" ፈተናውን መውሰድ ለማይችሉ ተለዋጭ መርሀ ግብር ይኖራል " - ትምህርት ሚኒስቴር
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ህወሓት ወረራ በመፈፀሙ ምክንያት የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን መውሰድ ለማይችሉ ተማሪዎች ተለዋጭ መርሀ ግብር ይኖራል አለ።
ሚኒስቴሩ ከወራር ነፃ በወጡ አካባቢዎች የመልሶ ግንባታ እንቅስቃሴ እንደተጀመረ ያሳወቀ ሲሆን ከጥቅምት 29 እስከ ኅዳር 2/2014 ዓ.ም የሚሰጠውን የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ በማይችሉ አካባቢዎች መደበኛ የተማሪዎች ፈተና በሌላ መርሀ ግብር ይሸፈናል ሲል አሳውቋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በህወሓት ወረራ በአማራ እና አፋር ክልሎች ከ3 ሺህ በላይ የትምህርት ተቋማት ጉዳት እንደደረሰባቸው አሳውቋል።
ከ2 ሺህ 900 በላይ የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች በአማራ ክልል የሚገኙ ናቸው ብሏል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው ለአሚኮ በሰጡት ቃል፤ "ቡድኑ ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ዘርፏል፣ ማንቀሳቀስ ያልቻለውን አውድሟል" ብለዋል ፤ "አንዳንድ ትምህርት ቤቶችንም የጦር ካምፕ ስላደረጋቸው ጦርነት ተካሂዶባቸዋል ፤ በሽንፈት ሲሸሽም ጣራ በመንቀል እና ሕንጻ በማፍረስ አስነዋሪ ድርጊት ፈጽሟል" ሲሉ ተናግረዋል።
ዶ/ር ጌታሁን የ12ኛ ክፍል ፈተናን በተመለከተም፥ “ፈተናውን መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች የአካባቢያዊ ሁኔታው ሲመቻች እና በሥነ ልቦና ለፈተና ዝግጁ ሲሆኑ በሌላ መርሀ ግብር እንዲወስዱ ይደረጋል" ብለዋል፡፡
ዶ/ር ጌታሁን "የተማሪዎችን ሥነልቦና በመጠገን፣ የትምህርት ቤቶች ምገባ በማስጀመርና የተለያዩ አጋዥ የትምህርት ቁሳቁስ በማበርከት ኢትዮጵያውያንና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
Credit : AMC
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
* Update በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሚያዚያ ወር 2013 ዓ/ም የተመረቀው የሞጆ - ሀዋሳ የመንገድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የሞጆ ባቱ የክፍያ ፍጥነት መንገድ የተሟላ የክፍያ ማከናወኛ ስርዓት ተሟልቶለት መስከረም 10 ቀን 2014 ዓ/ም ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ተብሏል። መንገዱ 92 ኪሜ ርዝመት ያለው ሲሆን 5 ደረጃቸውን የጠበቁ የክፍያ ጣቢያዎች ተጠነቀው ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሆኑ…
* Update
የሞጆ- መቂ-ባቱ የክፍያ መንገድ ዛሬ ሥራ ጀመረ።
የሞጆ- መቂ-ባቱ 92 ኪሎ ሜትር የክፍያ መንገድ በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
የመንገዱን መከፈት ምክንያት በማድረግየኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ እና የትራንስፖርት ሚንስቴር ዲኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ የተገኙበት መርሀ ግብር ተዘጋጅቶ ነበር።
በዚሁ መርሀ ግብር ላይ የፍጥነት የክፍያ መንገዱ በ6 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጭ የተገነባ መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ለሰባት አመታት ሲያስተዳድረው ከቆየው የአዲስ አበባ አዳማ እና የድሬደዋ ደወሌ የክፍያ መንገድ በመቀጠል ወደ ስራ የገባ 3ኛው የክፍያ መንገድ ነው መባሉ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

* የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት !
በአፋር ክልል ውስጥ እየተስፋፋ የመጣውን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በጋራ እንዲከላከል ጥሪ ቀረበ።
የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በክልሉ እያደገ የመጣውን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ለማሟላት በከፍተኛ የውጭ ማንዛሬ በማስገባት የማስፋፊያ፤ የመልሶ ግንባታ እና አዳዲስ ከተሞች ላይ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ በማከናወን የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን በማስፋት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
ነገር ግን በአንዳድ የክልሉ ከተሞች በተለይም #በአይሳኢታ እና #ዱብቲ ከስኳር ፋብሪካው ጋር የተመሰረቱ መንደሮች እንዲሁም ለውሃ አግልግሎት የሚሰጡ ትራንስፈርመሮች እና የኤሌክትሪክ ሽቦና መለዋወጫ ላይ አሁን ባለው ዋጋ 3.9 ሚሊዮን ብር በላይ ስርቆት ተፈፅሟል።
ተቋሙ ፤ ጉዳዩ በህግ ክትትል እየተደረገበት እንደሆነ የጠቆመ ሲሆን የችግሩን አሳሳቢነትም በመረዳት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገዙና ከፍተኛ የህዝብ ሃብት የፈሰሰባቸው በመሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ እንደራሱ ንብርት ጥበቃ ሊያደርግላቸው ይገባል ብሏል።
ህብረተሰቡ በየአካባቢው የኤሌክትሪክ የመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ግለሰቦችን በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ አልያም አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በስልክ ቁጥር 👉 0913834455 ላይ ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

#Sudan #Turkey
ጎረቤት ሀገር ሱዳን የኢትዮ- ሱዳን የድንበር ላይ ውዝግብን ለመፍታት #ቱርክ ያቀረበችውን የማደራደር ጥያቄ መቀበሏ ታውቋል።
የቱርክን የማደራደር ጥያቄ ሱዳን መቀበሏን ያሳወቁት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማሪያም አል-ሳዲቅ አል-መሃዲ ናቸው።
ይህንንም ጉዳይ የቱርክ የዜና ወኪል የሆነው አናዱሉ እና የሱዳን መንግሥት የዜና ወኪል ሱና ዘግበውታል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ፥ "የሱዳን የሉዓላዊ ም/ ቤት ሊቀ-መንበር አብዱል ፋታህ አል-ቡርሐን ባለፈው ወር ወደ ቱርክ በተጓዙ ወቅት ፤ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈጠረውን የድንበር አለመግባባት ለመፍታት ከቱርክ ባለሥልጣናት የቀረበውን የማደራደር ጥያቄ ተቀብለዋል" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በኩል በጉዳዩ ላይ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።
የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤቱ ሊቀ-መንበር አብዱል ፋታህ አል-ቡርሐን አብዱል ራህማን ሰኔ ወር ላይ ወደ ቱርክ መጓዛቸው ይታወሳል። አል-ቡርሐን በአንካራ ቆይታቸው ከፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ጋር ተገናኝተው በርካታ ምጣኔ ሀብታዊ ስምምነቶችን ተፈራርመው ነበር።
በተመሳሳይ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር የኢትዮጵያው ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ቱርክ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር የተወያዩ ሲሆን፤ የተለያዩ የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነቶችን ላይ ስምምነት ተፈራርመው እንደነበር ይታወሳል።
Credit : BBC/SUNA/ANADOLU

* ቁጥራዊ መረጃ
የገቢዎች ሚኒስቴር እንዳሳወቀው ባሳለፍነው ሳምንት ከ05/13/2013 ዓ.ም እስከ 06/01/2014 ዓ.ም ድረስ ከ101.8 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል፡፡
የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ እና ወደሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን የገቢ ኮንትሮባንድ 99ሚሊየን 494ሺ 237 ብር ወጪ ደግሞ 2ሚሊየን 345ሺ 048ብር በድምሩ የ101ሚሊየን 839ሺ 285ብር ግምት አላቸው፡፡
ከኮንትሮባንድ ቁሶቹ መካከል ፦
- የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣
- ወርቅ፣
- የወርቅ ማውጫ ማሽን፣
- የተለያዩ አልባሳት፣
- ጫማ፣
- ምግብ ነክ፣
- የጦር መሳሪያዎች፣
- ኤሌክትሮኒክስ፣
- ኮስሞቲክስ፣
- ሲጋራ፣
- ልባሽ ጨርቅ፣
- መለዋወጫ፣
- የሰው መድሀኒትና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ዕቃዎች ውስጥ በድምሩ 80 ሚሊየን 322 ሺ 616 ብር የሚሆነው በአ/አ ኤርፖርት ቅ/ጽ/ቤት በገቢ እና በወጪ የተያዘ ነው፤ ከነዚህ ውስጥ የዋጋ ግምታቸው 50 ሚሊየን 260 ሺ 216 ብር የሆኑት ኤሌክትሮኒክሶች እንዲሁም የዋጋ ግምታቸው 27 ሚሊየን 606 ሺ 384ብር የሆኑት ደግሞ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ናቸው ብሏል የገቢዎች ሚኒስቴር።

ጦርነት ጉዳት ያደረሰባቸው የጤና ተቋማት...
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ተከትሎ በጤና ተቋማት ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
ዶ/ር ሊያ ታደሰ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት ከ1 ሺህ 400 በላይ የጤና ተቋማት መጎዳታቸውን ገልጸዋል።
በአማራ ክልል አምስት ዞኖች ማለትም ፦
- ሰሜን ወሎ፣
- ደቡብ ጎንደር፣
- ደቡብ ወሎ፣
- ዋግ ኽምራ፣
- ምዕራብ ጎንደር ዞኖች በአጠቃላይ 20 ሆስፒታል 277 የጤና ተቋማት ከ1 ሺህ በላይ የጤና ኬላዎች በጦርነቱ መጎዳታቸው ተገልጿል።
በአፋር ክልል ደግሞ አንድ ሆስፒታል፣ 10 ጤና ጣቢያ፣ 38 የጤና ኬላዎች መጎዳታቸውን ተናግረዋል።
በዚህ ጦርነት ምክንያት በርካታ ዜጎች መፈናቀላቸውን ፤ በተለይም ህጻናት እና የሚያጠቡ እናቶች ለከፋ ጉዳት መዳረጋቸውን ተናግረዋል።
የተጎዱ የጤና ተቋማትን መልሶ ወደ አገልግሎት ለማስጀመር የጤና ሚንስቴር የህክምና ቁሳቁስ፣ ገንዘብ፣ የሰው ሀይልና ሌሎች ድጋፎችን ለ2ቱም ክልሎች በማድረግ ላይ መሆኑንም አስታውቋል።
Credit : አል ዓይን

" ሴት ሰራተኞች አርፋችሁ ቤት ተቀመጡ " - የካቡል ከንቲባ
የታሊባን አዲሱ የካቡል ከንቲባ [ስማቸው - ሐምዱላህ ኖማኒ] በካቡል የሚገኙ የማዘጋጃ ቤት ሴት ሠራተኞችን 'አርፋችሁ ቤት ተቀመጡ' ሲሉ ተናገሩ።
ከንቲባው ይህን ያሉት ታሊባን ለጊዜው ሴቶች ሥራ እንዳይሠሩ ማዘዙን በመጥቀስ ነው።
"ክፍት የሥራ መደቦች በወንዶች የማይሞሉ ከሆነ ብቻ ለሥራ ልትመጡ ትችላላችሁ፤ አለበለዚያ ግን አርፋችሁ ቤት ተቀመጡ" ብለዋል ከንቲባው።
የካቡል አዲሱ ከንቲባ እንዳሉት በከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ሠራተኞች ውስጥ አንድ ሦስተኛው ሴቶች ነበሩ። ቤት እንዲቀመጡ የተነገራቸውም በቁጥር ወደ አንድ ሺህ ይጠጋሉ።
ታሊባኖች ሥልጣን ከያዙበት ዕለት ጀምሮ ሥራ የነበራቸው ሴቶች በሙሉ የአገሪቱ የደኅንነት ሁኔታ እስኪሻሻል ድረስ ቤት እንዲቀመጡ አዟል።
ሕጉን በመቃወ ሰልፍ በወጡ ሴቶች ላይም ድብደባ ፈጽሟል።
ታሊባን የሴቶች ጉዳይ ሚኒስትርን ያፈረሰ ሲሆን በምትኩ ሐይማኖታዊ ደንቦች መከበራቸውን የሚቆጣጠር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት አቋቁሟል።
በዚህ ሳምንት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተከፈቱ ቢሆንም ወንድ ተማሪዎች እና ወንድ አስተማሪዎች ብቻ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ነው የተነገራቸው።
ሴት ተማሪዎቸና አስተማሪዎች ግን ለጊዜው ቤት እንዲቆዩ ተደርጓል።
ታሊባን ለሴቶች የተለየ ትምህርት ቤቶችን እያዘጋጀሁ ነው ብሏል።
መረጃው ከቢቢሲ ነው የተገኘው።

* ጊዜያዊ ቦሎ
በትግራይ ክልል በተፈጠረ ወቅታዊ ችግር ምክንያት በክልሉ የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች የቦሎ እና የተለያዩ አገልግሎቶች ማግኛት ያልቻሉ አካላት ጊዜያዊ ፋይል በመክፈት ለአንድ (1) አመት የሚያገለግል ጊዜያዊ ቦሎ እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።
ይህን የገለፀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ነው።
ጊዜያዊ ፋይል በመክፈት ለአንድ አመት የሚያገለግል ጊዜያዊ ቦሎ የሚሰጣቸው ተገልጋዮች ከዚህ በታች የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት አለባቸው ተብሏል።
- የባለቤትነት ማረጋገጫ ዋናውን እና ኮፒ ሊብሬ ማቅረብ
- ባለቤት ወይም ህጋዊ ተወካይ መሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ
- ተሽከርካሪው በአካል እና በባለቤትነት መታወቂው (ሊብሬ) ላይ ያለው የሻንሲ ቁጥር እና ሌሎች መረጃዎች ተመሳሳይ መሆናቸው ሲረጋገጥ
- ለኮድ 1 እና ለኮድ 3 ተሸከርካሪዎች ከሚመለከተው አካል ክሊራንስ ወይም የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ
- ሌሎች ለቦሎ አገልግሎት የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ሰነዶች ማሟላት
- ባለንብረቱ ወይም ህጋዊ ተወካይ በጊዜያዊነት ለአንድ አመት ብቻ ይህ የቦሎ አገልግሎት እንዲሰጠው የማመልከቻ ደብዳቤ ማቅረብ የሚሉት ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው።
ከቦሎ አገልግሎት ውጪ ማንኛውንም አገልግሎት የማይሰጥ እንደሆነ ግንዛቤ ተወስዶ አገልግሎቱ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በሰጠው አቅጣጫ መሰረት እንዲከናወን እና አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ እያሟሉ መገልገል እንደሚቻል ተገልጿል።
NB : አገልግሎቱ በየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ብቻ ነው የሚከናወነው ተብሏል።

#ETHIOPIA🇪🇹
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በመላው ኢትዮጵያ የሚታየውን የሰላም እና የጸጥታ ጉዳይ አስመልክቶ ግምገማ ማካሄዱን ዛሬ ከሰዓት አሳውቀዋል።
በስብሰባው ላይ የሀገሪቱን ጸጥታ እና ደኅንነትን ሊያስጠብቁ የሚችሉ ቀጣይ ተግባራት እንዲከናወኑ አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል።
ፎቶ : ፋይል (የጠ/ሚ ፅ/ቤት)

* ጥንቃቄ
በTIKVAH-ETHIOPIA ስም በተዘጋጀ ሀሰተኛ የቴሌግራም አካውንት የማጭበርበር ስራ እየተሰራ በመሆኑ አባላት ጥንቃቄ እንድታደርጉ አደራ እንላለን።
የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዛሬ ከሰዓት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ አንዳንድ ህገወጥ ድርጅቶች የአስተዳደሩ ማስታወቂያ እንደሆነ በማስመሰልና በሀሰተኛ የቴሌግራም አካውንት ሀሰተኛ ማስታወቂያ እያሰራጩ መሆኑ ገልጿል።
ይህ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የገለፀው ሀሰተኛ አካውንት በTIKVAH-ETHIOPIA ስም የተከፈተ ሀሰተኛና 25 ሺ ተከታዮች ያሉት ነው።
በዚህ ሀሰተኛ አካውንት ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የተለያዩ ሽልማቶች እንደሚሸልምና ሽልማቱም እስከ መስከረም 20 እንደሆነ የሚገልፅ ሀሰተኛ ማስታወቂያ ነው እየተሰራጨ ያለው።
አስተዳደሩ እንዲህ ዓይነት ሽልማቶች እንዳላዘጋጀ የገለፀ ሲሆን ህገወጦቹም በህግ እንደሚጠይቅ አሳውቋል።
ውድ የቲክቫህ አባላት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስር ያሉት ትክክለኛ አካውንቶች የሚከተሉት ብቻ ናቸው ፦
1. TIKVAH-ETHIOPIA (ከ1.2 ሚሊዮን በላይ አባላት ያሉት)
2. TIKVAH-MAGAZINE (ከ250 ሺ በላይ አባላት ያሉት)
3. TIKVAH-SPORT (ከ140 ሺህ በላይ አባላት ያሉት)
4. TIKVAH-UNIVERSITY (ከ91 ሺ በላይ አባላት ያሉት)
5. TIKVAH-AFAAN OROMOO (ከ20 ሺ በላይ አባላት ያሉት)
6. TIKVAH-AID (ከ5 ሺህ በላይ አባላት ያለቱ)
ከዚህ በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቴሌግራምና ከትዊተር ውጭ ምንም አይነት የ #ፌስቡክ አካውንት የለውም።

* Afar
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በ አፋር ክልል በጦርነቱ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ደግሞ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አመልክቷል።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፥ በአፋር ክልል ለሚገኙ ከ530 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የሆነ የምግብ ዕርዳታ ለማድረስ ድጋፉን እያጠናከረ እንደሚገኝ ገልጿል።

#ETHIOPIA😷
ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 34 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 34 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 5,351 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 737 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 831 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily