TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ውድ_ቤተሰቦቻችን_ጥንቃቄያችሁን_አጠናክሩ

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,621 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ13 ሰዎች ህይወት ደግሞ ጠፍቷል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 10,620 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1,621 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 13 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ በ #ኢትዮጵያ ጉዳይ ፦

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት (UNSC) በትግራይ ክልል ግጭት ዙሪያ ትላንት ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ የድርጅቱ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ የተገኙ ሲሆን፤ በጦርነቱ የተካፈሉ አካላት በሙሉ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ምንም እንኳን የኢትዮጵያ መንግስት የተናጥል ተኩስ አቁም በማወጅ ከትግራይ ቢወጣም የህወሓት ሀይሎች ወደ ጎረቤት አፋር እና አማራ ክልሎች ጥቃት በመክፈታቸው አጠቃላይ የተኩስ አቁም ላይ መደረስ እንደልተቻለ ገልጸዋል።

ከወራት በፊት በትግራይ ክልል የተከሰተው ግጭት አሁን ላይ እየተስፋፋ መሆኑን እና በርካታ ሰብአዊ ኪሳራዎች እያስከተለ መሆኑን ተናግረዋል።

በጦርነቱ ሳቢያ፦
- የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በየእለቱ እያሻቀበ መሆኑን
- ከ2 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን ግጭቱን ተከትሎ መፈናቀላቸውን
- ከትግራይ ክልል በተጨማሪም ወደ አማራ እና አፋር ክልል በተስፋፋው ግጭት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን፤
- ከሰብአዊ ቀውስ በተጨማሪም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ እየተጎዳ መሆኑን
- የበሀገሪቱ የብድር ጣራ እየጨመረ መሆኑን
- ሀገሪቱ እዳ የመክፈል አቅሟ እየተዳከመ መምጣቱን፣
- የኑሮ ውድነቱ በከፍተኛ ሁኔታ እያሸቀበ መምጣቱን ገልፀዋል።

ገተሬስ ፥ የኢትዮጵያ አንድነት እና የቀጠናው መረጋጋት ወሰሳኝ ናቸው ያሉ ሲሆን አሁን ላለው ሁኔታ ወታደራዊ መፍትሄ የለም ሲሉ ተናረዋል።

በጦርነቱ የተካፈሉ አካት በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም እንዲያድርጉ፣ የውጭ ሀገራት ሀይሎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ፣ ለሰብአዊ ድጋች መተላለፊያ መንገዶች እንዲከፈቱ እና ችግሩን ለመቅረፍ #በኢትዮጵያ_የሚመራና ሁሉንም አካታች የሆነ ውይይት እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

#Al_AIN

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሀገራት በፀጥታው ም/ቤት ምን አሉ?

#Russia

በUN ፀጥታ ም/ቤት የሩሲያ ተወካይ የኢትዮጵያ መንግስት ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ያወጀው የተናጥል የተኩስ አቁም በህወሓት ሀይሎች መጣሱ አሳዛኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የህወሓት ሀይሎች ከትግራይ ውጪ ወደ አማራና አፋር ክልሎች ጥቃት መክፈታውን፤የሀገር ውስጥ ፈናቃዮች ቁጥር በእጥፍ እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።

“የሰብአዊ ድጋፍ ጉዳይን ፖለቲካዊ ማድረግ ተገቢ አይደለም፣ በሚዲያ የሚካሄደው መርዛማ አካሄድ የመሳካት እድሉ አነስተኛ ነው” ብለዋል፤ሰብአዊ ድጋፍ ሲቀርቡ ለትግራይ ብቻ ተብሎ ሳይሆን፤ለአማራ፣ አፋር፣ ሶማሌና ኦሮሚያም ክልሎችም መሆን አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

“በኢትዮጵየ ፖለቲካው ውይይት እንደጀመር እንደግፋለን፤ ነገር ግን ውይይቱ ያለማንም ጣልቃ ገብነት #በኢትዮጵያውያን መሪነት ሊካሄድ ይገባል" ብለዋል።

ለኢትዮጵያ ሚደረጉ ድጋፎች የሀገሪቱን ሉአላዊነት እና አንድነት ባስጠበቀ መልኩ ሊካሄድ ይገባል ያሉ ሲሆን፤ ሰኔ ወር በተካሄደው ምርጫ ኢትዮጵያውያን የመረጡት መንግስት ሀገሪቱን ወደቀድሞ መስመር የመመለስ አቅም እንዳለው የሩሲያ መንግስት ያምናል ሲሉ ተግረዋል።

#China

የቻይና ተወካይ በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም አካላት በራሳቸው መንግድ በሚያድርጉት የፖለቲካ ውይይት ልዩነቶቻቸውን እንደሚፈቱ ቻይና ታምለች ብለዋል። በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ስራቸውን በሚሰሩበት ጊዜ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ባከበረ መልኩ መሆን ይገባል ብለዋል። ለኢትዮጵያ ሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። በሰብአዊ መብትና በሰብዓዊ ድጋፍ ስም በኢትዮጵየ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚደረጉ ጣልቃ ገብነቶችን ቻይና አጥብቃ ትቃወማለች ብለዋል።

ያንብቡ፦ telegra.ph/UNSC-08-27

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በፀጥታው ም/ቤት ስብሰባ የኢትዮጵያ ተወካይ ምን አሉ ?

በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፤ የህወሓትን ጸብ አጫሪነት ለምክር ቤቱ ያብራሩ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግሰት ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ተኩስ አቁም አውጆ መውጣቱ በአካባቢው ለሰብአዊ እንቅቃሴ እንዲሁም ሰላም እና መረጋጋትን ለማምጣት ነበር ብለዋል።

ሆኖም ግን ህወሓት ወደ ተኩስ አቁም የመምጣት ፍላጎት የላቸውም፤ ይባስ ብሎም ህጻናትን ወደ ውትድርና እያስገቡ ነው፤ ወላጆች ልጆቻውን ለውትድርና እንዲሰጡ እርዳታ እህልን እንደ ማስፈራሪያ እየተጠቀሙ ነው ብለዋል።

ህወሓት በአማራ እና በአፋር ክልሎች ላይ በከፈተው ጥቃት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀለቸውን እንዲሁም በህወሓት ተግባር ከትግራይ ክልል በተጨማሪ በአማራ እና አፋር ክልሎች የሚገኙ አርሶ አደሮች የግብርና ስራ መስራ እንዳልቻሉም አስረድተዋል።

ቡድኑ የእርዳታ እህሎች እንቅስቃሴን እያስተጓጎለ መሆኑን በመጥቀስ፤ ሀገሪቱ እንዳትረጋጋ ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀይሎች ጋር ጥምረት እየፈጠረ መሆኑን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ግብ ሰላም ነው፤ ነገር ግን ህወሓት በኢትዮጵያና በሰላም መካከል እንቅፋት ሆኖ ቆሟል ሲሉም ተናግረዋል።

ሁሉም አካል የህወሓት ቡድን ከዚህ ተግባሩ እንዲታቀብ ጫና እንዲፈጥሩ ጥሪ ያቀረቡት አማባሳደር ታዬ ፤ ሁሉም የም/ቤቱ አባላት እውነታ ላይ የተመሰረተ መረጃ ብቻ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ በልዩነት ውስጥ አንደነትን መፍጠር የቻለች ሀገር ነች፤ አሁን በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለው ለውጥም መድሎን ሳይሆን አንድነትን ማጠናከር ላይ የሚሰራ ነው ብለዋል።

#አልአይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የደ/ሱዳን ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ። የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚልና የመከለከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል ተብሏል። በኢትዮጵያ ቆይታቸው…
#Ethiopia #SouthSudan

ወደኢትዮጵያ ለስራ ጉብኝት የመጡት የጎረቤት ሀገር ደ/ሱዳን ፕሬዜዳንት ፥ "ኢትዮጵያ ነጻነቷን እና ሉአላዊነቷን ለማስጠበቅ በምታደርገው የህልውና ዘመቻ እየደረሰባት ያለውን የውጭ ጣልቃ ገብነት አንቀበለም" ማለታቸው ተሰምቷል።

የጠ/ሚ ፅ/ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም፥ ሳልቫ ኪር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ጋር በትላንትና እለት ከተወያዩ በኋላ ህወሃት እያደረሰ ያለውን ጥቃት ኮንነዋል ብለዋል።

“የጉብኝቱ ትኩረት ቁልፍ በሆኑ የሁለትዮሽ እና የክልል ጉዳዮች ላይ በጋራ መነጋገር ነበር” ሲሉም አክለዋል፡፡

ኪር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቢትሪስ ዋኒ-ኖህን ጨምሮ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የልዑካን ቡድን ጉብኝት ላይ “በተለይ ትኩረት የሰጠው ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን እና የጋራ የመሠረተ ልማት ግንባታን ማጠናከር ነበር” ማለታቸውን ሱዳን ፖስት ዘግቧል፡፡

ፕሬዜዳንት ሳልቫኪየር ፥ ህወሃትን በተመለከተ "ከኢትዮጵያ ጎን እንቆማለን" ስለማለታቸው የተገለፀ ሲሆን በሰኔ ወር የተከናወነው ሀገራዊ ምርጫ በስኬት መጠናቁንና በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተመለከተ ለዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንኳን ደስ አለዎት ሰሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopoa
TIKVAH-ETHIOPIA
#update አሁን ይፋ በሆነ ሪፖርት ከካቡል ኤርፖርት ውጭ በደረሰው ፍንዳታ ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች የተጎዱ ሲሆን ከጎጂዎቹ መካከል የአሜሪካ ሰዎች እንዳሉበት CNN ዘግቧል። በሌላ በኩል ደግሞ ቃላቸውን ለአልጀዚራ የሰጡ አንድ በታሊባን ቡድን ውስጥ በኃላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኙ ግለሰብ ከ " ካቡል ኤርፖርት " ውጭ በደረሰው ፍንዳታ 11 ሰዎች (ህፃናት ልጆችን ጨምሮ) መገደላቸውን ሪፖርት አድርገዋል።…
#Kabul

ትላንትና ከካቡል ኤርፖርት ውጭ በተፈፀመው አጥፍቶ ጠፊ የፈንጂ ጥቃት የሟቾች ቁጥር 60 መድረሱ ሪፖርት ተደርጓል።

ከ60 ሟቾች መካከብ 13ቱ የአሜሪካ ወታደሮች ናቸው።

በጥቃቱ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር በመቶዎች ናቸው።

ለጥቃቱ አፍጋኒስታን የሚገኘውና የISIS የአፍጋን ቅርጫፍ ኃላፊነቱን ወስዷል። ይህ የሽብር ቡድን እጅግ ወግ አጥባቂው የታሊባን ቡድን መለሳለስ የሚታይበት ለዘብተኛ ነው የሚል ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም ሌሎች የግድያ ጥቃቶችን የፈጸመ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kabul ትላንትና ከካቡል ኤርፖርት ውጭ በተፈፀመው አጥፍቶ ጠፊ የፈንጂ ጥቃት የሟቾች ቁጥር 60 መድረሱ ሪፖርት ተደርጓል። ከ60 ሟቾች መካከብ 13ቱ የአሜሪካ ወታደሮች ናቸው። በጥቃቱ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር በመቶዎች ናቸው። ለጥቃቱ አፍጋኒስታን የሚገኘውና የISIS የአፍጋን ቅርጫፍ ኃላፊነቱን ወስዷል። ይህ የሽብር ቡድን እጅግ ወግ አጥባቂው የታሊባን ቡድን መለሳለስ የሚታይበት ለዘብተኛ ነው…
"...ምህረት አይኖረንም፤ አንረሳውምም፤ የገባችሁበት ገብተን እናድናችኋለን፤ ዋጋ እንድትከፍሉም እናደርጋለን" - ጆ ባይደን

የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ትላንት በካቡል ከተፈፀመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ንግግር አድርገዋል።

የሽብር ጥቃቱን ለፈጸሙትም ሆነ አሜሪካን ለመጉዳት የሚመኙ አካላትን ጠንከር ባለ ንግግራቸው አስጠንቅቀዋል።

ባይደን ፥ "ምህረት አይኖረንም፤ አንረሳውምም፤ የገባችሁበት ገብተን እናድናችኋለን፤ ዋጋ እንድትከፍሉም እናደርጋለን" ሲሉ ዝተዋል።

አሜሪካ እና አፍጋኒስታንን የሚቆጣጠረው ታሊባን ቀደም ሲል በደረሱት ስምምነት መሳረት የአሜሪካ ወታደሮች እና ተልዕኮ ከ4 ቀናት በኋላ የፊታችን ረቡዕ ያበቃል።

የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር ፔንታጎን ተጨማሪ የሽብር ጥቃት ሊኖር ይችላል ሲል ስጋቱን በመግለጥ ጥንቃቄ እንዲደረግ ከወዲሁ አሳስቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፦ አፍጋኒስታን ውስጥ አሜሪካንን ሲያግዙ ከነበሩ የውጭ ኃይሎች መካከል የጀርመን ወታደሮች ሙሉ በሙሉ ያለምንም ጉዳት ወደ ጀርመን መመለሳቸው ተጠቅሷል።

Source : #DeutscheWelle (DW)

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የሐዋሳ ሀይቅን የማስዋብ ፕሮጄክትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል አካባቢን ነፃ ማድረግ ስራ መጀመሩን ከተማ አስተዳደሩ ዛሬ አሳውቋል።

የሐዋሳ ሀይቅ የማስዋብ ስራ በከተማዋ በ2014 በጀት አመት በይፋ ከሚጀመሩ ፕሮጄክቶች መካከል አንዱ እንደሆነ ተገልጿል።

ፕሮጄክቱ ሲጠናቀቅ የሐዋሳን ሀይቅ ለዘርፈ ብዙ የቱሪዝም መስህብነት ብቁ የሚያደርገው ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ ገልጿል።

@tikvahethiopia
ችሎት !

በአማራ ክልል፤ ምዕራብ ጎጃም ዞን፤ ጎንጂ ቆለላ ወረዳ ከሦስት ዓመት ግድም በደቦ በተመራማሪዎች ላይ ግድያ የፈፀሙ 32 ተከሳሾች ከ1 ዓመት እስከ 20 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ የባሕር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቅጣት ወሳኔ አስተላለፈ።

በእነ መላኩ አበበ የክስ መዝገብ የቀረቡ 32 ተከሳሾች በጋራ ሰው በመግደል፣ አካል በማጉደል፣ የግድያ ሙከራ በማድረግና ንብረት በማውደም ከጥቅምት 13 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ጀምሮ ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት ሲከታተሉ ቆይተዋል።

ጥቅምት 13 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ተከሳሾቹ "ተመራማሪዎቹ ልጆቻችንን የማይታወቅ መርፌ በመውጋት ለአደጋ አጋልጠዋቸዋል" በሚል ያልተረጋገጠ ወሬ ተነሳስተው፤ ለሦስተኛ ዲግሪ ማሟያ በወረዳው አዲስ ዓለም ከተማ የምርምር ሥራ ይሠራ በነበረ አንድ ተመራማሪ ላይና በሌላ ረዳቱ ላይ የሞት፤ በሌሎች ሦስት የጤና ባለሞያዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳትና በሌላ ግለሰብ ላይ ደግሞ የመግደል ሙከራ እንዲሁም መኪና የማቃጠል ተግባር መፈፀማቸውን የባሕር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት አመልክቷል።

ፍ/ቤቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በዋለው ችሎት በ32ቱ ተከሳሾች ላይ እንደየ ወንጀል ተሳትፏቸው ከ1 ዓመት እስከ 20 ዓመት የሚደርስ የፅኑእ እስራት ቅጣት አስተላልፎባቸዋል።

ሌሎች አምስት ተከሳሾች በወንጀሉ ስለመሳተፋቸው የቀረበ ማስረጃ ባለመኖሩ ቀደም ሲል በነፃ መሰናበታቸውን ፍ/ቤቱ አስታውሷል።

በዛሬው የፍ/ቤት ውሎ በርካታ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በፍርድ ቤቱ ቅጽር ግቢ ታይተዋል። በፍርድ ቤቱ ውስጥ የተወሰኑ ጉዳዩን የሚከታተሉ ታዳሚያንም ነበሩ። የፍርድ ውሳኔው ሲሰጥ የማረሚያ ቤት አልባሳት የለበሱ እስረኞች ውሳኔውን ቆመው ተከታትለዋል።

ምንጭ፦ ጀርመን ድምፅ ሬድዮ

@tikvahethiopia
#የጤና_ሚኒስቴር_ማስጠንቀቂያ !

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ፥ የኮቪድ-19 ክትባትን ከመንግስት የጤና ተቋማት ውጪ የሚሰጡ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀ።

በሚኒስቴሩ የብሄራዊ ክትባት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዮሃንስ ላቀው ፥ የኮቪድ 19 ክትባትን በግል እያስከፈሉ የሚሰጡ አካላት ህገ ወጥ በመሆናቸው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ህብረተሰቡም ይሄንን ተከትሎ ራሱን ለአደጋ ማጋለጥ እንደሌለበት ተናግረዋል።

አቶ ዮሃንስ ክትባቶቹ በእርዳታ የገቡ መሆናቸውን አስታውሰው፣ ለህብረተሰቡ በመንግስታዊ ጤና ተቋማት ብቻ በነፃ የሚሰጡ ሆነው ሳለ ክፍያ እየተጠየቀ እንደሚሰጥ ሰምተን እያጣራን ነው ብለዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በህገ ወጥ መንገድ ክትባቶቹን ለመገበያየት መሞከር በአያያዙና በአወሳሰዱ ላይ እክል የሚፈጥር በመሆኑ ጉዳቱ የከፋ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

እስካሁን ለየተኛውም የግል ተቋም የኮቪድ 19 ክትባትን መስጠት እንዲችል ያልተከፋፈለ መሆኑንና ፈቃድም እንዳልተሰጣቸው በማሳሰብ ለወደፊት በግል ጤና ተቋማት መሰጠት ሲጀመር ቀድመን የምናሳውቅ ይሆናል ብለዋል። እስካሁን ግን ክትባት እንዲሰጥ ፈቃድ የተሰጠዉ የግል የህክምና ተቋም የለም ሲሉ አስገንዝበዋል።

መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ነው።

@tikvahethiopia
ችሎት !

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ፥ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አቤቱታ ባቀረበባቸው በደቡብ ክልል በ4 የምርጫ ክልሎች የተካሄደው የክልል ምርጫ ውጤት ተሰርዞ በድጋሚ ምርጫው እንዲካሄድ ውሳኔ ሰጠ፡፡

ኢዜማ በ28 ምርጫ ክልሎች በድምፅ አሰጣጥ ሂደት በድምጽ ቆጠራና በ6 ምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ የዕጩዎቼ ፎቶና ዝርዝር ባለመካተቱ አልተወዳደርኩም ለዚህም 156 ገጽ የሰነድና የምስል ማስረጃ አያይዤ ለቦርዱ ባቀርብም ቦርዱ ማስረጃዬን ሳይመለከት ነው ውሳኔ የሰጠው ሲል ምርጫው እንዲደገም በማለት ተከራክሮ ነበር።

ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ኢዜማ ስርአቱን የተከተለ አቤቱታ አላቀረበም የቀረበው አቤቱታ እንጂ በማስረጃ የተደገፈ አደለም ስድስቱ ጣቢያ ላይዝርዝር ያቀረበ ቢሆንም ሁለቱ ባዶ ናቸው ሲል መከራከራያ ነጥብ አንስቶ ይግባኙን ተቃውሞ ነበር፡፡

ክርክሩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም መርምሮ ሰኔ 14 ቀን በደቡብ ክልል በላስካ መደበኛ ፣ በቁጫ ልዩ ፣ በጉመር ሁለት እና በብርብር ምርጫ ክልል የተካሄደው የክልል ምርጫ የኢዜማ ዕጩዎች በድምፅ መስጪያ ወረቀት ላይ ፎቶዋቸውና ስም ዝርዝራቸው ያልተካተተ በመሆኑ ዕጩዎቹ ሳይወዳደሩ በመቅረታቸው ምርጫው እንዲደገም ወስኗል።

በሌላ በኩል ኢዜማ በሰኔ14 ቀን 2013 ዓ/ም በ22 ምርጫ ክልሎች በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ በድምጽ አሰጣጥ እና በድምጽ ቆጠራ ሂደት ላይ ታዛቢዎቼ እንዳይሳተፉ ተደርጓል ሲል ያቀረበው አቤቱታን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ጥሰቱ በማን ላይ በየትኛው ጣቢያ መቼ የሚለው ዝርዝር ፍሬ ነገርና ማስረጃ አልቀረበም ሲል የኢዜማን ይግባኝ አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tarik-Adugna-08-27

የመረጃ ባለቤት : ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ዛሬ ከሰዓቱን በጠሩት የጂ-20 ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ የተሰኘ ጉባዔ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበይነ መረብ በመታገዝ ተሳትፈዋል።

“ለንግድ እና ለኢንቨስትመንት ማሕቀፋዊ ሁኔታዎች” በሚል ርዕስ የሚካሄደው ጉባዔ የስምምነቱ ፈራሚ የሆኑ ሀገራት ተጨማሪ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እንዲያገኙ በሚያስችል ሁኔታ ማሕቀፋዊ ሁኔታዎችን ወደ ቀጣይ ርምጃዎች ለመውሰድ የታለመ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር፣ ለሙዐለ ነዋይ ፍሰት ምቹ ነባራዊ ሁኔታ እንዲኖር ለማስቻል በኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አማካኝነት ማክሮ ኢኮኖሚያ፣ መዋቅር እና የዘርፍ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን ገልጸዋል።

#PMofficeEthiopia

@tikvahethiopia