TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምዕራፍ ሁለት!

ለ2 ሳምንት የሚቆይ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ #NoHateSpeechMovement /ETHIOPIA/ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጩ ያሉ የጥላቻ ንግግሮችን የምንዋጋበት፤ የተለያዩ መልዕክቶችን ፖስት በማድረግ ጥላቻን የምናሸንፍበት ሳምንታት ይሆናሉ! #ቲክቫህኢትዮጵያ

ዘመቻው የሚካሄደው፦
#Facebook
#Telegram
#Twitter ላይ ይሆናል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🚫STOP HATE SPEECH🚫

#TikvahEthiopia #Facebook #Telegram #Twitter ሀገራችንን እናድን! የጥላቻ ንግግሮች ሀገራችንን ወደአስፈሪ ሁኔታ ውስጥ እየከተታት ይገኛል። ሁላችም ከጥላቻ ንግግሮች ራሳችንን በማራቅ ሀገራዊ ሀላፊነታችንን እንወጣ!

#ከጥላቻ_ንግግሮች_እንቆጠብ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Twitter #Ethiopia

ጃክ ፓትሪክ ዶርሴይ ኢትዮጵያን እየጎበኙ ነው!

የትዊተር ዋና ስራ አስፈፃሚ ጃክ ፓትሪክ ዶርሴይ በኢትዮጵያን ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡ ዋና ስራ አስፈፃሚው ለአንድ ወር በቆየው የአፍሪካ ጉብኝታቸው ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጀሪያ እና ጋናን የጎበኙ ሲሆን የመጨረሻ መዳረሻቸን ኢትዮጵያ አድርገዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጠሪ የሆነው ማህበራዊ ሚዲያ ዋና ስራ አስፈፃሚ በኢትዮጵያን ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ጃክ ፓትሪክ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከቴክኖሎጂ ንግስቷ ቤተልሄም ደሴ እና የአፍሪካ ቴክ ኔክስት አንዱ መስራች ከሆነው ኖኤል ዳንኤል ጋር ውይይቱ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እንዲሁም ዋና ስራ አስፈፃሚው ከሌሎቸ በርካታ ስራ ፈጣሪዎች ጋር ሰፊ ጊዜን እንደሚያሳልፉ ነው የተነገረው፡፡ የትዊተር ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ጃክ ፓትሪክ ዶርሴይ በአሜሪካ የኮሙፒውተር ፕሮግራመር እና ኢንተርኔት ስራ ፈጣሪ እንዲሁም ስኩዌር የተባለው የሞባይል የክፍያ ኩባንያ ስራ አስፈፃሚ ናቸው፡፡

(ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Twitter

ትዊተር ላይ 88.7 ሚሊዮን ተከታዮች ያሏቸው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስከመጨረሻው ትዊተር እንዳይጠቀሙ አካውንታቸው ታገደ።

ትዊተር እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ትራምፕ በአካውንታቸው ላይ 'በቅርቡ ያሰፈሯቸውን መልዕክቶች በደንብ ከመረመረ' በኋላ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#twitter

ትዊተር ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ "ህግ የጣሱ " ያላቸዉን ተጠቃሚዎች ማገዱን ዛሬ አሳውቋል።

ትዊተር እንዳለው ብዙ አካዉንቶች ታግደዋል፤ ከታገዱት መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩት የትግራይ ደጋፊ ተጠቃሚዎች ይመስላሉ ብሏል።

ይሁንና ትዊተር የታገደዉ አካዉንት መጠን ምን ያህል እንደሆን በውል አልገለፀም።

ትዊተር እርምጃዉ የተወሰደው "የትዊተርን ህግ በመጣስ፣ የተወሰኑ ሃሽታጎች እና የትዊተር ገፆች፤ በተለጠፈዉ መረጃ ላይ በተደጋጋሚ በአላስፈላጊ ሁኔታዎች በማካተታቸው ነው። በተጨማሪ ርምጃዉ " በኢትዮጵያ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተገናኘ በትዊተር ላይ የሚደረጉ ውይይቶች ደኅንነታቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲሄድ ከምናደርገው ጥረት ጋር የተገናኘ ነው " ብሏል።

እገዳዉን በተመለከተ " በተጨባጭ በአካውንቶቹና ይዘቶቹ ላይ ያተኮሩ " መሆኑን እና " ከፖለተካዊ ማንነት እና ርዕዮተ ዓለም ገለልተኞች ነን " ሲል ገልጿል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ / ዶቼቨለ

@tikvahethiopia