TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GERD 🇪🇹 #UNSC

ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ ፅፋለች።

ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለወቅቱ የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት በላኩት ደብዳቤ ኢትዮጵያ ፦

- በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ ያላትን የፀና አቋም አስረግጣ ገልፃለች።

- ግብፅ እና ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሌትና አስተዳደርን በማስመልክት ወደሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር እንዲመለሱ፤ እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የድርድር ሂደት እንዲያከብሩ ሊያስስቧቸው ይገባል ብላለች።

- በኢትዮጵያ በኩል ጥልቅ ፍላጎት ቢኖርም ፤ግብፅ እና ሱዳን ሁሉንም ሀገራት ተጠቃሚ ወደሚያደርገው መፍትሄ ለመምጣት በሚያስችል ቅን ልቦና እየተደራደሩ አይደለም ብላለች።

- ግብፅ እና ሱዳን ድርድሩን “በማኮላሸት” እና ጉዳዩን “ዓለም አቀፍ በማድረግ” በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደርን መምረጣቸውን ገልፃለች።

- ሃገራቱ በአስገዳጅ ስምምነት ስም ኢ-ፍትሐዊ ሁኔታዎችን ለማስጠበቅ እና በግድቡ ውሃ እንዳትጠቀም ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት ተቀባይነት እንደሌለው ገልፃለች።

- የሶስቱ ሃገራት መሪዎች እ.ኤ.አ በ2015 በሱዳን ካርቱም ለፈረሙት የመርሆዎች ስምምነት ያላትን ቁርጠኝነትም ገልጻለች ግብጽ እና ሱዳን በስምምነቱ የገቡትን ቃል አለመጠበቃቸውን ጠቁማለች።

- ጫና ለማድረግ የሚደረጉ የትኛውም ዓይነት ሙከራዎች እና ድርድሩን ከህብረቱ ውጭ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች በሃገራቱ መካከል ያለውን መተማመን የበለጠ እንደሚጎዱ ገልፃለች። [Al AIN]

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#UNSC

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ሁኔታ ላይ እየመከረ ነው።

ይህ ስብሰባ ምክር ቤቱ በስምንት ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ጉዳይ #በግልጽ የመከረበት ነው።

ስብሰበውን #በቀጥታ በUN የYoutube ገፅ መከታተል ይቻላል።

@tikvahethiopia
#UNSC

ትላንት ምሽት በነበረው የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ሀገራት ምን አሉ ?

ሩሲያ ፦ በድጋሚ የኢትዮጵያ ጉዳይ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን አፅንኦት ሰጥታ ገልፃለች፤ ነገር ግን ሰላም ለእርሻም ይሁን የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቦታቸውን ለመመለስ አስፈላጊ መሆኑን አስንታለች፤ ትግራይ ውስጥ ስላለው ሁኔታ ውስብስብ የሆነውን የወታደራዊ እና የፖለቲካ ሁኔታ ሂደት በቅርበት እንደምትከታተል ገልፃ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ያወጀው የተናጠል ተኩስ አቁም ትክክለኛ እርምጃ ነው ብላለች።

ቻይና ፦ በድጋሚ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ባለቤትነት ሙሉ በሙሉ ማክበር እንዳለበት ገልፃለች፤ ትግራይ ውስጥ ሙሉ የተኩስ አቁም ስምምነት ይደረጋል ብላ ተስፋ እንደምታደርግ ገልፃ፤ በሁሉም ወገኖች በኩል ያለው ልዩነት በፖለቲካ ንግግር ሊፈታ ይገባል ብላለች።

ኬንያ በ #A3Plus1 ስም ፦ የእርዳታ ሰራተኞችን ጨምሮ ያልታጠቁ ሰዎችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችን አውግዘዋል፣ ወሲባዊ ጥቃት ስለደረሰባቸው ሴቶች እና ልጃገረዶች ሃዘናቸውን ገልፀዋል፣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ኃይል ከትግራይ እንዲወጣ ጠይቀዋል፤ መንግስት ያወጀውን የተናጠል የተኩስ አቁም ደግፈዋል፤ ለኢትዮጵያ የግዛት አንድነት እና ሉአላዊነት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፤ በዚህ ወሳኝ ወቅት ለሀገር ግንባታ፣ ለብልፅግና ፣ ለዘላቂ ሰላም ከኢትዮጵያ ጋር በአንድነት እንደሚቆሙ ገልፀዋል።

አሜሪካ ፦ የትግራይ ክልል ሰብዓዊ ሁኔታ እጅግ አስቸኳይ እና አሳሳቢ ነው ፤ ግጭቱ መቆም አለበት ፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ ተደራሽነት ሊኖር ይገባል፣ ተጠናቂነትም መስፈን አለበት ብላለች።

ቀጣዩን ያንብቡ : telegra.ph/UN-Security-Council-07-03

@tikvahethiopia
#UNSC

ዛሬ የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ይመክራል።

ስብሰባው ላይ ለመካፈል የኢትዮጵያ ዉኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ወደ ኒውዮርክ ማቅናታቸውን አል አል ዐይን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ የፀጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ እና ሱዳን በገጠሙት የግድቡ ዉዝግብ ላይ ለመነጋገር በሚያደርገው ስብሰባ ላይ #ኢትዮጵያን ይወክላሉ፡፡

በስብሰባው ላይም የኢትዮጵያን አቋም ያንጸባርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያን ከሚወክሉት ዶ/ር ኢ ር ስለሺ በቀለ በተጨማሪ በስብሰባዉ ላይ የግብፅና የሱዳን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች የሚገኙ ይሆናል፡፡

ከሶስቱ ሀገራት ሚንስትሮች በተጨማሪ ፦
- በአፍሪቃ ቀንድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ፣
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ኃላፊ
- የወቅቱ የአፍሪቃ ሕብረት ሊቀመንበር የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዲፕሎማት ለተሰብሳቢዎች ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አል ዓይን አስነብቧል።

@tikvahethiopia