TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Turkey

ቱርክ ለኢትዮጵያ 1 ነጥብ 7 ቶን መጠን ያለው የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባሳለፍነው ሳምንት ከቱርኩ ፕሬዘዳንት ረጂብ ጣይብ ኤርዶሃን ጋር በስልክ መወያየታቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በውይይታቸው ወቅት በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ቱርክ ድጋፍ እንድታደርግ ጠይቀው ፕሬዘዳንቱ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸው ተገልጾ ነበር።

በዚህም መሰረት ቱርክ 1 ነጥብ 7 ቶን መጠን ያላቸው የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጋለች።

ድጋፉን በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ለሴቶች ፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳዮች ሚኒስትር ፊልሳን አብዱላሂ ዛሬ በአዲስ አበባ አስረክበዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቱርክ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደሀገር ተመለሱ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት ፥ "ከተከበሩ የቱርክ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር የነበረንን ውድ ጊዜ አጠናቀን ወደ ሀገር ተመልሰናል።" ብለዋል። አክለውም ፥ "የቱርክ መንግስት እና ህዝብ ያደረገልንን የወሳኝ ጊዜ ትብብር ሀገራችን…
#Turkey #Ethiopia #Sudan

የቱርክ ፕሬዝዳንት ረጂብ ጣይብ ኤርዶጋን በኢትዮ - ሱዳን ድንበር ጉዳን ኢትዮጵያ እና ሱዳን ለሸማገላችሁ ሲሉ ሀሳብ አቅርበዋል።

ኤርዶሃን ሃሳቡን ያቀረቡት፤ ከጠ/ሚ አብይ አህመድ ጋር ትላንት በአንካራ በሰጡት መግለጫ ነው።

በትላትናው የዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ሪሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን መግለጫ ወቅት የትግራይ እና የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳዮች ተነስተዋል።

ኤርዶጋን ሀገራቸው ቱርክ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የሚወዛገቡበትን የድንበር ጉዳይ ለማደራደር ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል።

ኤርዶጋን “ውዝግቡ በ2ቱ አገሮች መካከል በሚደረግ ውይይት በመልካም ጉርብትና ላይ በመመስረት እንዲፈታ የልብ ፍላጎቴ መሆኑን ገልጫለሁ ፤ ቱርክ ጉዳዩ በሰላም እልባት እንዲያገኝ ሽምግልናን ጨምሮ ማናቸውንም አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ ናት" ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ኤርዶጋን በሰሜን ኢትዮጵያ ስለተፈጠረው ጦርነት ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አላት ያሉትን ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ እና ጠቀሜታ ጠቅሰው ለሀገሪቱ ሰላም፣ ጸጥታ እና አንድነት ትኩረት እንደሚሰጡ ገልጸዋል። 

“የቀጠናውን ሰላም እና መረጋጋት ከመጠበቅ አኳያ ለወቅታዊው ችግር በለዘብተኛ አካሄድ መፍትሔ ማበጀት ያስፈልጋል ብለን እናምናለን” ብለዋል።

አክለውም 9 ወራት በላይ ያስቆጠረው ውጊያ ከተባባሰ ዳፋው በአካባቢው አገራት ሊዳረስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።  

#EthiopiaInsider #Anadolu

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቱርክ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደሀገር ተመለሱ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት ፥ "ከተከበሩ የቱርክ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር የነበረንን ውድ ጊዜ አጠናቀን ወደ ሀገር ተመልሰናል።" ብለዋል። አክለውም ፥ "የቱርክ መንግስት እና ህዝብ ያደረገልንን የወሳኝ ጊዜ ትብብር ሀገራችን…
#Ethiopia #Turkey

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የልዑካን ቡድናቸው ወደ ቱርክ (አንካራ) አቅንተው የአንድ ቀን የስራ ጉብኝት አድርገው ወደሀገር ቤት መመለሳቸው ይታወቃል።

ዛሬ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን የቱርክ የስራ ጉብኝት የተጠቃለለ አጭር ሪፖርት አቅርቧል።

ይፋዊ ጉብኝቱ የኢትዮጵያ እና የቱርክ ሁለትዮሽ ግንኙነት 125ኛ ዓመት ላይ የተከናወነ ሲሆን 4 ስምምነቶችን በመፈራረም ነው የተጠናቀቀው።

4ቱ ስምምነቶች የሚከተሉት ናቸው፦

1. በውሀ ዘርፍ ትብብር ለማድረግ የጋራ መግባቢያ ሰነድ
2. የወታደራዊ ማህቀፍ ስምምነት
3. የፋይናንስ ድጋፍን የተመለከት የትግበራ ሰነድ
4. የወታደራዊ ፋይናንስ የትብብር ስምምነት

በጉብኝቱ መካከል ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በአኒትካቢር መካነ መቃብር የመታሰቢያ ጉንጉን አሰቀምጠው፣ “ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር ያላት ትስስር በመከባበር እና በመተማመን የጋራ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ የበለፀገ ባህል እና ትውፊት ለሞላቸው ሁለት የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤቶች የሚመጥን ነው” በማለት ተናግረዋል።

በፕሬዚደንቱ ቤተመንግሥት ለጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ደማቅ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ሁለቱ መሪዎች ከልዑካን ቡድኖቻቸው ጋር በመሆን የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ላይ ሁለቱም ወገኖች ትብብሩን በቀጣይነት ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

@tikvagethiopia
#Sudan #Turkey

ጎረቤት ሀገር ሱዳን የኢትዮ- ሱዳን የድንበር ላይ ውዝግብን ለመፍታት #ቱርክ ያቀረበችውን የማደራደር ጥያቄ መቀበሏ ታውቋል።

የቱርክን የማደራደር ጥያቄ ሱዳን መቀበሏን ያሳወቁት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማሪያም አል-ሳዲቅ አል-መሃዲ ናቸው።

ይህንንም ጉዳይ የቱርክ የዜና ወኪል የሆነው አናዱሉ እና የሱዳን መንግሥት የዜና ወኪል ሱና ዘግበውታል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ፥ "የሱዳን የሉዓላዊ ም/ ቤት ሊቀ-መንበር አብዱል ፋታህ አል-ቡርሐን ባለፈው ወር ወደ ቱርክ በተጓዙ ወቅት ፤ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈጠረውን የድንበር አለመግባባት ለመፍታት ከቱርክ ባለሥልጣናት የቀረበውን የማደራደር ጥያቄ ተቀብለዋል" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በኩል በጉዳዩ ላይ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤቱ ሊቀ-መንበር አብዱል ፋታህ አል-ቡርሐን አብዱል ራህማን ሰኔ ወር ላይ ወደ ቱርክ መጓዛቸው ይታወሳል። አል-ቡርሐን በአንካራ ቆይታቸው ከፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ጋር ተገናኝተው በርካታ ምጣኔ ሀብታዊ ስምምነቶችን ተፈራርመው ነበር።

በተመሳሳይ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር የኢትዮጵያው ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ቱርክ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር የተወያዩ ሲሆን፤ የተለያዩ የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነቶችን ላይ ስምምነት ተፈራርመው እንደነበር ይታወሳል።

Credit : BBC/SUNA/ANADOLU

@tikvahethiopia
#Turkey : ቱርክ ተዋጊ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለኢትዮጵያ እና ለሞሮኮ ለመሸጥ መስማማቷን 4 የመረጃ ምንጮች ገለፁልኝ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

አንድ ስማቸው ያልተገለፀ የቱርክ ባለልስጣን ለሮይተርስ በሰጡት ቃል፥ ኢትዮጵያ እና ምርኮ የመለዋወጫ አቅርቦትና ስልጠናን ባካተተ ስምምነት " ባይራክታር TB 2 " የተባሉ የጦር አውሮፕላኖችን ለመግዛት መጠየቃቸውን ተናግረዋል።

ስማንቸው እንዲገለፅ የልፈለጉ አንድ ዲፕሎማት ደግሞ ሞሮኮ ግንቦት ወር ላይ ያዘዘቻቸውን ተዋጊ አውሮፕላኖችን መረከቧን አሳውቀዋል።

ዲፕሎማቱ ፥ ኢትዮጵያም የሰው አልባ አውሮፕላኖችን ከቱርክ ለመግዛት ጥያቄ አቅርባ ትእዛዙን ምን ደረጃ ላይ እንዳለ አይታወቅም ብለዋል።

ኢትዮጵያ፣ ሞሮኮ፣ ቱርክ ስለስምምነቱ ምንም ያሉት ነገር ባይኖርም ሮይተርስ ግን ስምምነቱን በደንብ ከሚያውቁ የመረጃ ምንጮች ዝርዝር መረጃ እንዳገኘ ዘግቧል።

2 የግብፅ የፀጥታ ምንጮች አሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት ሽያጩን ለማስቆም ሀገራቸው መጠየቋን ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ሌላ ምንጭ ደግሞ የሽያጩ ስምምነት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማደስ ጥረት እያደረጉ ያሉት ግብፅና ቱርክ ውይይት ሊደረግበት ይገባል ብለዋል።

ቱርክ ለኢትዮጵያና ሞሮኮ የምትሸጣቸው የመከላከያ እና የአቪዬሽን ቁሳቁሶች ባለፉት 2 ወራት መጨመሩን ይፋዊ መረጃዎች ቢያሳዩም ስለ ድሮን የቀረበ መረጃ የለም።

የቱርክ የወጪ ንግድ ምክር ቤት መረጃ እንደሚያሳየው እኤአ 2021 የመጀመሪያ 3 ወራት 51 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የመከላከያ እና አቪዬሽን ቁሳቁስ ሸመታለች።

ግብይቱ በነሃሴ እና መስከረም ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ሮይተርስ ገልጿል።

የዜና ወኪሉ፤ ከመከላከያና ከጠ/ሚ ፅ/ቤት በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለማግኘት ጥረት እንዳደረገ ነገር ግን እንዳልተሳካለት ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Turkey_Africa

የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በአፍሪካ ሀገራት 4 ቀናት ይፋዊ የስራ ገብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።

በመጀመሪያው ቀን ጉብኝታቸው በአንጎላ፣ ላውንዳ ተገኝተው ከሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ጃኦ ሎሬንኮ ጋር መክረዋል።

በመቀጠል በበቶጎ ሎሜ ከፕሬዚዳንት ፋውሬ ናሲንግቤ ጋር ተገናኝተው መክረዋል፤ በተጨማሪ ከቡርኪና ፋሶ ፕሬዜዳንት ሮች ማርክ ክርስትያን ካቦሬ እንዲሁም ከላይቤሪያ ፕሬዝዳት ጆርጅ ዊሃ ጋር ተገናኝተው መክረዋል (ሁሉም ምክክሮች ለሚዲያ ዝግ ነበሩ) ።

ዛሬ በመጨረሻው የስራ ጉብኝት መርሃግብራቸው ፕሬዜዳንት ሬስፕ ጣይብ ኤርዶጋን ወደናይጄሪያ አቅንተው በአቡጃ በፕሬዜዳንት ሙሀመድ ቡሃሪ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፤ መሪዎቹ ምክክርም አድርገዋል።

ቱርክ እና ናይጄሪያ ከኃይል እስከ መከላከያ ድረስ በርካታ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፤ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከርም ስምምነት አድርገዋል።

ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን እ.ኤ.አ በ2003 ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ቱርክ በአፍሪካ ውስጥ ያላትን ተሳትፎ እና ከሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገች ነው።

@tikvahethiopia