TIKVAH-ETHIOPIA
ሙሐመድ አወል ሙሐመድ ሳላህ አረፉ። በበርካታ የጥበብ ስራዎች የሚታወቁት ድምፀ መረዋው ሙሐመድ አወል ሳላህ በልብ ህመም ማረፋቸው ተሰምቷል። ትውልዳቸው በደሴ ከተማ አራዳ አካባቢ ሲሆን ከእናታቸው ከወ/ሮ ሰዕዲያ ሰዒድ አህመድ እና ከአባታቸው ሐጅ ሙሐመድ ሳላህ አህመድ በ1958 ነበር የተወለዱት። ትምህርታቸውን በወ/ሮ ስህን ትምህርት ቤት ከተከታተሉ በኋላ ወደ ውትድርናው አለም በመቀላቀል ሃገራቸውን…
ሙሐመድ አወል ሙሐመድ ሳላህ ስርዓተ ቀርብ ተፈፀመ።
የሙነሺድ መሀመድ አወል ሳላህ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ነሀሴ 17 ቀን 2013 ተፈፅሟል።
ሥነ-ስርዓተ ቀብራቸው የተፈፀመው ኮልፌ በሚገኘው የሙስሊም መካነ መቃብር ነው።
በቀብር ስነስርዓቱ ላይ ቤተሰቦቻቸው ፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተው ነበር።
Photo Credit : MUBA (Tikvah-Family)
@tikvahethiopia

#CHINA 🇨🇳 #ETHIOPIA 🇪🇹
በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ለሚገኙ እና ይበልጥ ለኮቪድ-19 ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሆን 300 ሺህ ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ቻይና ለገሰች።
በዛሬው እለት ክትባቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዥያዎ ዢዮዋን ለዶክተር ሊያ ታደሰ አስረክበዋል።
በርክክቡ ወቅት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩት ይህ ከቻይና መንግስት ለሶስተኛ ግዜ ድጋፍ የተደረገው 300 ሺህ ዶዝ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት በዋናነት በስራቸው ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች በተለይም በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ይውላል ብለዋል፡፡
በተጨማሪ ድጋፉ ካለው የኮቪድ-19 ህሙማን መብዛትና የኮቪድ-19 ስርጭት መበራከት ጋር ተያይዞ ያለውን ጫና ከመቀነስ አንጻር ጉልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
ቻይና 🇨🇳 በዛሬው ዕለት የላከችውን 300 ሺህ ዶዝ ክትባትን ጨምሮ ለኢትዮጵያ 1 ሚሊየን ዶዝ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ድጋፍ አድርጋለች፡፡
#MoHEthiopia

#ምርጫ2013
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስተኛውን አጠቃላይ ምርጫን በዋናነት ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ማስፈፀሙ ይታወሳል።
- በመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ በታዪ ጉልህ ግድፈቶች፣
- በመራጮች ምዝገባ ላይ በቀረቡ አቤቱታዎችን ለማጣራት ጊዜ በማስፈለጉ
- ከጸጥታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የተነሳ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድምፅ አሰጣጥ ያልተደረገባቸው ቦታዎች እንዳሉ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ አመራር ቦርድ ቀሪ ምርጫ ያልተከናወነባቸው የምርጫ ክልሎችን፣ የምርጫው ሂደት ያለበትን ሁኔታ እና የመሳሰሉትን በመገምገም ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
* ውሳኔዎቹን ከላይ በተያያዘው ምስል ያንብቡ።

#SOMALIA 🇸🇴 #ETHIOPIA 🇪🇹
የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢተማዦር ሹሞች በአዲስ አበባ መከሩ።
የኢትዮጵያ መከላከያ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፣ ከሶማሊያ አቻቸው ጋር በፀጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
የሶማሊያ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል አዲዋ የሱፍ ራጌ አዲስ አበባ በመምጣት ነው ከኢትዮጵያው አቻቸው ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ጋር ውይይት ያደረጉት።
በውይይቱ ወቅት ጀነራል አዲዋ የሱፍ ራጌ ፥ በሶማሊያ ውስጥ የሚገኘው አሸባሪ ቡድን አልሸባ በሶማሊያ ህዝብ ላይ የሚያደረሰውን ጫና በመቀነስ ረገድ በአሚሶም ጥላ ስር ለግዳጅ የተሰማራው የኢትዮጵያ ሰራዊት የማይተካ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል።
ጀነራሉ አክለውም የሶማሊያን ሰላም ለማስጠበቅ ቃል እየገቡ ከሚሄዱት የውጭ ሀገራት ይልቅ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ጎረቤት ሀገሮች የሰሩት ተግባር ፅኑ ወዳጅነት በቃላት የሚነገር ብቻ ሳይሆን በተግባር የሚረጋገጥ መሆኑ ማሳያ መስታወት ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያው የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ በበኩላቸው ፣ ሶማሊያ ራሷን ለመቻል በምታደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ ትብብር እና አጋርነት እንደማይለያት ቃል ገብተዋል።
"የጎረቤት ሀገር ሰላም የእኛም ሰላም ፤ የጎረቤት ሀገር ሰላም መናጋት የእኛም ስጋት በመሆኑ የጋራ ጠላታችንን እስከ መጨረሻው ለመደምሰስ ዝግጁ ነን" ማለታቸውን ውይይቱን የተከታተሉት በመከላከያ ውጭ ግንኙነት የሁለትዮሽ ትብብር ጉዳዮች ዳይሬክተር ኮ/ል የኑስ ሙሉ ተናግረዋል ፡፡
መረጃው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ነው።

#BREAKING
ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ምርጫ ባልተካሄደባቸው ምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ቀን መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲሆን ውሳኔ አሳለፈ።
ድምፅ አሰጣጡ የሚከናወነው ፦
- በሶማሌ ክልል፣
- በሐረሪ ክልል
- በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል የሚሆን ሲሆን የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ህዝበ ውሳኔም በተመሳሳይ ቀን መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም የሚከናወን ይሆናል ተብሏል።
በቀሪ የምርጫ ክልሎች ላይ የሚኖረውን ሂደት አስመልክቶ ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ መረጃዎችን እሰጣለሁ ብሏል።
* ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ምሽት ያሰራጨው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

አሜሪካ በኤርትራ ጦር አዛዥ ላይ ማዕቀብ ጣለች።
አሜሪካ የኤርትራ ጦር በትግራይ ክልል ፈጽሟል ባለችው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት በጦሩ ዋና አዛዥ ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች።
ማዕቀቡ በኤርትራ ጦር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሀንስ ላይ የተጣለ ነው፡፡
ማዕቀቡን የተጣለው በአሜሪካ የፌዴራል ግምጃ ቤት (ትሬዠሪ) በኩል ሲሆን አዛዡ በአሜሪካ ያላቸው ሀብት እንዲታገድ እንደተወሰነ ግምጃ ቤቱ በድረገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
አሜሪካ በጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሀንስ የሚመራው የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽሟል፤ ሴቶችን ደፍሯል እንዲሁም ወጣቶችን እና ንጹሀን ዜጎችን ቤት ለቤት በመግባት ገድሏል ስትል ከሳለች።
የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም ካደረገ በኋላም ተመልሶ ወደ ትግራይ ክልል ገብቷል የሚለው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ጦሩ በአስቸኳይ ወደ ኤርትራ እንዲመለስ ጠይቋል።
ውሳኔው አሜሪካ ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ላላት ቁርጠኝነት ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችልም ነው ግምጃ ቤቱ ያስታወቀው።
አሁንም ጦርነቱ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው የሚለው የህ ተቋም በቀጠለው ግጭት ምክንያት እርዳታ የሰብአዊ መብት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ማድረስ ባለመቻሉ ሁሉም አካላት ግጭቱን እንዲያስቆሙ ጠይቋል።
ኤርትራ ማዕቀቡን በተመለከተ እስካሁን የሰጠችው ምላሽ የለም፡፡
የመረጃ ባለቤት፦ አል አይን ኒውስ
@tikvhethiopia

#መስከረም20
የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ህዝበ ውሳኔ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሚከናወን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ አስታውቋል።
@tikvahethiopia
የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ህዝበ ውሳኔ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሚከናወን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ አስታውቋል።
@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#BBC_HARDtalk
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከቢቢሲ ሀርድቶክ ፕሮግራም ጋር ሰኞ ዕለት ቆይታ አድርገው በትግራይ ከተከሰተው ጦርነት ጋር በተያያዘ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
ትግራይ ውስጥ ተጀምሮ ሌሎች ክልሎች ስለተስፋፋው ጦርነት ፣ በትግራይ ስለተቋረጡት መሰረታዊ አገልግሎቶች፣ ሰለሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ስለእርዳታ አቅርቦት እና ተያያዥ ጉዳዮች ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ከስቴፈን ሳከር ተወያይተዋል።
ዶ/ር ጌዲዮን በምን ጉዳዮች ላይ ምላሽ ሰጡ ?
- የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳይ
- ሰላማዊ መፍትሔ
- የትግራይ ተወላጆች እስር
- የሰብዓዊ መብት ጥሰት ክሶች
- ስለመሠረታዊ አገልግሎቶች ... ሌሎችም።
ያንብቡ : telegra.ph/BBC-HardTalk-08-24 / ጥሩ የሆነ የኢንተርኔት ግንኙነት ማግኘት ከቻላችሁም ከላይ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Credit : BBC Amharic Service

አሜሪካ በኤርትራ ጦር አዛዥ ላይ ማዕቀብ ጣለች። አሜሪካ የኤርትራ ጦር በትግራይ ክልል ፈጽሟል ባለችው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት በጦሩ ዋና አዛዥ ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች። ማዕቀቡ በኤርትራ ጦር ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሀንስ ላይ የተጣለ ነው፡፡ ማዕቀቡን የተጣለው በአሜሪካ የፌዴራል ግምጃ ቤት (ትሬዠሪ) በኩል ሲሆን አዛዡ በአሜሪካ ያላቸው ሀብት እንዲታገድ እንደተወሰነ…
#Eritrea
ኤርትራ፤ አሜሪካ በሀገሪቱ የጦር መሪ ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሀንስ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ "መሠረተ ቢስ" ስትል ውድቅ አድርጋዋለች።
ኤርትራ "ህገ ወጥ" ያለችውን የአሜሪካን ማዕቀብ በተመለከተ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል መግለጫ አውጥታለች።
አሜሪካ በጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሀንስ ላይ "ተቀባይነት የሌላቸውን ክሶች ሰንዝሯል" ያለው መግለጫው የኤርትራ መንግስት የተቃጣበትን መሠረተ ቢስ ውንጀላና ክስ በደብዳቤም ሆነ በመንፈስ እንደማይቀበል አስታውቋል።
የአሜሪካ አስተዳደር እንዲህ ዐይነት መሠረተ ቢስ የውንጀላ ዘመቻዎችን በኤርትራ ላይ ሲያርግ የመጀመሪያው እንዳይደለም ሲል ጠቁሟል።
ባሳለፍነው መጋቢት መባቻ ላይ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳሌህ ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን "እንዳለመታደል ሆኖ በሚዲያዎች በሚነዙ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ላይ ተመስርተው ማደማደሚያዎችን ይሰጣሉ" ሲሉ በጻፉት ደብዳቤ "ተከታታይ የአሜሪካ አስተዳደሮች ባለፉት 30 ዓመታት በኤርትራ ላይ ሲያራምዱት ወደነበረው ፖሊሲ የተመለሱ በሚያስመስለው ደብዳቤዎ አዝኛለሁ" ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸው እንደነበር አስታውሷል።
ሚኒስትሩ ወደ ዝርዝር ጉዳዮች አልገባም ባሉበት በዚህ ደብዳቤ መፍትሔዎች ሊኖሩ ይችላሉ በሚል ስለመግለጻቸው ነው የተጠቀሰው።
ኤርትራ ምክንያታዊ ያልሆኑ ተደጋጋሚ ክሶችን በዝምታ ልታልፍ እንደማትችልም ይጠቁማል። "ሃሰተኛ" ያለው ውንጀላ ሊጣራ የሚችል ነገር ካለው በገለልተኛ አካል እንዲጣራም ለአሜሪካ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል።
የUN የጸጥታው ም/ቤት ተደጋጋሚ የዓለም አቀፍ ህግጋትና የሃገራትን የሉዓላዊነት ጥሰቶች በመግታትና መፈትሔ በመፈለግ ረገድ ኃላፊነቱን እንዲወጣም አሳስቧል።
(አል-ዓይን)

#Ethiopia
የዋጋ ንረቱ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ፤ የኑሮ ውድነቱ ከፍ እያለ የሰዎችን ኑሮ በእጅግ እየተፈታተነው ነው።
በተለይ ዝቅተኛ ደሞዝ የሚያገኘ ሰራተኞች ኑሮ ለመግፋት ፈተና እየሆነባቸው ነው፤ በየዕለቱ ሚጨምረው የዋጋ ንረት የኑሮውን ጫና መቋቋም ከማይቻልበት ደረጃ እየደረሰ ነው።
ቤት ኪራይ፣ ምግብ የልጆች ት/ቤት ክፍያ፣ የቀን ወጪ ..ሌሎችም ወጪዎች ሲጨምሩ እንጂ ሲቀንሱ አይታይም፤ የሚገኘው ደሞዝ እዛው ነው።
ከቅርብ ጊዜ በኃላ ደግሞ በኢትዮጵያ ሰሜናዊው ክፍል የተፈጠረውን ጦርነት እንደመልካም አጋጣሚ የተጠቀሙ ነጋዴዎች በተለላያዩ ምርቶች ላይ ያለአንዳች ምክንያት ዋጋ በመጨመር ዜጎችን ክፉኛ እያማረሩ ነው።
በተለያዩ ከተሞች ዋጋን በሚጨምሩ ነጋዴዎች ላይ በመንግስት እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ ሪፖርት የሚደረግ ቢሆንም አሁንም የሚቀረው ስራ ብዙ ነው።
በሀገሪቱ ውስጥ የሚሰሩ ኢኮሮሚያዊ አሻጥሮች ፣ ሆን ተብሎ ዜጎች እንዲማረሩ ለማድረግ የሚደረገው ሸር ነገ ሳይሆን ዛሬ አስሸኳይ መፍትሄ የሚፈልግ ነው።
የዋጋ ንረት እየፈጠሩ የዜጎችን ኑሮ የሚፈታተኑ ለሀገር ህልውና አደገኛ የሆኑ አካላት ላይ እርምጃ መውሰድ ካልተቻለ መዘዙ ከባድ ነው። ዜጎችም ነገ ኑሯቸውን የሚያከዱ ህገወጦችን ፣ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላትን ለሚመለከተው አካል በመጠቆም ዜግነታዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል።
Pic Credit : Addis Maleda

በድሬዳዋ የልኳንዳ ቤቶች ዋጋ ተተመነላቸው ...
ከዛሬ ነሐሴ 18 ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የልኳንዳ ቤቶች አንድ ኪሎ ስጋ መሸጫ ዋጋ ተተመነላቸው።
በዚህም መሰረት ፦
- በሆቴል ቤቶች ተጠብሶ የሚሸጥ የበሬ ስራ በኪሎ ግራም 420.00 ብር
- ጥሬ (ወደ ቤት የሚሄድ) የሚሸጥ የበሬ ስጋ በኪሎ ግራም 400.00 ብር
- በልኳንዳ ቤት የሚሸጥ የፍየል ስጋ በኪሎ ግራም 450.00 ብር
- የፍየል ጥሬ ስጋ (ወደ ቤት የሚሄድ) በኪሎ ግራም 430.00 ብር መሆኑ ተገልጿል።
ከላይ ከተተመነው ዋጋ ውጭ ሲሸጥ የተገኘ ማንኛውም ነጋዴ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል ሲል የድሬዳዋ ከተማ ንግድ ፣ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስጠንቅቋል።
ውድ የድሬዳዋ ከተማ የቲክቫህ ኢትዮ. አባላት በከተማችሁ የከተማ አስተዳዳሩ በተመነው ዋጋ እየተሸጠ ስለመሆኑን በ @tikvahethiopiaBot አሳውቁን፤ በተተመነው ዋጋ የማይሸጥባቸው ቦታዎችንም እግረ መንገዳችሁን መጥቀስ እንዳትዘነጉ።

#ALERT🚨
ሶስተኛው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ተደሰ ገለጹ።
ዶክተር ሊያ በኢትዮጵያ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 5 ሺህ 547 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡
በአንድ ቀን ውስጥ ከ1ሺህ በላይ ሰዎች መያዛቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ÷ የወረርሽኙ መጠን ከዚህ በፊት ካለው በእጅጉ መጨመሩን ተናግረዋል።
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአሁኑ ሰአት ቫይረሱ የሚገኝበት ሰው ቁጥር ምጣኔ በእጅጉ መጨመሩ የሚያሳየው ሶስተኛው የኮቪድ 19 መረርሽኝ በኢትዮጵያ መከሰቱን እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
ማህበረሰቡም ከዚህ በፊት የሚያደርገውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሚኒስትሯ አሳስበዋል። #ኤፍቢሲ

#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ፥ "የዳቦ ዋጋን ተመን ለማውጣት የሚፈቅድ አሰራር የለንም" አለ።
ቢሮ ይህን ያለው ለአሀዱ ኤፍ ኤም 94.3 ሬድዮ ጣቢያ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ሚኤሳ በሰጡት ቃል ፥ በመዲናዋ በርካታ ነዋሪዎች የዳቦ ዋጋ በእጅጉ መጨመሩን እንዲሁም የዳቦው መጠንና ዋጋው እንደማይመጣጠን ተደጋጋሚ ቅሬታ ያቀርባሉ ብለዋል።
በመዲናዋ ያሉ ከ 2 ሺህ በላይ ዳቦ ቤቶች ካለፈው 1 አመት ወዲህ ከንግድ ቢሮው ጋር የነበራቸውን ትስስር ያቋረጡ በመሆኑ አሁን ላይ ቢሮው የዋጋ ተመንን ለማውጣት የሚፈቅድ አሰራር እንደሌለው ተናግረዋል፡፡
መንግስት የስንዴ ድጎማውን ማቋረጡን ተከትሎም በመዲናዋ ያሉ ከ 2ሺ በላይ ዳቦ ቤቶች ትስስራቸውን ማቋረጣቸውንም አስረድተዋል፡፡
አቶ ዳንኤል ፥ "ምንም እንኳን በርካታ የመዲናዋ ነዋሪዎች ቅሬታ ቢያቀርቡም አሁን ባለው የቢሮው አሰራር ዳቦ ቤቶቹ ባስቀመጡት የዳቦ ግራም እና ዋጋ በትክክል እየሸጡ መሆን አለመሆኑን ቁጥጥር ይደረጋል እንጂ ዋጋ በመተመን በገበያው ጣልቃ መግባት አይቻልም" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አክለው በተያዘው አመት ባስቀመጡት የዳቦ ግራም መጠን ዋጋ ሲሸጡ ያልተገኙ ወደ 24 የሚጠጉ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡
መረጃው የአሀዱ ኤፍ ኤም 94.3 ሬድዮ ጣቢያ ነው።