ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ❤️
ሀገራችን ከስምንት አመታት ቆይታ በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው በመመለስ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት 4:00 ላይ ታደርጋለች።
ብሄራዊ ቡድናችን በምድቡ የመክፈቻ ጨዋታ ኬፕ ቨርዴን የሚገጥም ይሆናል።
ቡድናችን ውድድሩ ሳይጀምር ቀደም ብሎ ካሜሮን በመግባት ጠናካራ ልምምድ ሲያደርግ መቆየቱ አይዘነጋም።
በካሜሩን የሚገኙ የቲክቫህ አባላት በቀጥታ ከስፍራው መረጃዎችን @tikvahethsport በኩል ይልኩላችኃል።
መልካም እድል ለብሄራዊ ቡድናችን !
@tikvahethsport

#UPDATE
በጎንደር ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተነስቷል።
በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ በአስቸካይ ጊዜ አዋጅ ተጥለዉ የነበሩ ክልከላዎች ዉስጥ የሰዓት ገደቡ ተነስቷል።
ከምሽቱ 4.00 እስከ 11.30 የነበረዉ ክልከላ የተነሳ እና 24 ሰዓት በሰላም ሁሉም አካል ፣ ተሸከርካሪም ጭምር መንቀሳቀስ እንደሚቻል ትላንት ተወስኗል።
ሌሎች ክልልከላዎች ግን የሚቀጥሉ ይሆናል።
በዚህም መሰረት ፦
• ከተፈቀደለት የጸጥታ አካሉ ዉጭ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
• ማንኛዉም ሰዉ መሳሪያ/ተተካሽ/ ይዞ ወደ መጥጥ ቤት ይዞ መግባት ሆነ መዝናናት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
• እንግዶችን ሆነ ማንኛዉንም ሰዉ ማዋከብ መረበሽ የተከለከለ ነው።
• አግባብነት የሌለዉ ዋጋ በማናቸዉም ሽያጮች አገልግሎቶች መጨመር የተከለከለ ነዉ።
• ማንኛዉም ሰዉ የሚመለከታቸዉ የጸጥታ አካላት መታወቂያ እንዲያሳይ ሲጠየቅ የማሳየት #ግዴታ አለበት።
• የብሎክ አደረጃጀት ጥበቃዉ የማይቃረጥና ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
• በፀጥታ አካሉ አማካኝነት የኬላ ፍተሸ የድነገተኛ ፍተሻ ተጠናክረዉ የሚቀጥሉ ይሆናል።
የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ዘንድ ሁሉም ሰዉ ከፀጥታ አካሉ ጎን እንዲቆም ፤ ከአቅም በላይ የሆኑ የጸጥታ ችግሮች ሲገጥሙ በአቅራቢያ ለሚገኘዉ የፖሊስ ጣቢያ ሪፖረት ማድረግ ወይም በየአካባቢዉ ለሚገኝ የፀጥታ አካል ሪፖርት በማድረግ የመተባበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
መረጃው ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ኮማንድ ፖስት የተገኘ ነው።
@tikvahethiopia

#DStvEthiopiaPoloTeam
ዲኤስቲቪ ኢትዮጵያ እንደ እግር ኳሱ ሁሉ የኢትዮጵያን ባህላዊ ስፖርት በመደገፍ ረጂም ዘመናትን አስቆጥሯል። የራሱን የገና ጨዋታ ቡድን በማዋቀርም በጃንሜዳ የሚከናወነውን ዓመታዊ የኢትዮጵያ ገና ጨዋታ ውድድር ሲካፈል ቆይቷል።
ዛሬ በጃንሜዳ በድምቀት የተከናወነው የዚህ ዓመቱ የገና ጨዋታ ውድድር በዲኤችገዳ አሸናፊነት ተጠናቋል።
የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ተወካይ፣ የገና ጨዋታ ፌደሬሽን ኃላፊዎች ና የዲኤስቲቪ ተወካዮች ለአሸናፊዎቹ የሜዳሊያ ሽልማት አበርክተዋል።የተራራ ቡና እና የዲኤች ገዳ ዱቄት ስጦታም ተበርክቶላቸዋል።
ዲኤስቲቪ ባህላዊ የኢትዮጵያ ስፖርት እንዲያድግ ወደፊትም ድጋፉን ይቀጥላል።
#DStvEthiopia
#GenaChewata
#PoloSport2022

የአፍሪካ ህብረት (AU) የታሳሪዎችን መፈታት በደስታ እንደሚቀበል አስታወቀ።
የአፍሪካ ህብረት ዋና ፀሀፊ ሙሳ ፋኪ ማሀመት ትላንት ቅዳሜ ባወጡት መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ እስረኞችን መፍታቱን በደስታ እንደሚቀበሉት አሳውቀዋል።
ዋና ፀሀፊው ፥ የታሳሪዎቹ መፈታይ በሀገሪቱ የፖለቲካ ንግግር ለማድረግ እንዲሁም ለብሄራዊ እርቅ አስፈላጊ እርምጃ ነው ብለዋል።

#ETHIOPIA
የአውሮፓ ህብረት (EU) በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች ከእስር መፈታት እና ብሄራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋም አውንታዊ እና በጎ እርምጃ መሆኑን አሳውቋል።
ከወቅታዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የአውሮጳ ህብረት የውጭ እና የደህንነት ጉዳይ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል መግለጫ አውጥተዋል።
ቦሬል ፥ የተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎችን ከእስር መፈታት እና የብሄራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋም የሰሜን ኢትዮጵያን ግጭት ለማስቆም አውንታዊ እና በጎ እርምጃ መሆኑን ገልፀዋል።
ለሰላማዊ እና ዘላቂ መፍትሄ ብቸኛው አማራጭ ማንንም ወደ ኋላ የማይተው ገለልተኛ፣ ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ ውይይት መሆኑን የአውሮፓ ህብረት ሁሌም ያሳስባል ብለዋል።
ይሁን እንጂ አወንታዊ እርምጃዎች ቢኖሩም ግጭቱ እንደቀጠለ ነው ያሉት ጆሴፕ ቦሬል ቅዳሜ በአገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎች በሚገኙበት ካምፕ ላይ በተፈፀመ የአየር ድብደባ የንፁሀን ዜጎች ህይወት አልፏል ፤ ተጎድተዋል ብለዋል።
ቦሬል ፥ በችግር ላይ ያሉ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ አፋጣኝ እና ያልተደናቀፈ ሰብአዊ እርዳታ መፍቀድ አለበት ፥ ከታህሳስ አጋማሽ ጀምሮ የሰብዓዊ እርዳታ ጭኖ ወደ ትግራይ ክልል የገባ ተሽከርካሪ የለም ብለዋል።

" ሁሉ በሕግ እና በሕግ ብቻ ይሁን " - እናት ፓርቲ
እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ አውጥቷል።
እናት ፓርቲ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ካለችበት ውጥንቅጡ የወጣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዞ ወጥታ፣ ችግሯ በዘላቂነት ተፈቶ፣ ሰላሟ የተረጋገጠ ሀገር እንድትሆን ጽኑ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
ነገር ግን ሕጋዊ ሂደትን ባልጠበቀ እና በማናለብኝነት ውሳኔዎችን መወሰንና ተግባራዊ ማድረግ የገዥው ፓርቲ አሠራር ሆኖ ቆይቷል፤ አሁንም እየሆነ ነው ሲል ተችቷል።
የትኛውም አካል የሀገር መሪዎችን ጨምሮ ሁሉም ሰው ከሕግ በታች መሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነው ያለው እናት ፓርቲ በወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብም ይሁን ድርጅት ህጋዊ ሂደት ሳይጠብቅ “ክስ ማቋረጥ” ማሰናበት በሕግ ተቋማት ሥራ ላይ ያለውን ጣልቃገብነት ከማሳየቱም ባሻገር የፈላጭ ቆራጭነት ማሳያ ነው ብሏል።
በሀገሪቱ መከላከያ ሠራዊት እንዲሁም በሰላማዊ ዜጎች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙ፣ የአካል ጉዳት ያደረሱ፣ ንብረት ያወደሙ ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአማራ እና አፋር ሕዝቦችን ያፈናቀሉ እና ለትግራይ ሕዝብ ለአሥርት ዓመታት በሰቆቃ ሕይወት መኖር ተጠያቂ የሆኑ፣ እናቶችና ሕጻናት እንዲደፈሩ ያደረጉ አመራሮች ላይ ኢሕጋዊ በሆነ ሁኔታ ታሕሳሥ 29 ቀን 2014 ዓ.ም የተወሰነው ውሳኔ የፓርቲውን አምባገነንነት የሚያሳይ ነው ሲል ፓርቲው ተችቷል።
ከብዙ ታሳሪዎች መካከል “ በእድሜ የገፉ ስለሆነ ” በሚል ምክንያት ሀገር ለሕልውና እያደረገች ያለውን ጦርነት ዓላማ የሳተ፣ የሕግ አሠራር ሂደትን የጣሰ፣ በግለሰቦችና ገዢው ፓርቲ ፍላጎት ብቻ ዜጎች የሚታሠሩበት እና የሚፈቱበት መሆኑን ማሳያ ነው ብሎታል።
* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

#HappeningNow
በአሁኑ ሰዓት የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የአውደ ውጊያ ውሎ የሜዳሊያ ሽልማት እና አዲሱ የመከለከያ ጠቅላይ መምሪያ ህንጻ ምረቃ እየተከናወነ ይገኛል።
በስነ ስርዓቱ ላይ የሰልፍ እና የአየር ትርዒትም ቀርቧል።
#FDREDefenseForce

#Update
ወደር የሌለው የጥቁር አንበሳ ጀግና ሜዳይ በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተሽለሙ ፦
1. ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
2. ጀነራል አበባው ታደሰ
3. ጀነራል ባጫ ደበሌ
4. ሌ/ጀ አለምሸት ደግፌ
የአደዋ ድል ጀግና ከፍተኛ ሜዳይ በጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተሽለሙ ፦
1. ጀነራል ጌታቸው ጉዲና
2. ሌ/ጀነራል በላይ ስዩም
3. ሌ/ጀነራል ዘውዱ በላይ
4. ሌ/ጀነራል መሰለ መሠረት
5. ሌ/ጀነራል ሹማ አብደታ
6. ሌ/ጀነራል አብዱራህማን እስማኤል
7. ሌ/ጀነራል ይልማ መርዳሳ
8. ሌ/ጀነራል ሰለሞን ኢተፋ
የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት የመዘከሪያና የመከላከያ ሠራዊት ዋና መሥሪያ ቤት የማስመረቅ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።
#PMOEthiopia #FDREDefenseForce