A.F-1.pdf
229.5 KB
#MiT
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፈጠራ ሥራ ሃሳብ ውድድር ለማድረግ ተወዳዳሪዎች እየመዘገበ ነው።
የኅብረተሰብን ችግር ሊቀርፉ እና ህይወትን በማዘመን አስተዋጽዖ ሊያበረክቱ የሚችሉ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።
ተማሪዎች፣ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ ተመራማሪዎች እና ተቋማት በውድድሩ እንዲሳተፉ ሚኒስቴሩ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
ለመመዝገብ ተከታዩን ሊንክ ይጫኑ፦
https://mint.gov.et/wp-content/uploads/2022/03/A.F-1.pdf
@tikvahuniversity

" የነዳጅ ዋጋ ኢትዮጵያን በ1 ወር ውስጥ ብቻ 10 ቢሊዮን ብር አክስሯታል " - አቶ ታደሰ ኃለለማርያም
በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ የጨመረው የነዳጅ ዋጋ በ1 ወር ውስጥ ብቻ ኢትዮጵያን 10 ቢሊዮን ብር እንዳከሰራት ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት ፤ የነዳጅ ዋጋ በበርሜል ይሸጥበት ከነበረው 60 እና 70 ዶላር ወደ 140 ዶላር ማሻቀቡ፣ ኢትዮጵያ 10 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ እንዳስወጣት ወይም እንዳከሰራት አመልክቷል።
የድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም ለሪፖተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፤ እንደ ሌሎቹ አገሮች ሁሉ የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ኢትዮጵያንም ዋጋ እያስከፈላት ነው ብለዋል።
በአንድ ወር ብቻ 10 ቢሊዮ ብር እንድታጣ ምክንያት መሆኑ እና ይህም ትልቅ ጉዳት መሆኑን ገልፀዋል።
" በወርኃዊ የነዳጅ ወጪዋም ወደ 250 ሚሊዮ ዶላር ከፍ እንዲል አስገድዷል " ያሉት አቶ ታደሰ ይህም መንግሥት ይህንን ልዩነት በመሸፈን በዓለም ዝቅተኛ በተባለ ዋጋ ነዳጅ እየተሸጠ የሚገኝ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል ብለዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መጨመር የበለፀጉ አገሮችን ጭምር እየፈተነ የሚገኝ ሲሆን እንደ ፈረንሣይ ያሉ አገሮች በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ በማድረግ ህብረተሰቡ ነዳጅን ቆጥቦ እንዲጠቀም ሁሉ ማወጃቸውን አቶ ታደሰ አስታውሰው በኢትዮጵያ ነዳጅ ጭማሪ ባይደረግም ህብረተሰቡ በቁጠባ የመጠቀም ባህሉን ማዳበር አለበት ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ አሁን ነዳጅ በምታስገባበት ዋጋ መሠረት ለገበያ ቢቀርብ የአንድ ሌትር የቤንዚን ዋጋ 76 ብር መሸጥ የነበረበት መሆኑንም የአቶ ታደሰ ገልፃ የሚያስረዳ ሲሆን አሁን ላይ ግን የአንድ ሌትር ቤንዚን ዋጋ 31 ብር ከ74 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል።
ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
@tikvahethiopia

ድሬዳዋ ፤ አቶ እስቂያስ ታፈሰን ሸለመች።
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ15 አመት በላይ በተለያየ የአገልግሎት ስፍራ እና በአመራርነት ላገለገሉት አቶ እስቂያስ ታፈሰ የሽልማትና የእውቅና መርሀ-ግብር ትላንት ተካሂዷል።
ከተማ አስተዳደሩ ለአቶ እስቂያስ ዘመናዊ የቤት መኪና እንዲሁም የ100 ሺህ ብር ሽልማት ሸልሟል።
ይህ እውቅናና ሽልማት እንዲካሄድ ፤ የከተማው ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ፣ የፕሮግራም አዘጋጅ ኮሚቴዎች፣ ወዳጆቹ፣ ጓደኞቹ፣ የከተማው ባለሃብቶች አስተዋፆ እንዳደረጉ ተነግሯል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ፤ አቶ እስቂያስ ታፈሰ ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር ለማረጋጋት ከሌሎች አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ከፍተኛ አስተዋፆ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።
በአመራርነት በቆየዩባቸው ጊዜያቶች ሁሉ ሰው አክባሪ ፣ ከሰው ጋር ዝቅ ብሎ ስራን መስራት የሚችሉ ፣ ከሰራተኞች ጋር እንደ አለቃ ሳይሆን እንደ ሰራተኛ መስራት የሚችሉ አመራር ነበሩ ብለዋል።
አቶ እስቂያስ ታፈሰ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከቀበሌ የህዝብ አደረጃጀት ኃላፊነት ቦታ አንስቶ በተለያዩ ቦታዎች ያገለገሉ ሲሆን እስከ ጥር 2014 የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሆነው መርተዋል።
አሁን በ " አማራ ባንክ " የቦርድ ሴክረቴሪ ጀነራል ሆነው ተመድበዋል።
ከዚህ ቀደም ድሬዳዋ በባለሃብቶች ተሳትፎ ለ3 ዓመታ በከተማው የነበረውን የፀጥታ ችግር እንዲፈታ እና አስተማማኝ ሰለም እንዲረጋገጥ ፤ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ አስተዋፆ ላደረጉ ለየቀድሞ ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ 3.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የዘመነ መኪና ስጦታ መስጠቷ ፤ ለፀጥታ አካላትም የተለያየ መጠን ያለው ሽልማት ማበርከቷ ይታወሳል።

#EthiopianAirlines🇪🇹
" ... የድርጅቱን ምርታማነት እና የኢንደስትሪ ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ ለመስራት ቁርጠኛ ነኝ " - አቶ መስፍን ጣሰው
ከትላንት በስቲያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሰራታዊ የሰራተኞች ማህበር አዲስ ለተሾሙት የአየር መንገዱ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የእንኳን ደህና መጡ መርሃ ግብር አከናውኖ ነበር።
በመርሃ ግብሩ ላይ የማህበሩ ፕሬዚደንት ኢ/ር ተሊላ ዴሬሳ ፤ አዲስ የተሾሙትን ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ እንኳን ደህና መጡ በማለት የሰራተኛ ማህበሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት በማህበሩ የተገኙ ድሎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ፣ የድርጅቱ ምርታማነት እና የኢንደስትሪ ሰላሙን በማስጠበቅ ሂደቱም የመሪነት ሚናውን በመጫወት እንደሚቀጥሉ እነታቸውን ገልፀዋል።
አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው የተደረገላቸውን አቀባበል አድንቀው እንደቀድሞው ሁሉ ከቀዳማዊ ማህበሩ ጋር የሰራተኞችን ጥቅም፣ የድርጅቱን ምርታማነትና የኢንደስትሪ ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ ለመስራት ቁርጠኝነት አስታውቀው ማህበሩም በዚህ ረገድ ከፍ ያለ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።
የማህበሩ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ኪያ ለማና የአየር መንገዱ የሰው ሃብት ም/ፕሬዝዳንት በመርሃ ግብሩ መልዕክታቸውን አስተላለፈው " በህብረት ፣ በንግግርና በድርድር ብዙ ውጤት እንዳመጣን ሁሉ ይህንኑ አጠንክረን ብንቀጠል የምናልማቸውን ስኬቶች ማሳካት እንችላለን " ብለዋል።
Via Abdi Kuma (Tikvah Family)

#Mekelle 📍
በቅርቡ የታወጀው የሰብዓዊ ግጭት ማቆም ስምምነት ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ እንዲገባና ጦርነቱ እልባት ሊያገኝ ይችላል የሚል ትልቅ ተስፋን አጭሯል።
ነዋሪው ላለፉት በርካታ ወራት መሰረተዊ አገልግሎቶች ስላላገኘ ነሮው የከፋ ሆኗል።
በትግራይ መዲና መቐለ የኑሮ ሁኔታ ምን ይመስላል ? በሚል ቢቢሲ ከነዋሪዎች ሰብሰበኩ ያለውን መረጃ ዛሬ ማለዳ ይዞ ወጥቷል።
በዚህም፦
👉 ለበርካታ ወራት ባንኮች ስለተዘጉ ነዋሪው ገንዘብ አውጥቶ መጠቀም አልቻለም።
👉 የቴሌኮም አገልግሎቶች ስልክ እና ኢንተርኔት በመቋረጣቸው የእርስ በእርስ ግንኙነት ተቋርጧል።
👉 ስር የሰደደ የጤና እክል ያለባቸው ህመምተኞች በመድኃኒት እጦት ምክንያት እየሞቱ ነው።
👉 የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ንሯል። ጤፍ፣ የስንዴ ዱቄት፣ በርበሬና ዘይት ዋጋ የማይቀመስ ሆኗል።
👉 ከአመት በፊት 100 ኪ.ግ ጤፍ ወደ 4 ሺ 200 ብር ገደማ ይሸጥ ነበር፤ በአሁኑ ወቅት እስከ 7 ሺ 600 ብር እየተሸጠ ነው።
👉 ለልጆች አዲስ ጫማ፣ ልብስ መግዛት እና ስጋ መብላት ቅንጦት ሆኗል።
👉 በአንድ ወቅት 3 ሺ 295 ብር ያወጣ የነበረ ባለ 21 ካራት የወርቅ ቀለበት በአሁኑ ወቅት ዋጋው ወርዶ በ700 ብር ይሸጣል።
👉 ከ800 ሺ ብር በላይ ይሸጥ የነበረ መኪና 300 ሺ ብር እየተሸጠ ነው።
👉 የማህበረሰቡ መገለጫ የሆኑት ሃይማኖታዊ በዓላት፣ ሰርግና ሌሎች ድግሶች የሩቅ ጊዜ ትዝታ ሆነዋል።
👉 1 ሊትር ቤንዚን ከጦርነቱ በፊት በነዳጅ ማደያዎች 22 ብር ይሸጥ ነበረ በአሁኑ ወቅት በሊትር 515 ብር እየተሸጠ ነው።
👉 በከተማዋ ጋሪዎች ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ውለዋል።
👉 ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል ብስክሌት ተወዷል።
ያንብቡ : telegra.ph/Mekelle-04-03

የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት መዘዝ !
በዩሮዞን የዋጋ ግሽበት ፦
🗓 መጋቢት , 2021 👉 1.3 %
🗓 መጋቢት , 2022 👉 7.5 %
በዩሮዞን ሀገራት በ30ና 40 ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ የዋጋ ግሽበት ተመዝግቧል።
የዩሮዞን ሀገራት እነማን ናቸው ?
🇦🇹 ኦስትሪያ
🇧🇪 ቤልጂየም
🇨🇾 ሳይፕረስ
🇪🇪 እስቶኒያ
🇫🇮 ፊንላንድ
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇩🇪 ጀርመን
🇬🇷 ግሪክ
🇮🇪 አየርላንድ
🇮🇹ጣልያን
🇱🇻 ላቲቪያ
🇱🇹 ሉቱንያ
🇱🇺 ሉክዘንበርግ
🇲🇹 ማልታ
🇳🇱 ኔዘርላንድስ
🇸🇰 ስሎቫኪያ
🇸🇮 ስሎቬንያ
🇪🇸 ስፔን
🇵🇹 ፖርቹጋል ናቸው።

አሰላ ከተማን ጨምሮ ዙሪያውን የኤሌክትሪክ ኃይል ያሳጣ ዝርፊያ ተፈፀሟል !
ከአዋሽ 2 ወደ አሰላ የተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ ትናንት መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ዝርፊያ ተፈፀመ።
በዶዶታ ወረዳ እና ጌራ ከተማ አቅራቢያ በተፈፀመው የምሰሶ አካላት ዝርፊያ 2 ምሰሶዎች በመውደቃቸው የተነሳ አሰላ ከተማን ጨምሮ በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች በከፊል ኤሌክትሪክ ተቋርጧል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጥገና ቡድን ዝርፊያ ወደተፈፀመበት አካባቢ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ጥገናውን በፍጥነት ለመጀመር የሚያስችል አሰሳ እያካሄደ ነው ተብሏል።
ጥገናው ከሳምንት ያላነሰ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ተገምቷል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ዝርፊያ እየተደጋገመ ሲሆን ይህም ለኃይል መቋረጥ ምክንያት እየሆነ ነው፡፡
ህብረተሰቡ በኤሌክትሪክ መሰረተልማት ላይ ዝርፊያ የሚፈጽሙ ግለሰቦችን ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት እንዲያሳውቅ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳስቧል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ፎቶ ፦ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተዘግቶ የቆየው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ከሱዳን ጋር የሚያገናኘው የጠረፍ ንግድ ኬላ በዚህ ሳምንት ዳግም ተከፍቷል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን በኩርሙክ በኩል ከሱዳን ጋር የሚያገናኘው የጠረፍ ንግድ ኬላ ዳግም መከፈት በሁለቱ ሃገሮች መካከል የሚኖረውን የህዝብ ለህዝብ ትስስር ከማጠናከር ባለፈ በኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል።
የሁለቱ የድንበር አካባቢ የማህበረሰብ ክፍሎች ኬላው ተከፈተ ብለው የፈለጉትን ማውጣት እና ማስገባት የማይችሉ መሆኑ ተገልጿል።
የሁለቱን ሃገሮች ሉዓላዊነት ሊዳፈር በማይችል አግባብ ከአሁን በፊት ሲካሄድ በነበረው የግብይት ስርዓት ሀሙስና እሁድ የንግድ እንቅስቃሴ ማካሄድ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
Credit : የኩርሙክ ኮሚኒኬሽን

#US
አሜሪካ በአስከፊው ጓንታናሞ ቤይ እስር ቤት አስራው የነበረችውን አልጄሪያዊ ወደ ሀገሩ መለሰች።
አሜሪካ በሀገሯ ውስጥ የ "ቦምብ ጥቃት ለማድረስ አቅደሃል" ብላ ለ20 ዓመታት ገደማ ያሰረችውን ሱፊያን ቡርሃሚ የተባለ አልጄሪያው ወደ ሀገሩ እንዲመለስ አድርጌዋለሁ ብላለች።
በአስከፊው ጓንታናሞ ቤይ እስር ቤት አሜሪካ አስራ ያቆየችው እና አሁን መልሸዋለሁ ያለችው አልጄሪያዊ በፈረንጆቹ 2002 ፓኪስታን ውስጥ ከአንድ ነባር የአል-ቃዒዳ አባል ጋር ነበር በቁጥጥር ሥር የዋለው።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ግለሰቡን ከዚህ በላይ ማሠር ጠቀሜታ ስለሌለው ለቅቄዋለሁ ብሏል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አልጄሪያ ሱፊያንን ስብዕና በተመላበት መንገድ እንከባከበዋለሁ ስትል ቃል ገብታለችም ብሏል።
አልጄሪያ እስካሁን ስለሱፊያን ቡርሃሚ ጉዳይ ይፋዊ አስተያየት አልሰጠችም።
በአሁን ሰዓት ጓንታናሞ ቤይ በተሰኘው በጭካኔያዊ አገዛዙ በሚታወቀው እሥር ቤት 37 ያለፍርድ የታሠሩ ሰዎች አሉ።
ጓንታናሞ ቤይ ከ2002 ጀምሮ አሜሪካ ሽብር ላይ በማደርገው ጦርነት በቁጥጥር ሥር የማውላቸውን ግለሰቦችን የማቆይበት ነው ስትል ያቋቋመች ነው።
በተለይም ከ9/11 የሽብር ጥቃት በኋላ በርካታ ተጠርጣሪዎች ተይዘው የታሰሩበት ሲሆን የአሜሪካ ደህንነት ሰዎች ተጠርጣሪዎችን ኢ-ሰብዓዊ በሆነ መንገድ አሰቃይተዋል ተብለው ይወቀሳሉ ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።
ባለፈው ወርም አሜሪካ በ9/11 ጥቃት ከአውሮፕላን ጠላፊዎች ጋር ለመቀላቀል ሞክሯል ያላቸውን ግለሰብ ከ20 ዓመት በኃላ ወደ ሀገሩ ሳዑዲ አረቢያ እንዲመለስ አድርጋለች። ይህ ሰው መሀመድ አህመድ አልቃህታኒ የሚባል ሲሆን እድሜው 46 ነው፤ ለ20 ዓመት በጓንታናሞ ከቆየ በኋላ ለአእምሮ ጤና ህክምና ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ተደርጓል።