TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር ሮበርት ሜንዴዝ የቀረበው S.3199 ረቂቅ ህግ ዛሬ ማለፉ ተሰምቷል። ኮሚቴው ፤ "በኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲ ለማበረታታ " በሚል ርዕስ የቀረበው S.3199 ላይ ተወያይቶ ማማሻያ ካደረገ በኃላ ነው ማሳለፉ የታወቀው። የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ኮሚቴ ተመልክቶ ያሳለፈው S.3199 ረቂቅ ህግ…
#USA
የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ ማዕቀቦችን ይጭናል የተባለውን ረቂቅ ህግ ለማዘግየት መስማማታቸውን ዘ አፍሪካን ሪፖርት ዘግቧል።
እንደ ዘ አፍሪካን ሪፖርት ዘገባ ይህ ውሳኔ የመጣው ከሳምንታት በፊት በሰብዓዊነት ላይ የተሰመሰረት ግጭት የማቆም ውሳኔ ላይ ተንተርሶ ሲሆን የተደረሰው ስምምነት ተግባር ላይ እስከዋለ ድረስ የኮንግረሱ አባላት ረቂቅ ህጎችን ለማዘግየት ተስማምተዋል።
ጦርነቱ የሚያገረሽ ከሆነ ግን እንዲዘገዩ የተደረጉት ረቂቅ ሕጎች እንደገና እንደሚንቀሳቀሱ ተሰምቷል።
አሁን ኮንግረሱ ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም የተወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ ረቂቅ ህጉ እንዲዘገይ የተስማማውን ውሳኔ በተመለከተ የኮሚቴው ህግ አውጪዎች ጉዳዩ ለኢትዮጵያ መንግስት፣ ለኤርትራ መንግስት፣ እና ለትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ግልፅ መልዕክት ያስተላለፈ ነው ፤ ረቂቅ ህጉ ለመጨረሻ ድምጽ አሰጣጥ ከቀረበ በፍጥነት ለማለፍ በቂ ድምጾች አሉ ብለዋል።
የአሜሪካ ኮንግረስንና ሴኔትን እንዲሁም የረቂቅ ሕጎችን ሂደት የሚከታተለው የGovTrack.us H.R. 6600 እና S.3199 ረቂቅ ህጎችን ስለመዘግየታቸው የሚገልጽ መረጃ ይፋ አላደረገም።
እ.ኤ.አ መጋቢት 29 የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ባለፈው አመት ህዳር ወር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቀውን S.3199 ረቂቅ ህግ (በኢትዮጵያ ሰላም እና ዴሞክራሲ ለማበረታታ) እንዳሳለፈው ይታወሳል።
NB : እንዲዘገይ ተደረገ ከተባለው ረቂቅ ህግ ጋር በተያያዘ በአንዳንድ ሚዲያዎች " ተቋረጠ " ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን በኢትዮጵያ የመረጃ አጣሪው ድረገፅ ኢትዮጵያ ቼክ አሳውቋል።
@tikvahethiopia

#Qatar2022
" ለኳታሩ 2022 የዓለም ዋንጫ በዳኝነት እንዳጫውት በፊፋ መመረጤን አላውቅም " - ባምላክ ተሰማ (ለቢቢሲ)
ዓለም አቀፍ ዳኛ ባምላክ ተሰማ "ለኳታሩ 2022 የዓለም ዋንጫ በዳኝነት እንዳጫውት በፊፋ መመረጤን አላውቅም" ሲል ተናግሯል።
ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ፥ " ምንም ነገር አላውቅም። በይፋ የደረሰኝ ነገር የለም " ብሏል።
ባምላክ ተሰማ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ እንዲዳኙ በFIFI ከተመረጡ 8 አፍሪካውያን ዳኞች መካከል አንዱ መሆኑን የምዕራብ አፍሪካ ድረ-ገጾች እና በሀገራችን የተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘግቡ ነበር።
" እንደዚህ ዓይነት መረጃ ከየት እንደሚመጣ አላውቅም" ያለው ኢንተርናሽናል አልቢትር ባምላክ ተሰማ ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ በፊፋ ስለመመረጡ የወጡ ዘገባዎችን መመልከቱን ግን ተናግሯል።
የተለያዩ ሚዲያዎች ባምላክ ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ መመረጡን የዘገቡት ፊፋን ዋቢ አድርገው ሲሆን በፊፋ ይፋዊ ድረ-ገጽ ላይ የተባለ ነገር የለም።
ባምላክ ፊፋ የዓለም ዋንጫን የሚመሩ ዳኞችን ማንነት ይፋ ለማድረግ ጊዜው የፈጠነ ነው ብሎ እንደሚያስብም ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ገልጿል።

Photo
#Update
እስር ላይ ከነበሩ ጋዜጠኞች መካከል እስካሁን ስይፈታ የቆየው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ዛሬ ረቡዕ ከእስር መፈታቱ ተገልጿል። [ https://t.iss.one/tikvahethiopia/65538 ]
" ተራራ ኔትዎርክ " የተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ አቋቁሞ ሲሰራ በነበረበት ወቅት ታህሳስ 1 ቀን የታሰረው ጋዜጠኛ ታምራት ከ118 ቀናት እስር በኃላ መፈታቱን የሚሰራበት ሚዲያ አሳውቋል።
ጋዜጠኛ ታምራት ከታሰረ በኃላ በተደጋጋሚ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን በ50 ሺህ ብር ዋስ ነው ከእስር የተፈታው።
ከዚህ ቀደም ጋዜጠኛ መአዛ መሃመድ፣ ጋዜጠኛ እና አክቲቪስት ኢያስፔድ ተስፋዬ ፣ ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ ፣ የአሶሴትድ ፕረስ (AP) ጋዜጠኛ አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያው ቶማስ እንግዳ ከእስር መፈታታቸው ይታወቃል።

#ZOnlineShopping
የጀርባና የወገብ ችግር አለቦት?
ሙሉ የጀርባ አና የወገብ ቀበቶ 950 ብር
የትከሻ ቀበቶ 650 ብር
የመቀመጫ (Cushion) 850 ብር
የጀርባ መደገፊያ (Pillow) 750 ብር
የጀርባ መጉበጥ ችግርን ፣ የጀርባ ዲስክ መንሸራተት በእድሜ መግፋት የሚመጡ የጀርባ ችግሮች የሚከላከልና ቀጥያል እና ማራኪ ቁመና የሚያላብስ
ስልክ ፦ 0989055551 ፡ ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን።
አድራሻ ፦ ቦሌ አቢሲንያ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት.pdf
Amnesty International & HRW .pdf
22.5 MB
#ሪፖርት
ከጥቂት ሳምንታት በፊት የትግራይ ኃይሎች በአማራ ክልል ገብተው በቆዩባቸው ወቅት የፈፀሟቸው ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ ወንጀሎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ሪፖርት ያቀረበው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ አዲስ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሂውማን ራይትስ ዎች ጋር በመተባበር ላለፉት 15 ወራት የሰራውን ሪፖርት ነው ይፋ ያደረገው።
ዛሬ ይፋ የሆነው ሪፖርት ፥" 'ከዚህ ምድር እናስወግዳችኋለን'፡ በሰብዓዊነት የሚፈጸም ወንጀል እና የዘር ማጽዳት በኢትዮጵያዋ ምዕራብ ትግራይ ዞን" የተሰኘ ነው።
ይህ ሪፖርት በምዕራብ ትግራይ የትግራይ ተወላጆች ላይ ተፈፀሙ የተባሉ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በስፋት ይዳስሳል።
ከጦርነቱ መቀስቀስ ጀምሮ የአማራ ኃይሎች እና ባለስልጣናት በምዕራብ ትግራይ ባሉ የትግራይ ተወላጆች ላይ ከጦር ወንጀል እና በሰብዓዊነት ላይ ከሚፈጸሙ ወንጀሎች ጋር የሚስተካከሉ መጠነ ሰፊ ወንጀሎች ፈጽመዋል ብሏል ሪፖርቱ።
ሪፖርቱ የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳበት ምዕራብ ትግራይ የሚንቀሳቀሱት የአማራ ልዩ ኃይል እንዲሁም ሚሊሻዎች "የዘር ማጽዳት እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን" መፈጸማቸውን ገልጿል።
የዛሬው ሪፖርት በጦርነቱ የመጀመሪያ ጥቂት ወራት ውስጥ የተፈጸሙ ጥፋቶችን ጭምር የዳሰሰ ሲሆን የትግራይ ሚሊሻዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪ ሲቪሎች በ ማይካድራ ከተማ አካባቢው ነዋሪ በሆኑ እና ለቀን ስራ በመጡ የአማራ ተወላጆች ላይ "የጦር ወንጀሎችን" መፈጸማቸውን አስታውሷል።
በሌላ በኩል ሁለቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በአካባቢው ያለውን አስከፊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ለማስቆም በአፍሪካ ሕብረት የሚመራ ሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲሰማራ ጠይቀዋል።
(ሙሉው 240 ገፅ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል)

#Qatar2022 " ለኳታሩ 2022 የዓለም ዋንጫ በዳኝነት እንዳጫውት በፊፋ መመረጤን አላውቅም " - ባምላክ ተሰማ (ለቢቢሲ) ዓለም አቀፍ ዳኛ ባምላክ ተሰማ "ለኳታሩ 2022 የዓለም ዋንጫ በዳኝነት እንዳጫውት በፊፋ መመረጤን አላውቅም" ሲል ተናግሯል። ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ፥ " ምንም ነገር አላውቅም። በይፋ የደረሰኝ ነገር የለም " ብሏል። ባምላክ ተሰማ በኳታሩ የዓለም…
#Update
FIFA የኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ ዳኞች ምርጫን በተመለከተ የወጡት ዘገባዎች ሀሰት መሆናቸውን አሳውቋል።
FIFA ከትላትን ጀምሮ ሲሰራጭ የነበረው መረጃ ከእሱ የወጣ እንዳልሆነ ገልጾ " መረጃዎቹ ሙሉ በሙሉ የFIFA አይደሉም። ሀሰተኛ ናቸው " ብሏል።
ወደፊት የዳኞች ሹመትን አሳውቃለሁ ሲልም ገልጿል።

#ዋግኽምራ📍
በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ህወሓት በሚቆጣጠረው አበርጌሌ በተፈጠረው የመድሃኒትና ምግብ እጥረት ሳቢያ ከሃምሌ ወር አንስቶ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 120 መድረሱ ተገልጿል።
ወረዳው ከሟቾቹ ውስጥ ብዛት ያላቸው ህፃናት እና አዛውንት እንደሆኑ፤ አብዛኞቹ ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነበረባቸው ነገር ግን የሞታቸው ምክንያት የመድሃኒት እጥረት መሆኑ አሳውቋል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አለሙ ክፍሌ ሲናገሩ፥ "ከ70 ሺ ህዝብ በላይ ነው አበርጌሌ የሚኖረው፤ አበርጌሌ ማለት ከትግራይ በሜትር ልዩነት የምንኖር ማህበረሰቦች ነን።
እዛ ያለው ማህበረሰብ አሁን በረሃብ እየሞተ ነው ያለው። ከ120 በላይ ሰው በረሃብ እና በመድሃኒት እጦት ሞቷል።
በአብዛኛው የሞቱት ሽማግሌዎች የነበሩ እና ከ50 በላይ እድሜ ያላቸው መንቀሳቀስ የማይችሉ በረሃብ እና በእድሜም ትንሽ ከፍ ያሉ ናቸው አንዳንዶቹ የግፊት መድሃኒት ይጠቀሙ የነበሩ ናቸው። አንዳንዶቹ የኤች አይቪ መድሃኒት የሚጠቀሙ ነበሩ።
ከዛ በዘለለ የተጠቁብን ህፃናቶች ናቸው በወባ እና በተለያዩ በሽታዎች ህክምና እና መድሃኒት የሚባል ስለሌለ ህፃናቶች ናቸው የሞቱት " ብለዋል።
አካባቢው በህወሓት ቁጥጥር ስር ከዋለ እንዴት የሟቾች ቁጥር ተረጋገጠ ? ለሚለውም ሲመልሱ፦
" አንደኛ ቤተሰቦቻችን ናቸው፣ አብዝሃኛው በየቀበሌው ያሉ ሰዎችም እዚህ ስለሚመጡ በተፈናቃይ መልኩ መረጃ ይሰጡናል።
በየቀኑም መረጃ የሚሰጡን ሰዎች አሉ እዛ ሆነው። በየቀኑ ምን እንደተፈጠረ ምን እንደሆነ ዝርዝር መረጃ የሚሰጡን አሉ።
እዛው አበርጌሌ ውስጥ አንዳንድ ቀበሌዎች ኔትዎርክ የሚሰራባቸው አሉ፤ ስልክ ስለሚሰራ በየቀኑ መረጃ እናገኛለን ይሄን በጣም እርግጠኛ ነኝ። " ሲሉ መልሰዋል።
telegra.ph/VOA-04-06

የሳንካራ ስም ዛሬም ድረስ ለምን ተደጋግሞ ይነሳል ? ቶማስ ሳንካራ ምድር ላይ ለ37 ዓመታት ብቻ የተራመደ ነገር ግን በማእበል የማይጠፋ ዱካ አሳርፎ ያለፈ የዘመናችን አፍሪካዊ አብዮተኛ ነው። በቅኝ ግዛት ወቅት "አፐር ቮልታ" ትባል የነበረችውን በርሀማ ደሀ ሀገሩን "ቡርኪና ፋሶ" ወደሚል ይፋዊ መጠሪያ የቀየረ፣ ተበታትነው ይኖሩ የነበሩትን ህዝቦቿን "ቡርኪናቤ" የተሰኘ የጋራ ማንነት እንዲጋሩ ያደረገ፣…
#Update
ኮምፓኦሬ እድሜ ልክ እንዲታሰሩ ተፈረደባቸው።
የኡጋዱጉ ፍርድ ቤት በቶማስ ሳንካራ ግድያ የቀድሞ የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ብሌዝ ኮምፓኦሬ ላይ የእድሜ ልክ እስራት ፈርዶባቸዋል።
የቶማስ ሳንካራ የፍርድ ሂደት 6 ወራት የፈጀ ሲሆን በመጨረሻም ኮምፓኦሬ እድሜ ልክ እንዲታሰሩ ተፈርዶባቸዋል።
በተጨማሪ የካምፓኦሬ ረዳቶቹ ጊልበርት ዳይንደርሬ እና ካፋንዶ ሃይሲንቴ እድሜ ልክ እንዲታሰሩ ፍርድ ቤት ወስኗል።
በጥቅምት 15/ 1987 የተገደለው ቶማስ ሳንካራ ምድር ላይ ለ37 ዓመታት ብቻ የቆየ ነገር ግን በማእበል የማይጠፋ ዱካ አሳርፎ ያለፈ የዘመናችን አፍሪካዊ አብዮተኛ ነው።
ቶማስ ሳንካራ ማን ነው ? ያንብቡ :https://t.iss.one/tikvahethiopia/67264

#ነዳጅ ኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ተቀራራቢ ለማድረግ እና ከጎረቤት ሀገራት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የዋጋ ተመን ለማውጣት መታቀዱ ታውቋል። የመንግስት ድጎማም ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች ብቻ እንዲሆን ታስቧል። አቶ ገብረመስቀል ጫላ (የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር) ለህ/ተ/ም/ቤት የሚኒስቴሩን የ8 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት የተናገሩት ፦…
#AddisAbaba📍
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ እና የታለመ ድጐማ አፈፃፀም ረቂቅ መመሪያ ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
በዚህም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሸከርካሪዎች የነዳጅ ድጎማ ማድረግ በሚያስችል ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የድጎማ ስርዓቱ በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉ ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የተሻለ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ያስችላል ተብሏል፡፡
በድጎማ ስርዓቱ GPS የሚደረግ ሲሆን ይህ የትራንስፖርት ስምሪቱን በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር ቁጥጥሩን ለማሳለጥ ዕድል ይፈጥራል ነው የተባለው።
ድጎማው ከሀምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
የነዳጅ ድጎማው ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ህብረተሰብ አገልግሎት የሚሰጡ በታሪፍ እና በስምሪት ቁጥጥር ላይ የተመሠረተ መለስተኛ፣ መካከለኛ የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት ተሸከርካሪዎችን የሚመለከት ነው።
በዚህም የህዝብ የትራንስፓርት አገልግሎት የሚሠጡ የመንግሥትና የግል አውቶቡሶች፣ የሳሎን ታክሲዎችን ሳይጨምር በከተማ ውስጥ እና በከተሞች መካከል የህዝብ የትራንስፓርት አገልግሎት የሚሠጡ ኮድ 1 እና ኮድ 3 ሚኒባስ (አዲስ አበባ ውስጥ የተመዘገቡ) ተሽከረካሪዎችን ያካትታል።
በመንግሥት መስሪያ ቤቶች፣ በግል እና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሠራተኛ አገልግሎት እንዲሁም በግል ትምህርት ቤቶች የተማሪ አገልግሎት የሚሠጡ ድጎማው አይመለከታቸውም።
በድጎማ ስርዓቱ የተመዘገቡ ተሸከርካሪዎች እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባሉት ጊዜ ውስጥ GPS መግጠም አስገዳጅ መሆኑ ተገልጿል።

#GoE
የኢትዮጵያ መንግስት አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች በጣምራ ባወጡት ሪፖርት ዙሪያ ምላሽ ሰጥቷል።
መንግስት በወልቃይት ላይ ትኩረቱን ያደረገውን ሪፖርት ይዘት በጥንቃቄ እየመረመረ እንደሚገኝ ገልጿል።
ሪፖርቱ በሰብአዊ መብት ላይ የሚነሱ ከባድ ጥሰቶች ከሚባሉት በተጨማሪ በሀገሪቱ ውስጥ የተከሰቱትንና በጥንቃቄ መታየት የሚገባቸውን የፖለቲካ ለውጦች፣ ሰላምና ደህንነት፣ የውስጥ ወሰን ጉዳዮችን ያካተተ መሆኑንም መገንዘብ ያስፈልጋል ብሏል።
የዘር ማጽዳት፣ የጦር ወንጀል እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ክስንም ያቀረበ ሪፖርት መሆኑን ገልጿል።
የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙትን ሁሉ ተጠያቂ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን የገለፀው መንግስት ለዚህም ነው የኢሰመኮ እና የተመድ የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ፅ/ ቤት የጋራ ምርመራ ዉጤቶችን ተከትሎ መንግስት የሚኒስትሮች ግብረ ሃይል ማቋቋሙን አስታውሷል።
ግብረሃይሉ ዛሬ ሁለተኛ ስብሰባ አካሂዶ የምርመራ ሂደቱን ለማፋጠን የተለያዩ መመሪያዎችን አውጥቷል፤ ለአሁኑ ሪፖርትም ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በቅርበት ይመረምራል ሲል አስረድቷል።
መንግስት ሁለቱ ተቋማት ጉዳዪን ለመመርመር የተጠቀሟቸውን በርካታ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ትክክለኛነት ላይ ጥያቄ ማቅረቡን ገልጿል።
ያንብቡ : https://telegra.ph/GoE-04-06

#ETHIOPIA የ2013 የ12ኛ ክፍል ፈተና በሁለት ዙር ተሰጥቶ ውጤት እና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ከሆነ ቀናት ተቆጥሯል። የፈተናው ውጤት እና የመቁረጫ ነጥቡ በተለያዩ ተማሪዎች/ወላጆች፣የትምህርት ቢሮና መምሪዎች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሮ ትልቅ አጀንዳ መሆኑ ይታወቃል። መንግስት ለቅሬታዎች ምላሽ እንዲሰጥም ግፊት እየተደረገ ነው። የትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ምደባ ለማድረግ ተማሪዎች…
#MoE
የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ የሚሆንበት ቀን አልተወሰነም።
@tikvahuniversity ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምደባ ጋር በተያያዘ በርካታ ጥያቄዎች በየዕለቱ ከተማሪዎች እና ወላጆች እየደረሱት ይገኛል።
ጉዳዩ የሚመለከታቸው የትምህርት ሚኒስቴር አካላትን የጠየቅን ሲሆን " የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ የሚሆንበት ቀን አሁንም አለመወሰኑን " ተገልጾልናል።
ምደባው ይፋ እስከሚሆን ተማሪዎች እና ወላጆች ለትንሽ ጊዜ በትግዕስት እንዲጠብቁ ጠይቀዋል።
ተማሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች እንዳይሸበሩም መልዕክት ተላልፏል።
ከዩኒቨርሲቲ ምደባ ጋር በተያያዘ የምናገኘውን አዲስ መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል።
@tikvahuniversity

#FINTEX2022
3ኛው የፈርኒቸር፣ ቤተ-ውበት እና ግንባታ አጨራረስ ኤክስፖ እና ጉባዔ (FINTEX 2022) ከመጋቢት 29-ሚያዝያ 01 ቀን 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል።
በፈርኒቸር፣ ቤተ ውበትና የግንባታ አጨራረስ ምርቶች የገበያ ሰንሰለት ላይ የተዘጋጀው ኤክስፖ በእንጨት ስራ፣ በቤት በቢሮ እና በኢንዱስትሪ ፈርኒቸሮች እንዲሁም የውስጥ እና የውጪ ማስዋቢያ ምርቶች፣ መብራቶች፣ መጋረጃዎች እና ልዩ ልዩ ግብዓቶች ላይ ትኩረታቸውን አድርገው የሚሰሩ ድርጅቶች በአንድ መድረክ አሰባስቦ ይጠብቅዎታል፡፡
ለመጎብኘት ቀድመው በድረገፃችን ይመዝገቡ : https://bit.ly/3IWUnMm
3ኛው የፈርኒቸር፣ ቤተ-ውበት እና ግንባታ አጨራረስ ኤክስፖ እና ጉባዔ (FINTEX 2022) ከመጋቢት 29-ሚያዝያ 01 ቀን 2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል።
በፈርኒቸር፣ ቤተ ውበትና የግንባታ አጨራረስ ምርቶች የገበያ ሰንሰለት ላይ የተዘጋጀው ኤክስፖ በእንጨት ስራ፣ በቤት በቢሮ እና በኢንዱስትሪ ፈርኒቸሮች እንዲሁም የውስጥ እና የውጪ ማስዋቢያ ምርቶች፣ መብራቶች፣ መጋረጃዎች እና ልዩ ልዩ ግብዓቶች ላይ ትኩረታቸውን አድርገው የሚሰሩ ድርጅቶች በአንድ መድረክ አሰባስቦ ይጠብቅዎታል፡፡
ለመጎብኘት ቀድመው በድረገፃችን ይመዝገቡ : https://bit.ly/3IWUnMm
TIKVAH-ETHIOPIA
Amnesty International & HRW .pdf
#EHRC
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ይፋ በሆነው የአምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ በርቀት የሚደረግ ምርመራ ውስንነቶች እና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አንዳንድ የቋንቋ ልዩነቶች ቢኖሩም ፦
👉 ከማይካድራ አንፃር በትግራይ ሚሊሻና ፖሊስ ድጋፍ በሳምሪ ቡድን በአማራ ሲቪሎች ላይ የተፈጸመው ግድያና ማፈናቀል፤
👉 በአፀፋ/በቀል የአማራ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻ እና የፋኖ ቡድን የትግራይ ተወላጆች ላይ ያደረሱት ጥቃት እና ህገወጥ መጠነ ሰፊ ማፈናቀል ፤ የሚገልፁ የሪፖርቱ ግኝንቶች ከኢሰመኮ ጋር እንዲሁም በትግራይ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (JIT) ጋር ከተሰራው የጣምራ ምርመራ ጋር ተመሳሳይ ናቸው ብለዋል።
በሁሉም ወገኖች የተፈፀሙ የግድያና መጠነ ሰፊ በኃይል የማፈናቀል ተግባራት የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ገልፀዋል።
ራኬብ ፥ የጣምራ ምርመራ ሪፖርት (JIT) ምክረ ሃሳቦች ተግባራዊ እንዲደረጉ ፤ ሁሉም ተዋናይ ወገኖች ተጨማሪ መፈናቀልን ሊያስከትሉ የሚችሉ እርምጃዎችን ከመውሰድ እንዲቆጠቡ፤ ሁሉም የውስጥ ተፈናቃዮች በፍቃደኝነት እንዲመለሱ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ ሁኔታን እንዲፈጥሩ፤ ለወልቃይት-ፀገዴ የተራዘመ የመሬት ውዝግብ በዘላቂነት እልባት እንዲገኝ አሳስበዋል።
የትላንቱን ሪፖርት ካዘጋጁት አንዱ ሂውማን ራይስት ዎች ከዚህ ቀደም በኢሰመኮና OHCHR ስለተሰራው የጣምራ ሪፖርት አስተያየት የሰጠ ሲሆን በግኝቶቻችን ውስጥ በርካታ ቁልፍ ልዩነቶች አሉ ብሏል። በጣምራ ሪፖርቱ ላይ በትግራይ ተወላጆች ላይ ስለተፈፀኑት ግፍፎችና የማሸብር ድርጊቶች ብዙም አልተጠቀሰም ሲል ገልጿል: telegra.ph/HRW-04-07