#BREAKING
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ፦
"ዛሬ ሀምሌ 12ቀን 2013 ዓ/ም የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ ፈሶአል። ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችም እንኩዋን ደስ አላችሁ: ይህ ውጤት ማለት 2 ተርባይኖችን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገውን የውሃ መጠን ማለት ነው።
በዘንድሮው አመት እየዘነበ ያለው ውሃ መጠን እጅግ ከፍተኛ ነው። ይህም ከፈጣሪ የተሰጠን ፀጋ ምን ያህል ትልቅ እንደህነና እንዴት እያገዘን እንደህነ መረዳት እንችላለን። ለዚሁም ምስጋና ይግባው።
እዚህ ደረጃ ለመድረስ በዘንድሮው አመት መጠነ ሰፊ ስራ ሰርተናል:: በቀጣይ ሁለቱ ተርባይኖች እንዲያመነጩ ብርቱ ስራዎች እየተሰሩ ነው እናም ያንን በቅርብ ወራት በማጠናቀቅ ልፋታችንን ውውጤት ላይ እናደርሳለን።"
@tikvahethiopia

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ItsMyDam🇪🇹
የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ያስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት እና ስለሁለተኛው የግድቡ ሙሌት ለብሄራዊ ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) የሰጡት ሙያዊ ማብራሪያ
Video : 133 MB (WIFI እንድትጠቀሙ እንመክራለን)

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ItsMyDam🇪🇹
ታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሊት የመጀመሪያውን ሃይል ለማመንጨት የሚያስችለውን ውሃ ይዟል፡፡
ዛሬ ሃምሌ 12/ 2013 የውሃ ሙሊቱ ተጠናቆ ከግድቡ አናት ውሃው መፍሰስ ጀምሯል።
ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሊት በያዝነው ሀምሌና ነሃሴ ወር ላይ ለማድረግ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም የዝናቡ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ከታሰበው ጊዜ ቀድሞ ውሃው ሊሞላ ችሏል።
በአመቱ የተከናወኑ ተግባራት የሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሊት ስኬታማ እንዲሆን እንዳስቻለው የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በስፍራው ተገኝተው ተናግረዋል።
22 በሮች እና ትራሽ ክሊነሮች ፤ የስዊች ያርድ ፤ እንዲሁም የትራንስፎርመር ገጠማ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል ሚንስትሩ። አሁን ደግሞ የተርባይነሮች ገጠማ ስራ እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል።
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ ፥ "በተለይ ዘንድሮ ግድቡን ለመገንባት የተኬደበት ፍጥንት የሚደነቅ ነው" ያሉ ሲሆን በቀጣይ ግድቡ እስኪጠናቀቅ በዚሁ ትጋት ስራው እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል፡፡ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ምንጭ፦ የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር

ነገ የሚዘጉ መንገዶች !
1,442ኛው ኢድ-አል አድሐ (አረፋ) በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጀት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
በአዲስ አበባ ስታዲዮም በሚኖረው የጠዋት ስግደት ምክንያት ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ የስግደቱ ሥነ-ሥርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የተወሰኑ መንገዶች ለጊዜዉ ለትራፊክ ዝግ ይሆናሉ።
በዚህም መሰረት ፦
• ከመገናኛ እና ከ22 ለሚመጡ ኡራኤል አደባባይ
• ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ
• ከሪቼ ወደ መስቀል አደባባይ የቀድሞ 4ኛ ክፍለ ጦር
• ከጦር ኃይሎች ወደ ስታዲዮም ሜክሲኮ አደባባይ
• ከመርካቶ በበርበሬ በረንዳ በተክለ ሐይማኖት ወደ ስታዲዩም ለሚመጡ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ
•ከሞላ ማሩ በጌጃ ሰፈር ወደ ስታዲዩም ለሚመጡ ጎማ ቁጠባ
• ከፒያሳ ወደ ስታዲዮም ለሚመጡ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከ4ኪሎ በፊት በር ወደ መስቀል አደባባይ ጊቢ ገብርኤል
የሚወስዱ እና በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ መጋቢ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።
ፖሊስ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ትብብር እንዲያደርጉ የጠየቀ ሲሆን በተጠቀሱት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሸከርካሪን አቁሞ መሔድ የተከለከለ መሆኑን አሳስቧል።

#ETHIOPIA
'በ24 ሰዓት የኮቪድ- 19 ሞት አልተመዘገበም'
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 3,447 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 84 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ ህይወቱ ያለፈ ሰው የለም፤ 143 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

እንኳን አደረሰን ፤ እንኳን አደረሳችሁ !
ለመላው እስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለ1442ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ አል-አድሐ (ዐረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሰሳሰብ ይሆን ዘንድ ከልብ እንመኛለን።

TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ፦ "ዛሬ ሀምሌ 12ቀን 2013 ዓ/ም የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ ፈሶአል። ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችም እንኩዋን ደስ አላችሁ: ይህ ውጤት ማለት 2 ተርባይኖችን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገውን የውሃ መጠን ማለት ነው። በዘንድሮው አመት እየዘነበ ያለው ውሃ መጠን እጅግ ከፍተኛ ነው። ይህም ከፈጣሪ የተሰጠን…
#SUDAN #EGYPT #GERD
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ፦
"... ሁሉ ነገሩ ፊዚክስ ነው፤ ውሃ ይገባል ይጠራቀማል ሲሞላ መያዝ የሚችለውን ያህል በአናቱ ይፈሳል ከዚህ የተለየ ነገር የለውም። ኒውክሌር ፊሲክስ አይደለም፤ ኖርማል ፊዚክስ ነው ፤ ይህንን ማየት ይቻላል።
ሁሉ ጊዜም እኛ ትክክለኛ ሳይንስ እና ያንን መሰረት ያደረገ ፖሊሲ ይዘን ነው የምንክተለው፤ ይህንኑ ነው በድርድሩ ወቅት ለማስረዳት የሞከርነው።
ነገር ግን ይህንን አልምተን የመጠቀም የኛ የኢትዮጵያውያን ሙሉ መብት ነው፤ ይህን እንድሄድበታለን፤ አስፈላጊ የሆነውን ክርክር እንቀጥልበታለን ክርክር የሚያስፈልግ ከሆነ። ነገር ግን ምንም አይነት መጥፎ እና በጎ ያልሆነ ተፅእኖ ስለማያሳድር ይልቅ ተባብረን ቶሎ ግድቡ የሚያልቅበትን ፣ ኔጌቲቭ ተፅእኖዎች በየማያስፈልግ ቦታ ሄደን ክርክር ከመግጠም ይልቅ እዚሁ አንድ ላይ አፍሪካ ውስጥ ቁጭ ብለን ሶስት ወንድማማች/እህትማማች ሀገሮች ተነጋግረን የሚገጥሙንን ችግሮች በጋራ እየፈታን ይልቅ ሪጅናችንን አስተሳስረን፣ እንዴት አድርገን በኢኮኖሚ ብልፅግና ማምጣት እንችላለን የሚሉት ነገሮች ላይ ትኩረት ሰጥተን መስራት ነው የሚያስፈልገን፤ ያ ነው የሚያዋጣው።
ዓለም ተመንጥቆ ሄዶ ይኸው ማርስና ሌሎች ፕላኔቶች ላይ ለማረፍ ይጥራሉ ፤ በቅርቡ ሰዎች ተመንጥቀው ሄደው ተመልሰው ያርፋሉ እኛ ግን ግድብ ስለሰራን እንደአዲስ ነገር አምጥተን ህዝባችንን ማስጨነቅ ፣ ተገቢ ባልሆኑና ፖለቲካዊ በሚመስሉ ንግግሮች ተጠምደን #መመቀኛኘት አይኖርብንም።
መተጋገዝ ፣ አብሮ ማደግ ለአፍሪካውያኖች በጣም አስገላጊ ነው፤ እኛ ይሄን ይዘን ነው የምንቀጥለው"

ነገ የሚዘጉ መንገዶች ! 1,442ኛው ኢድ-አል አድሐ (አረፋ) በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጀት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። በአዲስ አበባ ስታዲዮም በሚኖረው የጠዋት ስግደት ምክንያት ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ የስግደቱ ሥነ-ሥርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የተወሰኑ መንገዶች ለጊዜዉ ለትራፊክ ዝግ ይሆናሉ። በዚህም መሰረት ፦ • ከመገናኛ እና…
የፖሊስ ሪፖርት :
ዛሬ ሐምሌ 13 በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች በተገኙበት በአዲስ አበባ ስታዲዮምና በዙሪያው በሚገኙ ጎዳናዎች እንዲሁም በከተማው ልዩ ልዩ ስፍራዎች የተካሄደው የ1442ኛው የኢድ አል አድሃ የሶላት ስነ-ስርዓት በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ፣ የፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም ሌሎች አጋዥ አካላት፣ መላው የከተማው ነዋሪ እና ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር በማድረጋቸው የሶላት ስነ-ስርዓቱ በሰላም ተጠናቋል፡፡
ለስነ ስርዓቱ በስኬት መጠናቀቅ ድጋፍ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና ቀርቧል።

እንኳን አደረሰን ፤ አደረሳችሁ !
1442ኛው የኢድ አል አደሃ (ዐረፋ) በዓል በሀገራችን ዋና ከተማ አዲስ አበባ ጨምሮ በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል።
በተለያዩ ከተሞች ያለውን የበዓል አከባበር ድባብ የሚያሳዩ ፎቶዎችን በ @tikvahethmagazine መመልከት ይቻላል።
በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የፍቅር፣ ለተቸገሩ ወገኖቻችን የምንደርስበት ይሆንልን ዘንድ እንመኛለን።

#Update "የ7 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል" - ፖሊስ በማእከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ በጣና ሀይቅ 13 ሰዎችን አሳፍራ በጉዞ ላይ እንዳለች በተሰወረችው አነስተኛ ጀልባ ህይወታቸው ያለፈ የሰባት ሰዎች አስከሬን መገኘቱን ፖሊስ አስታውቋል። የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ቸርነት አስማረ እንደገለጹት አስከሬኑ የተገኘው በሃይቁ ላይ ላለፉት ሁለት ቀናት በጀልባና…
#Update
በጣና ሃይቅ ላይ 13 የሚደርሱ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችን ጀልባ መሰወሯን ተከትሎ ፖሊስ ተሳፋሪዎችን ለማግኘት አሰሳ እያደረገ መሆኑ መግለፁ ይታወሳል።
ፖሊስ ባደረገው አሰሳ ትናንት የሰባት ሰዎች አስከሬን መገኘቱን አስታውቆ እንደነበር አይዘነጋም።
አሁንም ፖሊስ አሰሳውን የቀጠለ ሲሆን ዛሬ የጀልባዋ ካፒቴን አስከሬን መገኘቱን ይፋ አድርጓል።
እስካሁን በተደረገ ፍለጋ የትላንት ሰባት ሰዎች አስክሬን ጨምሮ በድምሩ የስምንት ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል፤ የቀሪ ሰዎችን ለማግኘት አሰሳ እንደሚቀጥል ፖሊስ አሳውቋል።
መረጃውን አሚኮ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምሥራቅ ደንቢያ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ ቤትን ዋቢ አድርጎ ነው ይፋ ያደረገው።

#ቶኪዮ2020 : በ32ኛው የቶኪዮ 2020 (2021) ኦሊምፒክ ሀገራችንን በአትሌቲክስ የሚወክሉ አትሌቶችና ኦፊሻሎች ዝርዝር።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
@tikvahethiopia
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
@tikvahethiopia
#Orange
የፈረንሳዩ ኦሬንጅ የቴሌኮሙንኬሽን ኩባንያ የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ለመግዛት ፍላጎትን ማሳወቁ ተገለጸ።
ኢትዮጵያ የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ መግዛት የሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ፍላጎታቸውን ከሰኔ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ እንዲያሳውቁ መጠየቋ ይታወሳል።
በዚህ መሰረት የቀድሞው ፋራንስ ቴሌኮም የአሁኑ ኦሬንጅ ቴሌኮም ኩባንያ የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ለመግዛት በይፋ ጥያቄ ማቅረቡ ታውቋል።
በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራ ከዚህ ኩባንያ ከፍተኛ አመራሮች ጋር መወያየታቸውን በትዊተር ገፃቸው ገልፀዋል።
አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ፥ “በኢትዮ-ቴሌኮም ካፒታል ውስጥ ለመግባት በይፋ ካሳወቀው ኦረንዥ (ቴሌኮም) ኃላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። ኢኮኖሚዋና ገቢዋ በፍጥነት በማደግ ላይ የምትገኘውና ከ100 ሚሊየን ህዝብ በላይ ያላት አገራችን በውጭ ባለሀብቶች ዘንድ ያላት ተፈላጊነት እንደቀጠለ ነው” ብለዋል።
ኦሬንጅ ኩባንያ አሁን ላይ ፈረንሳይን ጨምሮ በአውሮፓ፤ መካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ የቴሌኮሙንኬሽን አገለግሎት በመስጠት ላይ ሲሆን አጠቃላይ የድርጅቱ አጠቃላይ ሀብት ከ100 ቢሊዮን ዩሮ በላይ ነው።
ድርጅቱ እስከ ፈረንጆቹ 2020 ድረስ በ26 የዓለማችን አገራት ከ250 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች አሉት። ከዚህ ውስጥ ከ200 ሚሊዮን በላይ ያህሉ የሞባይል ደንበኞች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የብሮድባንድ ተጠቃሚዎች ናቸው።
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ