TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Soamlia

ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ያለው የድርቅ ሁኔታ በከፍተኛ ፍጥነት እየተባባሰ መሆኑን UN አስጠንቅቋል።

በዚህም ተነሳ ሶማሊያ ውስጥ 2.3 ሚሊዮን ሰዎች የውኃ እና የምግብ እጥረት ሊገጥማቸው እንደሚችል ተገልጿል።

UNOCHA በድርቁ የተነሳ ወደ 100,000 የሚጠጉ ሰዎች ከቀዬያቸው መፈናቀላቸውን ማስታወቁን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#SouthOmoZone

በድርቅ ምክንያት ከብቶች እየሞቱ ነው።

በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ላይ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ምክንያት 98 ሺህ ሄ/ር ለግጦሽ ሲውል የነበረው መሬት ሙሉ በሙሉ በጎርፍ በመያዙ በተከሰተ ድርቅ የአርብቶ አደሩ የኢኮኖሚ ምንጭ የሆኑ ከብቶቻቸው በግጦሽ ሳር እጦት እየሞቱ ነው።

በዛሬው እለት የዞኑ ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ምህረት አስራቱ የተመራ ቋሚ ኮሚቴ የመስክ ምልከታ በማድረግ ይህንን አረጋግጧል።

በአካባቢው ያለውን ሁኔታ የሚያሳይ ፎቶ ከላይ ተያይዟል።

Photo Credit : የደቡብ ኦሞ ዞን ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ካማላ_ሃሪስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጤና ክትትል ላይ በመሆናቸው ምክትላቸው ሥልጣን ተረክበዋል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጤና ክትትል እያደረጉ በመሆኑ ምክትላቸው የሆኑት ካማላ ሃሪስን ፕሬዝዳንትነት ሥራውን መረከባቸውን ዛሬ የዋይትሐውስ ቃላቀባይ በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ የጤና ምርመራቸውን ለማድረግ ወደ ሆስፒታል ያቀኑት ዛሬ ሲሆን ከማደንዘዣው እስኪነቁ ድረስ ነው ምክትላቸው…
ባይደን ወደ ፕሬዜዳንት ስልጣናቸው ተመለሱ።

ለ85 ደቂቃዎች ያህል በህክምና ክትትል ምክንያት የአሜሪካ ፕሬዜዳንትነት ስልጣናቸውን ለምክትላቸው ካማላ ሃሪስ አስረክበው የነበሩት የ79 ዓመቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ፕሬዝዳንትነት መንበራቸው ተመልሰዋል።

ትላንት ካማላ ሐሪስ በአሜሪካ ታሪክ ለ85 ደቂቃዎች አገሪቱን በመምራት የመጀመሪያዋ ሴት ሆነዋል። በተጨማሪ የመጀመሪያዋ ጥቁር ደቡብ ኤስያዊት ሴት ፕሬዜዳንትም ሆነዋል።

ፕሬዝዳንቱ ሕክምና ላይ በነበሩበት ጊዜ ሐሪስ ከዋይት ሐውስ የምሥራቅ ክንፍ ካለው ቢሯቸው ሥራቸውን ሲያከናውኑ ነበር።

የጆ ባይደን ሐኪም ፕሬዝዳንቱ ደህና እንደሆኑ እና ወደ ሥራቸው መመለስ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

የጆ ባይደን ሐኪም ኬቨን ኦኮነር ፤ ፕሬዜዳንቱ ጤናማና ጠንካራ ናቸው ያሉ ሲሆን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት ይችላሉ ብለዋል።

ባይደን ከሆስፒታል ወደ ዋይት ሐውስ ሲመለሱ "ጥሩ ስሜት ይሰማኛል" ብለው መናጋረቸውን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

@tikvahethiopia
ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የከፋ ችግር ላይ ናቸው።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን፥ " አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች የሚገኙ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለከፋ የምግብና የመድሃኒት ችግር በመዳረጋቸው የበርካታ ዜጎች ሕይወት እያለፈ ነው " ሲል አሳወቀ።

የኮሚሽኑ ይህን ያሳወቀው ለኢፕድ በሰጠው ቃል ነው።

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ዕርዳታ ድርጅቶች ሕወሓት በወረራቸው አካባቢዎች በችግር ላይ ለሚገኙ ዜጎች የመድሃኒትና ምግብ ድጋፍ እንዲያቀርቡ ተደጋጋሚ ጥሪ ቢቀርብላቸውም ድጋፉን አላቀረቡም፡፡

በዚህም ምክንያት በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለከፋ የምግብና የመድሃኒት ችግር በመዳረጋቸው የበርካታ ዜጎች ሕይወት እያለፈ መሆኑን ኮሚሽኑ አሳውቋል።

በዋግኸምራ እና ሌሎች አካባቢዎች በርካታ ማኅበረሰብ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ በመሆኑ በሴፍትኔት ፕሮግራም ይረዳ ነበር ፤ ቡድኑ አካባቢዎችን ከወረረበት ጊዜ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ምንም ዓይነት የምግብና የመድሃኒት አቅርቦት የለም።

በዋግኸምራ፣ በመቄትና በሌሎችም ቦታዎች እየተገኙ ባሉ መረጃዎች በርካታ ወገኖች በረሃብና በመድሃኒት እጦት ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን የሚያመላክቱ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል።

@tikvahethiopia
አፋር ክልል የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።

የአፋር ክልል አደጋ ስጋት ጽ/ቤት በክልሉ ውስጥ የተፈናቃይ ተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አስታውቋል።

ጦርነቱ ተስፋፍቶ በቀጠለባቸው ባለፉት 3 ሳምንታት በአፋር የተፈናቃዮች ቁጥር ወደ 300 ሺህ ማሻቀቡን ፅ/ቤቱ ለዶቼቨለ ሬድዮ በሰጠው ቃል ገልጿል።

የአፋር ክልል አደጋ ስጋት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፥ " ጦርነት ቀጠና ውስጥ የዞን 2፦ በርሃሌ አለ፤ እንዲሁም ከዞን 2 ጀምሮ ያለው፦ እዋ፤ አውራ እንዲሁም ጭፍራ፤ ዞን አንድ ደግሞ ሐዳር እያለ ወደ ዞን አምስትም ይሻገራል። ስለዚህ በአጠቃላይ አሁን ያለን የተፈናቃይ ቁጥር ከ300,000 በላይ ይደርሳል " ብለዋል።

በዚሁ ጦርነት የተፈናቀሉትን የተሻለ ደህንነት ወዳለበት አከባቢዎች እንዲጠጉ እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል።

ጭፍራ አከባቢ የነበሩት 60 ሺ ገደማ ተፈናቃዮች ወደ ሚሌ አቅጣጫ 50 ኪ.ሜ. ያህል ርቀት ላይ በተገነባ መጠለያ እየተረዱ መሆናቸውን ፅ/ቤቱ አሳውቋል።

ለተፈናቃዮቹ ለመድረስ መንግሥት እና የርዳታ ተቋማት ድጋፍ እያደረጉ ቢሆንም፤ በቂ እንዳልሆነ ተገልጿል።

እስከ ከሚሴ አዋሳኝ ወረዳዎች ከ1.3 ሚሊየን የማያንስ ሕዝብ የጦርነ ገፈት ቀማሽ መሆኑንም የአፋር ክልል አደጋ ስጋት ጽ/ቤት ለሬድዮ ጣቢያው አሳውቋል።

@tikvahethiopoa
TIKVAH-ETHIOPIA
#SouthOmoZone በድርቅ ምክንያት ከብቶች እየሞቱ ነው። በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ላይ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ምክንያት 98 ሺህ ሄ/ር ለግጦሽ ሲውል የነበረው መሬት ሙሉ በሙሉ በጎርፍ በመያዙ በተከሰተ ድርቅ የአርብቶ አደሩ የኢኮኖሚ ምንጭ የሆኑ ከብቶቻቸው በግጦሽ ሳር እጦት እየሞቱ ነው። በዛሬው እለት የዞኑ ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ምህረት አስራቱ የተመራ ቋሚ ኮሚቴ የመስክ…
#Dasenech : የፍርኤል እርሻ ልማት በዳሰነች ወረዳ በተከሰተው የመኖ እጥረት እና የአርብቶ አደሮችን የኢኮኖሚ ምንጭ የሆነውን እንሰሳት ለመታደግ 4 ሚልዬን ብር በመመደብ ለአርብቶ አደሩ መኖ ለማቅረብ እየስራ አሳውቋል።

በዘላቂነት መኖ ለአርብቶ አደሩ ለማቅረብም በአሁኑ ሰዓት 60 ሄ/ር ማረስ መጀመራቸውን የፍርኤል እርሻ ልማት መግለፁን ከደቡብ ኦሞ ዞን ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ይገልፃል።

@tikvahethiopia
#MekdalaTreasures

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ በጀኔራል ናፒዬር ወታደሮች የተዘረፉ 13 የኢትዮጵያ ጥንታዊ የታሪክ አሻራ ማሳያ የሆኑ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶች በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል።

በኢትዮጵያ ቅርሶች አስመላሽ ኮሚቴ፣ በእንግሊዝ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሼሄራ ዛድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባባር ባደረጉት ጥረት ባለፈው ዓመት ጳጉሜን 3 /2013 ዓ.ም በለንደን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መመለሳቸው ይታወሳል።

ከተመለሱት ቅርሶች መካከል ፦
- በነሀስ የተለበጠ ጋሻ፣
- በቆዳ የተደጎሰ በእጅ የተፃፈ ጥንታዊ የብራና የፀሎት መፅሀፍ እስከነመያዣቸው፣
- በመጠን ተለቅ ያለ የብር መስቀል፣
- አነስተኛ መጠን ያለው የብር መስቀል፣
- ፅዋ ይወሰድበት የነበረ ዋንጫ እና ማንኪያ፣
- የጳጳሳት እና የካህናት አክሊል፣
- ሦስት ከቀንድ የተሰሩና በብር የተለበጡ የቀንድ ዋንጫዎች፣
- የአንገት ጌጥ (ሃብል)፣
- ክታብ እና የገበታ ስዕል ይገኙበታል፡፡

ምንጭ፦ ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የDAS ተሸላሚ ሆነዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የዘንድሮው የጀርመን አፍሪካ ፋውንዴሽን (DAS) ተሸላሚ ሆነዋል። ፋውንዴሽኑ በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው ዶ/ር ዳንኤል ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ላበረከቱት የህይወት ዘመን አስተዋፅኦ ከፍተኛውን ሽልማት ለመስጠት መወሰኑን አስታውቋል። ዶ/ር ዳንኤል ከ30 ዕጩዎች መካከል…
ፎቶ : የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑት እና በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን በዋና ኮሚሽነርነት እየመሩ የሚገኙት ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በርሊን ብራንድቡርግ የ2021 የጀርመን አፍሪካ ሽልማት ተቀብለዋል።

ዶ/ር ዳንኤል ሽልማቱን ያገኙት በህይወት ዘመናቸው ለሰብአዊ መብት መከበር ባደረጉት ከፍተኛ ትግል ነው።

ሽልማቱን የጀርመን አፍሪካ ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት ኡሺ አይድ እና የጀርመን አፍሪቃ ፋዉንዴሽን ዳኞች ፕሬዝዳንት ክላዉስ ሽቴከር በጋራ ለዶ/ር ዳንኤል በቀለ አበርክተዉላቸወዋል።

የጀርመን አፍሪቃ ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት ኡሺ አይድ ፦

" ሽልማቱ ለምሳሌ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ ሶማሌ ወይም አፋር ዉስጥ ያሉና ሳይፈሩ ለሰብአዊ መብት መከበር ለሚቆሙ ሁሉ ማበረታቻ ሊሆን ይገባል። " ብለዋል።

የጀርመን አፍሪቃ ፋዉንዴሽን ዳኞች ፕሬዝዳንት ክላዉስ ሽቴከር ፦

" ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት አስቸጋሪ ሁኔታ የኃላፊነት እና ድፍረት ምሳሌ ናቸው። " ሲሉ አሞግሰዋቸዋል።

ዶ/ር ዳንኤል ምን ያህል በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ሆነዉ ሥራቸዉን እያከናወኑ እንደሆነም ሽቴከር ተናግረዋል።

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፦

" ሽልማቱ  ለሰብአዊ መብቶች መከበር በየቀኑ ለሚሰሩ እና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንዲሁም በፖለቲካዊ ተቃውሞ ውስጥ እንኳን ሆነዉ የእኩልነት መርህን ለሚጠብቁ ባልደረቦቻቸዉ ሁሉ ይሁን " ብለዋል።

#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በሀሰተኛ መረጃዎች ትምህርት አቁመው የነበሩ ት/ቤቶች ወደ መማር ማስተማር ስራቸው መመለሳቸውን ተገለፀ።

ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት በአዲስ አበባ የሚገኙ የማህበረሰብና ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ጫና አድሮባቸው የመማር ማስተማር ስራቸውን እንዲያቆሙ ለማድረግ ጥረት ሲደረግ እንደነበር የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታውሷል።

በዚህ ጥረትም ጥቂት ት/ቤቶች የመማር ማስተማር ስራቸውን ለተወሰነ ጊዜ እንዲያቆሙ አድርጓቸው ነበር፤ ይህንንን ትምህርት ሚኒስቴር ባደረገው ምልከታ እና በወላጆች ጥቆማ ለመረዳት ተችሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር በተነዛው ሀሰተኛ መረጃ ላይ ተመስርተው የመማር ማስተማሩን ስራ ያቋረጡ 7 የማህበረሰብ ት/ቤቶች እና 19 ዓለም አቀፍ ት/ቤቶች ያለምንም በቂ ምክንያት ትምህርት ስራውን ማቆም እንደማይችሉ በይፋ አሳውቋቸዋል።

ሚኒስቴሩ የመማር ማስተማር ስራውን ያቋረጡ 3 ዓለም አቀፍ እና የማህበረስብ ትምህርት ቤቶች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንዲደርሳቸው አድርጓል።

ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ትምህርት ቤቶች ፦

- ሳንፎርድ ዓለም አቀፍ ት/ቤት
- ቤንግሃም ት/ቤት
- የዓለም አቀፍ ኮሚኒቲ (ICS) በተለምዶ የአሜሪካ ት/ ቤት ናቸው።

ትምህርት ቤቶቹ የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ወዲያው የፊት ለፊት የመማር ማስተማር ስራ እና በኦንላይን ከሀገር የወጡ መምህሮችን በመጠቀም ትምህርት መጀመራቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።

በህብረተሰቡ ላይ መደናገር ለመፍጠር እየተደረጉ ያሉት ጥረቶች የተቀናጀ ሀሰተኛ መረጃ የመንዛትና ዜጎችን ፍርሃት ውስጥ ለመክተት ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን የሚያሳዩና የሽብር ቡድኑ ህወሓት መጠቀሚያ መሆኑን በግልፅ የታየበት ነው ብሏል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ በሰጠው መግለጫ።

@tikvahethiopia
#Sudan

የሱዳን ጦር ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስቱን ለመቃወም አደባባይ በወጡ ሰዎች ላይ በወሰደው የኃይል እርምጃ እስካሁን የተገደሉ አጠቃላይ ሰላማዊ ሰዎች ቁጥር በትንሹ 40 ስለመድረሱ ፍራንስ 24ን ዋቢ አደርጎ አል አይን አስነብቧል።

ከሟቾች በተጨማሪ በርካቶች ተጎድተዋል።

የሱዳን የሙያተኞች ማህበር ፥ ሱዳናዊያን ወታደራዊ አመራሩ ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳድሩ እስከሚመልስ ድረስ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን እንደማያቆሙ አስታውቋል፡፡

የተቃውሞ ሰልፉ አሁን ላይ ከአገሪቱ መዲና ካርቱም ወደ ጎረቤት ከተሞች ባህሪ እና ኦምዱርማን ከተሞች እየሰፋ ሲሆን በቀጣይም ወደ ሌሎች ከተሞች እንደሚሰፋ ማህበሩ ገልጿል።

በዚህ በያዝነው ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በቀጣዮቹ ቀናት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ በከሰላ፣ ድንጉላ፣ ወደመደኒ እና ጅኔና ከተሞች የሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አስቀድሞ ጥሪ ተላልፏል።

የሱዳን ጦር በነዚህ ከተሞች ዋና ዋና መተላለፊያ መንገዶች እና አደባባዮች ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጦር አስቀድሞ መሰማራቱን የፍራንስ 24ን ዘገባ ዋቢ አድርጎ አል ዓይን አስነብቧል።

@tikvahethiopia