TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#twitter

ትዊተር ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ "ህግ የጣሱ " ያላቸዉን ተጠቃሚዎች ማገዱን ዛሬ አሳውቋል።

ትዊተር እንዳለው ብዙ አካዉንቶች ታግደዋል፤ ከታገዱት መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩት የትግራይ ደጋፊ ተጠቃሚዎች ይመስላሉ ብሏል።

ይሁንና ትዊተር የታገደዉ አካዉንት መጠን ምን ያህል እንደሆን በውል አልገለፀም።

ትዊተር እርምጃዉ የተወሰደው "የትዊተርን ህግ በመጣስ፣ የተወሰኑ ሃሽታጎች እና የትዊተር ገፆች፤ በተለጠፈዉ መረጃ ላይ በተደጋጋሚ በአላስፈላጊ ሁኔታዎች በማካተታቸው ነው። በተጨማሪ ርምጃዉ " በኢትዮጵያ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተገናኘ በትዊተር ላይ የሚደረጉ ውይይቶች ደኅንነታቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲሄድ ከምናደርገው ጥረት ጋር የተገናኘ ነው " ብሏል።

እገዳዉን በተመለከተ " በተጨባጭ በአካውንቶቹና ይዘቶቹ ላይ ያተኮሩ " መሆኑን እና " ከፖለተካዊ ማንነት እና ርዕዮተ ዓለም ገለልተኞች ነን " ሲል ገልጿል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ / ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
ግዙፉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንፃ ሊመረቅ ነው።

ባንኩ ፥ " ከምስራቅ አፍሪካ ረጅሙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ የዋና መ/ቤት ህንፃ ምርቃት ከባንኩ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ጋር ገጥሟል፡ " ብሏል።

በትክክል የሚመረቅበት ቀን ይፋ ይሆንም በቅርቡ ግን ህንፃው እንደሚመረቅ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የማኅደረ ስብሀት ወይብላ ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ ሚካኤል ታቦታት ወደ መንበረ ክብራቸው ገቡ። የማኅደረ ስብሐት ወይብላ ቅድስት ማርያምና የቅዱስ ሚካኤል ታቦታት ትላንት ካደሩበት ቀራንዮ መድኅኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በብጹእ አቡነ መልከጼዴቅ ፣ ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ፣በአድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፣ በብዙ መቶ…
" እየተፈጠረብን ያለውን ችግር ለመፍታት ቅዱስ ሲኖዶስ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል" - ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በማኅደረ መለኮት ወይብላ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው " እየተፈጠረብን ያለውን ችግር ለመፍታት ቅዱስ ሲኖዶስ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል" ሲሉ አስታውቀዋል።

ብፁዕነታቸው በቦታው ተገኝተው ሕዝበ ክርስቲያኑን ያፅናኑ እና ቡራኬ የሰጡ ሲሆን እየተፈጠሩ ያሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እስከ ሕይወት መስዋዕትነት እያስከፈለ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል ሲል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በፌስ ቡክ ገጹ አስነብቧል።

የተፈጠረውን ችግር ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ሪፖርት ማድረጋቸውን በመግለፅ ቅዱስ ሲኖዶስ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ብፁዕነታቸው አስታውቀዋል።

አክለውም ብፁዕነታቸው ምዕመናን አንድነታቸውንና ኅብረታቸውን በማጠናከር ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል ሲል ሀገረ ስብከቱ ገልጿል።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት

@tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ሕይወት አደጋ እንደተጋረጠበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) አስታወቀ።

በጦርነቱ ምክንያት የስደተኞቹ ኑሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበላሸ መሆኑንም ገልጿል።

በቅርቡ ማይ ዓይኒ እና አዲ ሐሩሽ በሚባሉ አካባቢዎች በሚገኝ የስደተኞች ጣብያ የሚኖሩ ስደተኞችን የመንግሥታቱ ድርጅት ሰራተኞች ጎብኝተዉ እንደነበር ድርጅቱ አስታውቋል።

ከ3 ሳምንት በፊት አካባቢዉ የአየር ድብደባ ከደረሰበት ወዲህ የድርጅቱ ሰራተኞች ስደተኞቹን መጎብኘት አልቻሉም ነበር።

ኤርትራዉያኑ ስደተኞች በቂ ምግብ፣ መድሐኒትና ንጹህ የመጠጥ ዉኃ የላቸዉም። ባለፉት 6 ሳምንታት ዉስጥ 20 ስደተኞች በመድሐኒት እጦት መሞታቸዉን ስፍራዉን የጎበኙት የUNHCR ሰራተኞች አስታዉቀዋል።

ትግራይ ዉስጥ የሚገኙ 25 ሺህ የኤርትራ ስደተኞን ወደ ሌላ ቦታ ለማዛወር ተኩስ አቁም እንዲደረግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠይቋል።

በሌላ በኩል ፤ በጦርነት ለተጎዳዉ የትግራይ ሕዝብ የሚሰጠዉ የአስቸኳይ ጊዜ ርዳታ እየተሟጠጠ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) ባወጣው ሪፖርት አሳውቋል።

ሙሉ ሪፖርት : https://reports.unocha.org/en/country/ethiopia/?s=09

ምንጭ፦ UNHCR , UN OCHA , DW

@tikvahethiopia
#Safaricom

" ሳፋሪኮም በፈረንጆቹ 2022 በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ 300 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ወጪ ያደርጋል " - አንዋር ሱሳ

የኬንያው የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም በፈረንጆቹ 2022 በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ 300 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ወጪ መዋዕለ ነዋይ እንደሚያፈስ ገልጿል።

የሳፋሪኮም የኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አንዋር ሱሳ ኩባንያው በተያዘው የፈረንጆቹ 2022 ወደ 300 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በኢትዮጵያ ፈሰስ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ስራውን ለመጀመር የኔትወርክ ዝርጋታ እያካሄደ መሆኑንና የመጀመሪያ የመረጃ ማዕከሉን በ100 ሚሊዮን ዶላር ወጪ መዘርጋቱን ተናግረዋል።

ሳፋሪኮም በመጪዎቹ ጥቂት ወራት ውስጥ አገልግሎቱን በይፋ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
" በሃይማኖታዊ በዓላት የታደሙ ምእመናንን መግደል ሃይማኖቱ ብሎም ሀገር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ነው " - እናት ፓርቲ

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እናት ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ጥር 12 እንደ ሃይማኖታቸው የአምልኮ እና ቀኖና ሥርዓት ታቦተ ሕጉን ወደ መንበረ ክብሩ ለመመለስ በማኅደረ መለኮት ወይብላ ማርያም ቤተክርስቲያን በታደሙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ላይ በጸጥታ ኃይሉ የተፈጸመው ግድያ ኢ ሕጋዊ፣ ኢ ሃይማኖታዊና የሞራል አልባነት ድርጊት ነው ብሎታል።

ጥንቱንም ላለፉት ዓመታት የመስቀልና የጥምቀት በዓላት በሚከበሩበት ጊዜ "ጠብ ያለሽ በዳቦ" ምክንያት እየፈለጉ ወከባ መፍጠር፣ ማሰር፣ መደብደብ ሕጋዊነት እስኪመስል ድረስ በተደጋጋሚ ሲፈጸም የቆየ ተግባር ቢሆንም በወይብላ ማርያም ያለፈውን ዓመት ጨምሮ መሰል ድርጊቶች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የጸጥታ አካላት እየተፈጸመ ነው ሲል ከሷል።

ፓርቲው ፥ " ሃይማኖት ለእኛ ለኢትዮጵያውያን እስትንፋሳችን መሆኑ እየታወቀ በየጊዜው ጸብ እየጫሩ ፓለቲካዊ ጉዳዮቻቸውን ሃይማኖታዊ ቀርጽ እንዲኖረው ለማስያዝ እየተሔደ ያለበት ርቀት በጊዜ ካልታረመ መዘዙ ከባድ ውጤቱም የከፋ መሆኑ የማይቀር ጉዳይ ነው " ሲል አሳስቧል።

እናት ፓርቲ ፥ የኦሮምያ ክልል መንግስት ሰለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሕዝብንም በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤ ድርጊቱን ባነሳሱ እና በፈጸሙ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ፣ የሕግ ውሳኔውም ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ፤ ለተጎጂ ቤተሰቦች እና ለሃይማኖቱ ተከታዮች የሞራል ካሳ እንዲከፈል፤ ያለአግባብ የታሰሩ ምዕመናንም በአስቸኳይ እንዲፈቱ አሳስቧል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
" መንግስት አጥፊዎችን ተከታትሎ ለህግ ማቅረብ ይገባዋል " - የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ

በጥምቀት በዓል ላይ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ወይብላ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን ድርጊት እንደሚያወግዝ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታውቋል።

ጉባኤው ሃይማኖቶች የትህትና፣ የሰላምና የአንድነት፣ የፍቅርና መከባበር መሠረቶች ናቸው ብሏል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት የሰላም መሠረት ሆና ዘልቃለች ያለው የጉባኤው መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን አጥብቀን እንቃዎማለን ሲልም ገልጿል።

ጉባኤው ፤ ጥር 12/2014 ዓ.ም በቡራዩ ከተማ አስተዳደር በሕግ ማስከበር ሽፋን በቤተክርስቲያኗ ላይ የተቃጣው ድርጊት ፍጹም ሕገ ወጥ ነው ያለው መግለጫው መንግሥት አጥፊዎችን ተከታትሎ ለሕግ እንዲያቀርብም ጠይቋል።

መንግሥት የሃይማኖትን እና የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የጠየቀው ጉባኤው የሕይዎት፣ የአካልና የመንፈስ ስብራት በደረሰባቸው ወገኖች የተሠማንን ጥልቅ ሐዘንም በተሰበረ ልብ እንገልፃለን ብሏል።

#EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ኢትዮጵያ 📍

ሞሊ ፊ እና ዴቪድ ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ ናቸው።

የአፍሪካ ህብረት (AU) ኮሚሽን ሊቀ መንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ መሀመት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ እና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሙሳ ፋኪ መሀመት ከሁለቱ የአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው ቆይታ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ገልፀዋል።

ሁለቱ የአሜሪካ ባለስልጣናት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በተለይ ለሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት መፍትሄ ለማፈላለግ ነው።

@tikvahethiopia
#Kenya #Ethiopia

" ... ምንም እንኳን ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም ኢትዮጵያ ከስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል አቅም አላት" - ራይቼል ኦማሞ

ኬንያ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቀውስ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ የምታደርገውን ጥረት ሁሉ በሰከነ ሁኔታ ተቀራርባ በመስራቷ እንደምትቀጥል አሳውቃለች።

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራይቼል ኦማሞ አገራቸው ኢትዮጵያን ችላ እንደማትላትና የሰከነና የተለሳለሰ ዲፕሎማሲን በመጠቀም በአገሪቱ የተከሰተው ችግር እንዲያበቃ አብራት መስራቷን ትቀጥላለች ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ሚኒስትሯ ይህንን የተናገሩት ትላንት የኬንያን የውጭ ፖሊሲ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች በተመለከተ ናይሮቢ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ራይቼል ኦማሞ ፥ " ምንም እንኳን ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም ኢትዮጵያ ከስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል አቅም አላት " ብላ ኬንያ እንደምታምን ገልጸው፣ ለዚህም በቅርቡ የፖለቲካ እስረኞች የመለቀቃቸው እርምጃን እንደ በጎ ጅማሬ ጠቅሰዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም በአገሪቱ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ በብሔራዊ ውይይት ፣ በተኩስ አቁም እና ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ መንገድ ማመቻቸትን በሚመለከት ከኢትዮጵያ ጋር ተቀራርበው ሲሰሩ እንደነበር መናገራቸውን ቢቢሲ በዘግባው አስፍሯል።

@tikvahethiopia
#SomaliRegion

የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሚካኤል ደንፎርድ ጋር ተወያይተዋል።

አቶ ሙስጠፌ በውይይቱ ፤ በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ሁኔታ ዙሪያ መክረዋል።

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመከላከል እና ህይወትን ለማዳን ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገውን የምግብ እርዳታን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተውበታል።

ምንጭ፦ የአቶ ሙስጠፌ የተረጋገጠ የትዊተር አካውንት

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

እድሳት የተደረገለት የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ህንፃ በነገው እለት እንደሚመረቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

ይህ ታሪካዊ እና የከተማዋ ምልክት የሆነ ህንፃ ከ57 ዓመት በኋላ ለእድሳት የበቃ መሆኑና የከተማዋ የዘመናት ጉዞ አሻራ የያዘ ታላቅ ቅርስ ጭምር መሆኑ ተገልጿል።

የከተማው አስተዳደር ፤ ህንፃውን እጀግ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲታደስ ማድረጉን ገልጾ ለተገልጋይ ምቹና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ሁሉ ባሟላ መንገድ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆን ታስቦ መሰራቱን አሳውቋል።

@tikvahethiopia