TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ItsMyDam🇪🇹 የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድባችን ሁለተኛው ዙር ሙሌት #ዛሬ_ለሊት ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተሰምቷል። የውሀው መጠን ግንባታው የደረሰበት ከፍታ ላይ ደርሶ ዛሬ ለሊት ሞልቶ ይፈሳል ተብሎ ይጠበቃል። ይህን መረጃ ይፋ ያደረገው "የሪፖርተር ጋዜጣ ድረገፅ" ሲሆን መረጃውን ከፕሮጀክቱ ስፍራ ማግኘቱን ገልጿል። @tikvahethiopia
#ItsMyDam🇪🇹

የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ በስፍራው ያሉ የግድቡ ሰራተኞች እየገለፁ ነው።

የውሀው መጠን ግንባታው የደረሰበት ከፍታ ላይ ደርሶ ሞልቶ ይፈሳል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ሂደቱ ትላንት ለሊት የተጠበቀ ቢሆንም ሳይሆን ቀርቷል።

Photo Credit : Boni Kita (ከፕሮጀክቱ ስፍራ)

@tikvahethiopia
የኪም ጆንግ ኡን ሀገር ሰሜን ኮሪያ ወጣቶቿን የደ/ኮሪያ መደበኛ ያልሆነ ቋንቋ ከመጠቀም እንዲቆጠቡ አሳሰበች።

የሰሜን ኮሪያ መንግስት መገናኛ ብዙኃን ወጣቶች የደቡብ ኮሪያ መደበኛ ያልሆነ ቋንቋ እንዳይጠቀሙ አሳስቧል፤ ወጣቶች የሰሜን ኮሪያን መደበኛ ቋንቋ እንዲገለገሉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል።

ወጣቶች ከደቡብ ኮሪያ የተቀዱ የፋሽን፣ የፀጉር ስታይል እንዳይጠቀሙም እና ሙዚቃ እንዳያዳምጡ የሰሜን ኮሪያ ይፋዊ ጋዜጦች አዲስ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር።

ይህ የውጭ ጫናን ለማስቆም ያለመና ከባድ ቅጣት የሚያስከትለው አዲስ ሕግ አካል ነው።

ሕጉን ጥሰው የተገኙም ከእስራት እስከ #ሞት ድረስ ሊቀጡ ይችላሉ።

ሮዶንግ ሲንመን ጋዜጣ ወጣቶች የደቡብ ኮሪያን የፖፕ ባህል መከተላቸው የሚያደርስባቸውን ተፅዕኖ አስጠንቅቋል።

"በተዋበና በቀለም ባሸበረቀ ስክሪን ሰርስረው የሚገቡ ርዕዮተ ዓለሞችና እና ባህሎች የጦር መሣሪያ ከያዙ ጠላቶች ይበልጥ አደገኛ ናቸው" ብሏል ጋዜጣው።

አክሎም ፥ ወጣቶች ኮሪያ ላይ የተመሠረተ የፕዮንግያንግ ቋንቋን በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አሳስቧል።

የውጭ ተፅዕኖ ኪም የሚመሩት የሰሜን ኮሪያ ኮሚዩኒስት ሥርዓት ስጋት ተደርጎ ይታያል።

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን 'ኬ ፖፕ' [ደቡብ ኮሪያ መሰረቱ የሆነ የሙዚቃ ስልት] የሰሜን ኮሪያ ወጣቶችን አዕምሮ ጨምድዶ የያዘ 'የማይለቅ ካንሰር' ሲሉ መጥራታቸውን ኒዮርክ ታይምስ ዘግቧል።

ከደቡብ ኮሪያ፣ ከአሜሪካ ወይም ጃፓን ከፍተኛ መጠን ያለው ሙዚቃ ይዞ የተገኘ ማንኛውም ሰው የሞት ቅጣት ይጠብቀዋል። ይህንን ሲመለከት የተያዘ ሰውም የ15 ዓመታት እስር ይተላለፍበታል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"...ሰዎቹን በህይወት የማግኘት እድሉ ጠባብ ነው" - ፖሊስ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ 13 የሚደርሱ ሰዎችን አሳፍራ በጣና ሃይቅ ጉዞ የጀመረች አነስተኛ ጀልባ ተሰወረች። የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ቸርነት አስማረ ጀልባዋ የተሰወረችው በወረዳው አዲሰጌ ድንጌ ተብሎ ከሚጠራ ቀበሌ አባን ላይ ጎጥ መነሻቸውን በማድረግ ወደ ጎርጎራ ወደብ ጉዞ ከጀመረች በኋላ…
#Update

"የ7 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል" - ፖሊስ

በማእከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ በጣና ሀይቅ 13 ሰዎችን አሳፍራ በጉዞ ላይ እንዳለች በተሰወረችው አነስተኛ ጀልባ ህይወታቸው ያለፈ የሰባት ሰዎች አስከሬን መገኘቱን ፖሊስ አስታውቋል።

የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ቸርነት አስማረ እንደገለጹት አስከሬኑ የተገኘው በሃይቁ ላይ ላለፉት ሁለት ቀናት በጀልባና በዋናተኞች በተካሄደ አድካሚ ፍለጋ ነው፡፡

አስከሬኑ የጣና ሀይቅ በሚያዋስናቸው በጎርጎራና አዲስጌ ድንጌ በተባለ የገጠር ቀበሌ መካከል በሀይቁ ላይ በማእበል ተገፍተው ዛሬ ንጋት ላይ ተንሳፈው መገኘቱን አስረድተዋል፡፡

የቀሪውን የስድስት ሰዎች አስከሬን ለማግኘት ፍለጋው ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመው የጀልባዋን መስመጥ የሚያጣራ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ምርመራ መጀመሩን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@tikvahethiopia