TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አርቲስት ኑሆ ጎበና ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

አርቲስት ኑሆ ጎበና ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አርቲስት ኑሆ ጎበና በአፋን ኦሮሞና በተለያዩ ቋንቋዎች በርካታ ዜማዎችን ለአድማጭ አበርክቷል፡፡

አርቲስት ኑሆ ፤ ከአባቱ አቶ መሃመድ ጎበና እና ከእናቱ ወይዘሮ ፋጡማ አደም በ1940 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ነበር የተወለደው፡፡

#ኤፍቢሲ/#ኦቢኤን

@tikvahethiopia
#Photo

የጥምቀት በዓል እየተከበረ ይገኛል።

የበዓሉን ገፅታ የሚያሳዩ ፎቶች ከአ/አ፣ ደሴ፣ ጎንደር፣ ሀይቅ ፣ ኮምቦልቻ፣ ቡሌ ሆራ ፣ ነቀምቴ፣ ቦንጋ፣ አርባ ምንጭ ፣ ሀዋሳ ፣ ወላይታ ሶዶ ፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ ፣ ግልገል በለስ ፣ ድሬዳዋ ፣ሀዋሳ እንዲሁም ከሌሎች ከተሞች በማሰባሰብ ወደ ስልካችሁ ልከናል።

የፎቶ ስብስቦቹ ይመልከቱ 👉 https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-19

ሁሉም ፎቶዎች ምንጫቸው የተገለፀበት ነው።
TIKVAH-ETHIOPIA
#AliBira አንጋፋው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል ህክምና እየተከታትሉ ይገኛሉ። የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ህክምና እየተከታተሉ በሚገኙበት ሆስፒታል በአካል በመገኘት እንደጠየቋቸው የጉሙሩክ ኮሚሽን አሳውቋል። ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ለክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ከህመማቸው ተፈውሰው የሚወዱትን ሙያ…
#AliBira

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፤ ክቡር ዶክተር አሊ ቢራን ህክምና በሚከታተሉበት ሆስፒታል ተገኝተው ጠይቀዋቸዋል።

ከዚህ ቀደም አንጋፋው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል ህክምና እየተከታትሉ እንደሚገኙ መገለፁ ይታወሳል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ህክምና እየተከታተሉ በሚገኙበት ሆስፒታል በአካል በመገኘት እንደጠየቋቸው መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

እስር ላይ ከነበሩት ጋዜጠኞች መካከል ጋዜጠኛ እና አክቲቪስት ኢያስፔድ ተስፋዬ ዛሬ ከእስር ተፈቷል።

ኡቡንቱ የተባለው ሚዲያ መስራችና ጋዜጠኛ እያስፔድ ተስፋዬ ዛሬ ከቀትር በኋላ ነው ከእስር እንደተፈታ ሚዲያው የገለፀው።

ጋዜጠኛ እና አክቲቪስት እያስፔድ 43 ቀናት በእስር ሲቆይ ፖሊስ አንድም ጊዜ ፍርድ ቤት እንዳላቀረበው እና ክስም እንዳልመሠረተበት ሚዲያው ገልጿል።

በትላንትናው ዕለት ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ ከእስር መፈታቷ ይታወቃል።

ሌሎች በእስር ላይ ከሚገኙ ጋዜጠኞች መካከል ተራራ ኔትዎርክ የተባለው ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ የአሐዱ ሬዲዮ ባልደረባ ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ ስለመፈታታቸው የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Somaliland በሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የሚመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ዛሬ ማለዳ ወደ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ማቅናቱ ተነግሯል። ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተደረገላቸው ይፋዊ ግብዣ መሰረት ነው ወደኢትዮጵያ እንደሚመጡ የተገለፀው። በሌላ በኩል ፥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢሳ ካይድ የሚመራ የልዑካን ቡድን ከፕሬዜዳንቱ ሙሴ ቢሂ አብዲ ቀደም…
የፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የኢትዮጵያ ቆይታ ፦

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ግብዣ ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡ የተነገረላቸው የሶማሊላንድ ፕሬዤዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ወደ ሀርጌሳ ተመልሰዋል።

ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የሲዳማ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈው ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥምቀት የኢፌዴሪ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዛሬ ባወጣው መግለጫ የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን አሳውቋል። የበዓሉ ታዳሚዎችና እንግዶች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆንና በዓሉን በሰላም እንዲከበር ግብረ ኃይሉ ከወትሮው በተለየ መልኩ በቂ ዝግጅት በማድረግ ስምሪት ወስዶ ወደ ተግባር መግባቱን ገልጿል፡፡ ግብረኃይሉ ፥ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች…
" የ2014 ዓ/ም የጥምቀት በዓል በሰላም ተጠናቋል " - የፀጥታና ደህንነት የጋራ-ግብረ ኃይል

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ -ግብረ ኃይል የጥምቀት በዓል በሰላም መጠናቀቁን አስታውቋል።

የጋራ-ግብረ ኃይሉ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማን ጨምሮ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በዓሉ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን ገልጿል።

ለበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ ሕዝበ ክርስቲያኑ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የደብር ኃላፊዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም በዓሉን ለማስተባበር በየደረጃው የተዋቀሩ ኮሚቴዎች ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ግብረ-ኃይሉ ምስጋና አቅርቧል።

በተመሳሳይም ይህ ታላቅ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡት የግብረ-ኃይሉ አባላት ምስጋና ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የተመድ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጎተሬዥ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ ክቡር ኦሊሲንጎ ኦቦሳንጆ በኢትዮጵያ ባለው ግጭት ዙሪያ በመቐለ እና በአዲስ አበባ ያደረጉትን ግብኝት ተከትሎ የስልክ ውይይት አድርጌያለሁ ሲሉ አስተውቀዋል።

ሰላም ለማስፈን የሚያስችል ተጨባጭ ጥረት በመኖሩ ተደስቻለሁ ብለዋል፡፡

" ኦሊሴንጉ ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ግጭቱን ለማስወገድ እያደረጉ ስላሉት ጥረት ገለጻ አድርገውልኛል” ያሉት ዋና ጸሀፊው ግጭቱና ጥቃቱ እንዲያበቃ አሁን ፖሊካዊና ዲፕሎማሲያዊ እልባት ለመስጠት የሚያስችል ትክክለኛ እድልና አጋጣሚ ስለመኖሩ ተስፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ጉተሬዥ ከአንድ ዓመት በላይ በመላው ኢትዮጵያና በአካባቢው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለጉዳት ከዳረገው ግጭት በኋላ አሁን ሰላም ለማስፈን የሚያስችል ተጨባጭ ጥረት በመኖሩ ተደስቻለሁ ብለዋል፡፡

በአንዳንድ የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች አሁንም የሚካሄደው ውጊያ ለሰላም ሂደቱ መራር ፈተና መሆኑን የገለጹት ዋና ጸሀፊው በሁሉም ወገኖች ዘንድ መተማመን የሚፈጥሩ ጠንካራ እምርጃዎች እየተወሰዱ ነው ብለው ተስፋ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ጎተሬዥ አሁንም ሰላምን ለማስፈን ትክክለኛው አቅጣጫ ሁሉም ወገኖች ግጭቱን ማቆሙ ያላባቸው መሆኑን ያቀረብኩትን ጥሬዬን እንደገና አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ኢትዮጵያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ባለቤትነት የሚመራ ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ የሰላም የደህንነትና የእርቅ ሂደትን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ሁሉም ወገኖች ለሰላሙ ሂደት በቅንነትና በቁርጠኝነት እንዲሳተፉ የሚያደርገውን ጥረት መቀጠል አለበት ማለታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዴቪድ ሳተርፊልድ እና ሞሊ ፊ ሳዑዲ አረቢያ ይገኛሉ። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ እና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ትላንት ሳዑዲ አረቢያ ገብተዋል። የሳውዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን ሁለቱን የአሜሪካ ባለስልጣናት ተቀብለው አነጋግረዋል። በውይይታቸው ወቅት በሳዑዲ አረቢያ እና…
#Update

ሞሊ ፊ እና ሳተር ፊልድ በሱዳን ውይይት አድርገዋል።

በቀናት በፊት ሳዑዲ አረቢያ የነበሩት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ እና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ሱዳን ገብተው በሱዳን ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

ሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቀጣይ በአዲስ አበባ ተገኝተው ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

@tikvahethiopia