TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AliBira

አንጋፋው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል ህክምና እየተከታትሉ ይገኛሉ።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ህክምና እየተከታተሉ በሚገኙበት ሆስፒታል በአካል በመገኘት እንደጠየቋቸው የጉሙሩክ ኮሚሽን አሳውቋል።

ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ለክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ከህመማቸው ተፈውሰው የሚወዱትን ሙያ እንዲቀጥሉ እና ሀገራቸውን በኪነጥበብ መስክ እንዲያገለግሉ መልካም ምኞታቸውን እንደገለፁላቸው ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AliBira አንጋፋው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል ህክምና እየተከታትሉ ይገኛሉ። የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ህክምና እየተከታተሉ በሚገኙበት ሆስፒታል በአካል በመገኘት እንደጠየቋቸው የጉሙሩክ ኮሚሽን አሳውቋል። ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ለክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ከህመማቸው ተፈውሰው የሚወዱትን ሙያ…
#AliBira

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፤ ክቡር ዶክተር አሊ ቢራን ህክምና በሚከታተሉበት ሆስፒታል ተገኝተው ጠይቀዋቸዋል።

ከዚህ ቀደም አንጋፋው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል ህክምና እየተከታትሉ እንደሚገኙ መገለፁ ይታወሳል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ህክምና እየተከታተሉ በሚገኙበት ሆስፒታል በአካል በመገኘት እንደጠየቋቸው መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#AliBira #NuhoGobena

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አንጋፋውን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራን በመኖሪያ ቤታቸው ተገኝተው መጠየቃቸውን ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የጉሙሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ህክምና ሲከታተሉበት በነበረው ሆስፒታል ተገኝተው መጠየቃቸው ይታወሳል።

በሌላ መረጃ በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የኦፌኮ ከፍተኛ አመራሮቹ አቶ ጃዋር መሐመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ እንዲሁም ሀምዛ ቦረና በአዳማ ተገኝተው በቅርቡ ከዚህ ዓለም ሞት የተለዩት አርቲስት ኑሆ ጎበና ቤተሰቦችን አጽናንተዋል።

በተጨማሪ በክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ መኖሪያ ቤት በመገኘት አርቲስቱን ጠይቀዋል።

Photo Credit : AA Mayor Adanech Abiebie & Meseret Daba

@tikvahethiopia