TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የምግብ ዘይት የፋብሪካ ዋጋ መወሰኛ በ1 ወር ውስጥ ተግባራዊ እንደሚያደርግ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መግለፁን ሪፖርተር አስነብቧል።

ሚኒስቴሩ ያለቀለት የፓልም ምግብ ዘይት ለሚያስመጡ እንዲሁም ከድፍድፍ የምግብ ዘይት ለሚያጣሩ የአገር ውስጥ ፋብሪካዎች ምርቱ ከፋብሪካ ለአከፋፋዮች የሚሸጥበት ዋጋ እንደሚወሰን ገልጿል።

ከዚህ በፊት አልፎ አልፎ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ፋብሪካዎች ላይ ቁጥጥር ለማድረግ ቢሞከርም ውጤታማ አለመሆኑንና ወጥ የሆነ አሠራር አልነበረም።

በተለይ ፋብሪካዎቹ ለድፍድፍ ዘይት ማስመጫ የሚወስዱት የውጭ ምንዛሪ ዋጋን ከማረጋጋት አንፃር የሚቀርብ ቢሆንም በዋጋ ላይ ግን ጭማሪ መኖሩን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ለዚህም በአከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች ላይ ከሚደረገው ቁጥጥር በተጨማሪ የፋብሪካ ዋጋ መወሰን ማስፈለጉን ተገልጿል።

እስካሁን በሊትር ከፋብሪካ የሚወጣበት ዋጋ ባይወሰንም በአንድ ወር ውስጥ ግን ተወስኖ ወደ ሥራ ይገባል ተብሏል።

ከዋጋ መወሰኛው በተጨማሪ ፋብሪካዎች እንዲያመርቱ የሚጠበቅባቸው የዘይት መጠን እንደሚወሰን የተገለፀ ሲሆን አዲስ ወደ ዘርፉ የሚገቡ ሆኑ የነባሮቹ ፋብሪካዎች ዝቅተኛ የማምረት አቅም ገደብ ይቀመጥለታል።

በዚህም መሠረት ፋብሪካዎቹ በቀን ውስጥ እስከ 200 ቶን እንዲያመርቱ ሊወሰን እንደሚችል ይህንን ለማድረግ የሚያስችል የማሽነሪና የቴክኖሎጂ አቅም እንዲኖራቸው ያስገድዳል ተብሏል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Reporter-Newspaper-04-03 (ሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopia
#Ukraine

በዩክሬን ዋና ከተማ ኬየቭ አቅራቢያ በምትገኝ " ቡቻ " በምትባል ከተማ የጅምላ መቃብር እና የሰዎች አስክሬን በከተማው ጎዳና ላይ ተጥሎ መገኘቱ ተሰማ።

ዩክሬን ፤ ሩስያ በቡቻ የጅምላ ግድያ ፈፅማለች ስትል ከሳለች።

የሩስያ ጦር ቡቻን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ የጅምላ መቃብር እና መንገድ ላይ የወዳደቁ አስክሬኖች መገኘታቸውን የዩክሬን ባለስልጣናት ገልፀዋል።

ፕሬዜዳንት ዜሌኒስኪ የተሰራጩ ፎቶዎችን በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ፥ " የሩስያ ወታደሮች እናቶች ይህንን ማየት አለባቸው ፥ እዩ ምን አይነት ገዳዮችን፣ ዘራፊዎችን... እንዳሳደጋችሁ " ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኩሌባ ፤ በቡቻ ሆን ተብሎ ጭፍጨፋ ተፈፅሟል ብለው G7 ጠንካራ ማዕቀብ እንዲጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የቡቻ ከተማ ከንቲባ እንደገለፁት ፥ ቢያንስ 300 ሰዎች በጅምላ መቃብር ተቀብረዋል። የተገደሉት ሰላማዊ ሰዎች ናቸው ግድያውን የፈፀመው የሩስያ ጦር ነው ብለዋል።

በተጨማሪ ከኬየቭ ውጭ ባሉ ሌሎች ከተሞችም በሩስያ ጦር ተፈፅመዋል የተባሉ የጅምላ መቃብሮች እና አስክሬኖች በየጎዳናው እየታዩ ነው።

ሀገራት በሩስያ ላይ ውግዘት እያሰሙ ሲሆን ጀርመን የጦር ወንጀል ነው ብላዋለች።

ሩስያ እየወጣ ያለውን ሪፖርት አጥብቃ አስተባብላለች።

የሩስያ ጦር ጉዳዩን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ፥ የሩስያ ወታደሮች ከአካባቢው እንዲወጡ የተደረገው እኤአ መጋቢት 30 እንደሆነ ገልጾ " የወንጀል ማስረጃዎች " ተብለው የታዩት የሩስያ ጦር ከወጣ በ4ኛ ቀን ነው ብሏል።

እኤአ መጋቢት 31 የቡቻ ከንቲባ በቪድዮ የሩስያ ጦር በከተማው እንደሌለ በቪድዮ እያሳዩ አረጋግጠዋል ነገር ግን አሁን የተባለውን አልጠቀሱም ብሏል።

ሩስያ ጉዳዩን ሀሰተኛ ዜና ስትል ውድቅ አድርጋዋለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#የዩኒቨርሲቲ_መውጫ_ፈተና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ከሁሉም መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚመረቁ ተማሪዎች በሰለጠኑባቸው ሙያዎች ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንዲወስዱ የሚጠበቀውን የመውጫ ፈተና ወደ ተግባር እንዲገባ ዝግጅት መደረጉን አስታውቋል። የመውጫ ፈተናውን በተመለከተ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምክክር እየተደረገ ይገኛል። የመንግስት…
#MoE

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በ2015 ዓ/ም ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ከዚህ ፈተና ጋር በተያያዘ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የተናገሩት ፦

" የመውጫ ፈተና ስትራተጂ የማዘጋጀት ስራ ተጠናቋል። ስትራቴጂውን ማስተግበሪያ መመሪያ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቷል።

ዝርዝር እቅድ ይህ የመውጫ ፈተና እንዴት ? ፤ መቼ ? ፤ በማን ? እንደሚሰጥ ፤ ፈተናው በማን እንደሚዘጋጅ ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ሚና የዩኒቨርሲቲዎች ሚና ምን እንደሚመስል በዝርዝር ምላሽ የሚሰጥ የድርጊት መርሃግብር ተዘጋጅቷል።

የመውጫ ፈተና ሌላ ከውጪ የሚጫን ፈተና አይደለም። በስርአተ ትምህርቱ ውስጥ የተቀመጡትን የምሩቃኑን ፕሮፋይል መሳካት አለመሳካቱን ፤ መጨበጥ አለመጨበጡን የሚያረጋግጥ ነው። "

@tikvahethiopia
#SouthSudan

የጎረቤታችን የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ኃይሎች በመካከላቸው የነበረውን የተካረረ መቃቃር ለመፍታት በዋና ከተማቸው ጁባ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነት ላይ የደረሱት በሌላኛዋ ጎረቤታችን ሱዳን አሸማጋይነት ነው።

የፖለቲካ ኃይሎቹ የተካረረ መቃቃር ውስጥ ገብተው ነበር የተባለ ሲሆን ይህንን ችግር ለመፍታት ተስማምተዋል።

ስምምነቱ ከሁሉም የተውጣጣና ጠንካራ ብሔራዊ ጦርን ለመመስረት የሚያስችል ሲሆን ይህን ለማጽናት የሚያስችል ሰነድ ተዘጋጅቶም ተፈራርመዋል፡፡

ፊርማው የፓለቲካ ኃይሎቹን የማሸማገሉን ሚና በወሰዱት የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄ/ል መሃመድ ሃምዳን ደገሎ በተገኙበት የተፈረመ ነው።

ለመገንባት በታሰበው ብሔራዊ ጦር ወጥነት ያለው እዝን ለመፍጠርና ስልጣን ለመከፋፈል እንደሚያስችል ተነግሮለታል።

ጄ/ል መሃመድ ሃምዳን ደገሎ (ሄሜቲ) ፥ " በፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና በምክትላቸው ሬይክ ማቻር (ዶ/ር) በሚመሩ ኃይሎች መካከል የተፈጠረውን መቃቃር በማርገብ ለማስማማት ያደረግነው ጥረት ተሳክቶልናል " ያሉ ሲሆን " ወንድሞቻችን የሃገራቸውን ሰላምና ደህንነት ለማስቀጠል በሚያስችል ትክክለኛ መንገድ ላይ በመገኘታቸው ደስተኞች ነን " ሲሉ መሪዎቹን አመስግነዋል፡፡

(አል ዓይን ኒውስ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኤርትራ በኢትዮጵያ ጉዳይ አስፈፃሚ ሾመች። አቶ ቢንያም በርሄ በኢትዮጵያ የኤርትራ ጉዳይ ፈፃሚ (Chargé d'affaire) ሆነው ተሹመዋል። አቶ ቢንያም የሹመት ደብዳቤያቸውን ትላንት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል ደመቀ አጥናፉ ማስረከባቸውን በአዲስ አበባ ከሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ሹመቱ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት…
#Update

ኤርትራ ፤ በኢትዮጵያ ለሚገኘው ኤምባሲዋ ቋሚ ጉዳይ አስፈፃሚ (Chargé d'affairs en pied) መሾሟ ምንም ሌላ የተለየ ትርጉም የለውም አለች።

" አዲሱ ሹመት በቋሚ ጉዳይ አስፈፃሚ ደረጃ (Chargé d'affairs en pied) መሆኑ ምንም ሌላ ትርጉም የለውም " ያለው በአዲስ አበባ የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ " በመላው አለም የሚሰራበት ጉዳይ ነው " ብሏል።

ኤርትራ በየትኛውም አለም ካላት ኤምባሲ ትልቁ ኢትዮጵያ የሚገኘው መሆኑን የሚገልፀው ኤምባሲድ በመሪዎች ደረጃም ሆነ በህዝብ-ለህዝብ መሀል ያለው ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን ገልጿል።

" አዲሱ ተሿሚ ኤርትራን በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረት እንዲሁም በ UNECA ወክለው ይሰራሉ። " ሲል አሳውቋል።

ኤርትራ ከቀናት በፊት አቶ ቢንያም በርሄን በኢትዮጵያ የኤርትራ ጉዳይ ፈፃሚ (Chargé d'affaire) አድርጋ መሾሟ ይታወሳል።

ሹመቱ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም የስራ ጊዜያቸውን አጠናቀው ከተሰናበቱ በኃላ የመጣ ሲሆን ኤርትራ ከአምባሳደር ይልቅ ለምን የጉዳይ አስፈፃሚ (Chargé d'affaire) እንደመደበች የተገለፀ ነገር አልነበረም።

ዛሬ በኤምባሲዋ በኩል በሰጠችው ማብራሪያ " ምንም የተለየ ትርጉም የለውም " ብላለች።

መረጃው ፦ የጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ነው።

@tikvahethiopia
#USA

በአሜሪካ ሀገር ካሊፎርኒያ ግዛት ሳክራሜንቶ ከተማ በተከፈተ ተኩስ በትንሹ 6 ሰዎች ሲገደሉ 12 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ድንገተኛው የተኩስ እሩምታ መጠጥ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች በሚበዙበት አካባቢ የተከፈተ ሲሆን ሰዎችም እራሳቸውን ለማዳን በየጎዳናዎቹ ሲሯሯጡ እና የድረሱልን ጥሪያቸውን ሲያሰሙ ነበር ተብሏል።

ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ በቦታው ሲደርስ በርካታ ሰዎች በአካባቢው ተሰብስበው እንደነበር የገለፀ ሲሆን እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር እንዳልዋለ አመልክቷል።

የሟቾች ቁጥር አሁን ከተጠቀሰውም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ተገምቷል።

የከተማዋ አስተዳዳሪ የሆኑት ዴረል ሰቲንበርክ በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፈና ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ቁጥር ማሰብ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጸዋል።

አክለውም ፤ " በጦር መሳሪያ የሚፈጸሙ ጥቃቶች የከተማችን፣ የግዛታችን እንዲሁም የአገራችን ስጋት ነው። ይህንን ለመቀነስ የሚደረጉ ማንኛውም አይነት እርምጃዎችን እደግፋለው " ማለታቸውን ቢቢሲ በደረገፁ አስነብቧል።

እንደ Gun Violence Archive ድረገፅ መረጃ በአሜሪካ ሀገር ከጦር መሳሪያዎች ጋር በተያያዘ በየዓመቱ #አርባ_ሺህ (40,000) ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን ይህ ደግሞ በመሳሪያዎች እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ያካታታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በ2015 ዓ/ም ተግባራዊ መሆን ይጀምራል። ከዚህ ፈተና ጋር በተያያዘ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የተናገሩት ፦ " የመውጫ ፈተና ስትራተጂ የማዘጋጀት ስራ ተጠናቋል። ስትራቴጂውን ማስተግበሪያ መመሪያ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቷል። ዝርዝር እቅድ ይህ የመውጫ ፈተና እንዴት ? ፤ መቼ ? ፤ በማን ? እንደሚሰጥ…
#MoE

ከሚቀጥለው ዓመት 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው የዩኒቨርሲቲ " መውጫ ፈተና " የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ አቅማቸው እስኪጎለብት፣ አካዳሚክ እና ተቋማዊ ነጻነታቸው ሙሉ በሙሉ እስኪረጋገጥ ድረሰ ፈተናው #በጊዜየዊነት በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ይህ የተገለፀው በአሁን ሰዓት የትምህርት ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶች ጋር በመውጫ ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ አውደ ጥናት እያካሄደ በሚገኝበት መድረክ ነው።

በአውደጥናቱ ላይ የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ በተለያዩ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ከመጪው ዓመት ጀምሮ እንዲሰጥ ለማድረግ ተገቢው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ ላይ መገለፁን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
#ዘይት

ዛሬ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በዘይት አምራች ፋብሪካዎች የመስክ ጉብኝት አድርገው ፤ ከባለሃብቶች ጋርም ውይይት አድርገው ነበር።

ጉብኝቱ የተገደረገው በፊቤላ ዘይት ማምረቻ ኢንዱስትሪ እና በደብሊው ኤ (WA) ዘይት ፋብሪካ ነው።

በዚህም ወቅት በቀን 1 ሚሊዮን 500 ሺ ሊትር ዘይት የማምረት አቅም ያለው ፊቤላ የዘይት ፋብሪካ ፦ በግብዓት አቅርቦት ችግር እና በመብራት መቆራረጥ ምክንያት ካለው የማምረት አቅም ከ40 በመቶ በታች እያመረተ መሆኑን አሳውቋል።

ፊቤላ ዘይት ፋብሪካ ስራ ከጀመረ አንድ አመት ያስቆጠረ ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ከ70 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት በማምረት ለህብረተሰቡ እንዳሰራጨ ገልጿል።

በተመሳሳይ የደብሊው ኤ (WA) ዘይት ፋብሪካ በግብዓት አቅርቦት እና በካፒታል እጥረት ምክንያት ካለው የማምረት አቅም እስከ 30 በመቶ ብቻ እያመረተ እንደሆነ አሳውቋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ በፋብሪካው በአካል በመገኘታቸው የችግሮችን ጥልቀት መረዳታቸውን ገልፀዋል።

ሀገር በቀል የሆነ ዘይት እንዲመረት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንሚያደርግ ተናግረው ፤ የተነሱትን የመብራት፣ የካፒታል እጥረት እና የግብዓት አቅርቦት ችግሮች በአጭር ጊዜ ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ጥረት እንደሚደረግ አሰረድተዋል፡፡

አሁን እየተስተዋለ ያለውን የዘይት እጥረት ለመቅረፍ መንግስት በልማት ድርጅቶች በቀጥታ ተገዝቶ እንዲቀርብ እያደረገ እና 322 ባለሀብቶች በፍራንኮ ቫሉታ ያለቀለት የምግብ ዘይት እንዲያስገቡ እየተደረገ መሆኑንና ፍትሀዊ ስርጭት እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
የደም እጥረት ተከስቷል።

አሁን ወቅቱ የፆም በመሆኑ አዲስ አበባ ከተማ ጨምሮ በሁሉም የደም ባንኮች የሚሰበሰበው የደም መጠን በመቀነሱ የደም እጥረት አጋጥሟል።

የብሔራዊ ደም ባንክ በላከልን መልዕክት ህብረተሰቡ ደም እንዲለግስ ጥሪ አቅርቧል።

#ይህንን_መልዕክት_ያጋሩ !!

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል። መንግስት የነዳጅ ዋጋ ከየካቲት 19 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ማስታወቁን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ውሳኔው ከቀላል ጥቁር ናፍጣ፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ እና ከአይሮኘላን ነዳጅ በስተቀር በሌሎች የነዳጅ ዓይነቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑም ነው የተገለፀው።…
#ሚያዚያ

የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፥ የሚያዚያ ወር የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በመጋቢት ወር ላይ ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የአውሮፕላን ነዳጅ ፣ የከባድ ጥቁር ናፍጣ እና የቀላል ጥቁር ናፍጣ የመሸጫ ዋጋ በዓለም አቀፍ ዋጋ መሰረት ተሰልቶ የመጣው ወደ ተጠቃሚው እንዲተላለፍ መወሰኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia