀመው ነው ያለው ባልደራስ ፤ በአሁን ሰዓት አመራሮቹ እና ልዑካኑ ጉዟቸውን ለማድረግ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ሄደዋል ሲል አሳውቋል።

" ... በጦርነቱ ሳቢያ የተከሰተው የምግብ ቀውስ ሰብአዊ ጥፋት ያስከትላል " - ዓለም ባንክ
በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት በተከሰተው የምግብ ቀውስ ዓለም " የሰብዓዊ ጥፋት " እያጋጠማት ነው ሲሉ የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ ተናግረዋል።
ማልፓስ ይህን የተናገሩት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው።
ማልፓስ ፤ ቀውሱ ከቀጠለ የምግብ ዋጋ ንረት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ወደ ድህነት እንደሚገፋና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንደሚያስከትል አስጠንቅቀዋል።
" ይህ የሰብዓዊ ጥፋት ነው። የተመጣጠነ ምግብ እየቀነሰ ይሄዳል። ምንም ማድረግ ለማይችሉ መንግስታት የፖለቲካ ፈተና ይሆናል። መንስኤ ባይሆንም የዋጋ መናር ያጋጥማቸዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
የዓለም ባንክ የምግብ ዋጋ በ37 በመቶ ሊጨምር እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል።
ይህም " ለድሆች ከፍተኛ የሚባል " ሲሆን " ትንሽ እንዲመገቡ እና እንደ ትምህርት ቤት ላሉት የሚኖራቸውን ወጪ ያሳንሳል። በእውነቱ ይህ ፍትሃዊ ያልሆነ ቀውስ ነው። በጣም ድሃ የሆኑት ላይ የበለጠ ጫናው ያርፋል። ይህ በኮቪድ ወቅት ተመሳሳይ ነበር።
ዴቪድ ፥ ማልፓስ የዋጋ ንረቱ ሰፊና ጥልቅ ነው ያሉ ሲሆን " በተለያዩ ዓይነት ዘይቶችና እህሎች ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ነው። የስንዴ ዋጋ መናር ደግሞ እንደበቆሎ ያሉ ሰብሎች ዋጋ እንዲንር ያደርጋል" ብለዋል።
" ዓለም ላይ ሁሉንም ሰው ለመመገብ የሚያስችል በቂ ምግብ ነበረ። በዓለም አቀፍ ደረጃ የነበሩ የምግብ ክምችቶች በታሪክ ደረጃ ከፍተኛውን ደረጃ ይዞ ነበር።
ነገር ግን ምግቡን ወደሚፈለገው ቦታ ለማድረስ የመጋራት ወይም የሽያጭ ሂደት ሊኖር ይገባል " ብለዋል።
ያንብቡ : telegra.ph/BBC-04-21

#Update የባልደራስ አመራሮች ተፈቱ። ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) በእስር ላይ የነበሩት አመራሮቹና ልዑካን ፣ ከእስር መፈታታቸው አሳውቋል። እስሩ አለአግባብ የተፈፀመው ነው ያለው ባልደራስ ፤ በአሁን ሰዓት አመራሮቹ እና ልዑካኑ ጉዟቸውን ለማድረግ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ሄደዋል ሲል አሳውቋል። @tikvahethiopia
" ለጠየቅናቸው ለጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በስሜታዊነት ከጸጥታ አባላት ጋር ወደ ተካረረ አለመግባባት በማምራታችው ልናስራቸው ችለናል " - አቶ ኃይለሚካኤል ጉላንታ
የአርባ ምንጭ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኃይለሚካኤል ጉላንታ የባልደረስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደረስ) ፕሬዝደንት እና አመራሮች የታሰሩት " የከተማው የጸጥታ አካላት በማያውቁት ሁኔታ የከተማው ወጣቶችን ሲያስፈርሙ በመገኘታችው ነው " ማለታቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።
" እኔ ራሴ በሥፍራው ነበርኩ " ያሉት አቶ ኃ/ሚካኤል " እኔ የካቢኔ አባልና የጸጥታ ኃላፊ ነኝ። ቢያንስ የራሳችሁን ደህንነት እንድንጠብቅላችሁ እንኳን ከየትና ለምን እንደመጣችሁ አስረዱኝ ብዬ ጠይቄያቸዋለሁ። ይሁን እንጂ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በስሜታዊነት ከጸጥታ አባላቱ ጋር ወደ ተካረረ አለመግባባት በማምራታችው ልናስራቸው ችለናል። " ብለዋል።
ኃላፊው ፥ ዛሬ ጠዋት ቃል የተቀበሏቸው መሆኑን እና ቀሪውን ጉዳይ በህግ አግባብ እንደሚተይ ለሬድዮ ጣቢያው ገልፀዋል።
ፓርቲው ፥ " እስሩ ያለአግባብ የተፈፀመ መሆኑን ፤ የታሰሩትም ባረፉበት ሆቴል በየመኝታ ክፍላቸው እያሉ መሆኑን እንዲሁም የከተማው የደህንነት መስሪያ ቤት ባልደረባና የገዥው ፓርቲ ካቢኔ አባል ' የምናስራችሁ እንቅስቃሴያችሁ ስላልተመቸን ነው ' ሲሉ መናገራቸውን " ገልፆ ነበር።
ትላንት በሴቻ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ታስረው ያደሩት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ከደቂቃዎች በፊት ከእስር ተፈተው ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ማቅናታቸውን ፓርቲው መግለፁ ይታወቃል።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የደቡብ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ተፈሪ አባተ ፦
" በሳውላ በውሃ ሃብት ልማት ፅ/ ቤት ውስጥ የውሃ ተቋም ግንባታ እንዲደረግ ከክልሉ የተላከውን ሃብት በመውሰድ የፕሮጀክት ማናጀር/ የውሃ ፕሮጀክት ፅ/ቤቱ ኃላፊ የራሱን ቤተሰብ ባለቤቱንና ሌሎች አካላት በማህበር እንደተደራጁ በማድረግ ከ5 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ሃብት መዝብሮ አካባቢውን በመልቀቅ አዲስ አበባ በመግባት የግል ድርጅት በማቋቋም ሲንቀሳቀስ የፋይናንስ ኦዲተሮች በመሄድ ኦዲት በማደርግ ለፍ/ቤት ቀርቦ ኦዲቱ ተገቢ መሆኑንና ጉድለቱ በመረጋገጡ ይህን በዋናነት የሰራው አካል በ9 ዓመት እና 50 ሺህ ብር ቅጣት፤ ባለቤቱ 8 ዓመት እና ተመሳሳይ የገንዘብ ቅጣት፤ ያስተባበሩ የመሩ ፣ አጠቃላይ ለብክነቱ ተዋናይ ናቸው የተባሉ የማናጅመንት አካላት እያንዳዳቸው 5 ዓመት የጎፋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ እንዲያሳልፍ ተደርጓል"
.
" በሃዲያ ዞን በአንዳንድ ወረዳዎች ላይ ከባንክ ጋር በመመሳጠር አንድ 6,500 ደሞዝተኛ የሆነ አንድ 0 በመጨመር 65,000 ብር ደሞዝ በባንክ ሲተላለፍለት እንደነበር እንዲሁም ደግሞ 130 ሺ ብር ደሞዝ በወር የሚከፈለው ሰው በማግኘት ግለሰቦቹንም ባንኩ ውስጥም የሚያስተዳድሩት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ገንዘቡ ተመላሽ እንዲሆን እያተሰራ ነው "
.
" በከምባታ ዞን ወረዳዎች ውስጥ በሌሉ ሰዎች ስም በገዛ ቤተሰብ ስም በባንክ አካውንት ደሞዝ በየወሩ የማስገባት ድርጊት በጥቆማ ተደርሶ ሰዎቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል "
.
" በሃላባ ዞን የፅህፈት ቤት ኃላፊ ከኃላፊነት ተነስተሻል ስትባል ወዲያው ባንክ ቤት በመሄድ ወደ ግለሰብ አካውን 700 ሺ ብር እንዲዞር በማድረግ ከባንክ ለማውጣት ስትል እርምጃ በመውሰድ፣ተባባሪዎችን በማሰር ሃብቱን ወደመንግስት ካዛና እንዲመለስ ተደርጓል "
📹40 MB

#አቢሲንያ_ባንክ
የባንካችን የስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ሳያሳስብዎት 24 ሰዓት ከ እሁድ እስከ እሁድ በመረጡት የቨርቹዋል ባንኪንግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመገኘት ገንዘብዎን ተቀማጭ ወይም ወጪ ማድረግ ይችላሉ።
የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth