TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba : በወሰን ማስከበር ችግር ምክንያት ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረው የሮባ ዳቦ ቤት - ገርጂ መብራት ሀይል የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣ አስታውቋል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ ካለው አጠቃላይ 973 ሜትር ርዝመት ውስጥ ከ100 ሜትር በላይ የሚሆነው በወሰን ማስከበር ችግር ምክንያት ለረጅም ጊዜ ግንባታው ተቋርጦ ቆይቷል።

የወሰን ማስከበር ችግሩ ከተፈታ በኋላ ቀሪውን የግንባታ ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቁ አሁን ላይ ለትራፊክ አገልግሎት ክፍት እንዲሆን ተደርጓል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ መጠናቀቅ መቻሉ ከሮባ ዳቦ ቤት በገርጂ መብራት ወደ ጃክሮስ አካባቢ ለሚደረገው ጉዞ አቋራጭ መንገድ በመሆን የሚያገለግል ይሆናል፡፡

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ ከሚገነባቸው ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ- ቱሉ ዲምቱ መንገድ በታቀደለት ግዜ ገደብ እንዳይጠናቀቅ የወሰን አለመከበር ማነቆ ሆኗል።

የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ- ቱሉ ዲምቱ አስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀከት በአሁን ሰአት ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

በህዳር 2011 ዓ.ም የተጀመረው የቃሊቲ ቶታል- አቃቂ ድልድይ- ቱሉ ዲምቱ አስፋልት መንገድ ፕሮጀከት አጠቃላይ ርዝመቱ 5.6 ኪ.ሜትር እና 25 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡

አሁን ላይ 2.7 ኪ.ሜትር የሚሆን የአስፋልት ማልበስ ስራ፣ ሰብ ቤዝ ፣ ድጋፍ ግንብ፣ የፓይፕ ቀበራ ፣ የእግረኛ መንገድና ተያዥ ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቪድዮ የኡጋንዳ ጦር ከጎረቤቱ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) ሃይሎች ጋር በመሆን በ Allied Democratic Force (ADF) ታጣቂ ቡድን ላይ በጋራ የአየር ድብደባ እና የመድፍ ጥቃት መፈፀሙን ትላንት አሳውቋል። ዛሬ ደግሞ ኡጋንዳ ይህን የታጠቀ ቡድን ለማደን እና ለመቅጣት ጦሯን ድንበር አሻግራ ወደ ኮንጎ መላኳ ተሰምቷል። የኡጋንዳ ባለስልጣናት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በካምፓላ ለደረሰው…
#Update

የኡጋንዳ እና የኮንጎ ዴሞክራቲኮ ሪፐብሊክ ሠራዊት ጥምረት በኮንጎ ምስራቃዊ ግዛት ውስጥ የሚገኙ አማጽያንን ጠንካራ ይዞታዎች መደምሰሳቸውንና 35 አማጽያንን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን አስታውቀዋል።

ከሁለቱ አገሮች የተውጣጣው ጦር “ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሰሜን ኩቩ እና ኢቱሪ ክፍለ ግዛት ውስጥ የሚገኙ አዳዲስ የጠላት ሰፈሮችን ” ማጥቃታቸውን የኮንጎ ጦር ሠራዊት ባወጣው መልዕክት አስታውቋል፡፡

እኤአ ህዳር 30 የሁለቱ አገሮች ጥምረት ጦር እምርጃ መውሰደ ከጀመረ ወዲህ፣ ብዙ ሰላማዊ ሰዎች ላይ በዩጋንዳና ኮንጎ ውስጥ ለደረሰው የሽብር እልቂት ተጠያቂ የሆነውን የተባበሩት ዴሞክራቲክ ኃይሎች ወይም ADF እየተባለ የሚጠራውን የአማጽያን ቡድን መደምሰሱን ማስታወቁን ቪኦኤ ዘግቧል።

ADF በዩጋንዳና ኮንጎ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ለደረሱ የቦምብ ፍንዳታዎች ተጠያቂ የተደረገ ድርጅት መሆኑም ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ለንግድ ወደ ሀገር የሚገቡ እቃዎች የሚባሉት የትኞቹ ናቸው ?

ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት በስተቀር ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ማናቸውም ዕቃዎች ለንግድ የሚውሉ ዕቃዎች ናቸው።

1. በፌደራል እና በክልል የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት ለመንግስት መ/ቤት በተሰጠው ትርጉም ውስጥ የተካተቱ የፌደራል መንግስት መ/ቤቶች እና የክልል መንግስታት መ/ቤቶች የሚያስገቧቸው ዕቃዎች፣

2. ለትርፍ ያልተቋቋሙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ማህበራት የሚያስገቧቸው እቃዎች (ከተቋቋሙበት አላማ ውጭ በንግድ መልክ የሚያስገቧቸውን ዕቃዎች አይጨምርም)፣

3. በዲፕሎማቲክ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት ከንግድ ትርፍ ግብር ነፃ የሆኑ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የውጭ ዲፕሎማቲክ ወይም ኮንሱላር ሚሲዮኖችና የእነዚሁ አባላት የሚስገቧቸው ዕቃዎች፡፡

4. የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ ቁጥር 51/2010 መሰረት የግል መገልገያ እቃዎችን ከቀረጥ ነፃ ወይም ቀረጥና ታክስ ከፍለው እንዲያስገቡ የተፈቀደላቸው ግለሰቦች የሚያስገቧቸው እቃዎች፣

5. በጉምሩክ ታሪፍ ደንብ 2ኛ መደብ (ለ) ተጠቃሚ ሆነው እቃዎችን የሚያስገቡ ግለሰቦችና ድርጅቶች፣

6. በፌደራልና በክልል ኢንቨስትመንት ባለስልጣን ከገቢ ግብር ነፃ የመሆን መብት የተፈቀደላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች በእፎይታው ጊዜ ውስጥ የሚያስገቧቸው እቃዎች፣

7. የአምራችነት ፍቃድ ያላቸው ሰዎች ወይም ድርጅቶች ለሚያመርቷቸው ዕቃዎች በግብዓትነት የሚጠቀሙባቸው ጥሬ ዕቃዎች እና ለካፒታል ዕቃዎች የሚያገለግሉ መለዋወጫዎች ፣

8. ኢንዱስትሪዎችን ለማቋቋም ወይም ለማስፋፋት ወይም ለሃይል ማመንጨት ወይም የመገናኛ አገልግሎት ለመዘርጋት ወዘተ ወደ አገር የሚገቡ የካፒታል ዕቃዎች ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከተው አካል የካፒታል ዕቃዎች መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከቀረበ፣

9. የንግድ ትርኢት ለመሳተፍ የሚመጡ የውጪ አገር ድርጅቶች ምርታቸውን ለማስተዋወቅ ወደ ውስጥ ይዘውት የሚገቡት እቃዎች፣

10. በማዕድን እንዲሁም በፔትሮሊየም ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ለነዚህ ስራዎች አገልግሎት እንዲሰጡ የማያስገቧቸው እቃዎች እና

11. ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውሉ እቃዎች

ከላይ ከተዘረዘሩት ውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ሌሎች ማናቸውም እቃዎች ለንግድ የሚውሉ ዕቃዎች ተብለው ይታያሉ፡፡

ወደ አገር ከሚገቡ ለንግድ ከሚውሉ ዕቃዎች የቅድሚያ ግብር ስለመሰብሰብ ፦

1. ዕቃዎቹ ወደ አገር በሚገቡበት ጊዜ በቅድሚያ ግብር የሚከፈለው በጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች በኩል ይሆናል ፡፡

2. በጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች ለንግድ ከሚውሉ እቃዎች የቅድሚያ ግብር ሲሰበስቡ የግብር ከፋዩን ሥም፤ አድርሻ እና የግብር ከፋዩን መለያ ቁጥር በመጠቀም መመዝገብና ሂሰቡን በዚሁ መሠረት መያዝ አለባቸው።

3. በጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤቶች ከተከፋይ ሂሣቦች ላይ በቅድሚያ ተቀናሽ የሚደረገው የቅድመ-ታክስ ክፍያ ገቢ ባለቤት ለሆኑት ገቢ ሰብሳቢ አካላት በተዘረጋው ሥርዓት መሠረት ይተላለፋል፡፡

ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#AfaanOromoo

ወደ አፋን ኦሮሞ እየተተረጎመ ባለው የቋንቋ ፖሊሲ ላይ ሰኞ ዕለት በኦሮሞ ባሕል ማዕከል ውይይት መካሄዱ ተገለጸ፡፡

ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ 5 የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የመንግስት የሥራ ቋንቋ ሆነው እንዲያገለግሉ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቁ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተዘጋጅቶ የነበረው የኢትዮጵያ የቋንቋ ፖሊሲ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ሥራ ላይ ውሏል ነው የተባለው፡፡

በውይይቱ በሀገራችን ተጨማሪ 5 ቋንቋዎች የመንግስት የሥራ ቋንቋዎች እንዲሆኑ መወሰኑን ተከትሎ የቋንቋ ፖሊሲውን ወደ አፋን ኦሮሞ መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ ተመላክቷል፡፡

የፖሊሲ ትርጉም ሥራውን ለማስጀመር የጥናትና ምርምር ኢኒስቲትዩት ከኦሮሚያ ባሕልና ቱሪዝም ጋር በመተባበር የቋንቋ ምሁራንን ያሳተፈ ውይይት በኦሮሞ ባሕል ማዕከል አድርገዋል፡፡

የቋንቋ ፖሊሲውን በጥንቃቄ ወደ አፋን ኦሮሞ ቋንቋ ለመተርጎም የቋንቋ ምሁራን ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንዳለው የኦሮሚያ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ ብርሃኑ ቡጤ ገልጸዋል፡፡

የቋንቋ ምሁራኑ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ እንደሆኑ መጠቆሙን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Vodafone #Safaricom #Ethiopia

የቮዳፎን ቡድን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሻሚል ጁሰብ እና የሳፋሪኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፒተር ንዴግዋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዋና አስተዳዳሪ ከሆኑት ዶ/ር ይናገር ደሴ ጋር እና ከተለያዩ ም/ አስተዳደሮች ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

የቮዳኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ድርጅታቸው ኢትዮጵያን አካቶ በመሥራቱ በአህጉሪቱ ትልቁ የፋይናንስና ቴክኖሎጂ ተቋም የመሆን ዕድሉ ያለው መሆኑን በማንሳት፤ ዶ/ር ይናገር ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ቡድን ላደረጉት አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል።

የሳፋሪኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፒተር ንዴግዋም የኢትጵያ መንግስት ጥረታቸውን ለመደገፍ ያሳየው ፈቃደኝነት የሚያነቃቃ መሆኑን አንስተው፤ በኬንያ እየተተገበሩ ያሉ የሞባይል የፋይናንስ ሥርዓቶችን ተሞክሮ ለማጋራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር ይናገር ደሴ በበኩላቸው ለቀጠለ አጋርነታቸው የአመራር ቡድኑን አመስግነው፤ የሞባይል የክፍያ መንገዶች ለአካታች የፋይናንስ ሥርዓት መንገድ የሚከፍቱ እንደሆኑና በኬንያ ከተገኘው ስኬት ለምድ በመቅሰም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሥርዓት ለማሻሻል ያላቸውን ጉጉት መግለፃቸውን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከአናዶሉ ኤጀንሲ ጋር ልዩ ቃለ ምልልስ አድርገዋል። የተነሱ ጉዳዮች ፦

• የግጭቱ ወቅታዊ ሁኔታ
• የውጭ ጣልቃገብነት
• የኢትዮ-ቱርክ የሁለትዮሽ ግንኙነት
• የኢትዮጵያ እና የሱዳን የድንበር ግጭትና ሌሎች ጉዳዮች ተነስተዋል።

ቃለምልልሱ ከላይ በቪድዮ (4 MB) ታያይዟል።

Credit : Anadolu Agency

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያላሳደሱ የጉምሩክ አስተላላፊዎች የተሰጠው ቀነ ገደብ ሊሰጠናቀቅ 3 ቀን ቀርቶታል።

የጉሙሩክ አስተላላፊዎች የሞያ እና የብቃት ማረጋገጫ አሰጣጥና አስተዳደር በተመለከተ በወጣው መመሪያ ቁጥር 153/2011 በማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 170/2013 መሰረት የጉሙሩክ አስተላላፊዎች የስራ ብቃት ማረጋገጫ መውሰድና በወቅቱ ማሳደስ ይጠበቅባቸዋል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ከዚህ ቀደም በተለያዩ በሚዲያዎች ዝርዝር መስፈርቶችን በማየት እና በማሟላት ከህዳር 15 - ታህሳስ 15 /2014 ድረስ እንዲወስዱ / እንዲያሳድሱ አሳውቆ ነበር።

የተሰጠው ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ሶስት ቀናት ብቻ የቀረው ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ የማይፈፅሙ ኮሚሽኑ እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ_አገራዊ_ምክክር_ኮሚሽን_ማቋቋሚያ_አዋጅ_Amhaic.doc
143 KB
#ያንብቡ

በኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ እና የሃሳብ መሪዎች እንዲሁም የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል እጅግ መሠረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የሃሳብ ልዩነት እና አለመግባባት የሚታይ በመሆኑ ይህን ልዩነት እና አለመግባባት ለማርገብና ለመፍታት ሰፋፊ አገራዊ የሕዝብ ምክክሮችን አካታች በሆነ መንገድ በማካሄድ አገራዊ መግባባት መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል።

መሠረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ አካታች አገራዊ ምክክሮችን ማካሄድ የተሻለ አገራዊ መግባባትን ለመገንባትና በሂደትም የመተማመንን እና በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ የመሥራት ባህልን ለማጎልበት፣ እንዲሁም የተሸረሸሩ ለማሳለጥ የሚያስችል ሥርዓት በሕግ መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ተብሏል።

አገራዊ ምክክሮች ተቀባይነት እና ተዓማኒነት ያላቸው እንዲሆኑ ከሚያስችላቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ምክክሮቹን የሚያመቻቸውና የሚመራው አካል ብቃትና ገለልተኝነት በመሆኑ፤ ምክክሮቹን በብቃትና በገለልተኝነት ለመምራትና ለማስተባበር የሚችል ሰፊ ቅቡልነት ያለው ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

በዚህም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 55(1) መሠረት ከላይ የተያያዘው አዋጅ ታውጇል።

ይህ ኮሚሽኑ በሀገሪቱ ለዘመናት የቀጠለውን ያለመግባባት አዙሪት በማስወገድ አገራዊ አንድነት እንደሚያረጋገጥ ተስፋ እንደተጣለበት ተነግሯል።

የህ/ተ/ምክር ቤት በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ዜጎች ረቂቅ አዋጁን አንብበው ም/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ ሊያየው ይገባል የሚሉትን ሀሳብ እንዲሰጡ ጠይቋል።

(እንደ ዜጋ ከላይ የተያያዘውን ረቂቅ አዋጅ አንብበው በም/ቤቱ ገፅ https://www.facebook.com/599208023518983/posts/4270721263034289/ ገብተው ሀሳቦትን ያካፍሉ)

@tikvahethiopia
#DStv

ዙረት

ወንጀል እና ፍቅርን የሚያሳይ ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ ድራማ ዘወትር ሰኞ ማታ 2፡30 በድጋሚ እሁድ ከጠዋቱ 04፡00 ሰዓት እና ማታ 02፡00 ሰዓት በአቦል ቻናል (146) ይጠብቁን !

#DStvየራሳችን
አቶ አሕመድ አሊ የኦሮሞ ብ/ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳዳር ም/ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ አቶ አሕመድ አሊን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የቀድሞው ዋና አሰተዳዳሪ አቶ አሕመድ ሐሰን እና አዲሱ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሕመድ አሊ የስልጣን ርክክብ አድርገዋል።

ም/ቤቱ የዞን ካቢኔ አባላትን ሹመት አፅድቋል (የተሿሚዎች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)

በተጨማሪም የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ አቶ ከድር አሊን የዞኑ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ፣ አቶ ጀማል ሐሰንን የዞኑ ፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ እና አቶ መሐመድ ሙሳን የዞኑ አደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ አድርጎ ሹሟል።

#AMC

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ "ታላቅ ጉዞ ወደ ሐገር ቤት " የትኬት ሽያጭ እስከ ታህሳስ 16 ቀን 2014 መራዘሙን አሳውቋል።

በሌላ በኩል ኢትዮ ቴሌኮም ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት እየተዘጋጁ ያሉ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆችን በአገልግሎቱ ላይ እስከ 51 በመቶ ቅናሽ አድርጎ ሊቀበል መሆኑ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
ፈረንሳይ በድሮን ጥቃት ስምንት ሰዎችን እንደገደለ የተጠረጠረ የIS አባል ገደለች።

የፈረንሳይ ጦር ባለፈው አመት በኒጀር 6 የፈረንሳይ ዜግነት ያላቸው የእርዳታ ሰራተኞችን እና 2 ኒጀርያውያን አስጎብኚዎቻቸውን በመግደል ከተጠረጠሩት መካከል አንዱ የሆነውን ሱማና ቡራ የተባለ ግለሰብ በድሮን ጥቃት መግደሉን አሳውቋል።

የፈረንሳይ ጦር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ትላንት ሰኞ የተገደለው ግለሰብ ሱማን ቡራ በምእራብ ኒጀር በደርዘን የሚቆጠሩ የIS ተዋጊዎችን ይመራ እንደነበር ገልጿል።

የፈረንሳይ ጦር ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል በሰጠው ቃል ቦራ የሞተር ሳይክሉን እያሽከረከረ ሲሄድ በነበረበት ወቅት በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት ተመቶ መገዱሉን ተናግሯል።

ስድስቱ ACTED የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አባላት እና አስጎብኝዎቻቸው የተገደሉት እኤአ በነሀሴ 2020 ከኒጀር ዋና ከተማ ኒያሜ 65 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን የኩሬ ብሔራዊ ፓርክን እየጎበኙ በነበረበት ወቅት ነበር።

@tikvahethiopia
#EthiopiaAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተከታታይ 4 ዓመታት የአለም አየር መንገዶች ብቃት መዛኝና ደረጃ መዳቢ በሆነው ስካይትራክስ የሚሰጠውን "የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማት" አሸነፈ።

ይህ ሽልማት በብዙዎች ዘንድ "የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ኦስካር" በመባል ይታወቃል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopia